October 23, 2023 – Konjit Sitotaw
በኢትዮጵያ 7 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሕጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን ዩኒሴፍ አስታወቀ
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 7 ነጥብ 6 ሚሊዮን የሚጠጉ ሕጻናት በአገሪቱ ባለው አደጋና ግጭት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው ውጨ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕጻናት አድንድ ድርጅት ዩኒሴፍ አስታውቋል፡፡
ዩኒሴፍ የኢትዮጵያን የትምህርት ኹኔታ አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት፤ “በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ሌሎች ክልሎች በመካሄድ ላይ ያሉ ግጭቶች፤ በአገሪቱ በትምህርት ገበታቸው ላይ የማይገኙ ሕጻናት ቁጥር እንዲጨምር ዋነኛ ምክንያ ሆኗል” ብሏል፡፡
በዚህም በአገሪቱ በተከሰቱ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ምክንያት፤ በአሁኑ ወቅት 7 ነጥብ 6 ሚሊዮን የሚጠጉ ሕጻናት ከትምህርት ገበታቸው ውጨ መሆናቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ ሕጻናቱ ከትምህርት ገበታቸው ውጭ ሆነው ይበልጥ ሲቆዩ፤ ወደ መደበኛ ትምህርት የመመለስ እድላቸው ይቀንሳል።” ሲል አሳስቧል፡፡
በአገሪቱ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች በድምሩ 8 ሺሕ 552 የሚሆኑት በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ጉዳት እንደደረሰባቸው በመግለጽም፤ ይህም 20 በመቶ የአገሪቱን ትምህርት ቤቶች እንደሚሸፍን አመላክቷል፡፡
