አውራ ጎዳና ከአማራ ክልል ካርታ ላይ እንድትጠፋ በዶዘር እየፈረሰች ነው። ( አንዳርጋቸው ፅጌ)

የመከላከያው ብርሃኑ ጁላ፣ የፌደራሉ ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣ የኦሮሚያ ክልል መሪ ሽመልስ አብዲሳ በጋራ አሲረውና አቅደው፣ በኦሮሚያ ልዩ ሃይል ወረራ የተፈጸመባት፣ በጠጡጢ ወረዳ የኦሮሞ ብልጽግና አስተዳዳሪ መሪነት ህዝብ ለዘረፋ የተሰማራባት፣ በአማራ ክልል የምትገኘው የአውራ ጎዳና ቀበሌ 3500 አባወራዎቿ ከተፈናቀሉባት፣ መሸሽ ያልቻሉት አረጋውያን ህጻናትና የአእምሮ ህመምተኞቿ ከተገደሉባት ይኸው ሁለተኛ ወሯን ልትይዝ ነው።
በዛሬው እለት ደግሞ በኦሮሞ ልዩ ሃይል አስፈጻሚነት፣ በመከላከያ ታዛቢነት የቆርቆሮ ጣራቸው ሳይቀር በዘረፋ የተራቆቱት የተፈናቃዮቿ ቤቶች በዶዘር እየፈረሱ ነው። ቀብሌዋ እንዳልነበረች አድርጎ ከአማራ ክልል ካርታ ላይ የመሰዘርና በኦሮሚያ ክልል የመሰልቀጡ ስራ ተጀምሯል።
የአውራ ጎዳና እጣ የተፈረደባቸውን ተጨማሪ ቀበሌዎችን ስምና በአውራ ጎዳና የተፈጸመውን ወንጀል የሚያሳይ ዝርዝር ዘገባ በቅርቡ ይዤ እመለሳለሁ። ይህን የኦሮሞ ብልጽግና የተስፋፊነት ሴራ ከማጋለጥና ለማስቆም ተግተን ከመስራት እንድንቦዝን የወደብ አጀንዳ ሆን ብሎ የተወረወረልን አጥንት መሆኑን አውቀን፣ በአማራ ህዝብ ላይ አብይ አህመድ ያወጀውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለመመከት አይናችንን ከህልውና ትግሉ ላይ አንንቀል።
ለመሆኑ የአማራ ክልሉ መሪ ተብዬዎች የአብይ አህመድ ተላላኪዎች እስካሁን በአውራ ጎዳና ጉዳይ አንድም ቃል ትንፍሽ እንዳላሉ ታውቃላችሁ?
