ቀይ ባህር፣ የኦሮሙማ ፕሮጀክት፣ የታላቋ ትግራይ ፕሮጀችት፣ ኤርትራ፣ አማራ፤ አማራዊያን ከመቸውም ጊዜ በላይ በጣም በጥብቅ ማሰብ አለብን!
( ምስጋናው አንዷለም )
የህልውና ትግሉ ወሳኝ ምእራፍ ላይ ደርሷል፡፡ ተያይዞም የኦሮሙማ ምስራቅ አፍሪካ ፕሮጀክት እየተፋጠነ ነው፡፡ ከመጀመሪያውም በኦሮሙማ አራማጆች ዘንድ ይሄ የራስን ብሄር የምስራቅ አፍሪካ ኢምፓየር የማድረግ ህልም ነበር፡፡ የቀይ ባህር አጀንዳነት የቆየ የውስጥ ጉዳያቸው ነው፡፡ አሁን ለህዝብ ይፋ የተደረገበት ምክንያት በፋኖ ግስጋሴ የተነሳ ይሄ ፕሮጀክት መና ከመሆኑ በፊት ጊዜን ለመቅደም ታስቦ ነበር፡፡ ኦሮሙማ በቅደም ተከተል ካስቀመጣቸው ተፈጻሚ ተግባራት አንዱ የሆነው ይህ የቀይ ባህርና የምስራቅ አፍሪካ ኢምፓየር ፕሮጀክት ዋና ነው፡፡ አሁን ከታቀደለት ጊዜ ቀድሞ መጥቷል፡፡ ምክንያቱ ፋኖ ነው፡፡
በጣም የሚገርመው ይሄ አጀንዳ ከወያኔ አጀንዳ ጋር የዘፍጥረትም የግብም ተመሳስሎ ያለው መሆኑ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ወያኔ “አሰብ የኢትዮጵያ ናት” የሚሉትን ሁሉ ሲያሸማቅቅ እና ሲያሳድድ ነበር፡፡ ለምን? ከቀድሞዋ ትግራይ ክፍለ ሀገር ራሱ የተወሰነውን ቆርሶ፤ ከቀድሞው የወሎ ራስገዝ ክፍለ ሀገር የተወሰነውን ቆርሶ ነበር አፋር ክልልን የፈጠረው፡፡ አንድም ወያኔ መሬቴ በአፋር ተይዟል ሲል ተሰምቶ ግን አይታወቅም፡፡ ለምን? ይህ ቦታ በመጨረሻ የትግራይ ይሆናል ተብሎ ስለታሰበ፡፡ ባጭር አማርኛ አፋር ክልልና አሰብ የወያኔ የኋላ ጊዜ ተፈጻሚ እቅድ ነበር፡፡ ይሄም ከኦሮሙማ ፕሮጀክት ህልም ጋር መሳ ለመሳ ተገናኝቷል፡፡ በተፍጥሮ ድንበር የሌላቸው ትግራይ እና ኦሮሙማ ፕሮጀክት አሁን አፋርን፤ ማለትም የቀድሞውን ወሎራስ ገዝ ግዛትን በመቀራመት ድንበርተኛ ሊሆኑ ነው፤ ሁለቱም የባህር በር ባለቤት ሊሆኑ ነው፡፡ ይሄንን ጉዳይ በቤተ አማራ እንቅስቃሴ የመጀመሪያዎቹ አመታት ጊዜ “እኛ ቁጭ ብለን ትግሬና ኦሮሞ በአማራ መሬት ላይ የድንበር ጦርነት ሊገጥሙ ነው” እያልን እንገልጸው ነበር፤ የምታስታውሱ ታስታውሱታላችሁ፡፡ አሁንም ህልማቸው ያ ነው፡፡
እዚህ ላይ አንድ ነገር እናውሳ፡፡ እንደሚታወቀው የትግራይ ፖለቲካ በአክቲቪስቶች ጫና ስር የወደቀ ነበር፡፡ የመጨረሻው ዙር ግጥሚያ እየተደረገ፤ አቅም እያጠራቸው ሲሄድ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ አንድ ነገር እንዲሆን ይወተውቱ ነበር፡፡ የደቡቡን ማለትም አብይን እና አማራን በሆነ መንገድ ዘመቻቸውን እንዲያቆሙ አድርገን ወደ ሰሜን መዝመት አለብን የሚል፡፡ ወዲያው ያው የፕሪቶሪያ ስምምነት ተደረገ ተባለ፡፡ ከዚያ በኋላ ኤርትራን ለመውረር እንደተዘጋጁ ናቸው፡፡ ያን ጊዜ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የቅደም ተከተል ለውጥ ሲያወሩ ነበር፡፡ መጀመሪያ ወደ አማራና አፋር ከመዝመታቸው በፊት ኤርትራን መውረር እንደነበረባቸው በጸጸት ሁሉ ነበር የሚያወሩት፡፡ እናም አሁን ላይ 270 000 የታጠቀ ጦር አላቸው፡፡ የፕሪቶሪያ ስምምነት ሲፈረምም በጦርነቱ የመሸነፍ አዝማሚያ እንጅ ሰራዊታቸው የማለቅ አዝማሚያ አልነበረውም፡፡ ያኔ የነበረውንም በኋላ የሰለጠነውም ደማምረው ይሄንን ያህል ሀይል አላቸው፡፡ ይህ ደግሞ አብይ አህመድ ካከማቸው የኬሚካል የጦር መሳሪያ እና ጥቂት ትርፍራፊ ሰራዊት ጋር፤ ከበስተጀርባውም አይዞህ ባይ ሀያላን አገራት ተደምሮበት ሁኔታውን ለኤርትራ አስጊ ያደርገዋል፡፡ የትግራይ ጦር ብቻውን ከኤርትራ ጦር ይበልጣል፡፡ ትግራይ 270 000 ሲኖራት፤ ኤርትራ ደግሞ 210 000 ገደማ አላት፡፡ በ2020 ዓ.ም 202 000 ያህል ሰራዊት እንደነበራት ታሳቢ በማድረግ፡፡ እንግዲህ አማራና ኦሮሚያ የተባሉ ሁለት አገሮች ለመወለድ ምጥ ላይ ናቸው ነው የነገሩ ጭብጥ፡፡
እቅዳቸው አይሳካም እንጅ ከተሳካ ሁለቱም የባህር በር ይኖራቸዋል፡፡ ሁለቱም አማራንም ኤርትራንም ለማሸነፍ ይሞክራሉ፡፡ አማራና ኤርትራ ካልተሸነፉ እነዚህ ምጥ ላይ ያሉ አገራት ሊወለዱ ስለማይችሉ፡፡ በመሆኑም አማራና ኤርትራ ማሸነፍ አለባቸው፡፡ በጣም የሚገርመው የወያኔን የበቀል ንግግሮች ሲከታተል ለቆየ ሰው ኤርትራ የህልውና አደጋ ውስጥ መግባቷን በቀላሉ መረዳት ይችላል፡፡ የኤርትራ የህልውና አደጋ እንደ አገር ያለመቀጠል ብቻ አይደለም፡፡ እንደ ህዝብ የተዘጋጀላቸው የበቀል በትር ጽኑ መሆኑ ነው፡፡ እንደ ህዝብ አደጋ ውስጥ ናቸው፡፡ አማራ ያው የህልውና ትግል እያካሄደ ይገኛል፡፡ አሁን በኬሚካል የጦር መሳሪያዎች ሁሉ ለመምታት ይሞከር ይሆናል፡፡ የሀዋሳ ቤዝ በርካታ የኬሚካል የጦር መሳሪያ ሲከዘን እንደነበረ ቀደም ባሉት ጊዜ ጀምሮ ተነግሯል፡፡ ኤርትራም አሁን ምርጫ ስለሌላት የህልውና ትግሉን ትቀላቀላለች፡፡ እንግዲህ የአማራ የህልውና ትግል አሁን ላይ እጥፍ ድርብ የህልውና ትግል ሆኖ ይገኛል፡፡ የኦሮሞና የትግሬ ሪፑብሊኮች አማራን ለሁለት ይካፈላሉ፤ ህዝቡን ያጠፋሉ፣ መሬቱን ይወራሉ፡፡ አለቀ፡፡ አማራ አናሳ ሆኖ እንኳን እንዲኖር እድል አይሰጡም፡፡ በቀጥታ ለማጥፋት ነው የሚሰሩት፡፡ በዚህም ምክንያት የአማራ ህዝብ ከመቸውም ጊዜ በላይ በአንድነት በጽናት የሚቆምበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ነው እንላለን፡፡ አሁን ኦነጉ አብይ እና ወያኔ የሚያቀነቅኑት የቀይ ባህር ጉዳይ የኢትዮጵያ ጉዳይ አይደለም፡፡ የታላቋ ትግራይ እና የኦሮሙማ የምስራቅ አፍሪካ ኤምፓየር ፍላጎቶች ናቸው፡፡
ስለዚህ አማራ ይሄ እቅድ እንዳይሳካ ከመቸውም ጊዜ በላይ መቃወም እና መታገል አለበት፡፡ ይሄ እቅድ ተሳካ ማለት አማራ አለቀለት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሰንደቅ አላማ ቢያሳዩ፣ የድሮ ታሪክ ቢያወሩ፣ እምዬ ኢትዮጵያ ቢሉ፣ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት ነው፡፡ አማራ የመኖር መብት እንደኦክሲጂን እንደሚያስፈልገው ሁሉ ለኤርትራዊያንም ህልውና ያስፈልጋቸዋል፡፡ ሁለቱም የመኖር መብት አላቸው፡፡ ስለሆነም የቀይ ባህር አጀንዳ ለአማራ ወጥመድ ነው፡፡ ይሄንን ለሁሉም እናስረዳ፡፡ በአካል ለምናገኛቸው አማሮች፣ በስልክም በምንም ለምናገኛቸው እናስረዳ፤ እንጻፍ፤ አቋም እንያዝ፣ አቋም እናስይዝ፡፡ ለምን? ታሪካዊ አደራ አለብን፡፡ ይሄ ትውልድ የአማራ ህዝብ እንዲቀጥል ታሪክ ትከሻው ላይ ታላቅ አደራ ጥሎበታል፡፡ ያለፉት ትውልዶች አደራቸውን ስለተወጡ ነው እኛ ተወልደን መኖር የቻልነው፡፡ ቀጣዩ ትውልዳችን እንዲወለድና እንዲኖር ደግሞ ይሄ ትውልድ አደራውን በብቃት መወጣት አለበት፡፡ በበሻሻ “አራዳ” እና በአድዋ ሰካሮች ተታሎ የትውልዱን፣ የህዝቡን ህልውና አደጋ ላይ በመጣል የሚተባበር ካለ እሱ ልሀጭ፣ ልፋጭ፣ አተላ፣ ጅላጅል፣ ዝክንትል፣ ዘባተሎ ይባላል፡፡( ምስጋናው አንዷለም )
