https://www.bbc.com/amharic/live/news-67184520

Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 23 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 23 SECONDS1:23

Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBCሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?

Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. በፍልስጤማዊያን ጉዳይ የተጠራው የካይሮ የሰላም ጉባኤ ያለ ውጤት ተበተነ
  2. ሐማስ፣ እስራኤል እና ምዕራባውያንን የተቹት የሳዑዲው ልዑል ለምን አነጋጋሪ ሆኑ?
  3. የተመድ ኤጀንሲዎች በጋዛ ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ
  4. እስራኤል በዌስት ባንክ የስደተኞች መጠለያ ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች
  5. እርዳታ የጫኑ የመጀመሪያዎቹ ተሸከርካሪዎች ጋዛ ገቡ
  6. እስራኤል በጋዛ ላይ የምታካሂደው ‘ወታደራዊ ዘመቻ’ ወራት ሊወስድ እንደሚችል አስታወቀች
  7. እስራኤል የጋዛን ጦርነት ካላቆመች ቀጠናው ከቁጥጥር ውጭ ሊወጣ እንደሚችል ኢራን አስጠነቀቀች
  8. ሆስፒታሎቿ በቁስለኞች እና በአስከሬን በተጨናነቁባት ጋዛ የአየር ጥቃቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል
  9. ግጭቱ ከጀመረ ቢያንስ 22 ጋዜጠኞች መገደላቸው ተገለጸ
  10. ፍልስጥኤምን የሚደግፉ ሰልፎች በተለያዩ አገራት ተካሄዱ

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 4:134:13በጋዛ በቅርቡ ከተፈጸሙ የአየር ጥቃቶች የተገኙ ምስሎችበጋዛ ላይ የደረሰው የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እያደረገችው ያለው ወታደራዊ ዘመቻ ወራት ሊፈጅ እንደሚችል አስታውቃ የአየር ጥቃቷንም አጠናክራ ቀጥላለች።በነዚህ ጥቃቶች ከተገደሉት አብዛኛዎቹ ህጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን ከጋዛ የጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።በአጠቃላይም 4 ሺህ 651 ፍልስጥኤማውያን ተገድለዋል።እሁድ ምሽቱን በሙሉ እስራኤል በፈጸመቻቸው ጥቃቶች በርካታ ህንጻዎች መውደማቸውን እና መቁሰላቸውንም ከስፍራው የተገኙ ምስሎች ያሳያሉ።ከተለያዩ የዜና ኤጀንሲዎች የተገኙት እነዚህ ምስሎች የሚረብሽ ይዘት አላቸው።በጋዛ ላይ የደረሰው የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበጋዛ ላይ የደረሰው የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበጋዛ ላይ የደረሰው የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበጋዛ ላይ የደረሰው የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty ImagesArticle share tools
  2. የታተመዉ 3:353:35እስራኤል በጋዛ ላይ የምታካሂደው ‘ወታደራዊ ዘመቻ’ ወራት ሊወስድ እንደሚችል አስታወቀችበጋዛ ላይ የደረሰው የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት በጋዛ የሚካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ “አንድ፣ ሁለት ወይም ሶስት ወራት ሊወስድ እንደሚችል አስታወቁ።ነገር ግን በመጨረሻም ሐማስ መኖሩ ያከትማል” ሲሉም በእስራኤል የአየር ኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።”ወታደራዊ ዘመቻውን በተመለከተ የእስራኤልን መከላከያ ሰራዊት ምንም ነገር አያቆመውም” ሲሉም ተናግረዋል።”ይህ በጋዛ ላይ የምናደርገው ዘመቻ የመጨረሻችን ሊሆን ይገባል ምክንያቱም ከዚህ በኋላ ሐማስ አይኖርም” ሲሉም ተደምጠዋል።ሚኒስትሩ የእስራኤል ኃይል በጋዛ ላይ እያደረሰ ላለው ጥቃት አድናቆታቸውን ገልጸው ሲጠበቅ የነበረውም የእግረኛ ጦር በቅርቡ ወደ ጋዛ እንደሚገባ ናግረዋል።እስራኤል ላለፉት ሁለት ሳምንታት ቀን ተሌት ጋዛን በቦምብ በመደብደብ ላይ የምትገኝ ሲሆን በዚህም 4 ሺህ 651 ፍልስጥኤማውያን ተገድለዋል።መቼ ሊሆን እንደሚችል ግን ቀኑን አልጠቀሱም።የሆላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት እና ፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት እስራኤልን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።Article share tools
  3. የታተመዉ 2:582:58ሆስፒታሎቿ በቁስለኞች እና በአስከሬን በተጨናነቁባት ጋዛ የአየር ጥቃቱ ተጠናክሮ ቀጥሏልማስጠንቀቂያ፡ በዚህ ጽሑፍ አንዳንዶችን ሊረብሹ የሚችሉ መረጃዎች ተካተውበታል በማዕከላዊ ጋዛ የሚገኘው አል-አቅሳ ሰማዕታት ሆስፒታል የአስከሬን መሸፈኛ እያለቀበት ነው። አስከሬኖች ግቢ ውስጥ ተከማችተዋል። ጸሎት ሲካሄድና ዘመድ አዝማድ በሐዘን ብዛት ራሳቸውን ሲስቱ ይታያል። የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች የቆሰሉትን ለማከም እና በጣም የተጎዱትን ለማዳን ደፋ ቀና ይላሉ። የመድኃኒት እና የሕክምና ቁሳቁስ ቀን ከቀን ወደ ቀን እየተመናመነ ነው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  4. የታተመዉ 1:571:57በጋዛ- እስራኤል የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮችወደ ጋዛ የሚገባው እርዳታReutersCopyright: Reutersእስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ ሌት ተቀን የምትፈጽመው የአየር ጥቃት ለ16ኛ ቀን ቀጥሏል። እሁድ አመሻሽ ላይ የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮችን እንመልከት፦
    • እርዳታ የጫኑ 14 ተሽከርካሪዎች በከበባ ላይ ባለችው ጋዛ ሰርጥ እንዲገቡ ፍቃድ አግኝተዋል። ግጭቱ ከተጀመረ በኋላ እርዳታ ሲገባ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ ዋና ጸሐፊ ማርቲን ግሪፍትስ በግዛቲቱ ላሉ ነዋሪዎች “የተስፋ ጭላንጭል” የፈነጠቀ ነው ብለውታል።
    • “በቀን እርዳታ የጫኑ ጥቂት የጭነት መኪናዎችን እንዲገቡ መፍቀድ በቂ አይደለም” ሲሉ የኦክስፋም የሰብዓዊ እርዳታ ኃላፊ ማግኑስ ኮርፊሰን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የረድዔት ድርጅቶቹ ወደ ጋዛ “ያልተገደበ እርዳታ እንዲያደርሱ” ሊፈቀድላቸውም ይገባል ሲሉም አክለዋል።
    • የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁን ካናገሩ በኋላ መሪዎቹ “ለተቸገሩ ፍልስጥኤማውያን እርዳታ ባልተቋረጠ መልኩ እንዲገባ” ተስማምተናል ብለዋል።
    • የእስራኤል ቀኝ አክራሪ የደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን ጊቨር ሐማስ በእጁ ያሉ ታጋቾችን በሙሉ ለመልቀቅ ካልተስማማ ለጋዛ “ቀጣይ እርዳታ” ዋስትና ሊሰጥ አይገባም ሲሉ አቋማቸውን አንጸባርቀዋል።
    • የምዕራባውያኑ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ጣልያን መሪዎች እስራኤል “ራሷን ከሽብርተኝነት የመከላከል መብት” አላት በማለት በጋራ ድጋፋቸውን በድጋሜ ገልጸዋል። ሆኖም “ለአለም አቀፉ የሰብዓዊ ህግጋት ተገዢ እንድትሆን” ጥሪ አቅርበዋል።
    • የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩቴ እና የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሚቀጥለው ሳምንት እስራኤልን እንደሚጎበኙ አስታውቀዋል።
    • ጸረ ታንክ ሚሳኤሎችን እና ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ለማስወንጨፍ የታቀደበትን ሁለት የሄዝቦላህ የጦር ማዕከላት መምታቱን የእስራኤል መከላከያ አስታውቋል።
    • በመቶዎች የሚቆጠሩ እሰራኤላውያን በለንደን ታርፋልጋር አደባባይ ለሰልፍ የወጡ ሲሆን በጋዛ የታገቱ ሰዎች እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።
    Article share tools
  5. የታተመዉ 1:571:57የአሜሪካዋ ዲትሮይት ከተማ ምኩራብ ኃላፊ ተገድለው ተጣሉበአሜሪካ የዲትሮይት ከተማ ምኩራብ ፕሬዝደንት የሆኑት ሳማንታ ዎል ከቤታቸው አቅራቢያ ከሚገኝ አንድ ፓርክ ውስጥ ተገድለው ተጣሉ። ፖሊስ እንደገለጸው ቅዳሜ ዕለት ከላፋየት ፓርክ አካባቢ በደረሰው ጥሪ መሠረት ወደ ሥፍራው ሲያቀና ግለሰቧ ሕይወታቸው አልፎ ነበር። ፖሊስ እንደሚለው የምኩራቡ ፕሬዝደንት ቤታቸው ተገድለው ነው ፓርክ ውስጥ የተጣሉት።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  6. የታተመዉ 0:570:57እስራኤል የጋዛን ጦርነት ካላቆመች ቀጠናው ከቁጥጥር ውጭ ሊወጣ እንደሚችል ኢራን አስጠነቀቀችየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤልን አስጠነቀቁ። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አሚር አብዱላሂያን እንዳሉት ኢራን ጋዛን በጦር መሣሪያ መደብደብ የማታቆም ከሆነ መካከለኛው ምሥራቅ ወደ ቀውስ ቀጠናነት ሊሸጋገር ይችላል ብለዋል። አብዱላሒያን በዚህ አስተያየታቸው አሜሪካንን ተጠያቂ አድርገዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  7. የታተመዉ 0:480:48በጋዛ ከተገደሉት የህጻናቱ ቁጥር ከፍተኛውን ይይዛል- የጋዛ የጤና ሚኒስቴርበጋዛ ላይ የደረሰው የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበጋዛ ሰርጥ ከተገደሉት የህጻናት ቁጥር ከፍተኛውን እንደሚይዝ የጋዛ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።በባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ከተገደሉት 4 ሺህ 651 ፍልስጥኤማውያን መካከል 1 ሺህ 873 ህጻናት እንዲሁም 1 ሺህ 101 ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።በአጠቃላይም 4 ሺህ 651 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን እንዲሁም 14 ሺህ 245 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውንም አክሏል።በሐማስ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር ከተገደሉት ውስጥ 839 የሚሆኑት በእስራኤል አስገዳጅ ትዕዛዝ ከሰሜን ጋዛ እንዲሸሹ የተነገራቸው መሆናቸውንም አስታውቋል።ከሁለት ሳምንታት በፊት ሐማስ በወሰደው ያልተጠበቀ ወታደራዊ እርምጃ 1ሺህ 400 ሰዎች በእስራኤል ተገድለዋል።እስራኤል ላለፉት ሁለት ሳምንታት ቀን ተሌት ጋዛን በቦምብ በመደብደብ ላይ የምትገኝ በቅርቡም እግረኛ ጦሯን እንደምታስገባም እየተጠበቀ ይገኛል።Article share tools
  8. የታተመዉ 0:100:10ከሐማስ እና ከሒዝቦላህ ማን ጠንካራ ጦር አለው? አሜሪካ እና ኢራንስ ወደ ግጭቱ ይገቡ ይሆን?በጋዛ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በርካታ የቢቢሲ አንባቢያን መሠረታዊ ጥያቄዎችን ያነሳሉ። ለእነዚህ ጥያቄዎች በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ የሚገኙ እና ጉዳዩን በጥልቅ የሚረዱ የቢቢሲ ዘጋቢዎች ምላሽ እንዲሰጡባቸው አድርገናል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  9. የታተመዉ 0:100:10ፀረ – ሴማዊነት ምንድን ነው? ፀረ – ጽዮናዊነትስ?ለሁለት ሳምንታት ከቀጠለው የእስራኤል-ጋዛ ግጭት ጋር ተያይዞ ፀረ – ሴማዊነት፣ ፀረ – ጽዮናዊነት የሚሉ እሳቤዎች መነጋገሪያ ሆነዋል። በተለይም ለፍልስጥኤም የሚደረጉ ዓለም አቀፍ ድጋፎች በተበራከቱበት እና የእስራኤልን መንግሥት የሚቃወሙ ድምጾች መሰማትን ተከትሎ እነዚህ ሃሳቦችም እየተንሸራሸሩ ይገኛሉ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  10. የታተመዉ 6:41 22 ጥቅምት 20236:41 22 ጥቅምት 2023በጋዛ በቅርቡ ከተፈጸመው የአየር ጥቃት የተገኙ ፎቶዎችበጋዛ ላይ የተፈጸመው የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ በአንድ ሌሊት በፈጸመችው ጥቃት 55 ሰዎች መገደላቸውን ሐማስ አስታውቋል።እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈጽመው የማያባራ ጥቃት በቀጠለበት ወቅት ህንጻዎች መውደማቸውን፣ ነዋሪዎች ከወደሙ ህንጻዎች ፍርስራሽ ስር ያሉትን ለማዳን እየታገሉ የሚያሳዩ ምስሎችም ወጥተዋል።በሙሉ ከበባ ላይ ባለችው ጋዛ የምግብ እጥረትና ነዳጅ ያጋጠመ ሲሆን በርካቶችም ዳቦ ለመግዛት ከዳቦ ቤቶች ውጭ በወረፋዎች ላይ ታይተዋል።እስራኤል በጋዛ ላይ ጠንከር ያለ የአየር ጥቃት እንደምትፈጽም አስጠንቅቃለች።በሰሜን ጋዛ የሚገኙ ፍልስጥኤማውያንም በፍጥነት ወደ ደቡብ ጋዛ በመሸሽ ህይወታቸውን እንዲያድኑም የእስራኤል መከላከያ ኃይል በድጋሚ አሳስቧል። ጦሩ በቀጣይ በሚወስደው እርምጃ ሐማስን ከምድረ ገጽ እንደሚያጠፋም ዝቷል።በጋዛ ላይ የተፈጸመው የአየር ጥቃትReutersCopyright: Reutersበጋዛ ላይ የተፈጸመው የአየር ጥቃትEPACopyright: EPAበጋዛ ላይ የተፈጸመው የአየር ጥቃትEPACopyright: EPAArticle share tools
  11. የታተመዉ 5:38 22 ጥቅምት 20235:38 22 ጥቅምት 2023ዓለም አቀፉ የቀይ ጨረቃ ድርጅት የጋዛ ሆስፒታሎች ነዳጅ ካላገኙ እንደሚዘጉ አስጠነቀቀወደ ጋዛ የገባው እርዳታReutersCopyright: Reutersዓለም አቀፉ የቀይ ጨረቃ ድርጅት የጤና ማዕከላት አገልግሎታቸውን እንዲሰጡ ነዳጅ ወደ ጋዛ መግባት እንዳለበት አስጠነቀቀ።ትናንትና በራፋህ ድንበር በኩል ወደ ጋዛ የገባው የሰብዓዊ እርዳታ ነዳጅ አለማካተቱንም ተከትሎ ነው ተቋሙ ማሳሰቢያውን ያወጣው።የፍልስጥኤም የቀይ ጨረቃ ቢሮ ሰራተኛ የሆኑት ኔባል ፋስካህ “ሰብዓዊ እርዳታው ሆስፒታሎች አገልግሎት ማስቀጠል የሚያስችላቸውን መሰረታዊ የሆነውን ነዳጅ አልያዘም” ሲሉም ለቢቢሲ ተናግረዋል።”ነዳጅ ካለቀብን ሆስፒታሎች ይዘጋሉ” ያሉት ኔባል የጋዛ ሰርጥ ሁኔታ “ልብን የሚሰብር ነው” ሲሉም ገልጸውታል።20 የሰብአዊ እርዳታ ምግብና ቁሳቁስ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች በራፋህ ድንበር በትናንትናው ዕለት አልፈዋል።የጋዛ ነዋሪዎች ሰብአዊ እርዳታ ሲቀርብላቸው ከጦርነቱ ወዲህ የትናንቱ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። ቅዳሜ እለት ወደ ጋዛ የገባው የእርዳታ አቅርቦት መድኃኒት፣ ምግብ፣ ውሃ እና የሬሳ ሳጥን ያካተተ ቢሆንም እስራኤል ነዳጅ ድንበር ተሻግሮ እንዲገባ አልፈቀደችም።እስራኤል ጋዛ ሰርጥን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ከበባ እንዲደረግ ያዘዘች ሲሆን፣ በጋዛ ‘ኤሌክትሪክ፣ ምግብ፣ ነዳጅ መግባት ተከልክሏል።Article share tools
  12. የታተመዉ 3:43 22 ጥቅምት 20233:43 22 ጥቅምት 2023በጋዛ በአንድ ሌሊት በተፈጸመ የአየር ጥቃት 55 ሰዎች መገደላቸውን ሐማስ አስታወቀእስራኤል በጋዛ ሰርጥ የፈጸመችው የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል በጋዛ ሰርጥ ትናንት ሌሊት በፈጸመችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 55 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን ሐማስ አስታወቀ።በዚህ የአየር ጥቃት 30 መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውንም ኤኤፍፒ ሐማስን ዋቢ አድርጓል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የምትፈጽመውን የአየር ጥቃት አጠናክራ እንደምትቀጥል እና የእግረኛ ጦሯንም ለማስገባት በዝግጅት ላይ መሆኗን አስታውቃለች።በሰሜን ጋዛ የሚኖሩ ፍልስጥኤማውያንም ሙሉ በሙሉ ወጥተው ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲሄዱም ጦሩ እያስጠነቀቀ ይገኛል።የእስራኤል ጦር ቃለ አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ ጥቃቱ በጋዛ ድንበር አካባቢ ለተከማቸው የእስራኤል ጦር ላይ የደቀነውን አደጋም ለመቀነስ ይረዳል ብለዋል።ከጋዛ በተጨማሪ እስራኤል በተቆጣጠረችው ዌስት ባንክ ላይ የአየር ጥቃት ፈጽማለች።ጦሩ የ”አሸባሪዎች ማዘዣ ማዕከል” እንደሆነ የገለጸውን በጄኒን የስደተኞች መጠለያ የሚገኘው መስጂድን ኢላማ አድርጌያለሁ ብሏል።Article share tools
  13. የታተመዉ 3:23 22 ጥቅምት 20233:23 22 ጥቅምት 2023በዩኬ እና አሜሪካ ለፍልስጥኤም ድጋፋቸውን ለመግለጽ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አደባባይ ወጡበዩኬ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍReutersCopyright: Reutersበዩኬ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍImage caption: በዩኬ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍበአሜሪካ እና በዩናይትድ ኪንግደም ከተሞች ፍልስጥኤምን የሚደግፉ ሰልፎች ተካሄዱ።በሁለቱም አገራት ድጋፋቸውን ለፍልስጥኤም ለመግለጽ በአደባባይ የወጡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች “ነጻ ፍልስጥኤም ሲሉም” ተደምጠዋል።የፍልስጥኤምንም ሰንደቅ ዓላማ ሲያውለበልቡ ታይተዋል።ለሁለተኛ ሳምንት በለንደን በተደረገው የፍልስጥኤም የድጋፍ ሰልፍ እስከ 100 ሺዎች ተሳትፈውበታል።የምዕራቡ አገራት መንግሥታት ለእስራኤል እያሳዩት ያለውን ድጋፍም ተቃውመዋል።በዩኬ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍReutersCopyright: Reutersበዩኬ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍImage caption: በዩኬ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍበአሜሪካ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበአሜሪካ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍImage caption: በአሜሪካ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍበአሜሪካ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበአሜሪካ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍImage caption: በአሜሪካ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍበአሜሪካ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበአሜሪካ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍImage caption: በአሜሪካ ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍArticle share tools
  14. የታተመዉ 3:07 22 ጥቅምት 20233:07 22 ጥቅምት 2023የተመድ ኤጀንሲዎች በጋዛ ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ኤጀንሲዎች በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ያለው ሁኔታ እየከፋ መምጣቱን ተከትሎ ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ። የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና የዓለም የጤና ድርጅትን ጨምሮ አምስት የተመድ ኤጀንሲዎች የጋዛን ሁኔታ “አሰቃቂ” ሲሉም በጋራ ባወጡት መግለጫ አስፍረዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  15. የታተመዉ 2:33 22 ጥቅምት 20232:33 22 ጥቅምት 2023ሐማስ፣ እስራኤል እና ምዕራባውያንን የተቹት የሳዑዲው ልዑል ለምን አነጋጋሪ ሆኑ?የሐማስ ጥቃትን እና የእስራኤል ያልተቋረጠ የአጸፋ እርምጃን ተከትሎ ከሳዑዲ አረቢያ ንጉሣውያን መካከል ጉልህ ተጽእኖ ያላቸው ልዑል ቱርኪ አል-ፋይሳል የሰነዘሩት ትችት ከሌሎች አረብ አገራት ባለሥልጣናት የተለየ መሆኑ ትኩረትን ስቧል። በተለይ መካከለኛው ምሥራቅን ባቃወሰው በዚህ ግጭት ዙሪያ የልዑሉ አስተያየት የሳዑዲ መሪዎችን አቋም በግልጽ የሚያንጸባርቅ ነው ተብሎ ታምኗል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  16. የታተመዉ 2:33 22 ጥቅምት 20232:33 22 ጥቅምት 202390 ሰዎችን ያስጠለለው ባለአራት መኝታው የጋዛ መኖሪያ ቤትኢብራሂም አል አጋ እና ሚስቱ ሐሚዳ ጋዛ ሽርሽር ላይ ሳሉ ነው እስራኤል የአየር ጥቃት የጀመረችው። የአየርላንድ ዜግነት ያላቸው ጥንዶቹ ደብሊን የተወለዱ ሦስት ልጆቻቸውን ይዘው ወደ ጋዛ ያቀኑት ልጆቻቸው ቋንቋ እና ባሕላቸውን እንዳይረሱ በሚል ነው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  17. የታተመዉ 2:24 22 ጥቅምት 20232:24 22 ጥቅምት 2023በፍልስጤማዊያን ጉዳይ የተጠራው የካይሮ የሰላም ጉባኤ ያለ ውጤት ተበተነበግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ በፍልስጤም ዙርያ የመከረው ጉባኤ ያለ ውጤት ተበተነ። ጉባኤው ያለ ውጤት የተበተነው የአውሮፓ ልኡካን አረብ አገራት ሐማስን እንዲያወግዙ በመጠየቃቸው ነው። በዚህ ጉባኤ አንድም የእስራኤል ባለሥልጣን አልታደመም። የአውሮፓ ኅብረት እና አረብ አገራት በጉባኤው ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። የሰላም ጉባኤው የጋራ የአቋም መግለጫ ለማውጣት ስምምነት ባይደርስም ግብጽ በተናጥል የአረብ አገራትን ይሁንታ ያገኘ መግለጫ አውጥታለች።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  18. የታተመዉ 1:53 22 ጥቅምት 20231:53 22 ጥቅምት 2023እስራኤል በዌስት ባንክ የስደተኞች መጠለያ ላይ በፈጸመችው ጥቃት 13 ሰዎች ተገደሉ- ተመድየእስራኤል ጦርReutersCopyright: Reutersእስራኤል በኃይል በተቆጣጠረችው ዌስት ባንክ በሚገኘው ኑር ሻምስ በተሰኘው ስደተኞች መጠለያ ላይ በፈጸመችው ጥቃት 13 ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።ከተገደሉት መካከል አምስቱ ህጻናት መሆናቸውን ነው የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች የእርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ የገለጸው።ቢሮው ባወጣው መግለጫ አንድ የእስራኤል ወታደርም መሞቱን እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ቆስለዋል ብሏል። የተባበሩት መንግሥታት ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና እና ሌሎች አገልግሎቶችን ለማቆም መገደዱንም በመግለጫው አትቷል።እስራኤል በኃይል የተቆጣጠረቻችው ዌስት ባንክ ሶስት ሚሊዮን የሚሆኑ ፍልስጥኤማውያን መኖሪያ ነው።እስራኤል ዌስት ባንክ እና ምስራቅ እየሩሳሌምን ጨምሮ በኃይል የተቆጣጠረቻቸው በአውሮፓውያኑ 1967 የስድስቱ ቀናት ጦርነት ነበር።ባለፉት 50 ዓመታት እስራኤል በነዚህ ግዛቶች የሰፈራ መንደሮችን የገነባች ሲሆን ከ700 ሺህ በላይ አይሁዳውያንም ይኖራሉ።እስራኤል በኃይል በያዘቻቸው መሬቶች ላይ የምታደርገው የሰፈራ ፕሮግራም በአለም አቀፉ ህግ ተቀባይነት የላቸውም፤ ህገወጥ ናቸው።እስራኤል ውድቅ ብታደርገውም የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ ሌሎች አገራትና ተቋማት ህገወጥ ነው ሲሉም አቋማቸውን አሰምተዋል።እስራኤል በነዚህ በተቆጣጠረቻቸው ግዛቶች ለሚኖሩ ፍልስጥኤማውያን አስከፊው ዓመት ነው።በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መሰረት በዚህ ዓመት ከ270 በላይ ፍልስጥኤማውያን የተገደሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 82ቱ ሐማስ በእስራኤል ላይ ካደረሰው ጥቃት በኋላ የተገደሉ ናቸው።