October 23, 2023 – Konjit Sitotaw
ከቡሬ ወደ ለቀምት በሚወስደው መንገድ ላይ 27 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘዉ ቁጭ ከተማ መከላከያ ወደ ንጹሀን መድፍ እያዘነበ ነው። ቁጭ ከተማ ጤና ጣቢያው አካባቢ በተደጋጋሚ የከባድ መሳሪያ ቅንቡላ አርፏል።
እናርጅ እናውጋ ደብረወርቅ ከተማ ለሶስት ቀናት በተደረገ ከባድ የተባለ ውጊያ ፋኖ ሁለት ዲሽቃ፣ 78 ክላንሽኮብ፣ 12 ብሬን ከጠላት ሀይል ማርኳል። በሚገርም ሁኔታ የእናርጅ እናውጋ ገደብ ቀበሌ ሊቀመንበር ከፋኖ ጋር ሲዋጋ የተሰዋ ሲሆን፣ ገደብ ቀበሌ የአረጋ ከበደ የትውልድ መንደር ናት። ከፋኖ ጋር ሆነው ሲዋጉ አራት የአረጋ ከበደ ዘመዶች በመከላከያ ተገለዋል። የአቶ ተመስገን ጥሩነህ ዘመዶችም ከፋኖ ጋር ቆመው እየተዋጉ ነው።
እነዚህ ሰዎች የራሳቸውን ዘመዶች እያስገደሉ ለወንበር ታምነው መቀጠላቸው አስገራሚ ሆኗል። በዚህም ተባለ በዚህ ግን የእናርጅ እናውጋ ደብረወርቅ ፋኖ በሚገርም የውጊያ ጥበብ ዓላማ ቢስ፣ ደምዝተኛ እና የፓርቲ ዘበኛ የሆነውን የመከላከያ ሀይል እየበታተነው ይገኛው። በሌላ በኩል በቡሬ ዳሞት ቁጭ ከተማ ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው። በጎጃም አካባቢ ያሉ ሚኒሻዎች በብዛት መከላከያ ካልወጣ ሚኒሻ አንሁንም፣ አሁን ፋኖ ነን ብለዋል። የአዲስቅዳም ሚኒሻዎች ስብሰባ ተጠርተው ቀርተዋል። የወረዳ ካድሬዎችም ህዝባችን እየተጨፈጨፈ አንሾሞምም ብለዋል። የብርሃኑ ጁላ ጦር ወደ ቡሬ ቁጭ ከባድ መሳሪያ ተኩሶ ቤተክርስቲያን እና ጤና ጣቢያ ላይ አርፏል።
