ቀጥታ እስራኤል በጋዛ ላይ ጠንከር ያለ የአየር ጥቃት እንደምትፈጽም አስጠነቀቀች
ጭምቅ ሃሳብ
- በፍልስጤማዊያን ጉዳይ የተጠራው የካይሮ የሰላም ጉባኤ ያለ ውጤት ተበተነ
- ሐማስ፣ እስራኤል እና ምዕራባውያንን የተቹት የሳዑዲው ልዑል ለምን አነጋጋሪ ሆኑ?
- የተመድ ኤጀንሲዎች በጋዛ ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ
- እስራኤል በዌስት ባንክ የስደተኞች መጠለያ ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች
- እርዳታ የጫኑ የመጀመሪያዎቹ ተሸከርካሪዎች ጋዛ ገቡ
- ግጭቱ ከጀመረ ቢያንስ 22 ጋዜጠኞች መገደላቸው ተገለጸ
- ፍልስጥኤምን የሚደግፉ ሰልፎች በተለያዩ አገራት ተካሄዱ
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 6:416:41በጋዛ በቅርቡ ከተፈጸመው የአየር ጥቃት የተገኙ ፎቶዎች
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ በአንድ ሌሊት በፈጸመችው ጥቃት 55 ሰዎች መገደላቸውን ሐማስ አስታውቋል።እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈጽመው የማያባራ ጥቃት በቀጠለበት ወቅት ህንጻዎች መውደማቸውን፣ ነዋሪዎች ከወደሙ ህንጻዎች ፍርስራሽ ስር ያሉትን ለማዳን እየታገሉ የሚያሳዩ ምስሎችም ወጥተዋል።በሙሉ ከበባ ላይ ባለችው ጋዛ የምግብ እጥረትና ነዳጅ ያጋጠመ ሲሆን በርካቶችም ዳቦ ለመግዛት ከዳቦ ቤቶች ውጭ በወረፋዎች ላይ ታይተዋል።እስራኤል በጋዛ ላይ ጠንከር ያለ የአየር ጥቃት እንደምትፈጽም አስጠንቅቃለች።በሰሜን ጋዛ የሚገኙ ፍልስጥኤማውያንም በፍጥነት ወደ ደቡብ ጋዛ በመሸሽ ህይወታቸውን እንዲያድኑም የእስራኤል መከላከያ ኃይል በድጋሚ አሳስቧል። ጦሩ በቀጣይ በሚወስደው እርምጃ ሐማስን ከምድረ ገጽ እንደሚያጠፋም ዝቷል።
ReutersCopyright: Reuters
EPACopyright: EPA
EPACopyright: EPAArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ

- የታተመዉ 5:385:38ዓለም አቀፉ የቀይ ጨረቃ ድርጅት የጋዛ ሆስፒታሎች ነዳጅ ካላገኙ እንደሚዘጉ አስጠነቀቀ
ReutersCopyright: Reutersዓለም አቀፉ የቀይ ጨረቃ ድርጅት የጤና ማዕከላት አገልግሎታቸውን እንዲሰጡ ነዳጅ ወደ ጋዛ መግባት እንዳለበት አስጠነቀቀ።ትናንትና በራፋህ ድንበር በኩል ወደ ጋዛ የገባው የሰብዓዊ እርዳታ ነዳጅ አለማካተቱንም ተከትሎ ነው ተቋሙ ማሳሰቢያውን ያወጣው።የፍልስጥኤም የቀይ ጨረቃ ቢሮ ሰራተኛ የሆኑት ኔባል ፋስካህ “ሰብዓዊ እርዳታው ሆስፒታሎች አገልግሎት ማስቀጠል የሚያስችላቸውን መሰረታዊ የሆነውን ነዳጅ አልያዘም” ሲሉም ለቢቢሲ ተናግረዋል።”ነዳጅ ካለቀብን ሆስፒታሎች ይዘጋሉ” ያሉት ኔባል የጋዛ ሰርጥ ሁኔታ “ልብን የሚሰብር ነው” ሲሉም ገልጸውታል።20 የሰብአዊ እርዳታ ምግብና ቁሳቁስ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች በራፋህ ድንበር በትናንትናው ዕለት አልፈዋል።የጋዛ ነዋሪዎች ሰብአዊ እርዳታ ሲቀርብላቸው ከጦርነቱ ወዲህ የትናንቱ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። ቅዳሜ እለት ወደ ጋዛ የገባው የእርዳታ አቅርቦት መድኃኒት፣ ምግብ፣ ውሃ እና የሬሳ ሳጥን ያካተተ ቢሆንም እስራኤል ነዳጅ ድንበር ተሻግሮ እንዲገባ አልፈቀደችም።እስራኤል ጋዛ ሰርጥን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ከበባ እንዲደረግ ያዘዘች ሲሆን፣ በጋዛ ‘ኤሌክትሪክ፣ ምግብ፣ ነዳጅ መግባት ተከልክሏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:433:43በጋዛ በአንድ ሌሊት በተፈጸመ የአየር ጥቃት 55 ሰዎች መገደላቸውን ሐማስ አስታወቀ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል በጋዛ ሰርጥ ትናንት ሌሊት በፈጸመችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 55 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን ሐማስ አስታወቀ።በዚህ የአየር ጥቃት 30 መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውንም ኤኤፍፒ ሐማስን ዋቢ አድርጓል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የምትፈጽመውን የአየር ጥቃት አጠናክራ እንደምትቀጥል እና የእግረኛ ጦሯንም ለማስገባት በዝግጅት ላይ መሆኗን አስታውቃለች።በሰሜን ጋዛ የሚኖሩ ፍልስጥኤማውያንም ሙሉ በሙሉ ወጥተው ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲሄዱም ጦሩ እያስጠነቀቀ ይገኛል።የእስራኤል ጦር ቃለ አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ ጥቃቱ በጋዛ ድንበር አካባቢ ለተከማቸው የእስራኤል ጦር ላይ የደቀነውን አደጋም ለመቀነስ ይረዳል ብለዋል።ከጋዛ በተጨማሪ እስራኤል በተቆጣጠረችው ዌስት ባንክ ላይ የአየር ጥቃት ፈጽማለች።ጦሩ የ”አሸባሪዎች ማዘዣ ማዕከል” እንደሆነ የገለጸውን በጄኒን የስደተኞች መጠለያ የሚገኘው መስጂድን ኢላማ አድርጌያለሁ ብሏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:233:23በዩኬ እና አሜሪካ ለፍልስጥኤም ድጋፋቸውን ለመግለጽ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አደባባይ ወጡ
ReutersCopyright: Reutersበዩኬ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍImage caption: በዩኬ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍበአሜሪካ እና በዩናይትድ ኪንግደም ከተሞች ፍልስጥኤምን የሚደግፉ ሰልፎች ተካሄዱ።በሁለቱም አገራት ድጋፋቸውን ለፍልስጥኤም ለመግለጽ በአደባባይ የወጡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች “ነጻ ፍልስጥኤም ሲሉም” ተደምጠዋል።የፍልስጥኤምንም ሰንደቅ ዓላማ ሲያውለበልቡ ታይተዋል።ለሁለተኛ ሳምንት በለንደን በተደረገው የፍልስጥኤም የድጋፍ ሰልፍ እስከ 100 ሺዎች ተሳትፈውበታል።የምዕራቡ አገራት መንግሥታት ለእስራኤል እያሳዩት ያለውን ድጋፍም ተቃውመዋል።
ReutersCopyright: Reutersበዩኬ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍImage caption: በዩኬ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበአሜሪካ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍImage caption: በአሜሪካ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍ

Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበአሜሪካ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍImage caption: በአሜሪካ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:073:07የተመድ ኤጀንሲዎች በጋዛ ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ኤጀንሲዎች በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ያለው ሁኔታ እየከፋ መምጣቱን ተከትሎ ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ። የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና የዓለም የጤና ድርጅትን ጨምሮ አምስት የተመድ ኤጀንሲዎች የጋዛን ሁኔታ “አሰቃቂ” ሲሉም በጋራ ባወጡት መግለጫ አስፍረዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:332:33ሐማስ፣ እስራኤል እና ምዕራባውያንን የተቹት የሳዑዲው ልዑል ለምን አነጋጋሪ ሆኑ?የሐማስ ጥቃትን እና የእስራኤል ያልተቋረጠ የአጸፋ እርምጃን ተከትሎ ከሳዑዲ አረቢያ ንጉሣውያን መካከል ጉልህ ተጽእኖ ያላቸው ልዑል ቱርኪ አል-ፋይሳል የሰነዘሩት ትችት ከሌሎች አረብ አገራት ባለሥልጣናት የተለየ መሆኑ ትኩረትን ስቧል። በተለይ መካከለኛው ምሥራቅን ባቃወሰው በዚህ ግጭት ዙሪያ የልዑሉ አስተያየት የሳዑዲ መሪዎችን አቋም በግልጽ የሚያንጸባርቅ ነው ተብሎ ታምኗል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:332:3390 ሰዎችን ያስጠለለው ባለአራት መኝታው የጋዛ መኖሪያ ቤትኢብራሂም አል አጋ እና ሚስቱ ሐሚዳ ጋዛ ሽርሽር ላይ ሳሉ ነው እስራኤል የአየር ጥቃት የጀመረችው። የአየርላንድ ዜግነት ያላቸው ጥንዶቹ ደብሊን የተወለዱ ሦስት ልጆቻቸውን ይዘው ወደ ጋዛ ያቀኑት ልጆቻቸው ቋንቋ እና ባሕላቸውን እንዳይረሱ በሚል ነው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:242:24በፍልስጤማዊያን ጉዳይ የተጠራው የካይሮ የሰላም ጉባኤ ያለ ውጤት ተበተነበግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ በፍልስጤም ዙርያ የመከረው ጉባኤ ያለ ውጤት ተበተነ። ጉባኤው ያለ ውጤት የተበተነው የአውሮፓ ልኡካን አረብ አገራት ሐማስን እንዲያወግዙ በመጠየቃቸው ነው። በዚህ ጉባኤ አንድም የእስራኤል ባለሥልጣን አልታደመም። የአውሮፓ ኅብረት እና አረብ አገራት በጉባኤው ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። የሰላም ጉባኤው የጋራ የአቋም መግለጫ ለማውጣት ስምምነት ባይደርስም ግብጽ በተናጥል የአረብ አገራትን ይሁንታ ያገኘ መግለጫ አውጥታለች።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:531:53እስራኤል በዌስት ባንክ የስደተኞች መጠለያ ላይ በፈጸመችው ጥቃት 13 ሰዎች ተገደሉ- ተመድ
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል በኃይል በተቆጣጠረችው ዌስት ባንክ በሚገኘው ኑር ሻምስ በተሰኘው ስደተኞች መጠለያ ላይ በፈጸመችው ጥቃት 13 ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።ከተገደሉት መካከል አምስቱ ህጻናት መሆናቸውን ነው የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች የእርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ የገለጸው።ቢሮው ባወጣው መግለጫ አንድ የእስራኤል ወታደርም መሞቱን እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ቆስለዋል ብሏል። የተባበሩት መንግሥታት ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና እና ሌሎች አገልግሎቶችን ለማቆም መገደዱንም በመግለጫው አትቷል።እስራኤል በኃይል የተቆጣጠረቻችው ዌስት ባንክ ሶስት ሚሊዮን የሚሆኑ ፍልስጥኤማውያን መኖሪያ ነው።እስራኤል ዌስት ባንክ እና ምስራቅ እየሩሳሌምን ጨምሮ በኃይል የተቆጣጠረቻቸው በአውሮፓውያኑ 1967 የስድስቱ ቀናት ጦርነት ነበር።ባለፉት 50 ዓመታት እስራኤል በነዚህ ግዛቶች የሰፈራ መንደሮችን የገነባች ሲሆን ከ700 ሺህ በላይ አይሁዳውያንም ይኖራሉ።እስራኤል በኃይል በያዘቻቸው መሬቶች ላይ የምታደርገው የሰፈራ ፕሮግራም በአለም አቀፉ ህግ ተቀባይነት የላቸውም፤ ህገወጥ ናቸው።እስራኤል ውድቅ ብታደርገውም የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ ሌሎች አገራትና ተቋማት ህገወጥ ነው ሲሉም አቋማቸውን አሰምተዋል።እስራኤል በነዚህ በተቆጣጠረቻቸው ግዛቶች ለሚኖሩ ፍልስጥኤማውያን አስከፊው ዓመት ነው።በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መሰረት በዚህ ዓመት ከ270 በላይ ፍልስጥኤማውያን የተገደሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 82ቱ ሐማስ በእስራኤል ላይ ካደረሰው ጥቃት በኋላ የተገደሉ ናቸው።