October 21, 2023 

( በነዓመን ዘለቀ )

በአብይ አህመድና ብርሃኑ ጁላ የማይደፍሩ ሃቆች:-

የፋኖ ህዝባዊ ሃይሎችና ኦነግ ሸኔ፣ 

1. ባለፉት አመታት ኦነግ ሸኔ የአማራ ህዝብ ትልቅ ስጋት ሆኖ ከኦሮሚያም አልፎ በአማራ ክልል፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ፣ በሰሜን ሸዋ ልዩ ልዩ አካባቢዎች በአጣዬ፣ በምንጃር፣ በማጀቴ ንጹሃንን ይገላል፣ ያግታል፣ ይዘርፋል። ከ40 ሺ በላይ የአማራ ተወላጆች በዘር ተኮር ጥቃት ህይወታቸውን አጥተዋል። ከ 250, 000 በላይ ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው በየመጠለያው በአስከፊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።

2. ኦነግ ሸኔ ባንክ ይዘርፋል፣ በተቃራኑው ፋኖ የትኛውንም ባንክ አልዘረፈም፣ እንዲያውም በተቆጣጠራቸው ከተሞችና ወረዳዎች ሁሉ ተቋማትን፣ ባንኮች እንዳይዘረፉ አድርጎአል።

3. ኦነግ ሸኔ በንጿሃንን ላይ ተደጋጋሚ አረሜኔያዊ ጭፍጨፋ ፈጸመ፣ እርጎዞች፣ ህጻናት፣ ሴቶች ገድሎ አልበቃውም፣ አርዶአል። ፋኖ ንጽሃንን አልገደለም፣ የአብይ ሰራዊት በየቦታው ንጹሃንን ሲገድል፣ በድሮን ሲጨፈጭፍ፣ የጦር ወንጀሎች ሲፈጽም፣ ፋኖ የአገዛዙን ምርኮኖችን በተሸነፉባቸው፣ ሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ጎጃም ሲንከባከብ፣ በስብአዊነት አግባብ ሲይዝ በተደጋጋሚ እይተናል፣ አረጋግጠናል።

4. ኦነግ ሸኔ ዜጎችን፣ የውጭ ዜጎችን ያግታል፣ ክፍያ/ራንሰም በሚሊዮኖች ይጠይቃል፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዲኖሩ ምክነያት ሆኖአል፣ ከአዲስ አባባ 50-100 ኪ ሜ መንቀሳቀስ ለዜጎች ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ነው። ፋኖ የአገዛዙ እንጂ የኢትዮጵያውያን ዜጎች ስጋት እንዳልሆነ በተግባሮቹ ፣ በዲስፕሊኑ፣ በህዝባዊነቱ አረጋግጦአል ። ኢትዮጵያውና ዜጎችን ፣ ንጿህንን አላገተም፣ አልዘረፈም፣ አልጨፈጨፈም።

5. በኦነግ ሸኔ ጭፍጨፋ፣ መሰደድ፣ መዘረፍ ፣ በማንነቱ ዘርፈ ብዙ ጥቃት የደረሰበትን የአማራ ህዝብ አብይና የብርሃኑ ጁላ ሊያድኑት ፣ ሊታደጉት እንዳልቻሉ፣ በተደጋጋሚ ታይቶአል። ኦነግ ሸኔን ማሸነፍ ያቃተው የአብይ አገዛዝ ለምን የአማራን ህዝብ ማንበርከክ፣ ፋኖን ትጥቅ ማስፈታት ፈለገ፣ በላፈው ጦርነት ይህ ነው የማይባል መስዋእትነት የክፈለ ህዝብ፣ ፋኖን ለምን ካደ፣ ለምንስ በጦርነት የደቀቀ ህዝብ፣ ኢኮኖሚ በሌላ ዙሪ ጦርነት ለማድቀቅ ፈለገ? ፣ አሁን እንደተረጋገጠው የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ሳያፈርሱ ልናፈርስ ነው/ አፍርሰናል በማለት የኢትዮጵያን ህዝብ አጭበርብረው የአማራን ልዩ ሃይል ለምን ለመበተን ፈለጉ?። እነዚህን ተቃርኖዎች መርምሩ፣ ፈትሹ። ( በነዓመን ዘለቀ )