October 23, 2023 – Konjit Sitotaw
በአብን አመራር በሆነው የአብይ ተሿሚ ጋሻው መርሻ አስተባባሪነት 800 የፖስታ ቤት ሰራተኞች ከስራ ተባረሩ

በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ለመረጃኮም የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በመዋቅር ሰበብ ከ800 ሰራተኞች በላይ የአብን አመራር የአብይ ተሿሚ በሆነው ጋሻው መርሻ ፊርማ ከስራ መባረራቸውን አምርረው ተናግረዋል። እነዚሁ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ውስጥ ከ25 አመት በላይ የሰሩና ካለምንም ምክኛት በመዋቅር ሰበብ ከስራ መባረራቸው እና በአንድ ስብሰባ ጥሪ ካለምክኛት ድንገት ትፈለጋላችሁ ተብለው በዚሁ ጋሻው መርሻ በሚባል ግለሰብ አዲስ ተሿሚ ማስፈራራትና ዛቻ የተሰነዘረባቸው ሲሆን ይህ ጋሻው መርሻ የሚባል የአብን አመራር ከባለጊዜዎቹ በላይ በመሆን በተባረሩ ሰራተኞች ምትክ ከኦሮሚያ ክልል ምደባ እንዲደረግልን ጠይቀናል ሲል ካለሃፍረት ተናግሯል።
ድርጅቱ ከመቼውም ጊዜ በላየወ ትርፋማ ትርፋማና ተሸላሚ በሆነበት ባሁን ወቅት ሰራተኛ ግልፅ ባልሆነ ምክንያት 800 በላይ ሰራተኛ አሰናብቷል ሲሉ ሰራተኞቹ ይገልጻሉ። ድርጅቱ የመዋቅር ለውጥ ያስፈልገዋል ነባር ሰራተኞች መባረር አለባቸው ድርጅቱ በአዳዲስ ሰራተኞች መሞላት አለበት በሚል ጋሻው መርሻ በሃሳብ አመንጭነትና አስተባባሪነት በድርጅቱ ተቀጥረው በርካታ ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ ሰራተኞችን ካለምንም ማስረጃ እና ቅድመ ሁኔታ ሰራተኞቹ ከነቤተሰባቸው ጎዳና ላይ እንዲበተኑ አድርጓል። ጋሻው መርሻ ወደ ድርጅቱ ከመጣ ጀምሮ ሰራተኞች በስቃይ ላይ መሆናቸውን ሁሉም ሰራተኞች በስምምነት ይናገራሉ።
ውይይት ተብለው ተጠርተው የስንብት ደብዳቤ የተሰጣቸው የፖስታ አገልግሎት ሰራተኞች በጠቅላላ 800 በላይ ሰራተኞች ከ6-25 ኣመት በላይ ያገለገልን ሰራተኞች በቅዳሜ እለት ያለምንም ማስረጃ ተገፍተናል ሲሉ ምሬታቸውን ለመረጃ ኮም ገልጸዋል። በፖስታ ቤቱ ውስጥ ከሸራ መጎተት ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የስራ ድርሻ ላይ የደረሱና ፖስታ አገልግሎት ድርጅቱን ለትርፍ ያበቁ አሁን ላለበት ደረጃ ያደረሱ ሰራተኞች በተረኞቹና በአዳዲስ ተሿሚዎች የመባረራቸው ነገር በድርጅቱ ውስጥ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን ቀሪ ሰራተኞች የነገ እጣ ፈንታቸው አተያያቂ እንደሆነ ይናገራሉ።
ሰራተኞቹ እውቀትና ችሎታ እያላቸው እነሱን አባሮ በምትካቸው አዳዲስ ሰራተኞችን በትዕዛዝ ለማስገባት እየሰሩ እንደሆነ የሚነገርላቸው እነ ጋሻው መርሻ ለሕዝብ መብት እንታገላለን ብለው ሲያጭበረብሩ ኖረው ስልጣን ሲያገኙ ተሽቀዳድመው ከተረኞች ጋር በመመሳጠር ነባር ሰራተኞችን ካለምንም ማስረጃ ማባረራቸው ነገን ከተጠያቂነት እንደማይድኑ እና አብይ አሕመድም እንደሾማቸው በቅርቡ ሰበብ ፈልጎ እነሱንም እንደሚተፋቸው ሰራተኞቹ ይናገራሉ። ሰራተኞቹ ጋሻው መርሻ ውይይት ብሎ ተርቶን ድራማ ሰራብን ሲሉ አማረው ተናግረዋል።
ቀጥታ ከስራ ቦታቸው ለውይይት የተጠሩት ሰራተኞች ርክክብ ያላደረጉ ከመሆኑም በላይ የሰራተኞች ማሕበሩ ምንም ሰራተኛ አይባረርም በማለት ሲያዘናጋቸው እንደነበረና ሰራተኛ ማሕበሩ በራሱ በተረኞች የተሞላና በመንግስት ካድሬዎች የሚተዳደር መሆኑ 800 ሰራተኞች ተባረው ምንም ያልመሰለውና ለመከራከር እንኳን ያልደፈረ ጥርስ አልባ ነው ሲሉ ሰራተኞቹ አምርረው ይናገራሉ። መዋቅሩን ሰርቶ ለመንግስት ካቀረበ በኋላ አፀድቆ ሰራተኛን ወደማባረር ሮጦ የገባው ጋሻው መርሻ ሃላፊነቱን እና ተጠያቂነቱን እንደሚወስድ ሰራተኞቹ ተናግረዋል።
