ቀጥታ

የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሥልጣን እንዲለቁ እስራኤል ጠየቀች

Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 23 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 23 SECONDS1:23

Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBCሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?

Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. የተመድ ዋና ፀሐፊ ሥልጣን እንዲለቁ እስራኤል ጠየቀች
  2. ተመድ በነዳጅ ችግር ምክንያት ጋዛ ውስጥ ሥራ ሊያቆም ነው
  3. እስራኤል ታጋቾች ያሉበትን ለጠቆመ ወሮታ እከፍላለሁ ስትል በራሪ ወረቀት በተነች
  4. እስራኤል ሁለት ተጨማሪ ታጋቾች ከጋዛ መለቀቃቸውን አረጋገጠች
  5. የእስራኤል መከላከያ በጋዛ ባለፉት 24 ሰዓታት 400 ኢላማዎችን መምታቱን አስታወቀ
  6. የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ማክሮን እስራኤል ገቡ
  7. የተባበሩት መንግሥታት 35 ሰራተኞቹ በጋዛ እንደተገደሉበት ገለጸ
  8. በፍልስጤማዊያን ጉዳይ የተጠራው የካይሮ የሰላም ጉባኤ ያለ ውጤት ተበተነ
  9. ሐማስ፣ እስራኤል እና ምዕራባውያንን የተቹት የሳዑዲው ልዑል ለምን አነጋጋሪ ሆኑ?
  10. የተመድ ኤጀንሲዎች በጋዛ ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ
  11. እስራኤል በዌስት ባንክ የስደተኞች መጠለያ ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች
  12. እርዳታ የጫኑ የመጀመሪያዎቹ ተሸከርካሪዎች ጋዛ ገቡ
  13. እስራኤል በጋዛ ላይ የምታካሂደው ‘ወታደራዊ ዘመቻ’ ወራት ሊወስድ እንደሚችል አስታወቀች
  14. እስራኤል የጋዛን ጦርነት ካላቆመች ቀጠናው ከቁጥጥር ውጭ ሊወጣ እንደሚችል ኢራን አስጠነቀቀች
  15. ሆስፒታሎቿ በቁስለኞች እና በአስከሬን በተጨናነቁባት ጋዛ የአየር ጥቃቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል
  16. ግጭቱ ከጀመረ ቢያንስ 22 ጋዜጠኞች መገደላቸው ተገለጸ
  17. ፍልስጥኤምን የሚደግፉ ሰልፎች በተለያዩ አገራት ተካሄዱ

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 12:2112:21የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሥልጣን እንዲለቁ እስራኤል ጠየቀችAmbo GiladReutersCopyright: Reutersየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሥልጣናቸውን በፍቃዳቸው እንዲለቁ እስራኤል ጠየቀች።በድርጀቱ የእስራኤል አምባሳደር ጊላድ ኤርዳን ዋና ፀሐፊው “ሐማስ ጥቃቱን የከፈተው ያለ ምክንያት አይደለም” ማለታቸውን ተከትሎ ነው ጉቴሬዝ ሥልጣን እንዲለቁ የጠየቁት።አምባሳደሩ አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀ ቡድን በእስራኤላውያን ላይ ያደረሰውን ጥቃት ትክክለኛነት ለማሳየት ከሚጥሩት ጋር ምንም አይነት ንግግር ማድረግ አያስፈልግም ብለዋል።ዛሬ [ማክሰኞ] በኒው ዮርክ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ጉቴሬዝ “የፍልስጤም ሕዝብ ለ56 ዓመታት በአፋኝ በሆነ ግዞት ውስጥ ቆይቷል። መሬታቸው በፍጥነት በሰፈራ ሲከፋፈል እና በአመጽ ሲታመስ ተመልክተዋል። ምጣኔ ሃብታቸው ደቋል። ሕዝባቸው ተፈናቅሎ ቤታቸው ፈርሷል። ለስቃያቸው ፖለቲካዊ መፍትሄ ይገኛል በሚል የነበራቸው ተስፋ መሻታቸው ምላሽ አላገኝም” ሲሉ ተናግረዋል።antonioGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበዚህ የአንቶኒዮ ጉተሬዝ ንግግር ደስተኛ ያልሆኑት የእስራኤል አምባሳደር ጊላድ ኤርዳን በኤክስ (ትዊተር) ገጻቸው ላይ ዋና ፀሐፊው ጉቴሬዝ በአስቸኳይ ከመንግሥታቱ ድርጅት ሥልጣናቸው እንዲነሱ ጠይቀዋል።አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚህ ንግግራቸው ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ሳያወግዙ አላለፉም።“የፍልስጥኤማውያን ሕመም ሐማስ ላደረሰው አሰቃቂ ጥቃት ምክያት ሊሆን አይችልም፤ እንዲሁም ይህም ጥቃት በፍልስጥኤም ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን የጅምላ ቅጣትን ትክክል አያደርገውመ” ብለዋል።Article share tools
  2. የታተመዉ 11:0011:00የተባበሩት መንግሥታት በነዳጅ ችግር ምክንያት ጋዛ ውስጥ ሥራ ሊያቆም ነውበጋዛ እንደ ጤና ተቋማት ያሉ መሠረተ ልማቶች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበጋዛ እንደ ጤና ተቋማት ያሉ መሠረተ ልማቶች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።Image caption: በጋዛ እንደ ጤና ተቋማት ያሉ መሠረተ ልማቶች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የነዳጅ አቅርቦት ካላገኘ በጋዛ ውስጥ የሚያከናውነውን የሰብአዊ እርዳታ ተግባር ከነገ ረቡዕ ጀምሮ እንደሚያቋርጥ ገለጸ።በፍልስጥኤም ውስጥ የስደተኞች ጉዳይን የሚከታተለው የድርጅቱ ተቋም ዛሬ ማክሰኞ እንዳስጠነቀቀው በሰብአዊ ቀውስ ውስጥ በምትገኘው ጋዛ ሰርጥ ውስጥ ሥራውን ለማቆም ከጫፍ ደርሷል።የድርጅቱ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ሬዲዮ 4 እንደተናገሩት “በአስቸኳይ ነዳጅ ማግኘት ካልቻልን፣ ከነገ ረቡዕ ምሽት ጀምሮ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ የምናካሂደውን ሥራ እንቆማለን” ብለዋል።Article share tools
  3. የታተመዉ 10:5810:58ድንበር ተሻጋሪ ግጭቶችን በመሸሽ የሊባኖስ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቀሉየወደመ ታንክEPACopyright: EPAመቀመጫውን ሊባኖስ ባደረገው ሒዝቦላህ እና በእስራኤል መካከል የሚደረገው ግጭት መባባሱን ተከትሎ ድንበር ላይ ያሉ የሊባኖስ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀል ጀመሩ።የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንደሚለው ከሁለት ሳምንታት ገደማ በፊት በሐማስ እና በእስራኤል መካከል ግጭት ከተከሰተ ወዲህ ወደ 20ሺህ የሚጠጉ የሊባኖስ ዜጎች ከደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል ተፈናቅለዋል።ድንበር ላይ የሚገኙ የሊባኖስ መንደሮች፣ መደብሮች እና መንገዶች ጭር ብለው ታይተዋል።ታይሬ በምትባለው ከተማ መሄጃ የሌላቸው ነዋሪዎች ወደ መጠለያነት በተቀየሩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ።ስለ ሒዝቦላህ ተጨማሪ ለማንበብ ይህን ይጫኑ፡ ሊባኖስ የሚገኘው የእስራኤል ጠላት ሒዝቦላህ ማን ነው?Article share tools
  4. የታተመዉ 8:118:11እስራኤል ታጋቾች ያሉበትን ለጠቆመ ወሮታ እከፍላለሁ ስትል በራሪ ወረቀት በተነችእስራኤል የበተነችው በራሪ ወረቀትBBCCopyright: BBCእስራኤል የበተነችው በራሪ ወረቀትImage caption: እስራኤል የበተነችው በራሪ ወረቀትእስራኤል በሐማስ የታገቱ ሰዎች መገኛን ለጠቆመ ወሮታ እከፍላለሁ ስትል በራሪ ወረቀቶችን በጋዛ ላይ በተነች።የእስራኤል ጦር በሰሜናዊ ጋዛ በበተነው በራሪ ወረቀት፣ ታጋቾች የሚገኙበትን ትክክለኛ መረጃ ለጠቆመ ወሮታ እና የደኅንነት ጥበቃ እሰጣለሁ ብላለች።“ፍላጎትዎ በሰላም መኖር እና ለልጅዎ የተሻለ ሕይወትን የሚመኙ ከሆነ ሰብዓዊነት ያለው ተግባር በመፈጸም በአካባቢዎ የታገቱ ሰዎች ያሉበትን ቦታ ይጠቁሙ” ይላል እስራኤል በአረብኛ ቋንቋ የበተነችው በራሪ ወረቀት።እስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ በበተነችው ወረቀት ጥቆማ የሚሰጡ ሰዎች ማንነትን በምሥጢር እንደምትይዝ እና የገንዘብ ሽልማትም እንደምትሰጥ ቃል ገብታለች።እስራኤል የበተነችው በራሪ ወረቀት በአንዳንዶች በተቃውሞ ተቀዶ ተጥሏል።ReutersCopyright: Reutersእስራኤል የበተነችው በራሪ ወረቀት በአንዳንዶች በተቃውሞ ተቀዶ ተጥሏል።Image caption: እስራኤል የበተነችው በራሪ ወረቀት በአንዳንዶች በተቃውሞ ተቀዶ ተጥሏል።እስራኤል ይህን ትበል እንጂ የሰሜናዊ ጋዛ ነዋሪዎች በራሪ ወረቀቶቹን እየቀደዱ ሲበትኑ መመልከቱን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።አቡ ራማዳን የተባለ ሰው በራሪ ወረቀቱን ቀዶ በመበተን፤ “. . . የፈለጋችሁትን አድርጉ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በጋዛ ያለን ሰዎች አንንበረከክም። ከፈለጋችሁ በቦምብ ደብድቡን። ሕይወታችንን እና መኖሪያችንን ጥለን አንሰደድም” ሲል ከበውት የነበሩት ሰዎች በጭብጨባ ድጋፋቸውን ገልጸውለታል ብሏል ሮይተርስ በዘገባው።Article share tools
  5. የታተመዉ 8:098:09ሐማስ ባለፉት 24 ሰዓታት ከ700 በላይ ሰዎች ተገድለዋል አለበጋዛ በእስራኤል አየር ጥቃት የወደመ ነዳጅ ማደያReutersCopyright: Reutersበጋዛ በእስራኤል አየር ጥቃት የወደመ ነዳጅ ማደያImage caption: በጋዛ በእስራኤል አየር ጥቃት የወደመ ነዳጅ ማደያበሐማስ የሚተዳደረው የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ከ700 ያላነሱ ሰዎች ጋዛ ውስጥ ተገድለዋል አለ።የጤና ሚኒስቴሩ የሐማስ እና የእስራኤል ግጭት ከጀመረ ወዲህ የሟቾች ቁጥር ወደ 5 ሺህ 791 ደርሷል።ከ700 ያላሱት ሰዎች ባለፉት 24 ሰዓታት የመገደላቸው ዜና የተሰማው የእስራኤል ጦር ትናንት ከ400 ያላነሱ ዒላማዎችን ጋዛ ውስጥ በአየር መደብደቡን ካሳወቀ በኋላ ነው።የእስራል ጦር የዒላማ ያደረኩት ሐማስ የሚጠቀምባቸውን መሠረተ ልማቶችን ነው ይላል።Article share tools
  6. የታተመዉ 6:146:14″በቁርዓን እናምናለን፤ አንጎዳችሁም” በሐማስ ታግተው ከተለቀቁትጋዛ ውስጥ ታግተው ከነበሩት አንዷ ዮቼቭድ ሊቭሺትዝ አጋቾቻቸውEPACopyright: EPAጋዛ ውስጥ ታግተው ከነበሩት አንዷ ዮቼቭድ ሊቭሺትዝ አጋቾቻቸው “በቁርዓን እናምናለን” አንጎዳችሁም እንዳሏቸው ተናገሩ።በትናንትናው ምሽት የተለቀቁት የ85 ዓመቷ የዕድሜ ባለጸጋ በሞተር ሳይክል በማይመች ሁኔታም እንደተወሰዱና መተንፈስም ተቸግረው እንደነበር ገልጸዋል።በሐማስ ታጋቾች ሲወሰዱም ጌጣጌጦች እና ሰዓታቸው እንደተወሰደባቸው እንዲሁም መመታታቸውንም የገለጹት የዕድሜ ባለጸጋዋ “ሲዖል ውስጥ ነበርኩ” ብለዋል።ከሞተር ብስክሌቱ ከወረዱ በኋላ ሰላምታ የሰጧቸው ሰዎች ” በቁርዓን እናምናለን” ሲሉም ጉዳት እንደማያደርሱባቸው ነግረውኛል ብለዋል።እሳቸው እና ሌሎች 24 ሰዎች ወደ ዋሻዎች መወሰዳቸውን በአስተርጓሚ ልጃቸው በኩል ተናግረዋል።የዋሻዎቹ መተላለፊያዎች “እርጥበት የተሞላበት መሬት” መሆኑን መግለጻቸውንም ነው ልጃቸው የተናገረችው።ከሁለት ወይም ከሶስት ሰዓታት ገደማ በኋላ ከኪቡትዝ ኒር ኦዝ አካባቢ የመጡ አምስት ሰዎችን ወደተለየ ክፍል ወሰዷቸው ብለዋል።በስፍራው ጠባቂዎች፣ የድንገተኛ አደጋ የጤና ባለሙያ እንዲሁም ዶክተር መኖራቸውንም ገልጸዋል።እሳቸው እና ሌሎች ታጋቾች ንጽህናው በተጠበቀ መልኩ መያዛቸውንም አስረድተዋል።በዋሻዎች ውስጥ እያሉም ነጭ አይብ እና ኩከምበር እንዲመገቡ ይሰጣቸው እንደነበርም ነው በዚህ ወቅት ያስረዱት።የሐማስ ታጣቂዎችም እየተመገቡት የነበረው ተመሳሳይ ምግብም እንደነበርም ገልጸዋል። በጋዛ ስር ባሉ ዋሻዎች ውስጥ ፍራሽ ላይ ያድሩ እንደነበር እና ዶክተሩም በየሁለት እና ሶስት ቀናት ልዩነት ይጎበኘን ነበር ብለዋል።ወደ ጋዛ በሚወስደው የሞተር ሳይክል ጉዞ ላይ አደጋ የደረሰበት ታጋች ህክምና እንዳገኘም ገልጸዋል።የድንገተኛ አደጋ የጤና ባለሙያውም የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒቶች እንዳመጣላቸውም ነው የተናገሩትሐማስ ሁለቱን አረጋውያን ሴቶች ለመልቀቅ የወሰነው በሰብዓዊነት እና በጤና ምክንያት እንደሆነም አስታውቋል።የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ ግለሰቦቹን ለአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ድርጅት ተወካዮች ሰኞ ዕለት አስረክቧል።ታጋቾቹ የተለቀቁት በግብጽ እና ኳታር አሸማጋይነት ነው። እስራኤል ሁለቱን ታጋቾች ለማስመለስ ግብጽ በማሸማገሉ ረገድ ላደረገችው ጥረት እንዲሁም ቀይ መስቀል ስላበረከተው አስተዋጽኦ አመስግናለች።Article share tools
  7. የታተመዉ 4:404:40በጋዛ ባለፉት 24 ሰዓታት ከተፈጸሙ የአየር ጥቃት የተገኙ ምስሎችበአየር ጥቃቱ ለተገደሉ የቀብር ስነ ስርዓትReutersCopyright: Reutersየእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር በጋዛ ሰርጥ ባለፉት 24 ሰዓታት 400 ኢላማዎችን መምታቱን አስታውቋል።በዚህም የሐማስ ተዋጊዎች የሚገኙባቸው ዋሻዎች እና የቡድኑ የቅኝት ማማዎች ተመትተዋል ብሏል።ከስፍራው የተገኙ ምስሎች ህንጻዎች መውደማቸውን እና የቆሰሉ ፍልስጥኤማውያንንም አሳይተዋል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመችው ባለችው ጥቃት ከ5 ሺህ ፍልስጥኤማውያን በላይ መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በጋዛ ላይ የተፈጸመው የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበጋዛ ላይ የተፈጸመው የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty ImagesArticle share tools
  8. የታተመዉ 4:204:20የተባበሩት መንግሥታት 35 ሠራተኞቹ በጋዛ እንደተገደሉበት ገለጸየተባበሩት መንግሥታት ሰራተኞችReutersCopyright: Reutersየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 35 ሠራተኞች ጋዛ ሰርጥ ውስጥ እንደተገደሉበት አስታወቀ።የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች ኤጀንሲ ስድስት ሠራተኞች ባለፉት 24 ሰዓታት መገደላቸውን ገልጾ፣ በአጠቃላይም በባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ 35 የድርጅቱ ሠራተኞች ተገድለዋል ብሏል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ “በህልፈታቸው አዝነናል እናም በዚህ ወቅት የተቸገሩትን ለመርዳት እየጣሩ ካሉ የሥራ ባልደረቦቻችን ጋር አብረን እንቆማለን” ሲሉም በኤክስ (ትዊተር) ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እያደረገችው ያለው ወታደራዊ ዘመቻ ወራት ሊፈጅ እንደሚችል አስታውቃ፣ የአየር ጥቃቷንም አጠናክራ ቀጥላለች።በእነዚህ ጥቃቶች ከተገደሉት አብዛኞቹ ሕጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን ከጋዛ የጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።ከተገደሉት መካከል 2,055 ሕጻናት፣ 1,119 ሴቶች፣ 217አረጋውያን እንደሚገኙበት ተገልጿል። በአጠቃላይ የተገደሉ ሰዎች ከ5 ሺህ አልፏል።Article share tools
  9. የታተመዉ 3:273:27የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ማክሮን እስራኤል ገቡየፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ማክሮንReutersCopyright: Reutersየፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ እስራኤል አቅንተዋል።ቤን ጉሪዮን አለም አቀፍ ማረፊያ በዛሬው ዕለት የደረሱት ፕሬዚዳንቱ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሏል።የፕሬዚዳንቱ የጉብኝቱ አላማ አገራቸው ለእስራኤል ያላትን አጋርነት ለማሳየት፣ በሐማስ ቁጥጥር ስር ያሉ ታጋቾችን እንዲፈቱ ለማገዝ እና ግጭቱ እንዳይባባስ ለማድረግ መሆኑን አማካሪዎቻቸው ለሮይተርስ ተናግረዋል።ማክሮን በዚህ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁ በተጨማሪ ከእስራኤሉ ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ እና ከሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጋር ይመክራሉ ተብሏል።Article share tools
  10. የታተመዉ 3:113:11ሰበርየእስራኤል መከላከያ በጋዛ ባለፉት 24 ሰዓታት 400 ኢላማዎችን መምታቱን አስታወቀበጋዛ የደረሰው የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል መከላከያ በጋዛ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከ400 በላይ ኢላማዎችን መምታቱን አስታወቀ።በትናንትናው ዕለት የእስራኤል ጦር ጋዛ ውስጥ የሚገኙ 320 ዒላማዎችን መምታቱን ገልጾ በዚህም የሐማስ ተዋጊዎች የሚገኙባቸው ዋሻዎች እና የቡድኑ የቅኝት ማማዎች ወድመዋል ብሎ ነበር።እንደ መከላከያው ከሆነ በዚህኛው ጥቃት ኢላማ የተደረጉት ወደ እስራኤል ሮኬት ሊያስወነጭፉ የነበሩ የሐማስ ታጣቂዎች እንዲሁም እስራኤልን በባህር ለማጥቃት የሚያስችል የዋሻ መተላለፊያ ነው ብሏል።እንዲሁም ታጣቂዎች እንደ ጦር መሳሪያ ይጠቀሙበታል የተባለ በመስጊዶች ውስጥ የሚገኙ የማዘዣ ማዕከላት ኢላማ እንደተደረገባቸውም ገልጿል።መከላከያው “የንጹሃን ዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥም ጥረቱን ይቀጥላል” ሲልም አክሏል። እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እያደረገችው ያለው ወታደራዊ ዘመቻ ወራት ሊፈጅ እንደሚችል አስታውቃ የአየር ጥቃቷንም አጠናክራ ቀጥላለች።በነዚህ ጥቃቶች ከተገደሉት አብዛኛዎቹ ህጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን ከጋዛ የጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።ከተገደሉት መካከል 2,055 ሕጻናት፣ 1,119 ሴቶች፣ 217አረጋውያን እንደሚገኙበት ተገልጿል። በአጠቃላይ የተገደሉ ሰዎች ከ5 ሺህ አልፏል።Article share tools
  11. የታተመዉ 2:372:37በእስራኤል ማስጠንቀቂያ ከሰሜን ጋዛ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው- ተመድእስራኤል በሰሜን ጋዛ ለምታደርገው ወታደራዊ ዘመቻ አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲሸሹ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ፍልስጥኤማውያን ወደ ቀያቸው እየተመለሱ እንደሆነ የተባበሩት መንግስት አስታወቀ። በደቡብ ጋዛ በገጠማቸው አስከፊ ሁኔታ ምክንያትም ወደ ቤታቸው መመለስ መጀመራቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣን ተናግረዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  12. የታተመዉ 1:271:27እስራኤል ሁለት ተጨማሪ ታጋቾች ከጋዛ መለቀቃቸውን አረጋገጠችበጋዛ ውስጥ ታግተው የነበሩ ሁለት እስራኤላዊ አረጋውያን ሴቶችGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበጋዛ ውስጥ ታግተው የነበሩ ሁለት እስራኤላዊ አረጋውያን ሴቶች ሐማስ መልቀቁን እስራኤል አረጋገጠች።ግለሰቦቹ የ79 ዓመቷ ኑሪት ኩፐር እና የ85 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ የሆኑት ዮቼቭድ ሊቭሺትዝ ቴልአቪአቭ መግባታቸውም ተገልጿል።ሐማስ ሁለቱን አረጋውያን ሴቶች ለመልቀቅ የወሰነው በሰብዓዊነት እና በጤና ምክንያት እንደሆነም አስታውቋል።የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ ግለሰቦቹን ለአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ድርጅት ተወካዮች ሰኞ ዕለት አስረክቧል።ታጋቾቹ የተለቀቁት በግብጽ እና ኳታር አሸማጋይነት ነው። እስራኤል ሁለቱን ታጋቾች ለማስመለስ ግብጽ በማሸማገሉ ረገድ ላደረገችው ጥረት እንዲሁም ቀይ መስቀል ስላበረከተው አስተዋጽኦ አመስግናለች።ሁለቱ የዕድሜ ባለጸጎች ቢለቀቁም የግለሰቦቹ ባለቤት የሆኑት የ85 እና የ83 ዓመት አረጋውያን አሁንም በጋዛ ውስጥ በሐማስ ታግተው እንደሚገኙ የእስራኤል ባለስልጣናት ገልጸዋል።Article share tools
  13. የታተመዉ 1:051:05አሜሪካ የጋዛ የተኩስ አቁም ጥሪን ተቃወመችየብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃለ አቀባይ ጆን ኪርቢGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት መደረግ የለበትም ስትል አሜሪካ ተቃወመች።የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ጊዜው አሁን አይደለም ሲሉም የዋይት ሐውስ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ገልጸዋል።”የተኩስ ማቆም ስምምነት ወቅቱ አሁን ነው ብለን አናምንም” በማለት የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃለ አቀባይ ጆን ኪርቢ ሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።”እስራኤላውያን ራሳቸውን የመከላከል መብት አላቸው። ከሐማስ አመራሮች ጋር ተያይዞ አሁንም የሚቀሩ ስራዎች አሉ” በማለት የተናገሩት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ቃለ አቀባይ ማቲው ሚለር ናቸው።አክለውም “ይህንን በተመለከተ የምናከናውነው ተግባር ወደ ጋዛ ሰብዓዊ እርዳታ በማግኘት ላይ ያተኮረ ነው” ብለዋል።አሜሪካ ይህንን ግጭት በዋነኝት እንዲከታተሉ ዴቪድ ሳተርፊልድ የተባሉ ልዑክ መሾሟን ሚለር ገልጸዋል። ልዑኩም ” የሰብዓዊ እርዳታ ቀጣይነት እንዲኖረው የማድረግ እና በጋዛ ውስጥ ያሉ ሲቪሎች ጉዳት የማይደርስባቸውን ቦታዎችንም ለመለየት እየሰራን ነው” ብለዋል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ኤጀንሲዎች በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ያለው ሁኔታ እየከፋ መምጣቱን ተከትሎ ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ከሰሞኑ ጥሪ አቅርበዋል።የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና የዓለም የጤና ድርጅትን ጨምሮ አምስት የተመድ ኤጀንሲዎች የጋዛን ሁኔታ “አሰቃቂ” ሲሉም በጋራ ባወጡት መግለጫ አስፍረዋል።እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ አስገብቻታለሁ ባለቻት ጋዛ ሰርጥ የተጠናከረ ጥቃት እንደሚቀጥል እያስጠነቀቀች ባለችበት ወቅትም ነው የተባበሩት መንግሥታት ግጭቱ እንዲረግብ እየተማጸነ ያለው።Article share tools
  14. የታተመዉ 0:150:15በፍልስጥኤማውያን ላይ የተባባሰው የእስራኤላውያን ሰፋሪዎች ጥቃትአቤድ ዋዲ ለቀብር እየተዘጋጀ ነበር አንድ መልዕክት የደረሰው። ምስሉ ከጓደኛው ነበር ደረሰው። በምስሉ ላይ ጭምብል ያጠለቁ ሰዎች ይታያሉ። መጥረቢያ፣ ነዳጅ እና የእንጨት መጋዝ ይዘዋል። በእብራይስጥ እና በአረብኛ ደግሞ መልዕክት ሰፍሮበታል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  15. የታተመዉ 0:150:15የጋዛን ሰፈር ወደ ፍርስራሽ ክምርነት የቀየረው ጥቃትአል ዛህራ ከጋዛ መናገሻዎች አንዷ ነበረች። ጋዛ አሉኝ ከምትላቸው ዩኒቨርስቲዎች ‘የፍልስጥኤም ዩኒቨርስቲ እና ኡማህ ዩኒቨርስቲ’ በዚህች ሰፈር ነው የሚገኙት። በአንድ ወቅት ጋዛ በጥሩነት ከምትጠቅሳቸው ሰፈሮች አንዷ ነበረች። አሁን ያ ሁሉ ታሪክ ሆኗል። አል ዛህራ ወደ ፍርስራሽ ክምርነት ተቀይራለች።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  16. የታተመዉ 13:10 23 ጥቅምት 202313:10 23 ጥቅምት 2023የእስራኤል ራስን የመከላከል መብት ገደቦች አሉበት፡ ጆሴፍ ቦሬልጆሴፍ ቦሬልBBCCopyright: BBCጆሴፍ ቦሬልImage caption: ጆሴፍ ቦሬልየአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል እስራኤል ያላት ራስን የመከላከል መብት ገደቦች አሉበት በማለት ተናገሩ።ቦሬን ላክሰንበርግ ውስጥ ከተካሄደው የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ስበሰባ በኋላ እንደተናገሩት “ገደቦቹ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት የተቀመጡ ናቸው።“እስራኤል እራሷን የመከላከል መብት አላት፤ ይህም በዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ መሠረት ተግባራዊ መሆን አለበት። ይህ እንዲሁ በቃል ብቻ የሚነገር መሆን የለበትም።“በዚህም መሠረት ለሲቪል ሰዎች የሚቀርበውን ውሃ እና የኤሌክትሪክ ኃይል ማቋረጥ አይቻልም። በዓለም አቀፍ ሰብአዊነት ሕግ ስር በከበባ ስር ያለ ሕዝብ ውሃ እና ኤሌክትሪክ እንዳያገኝ ማድረግ አይቻልም” ብለዋል።ቦሬል ጨምረውም ሰብአዊ እርዳታን ጭነው ከግብፅ ወደ ጋዛ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው ተሽከርካሪዎች በቂ እንዳልሆኑ እና በተለይ ነዳጅ ለጋዛ በጣም አስፈላጊ አቅርቦት መሆኑን ተናግረዋል።“ጋዛ ውስጥ እየሆነ ያለው በሰብአዊነት ላይ የሚደርሰው መቅሰፍት ነው። ሰብአዊ እርዳታ ማቅረብም በእጅጉ አስፈላጊ ጉዳይ ነው” ሲሉ ቦሬል አሳስበዋል።Article share tools
  17. የታተመዉ 9:33 23 ጥቅምት 20239:33 23 ጥቅምት 2023ባለፉት 24 ሰዓታት ጋዛ ውስጥ 436 ሰዎች ተገድለዋል፡ የጋዛ ጤና ሚኒስቴርጋዛ ከአየር ድብደባ በኋላReutersCopyright: Reutersጋዛ ውስጥ የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር አንዳስታወቀው የእስራኤል የአየር ጥቃት በቀጠለበት ሁኔታ በአንድ ቀን ውስጥ 436 ሰዎች ተገድለዋል።ሁለት ሳምንት ባለፈው የአየር ጥቃት ጋዛ ውስጥ የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር ከ5,000 ማለፉ ተገልጿል።በጋዛ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር በአሁኑ ወቅት 5,087 የደረሰ ሲሆን፣ ትናንት ብቻ የሟቾች ቁጥር በ436 ጨምሯል።ከተገደሉትመካከል 2,055 ሕጻናት፣ 1,119 ሴቶች፣ 217አረጋውያን እንደሚገኙበትተገልጿል።በአስራኤል የአየር ጥቃት ከተገደሉት ሰዎች በተጨማሪ ከ15,273 በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።በጋዛ የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር ግዛቲቱን በሚቆጣጠረው እና ከእስራኤል ጋር ግጭት ውስጥ በገባው በሐማስ ቁጥጥር ስር የሚገኝ ነው።እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈጽመው የቦምብ ድብደባ ትናንትና ቀን እና ሌሊቱንም የቀጠለ ሲሆን፣ ከጋዛ የወጡ ፎቶዎች የወደሙ ሕንጻዎችን እና በጥቃቱ የተጎዱ ሰዎች ከሆስፒታሎች አቅራቢያ ባሉ መንገዶች ላይ ተኝተው አሳይተዋል።ዛሬ ጠዋት የእስራኤል ጦር ሠራዊት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ጋዛ ውስጥ የሚገኙ 320 ዒላማዎችን መምታቱን ገልጿል። በዚህም የሐማስ ተዋጊዎች የሚገኙባቸው ዋሻዎች እና የቡድኑ የቅኝት ማማዎች ወድመዋል።የአስራኤል ሠራዊት በሲቪሎች ላይ የደረሰን ጉዳት በተመለከተ በሰጠው ምላሽ፣ ዓለም አቀፍ ሕግን በመከተል “በሲቪሎች ላይ የሚደርስን ጉዳት ለማስወገድ አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ ይደረጋል” ብሏል።Article share tools
  18. የታተመዉ 9:07 23 ጥቅምት 20239:07 23 ጥቅምት 2023እስራኤል በጋዛ ስለምታደርገው ዘመቻ እስካሁን የምናውቀውባለፉት 24 ሰዓታት የእስራኤል ወታደሮች ወደ ጋዛ ወረራ መፈጸማቸው ተገልጿል። እስካሁን የምናውቃቸው ዋና ዋና ነጥቦች ቀጣዮቹ ናቸው።እሑድ:• እሑድ የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ሰርጥ ምዕራባዊ ክፍል ገብተው ታጋቾችን እንደፈለጉ፣ አካባቢውን ከአሸባሪዎች እና ከመሣሪያ ለማጽዳት እንደሞከሩም እስራኤል አስታውቃለች።• የእስራኤል መከላከያ ኃይል እንዳለው ሚሳኤሎች በሐማስ ተተኩሰውባቸዋል። አንድ የእስራኤል ወታደር እንደተገደለ እና ሦስት ወታደሮች እንደቆሰሉ ተገልጿል።• የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ እንዳለው ይህ የተከሰተው በደቡባዊ ጋዛ ኻን ዩኒስ ነው። ይህ ከተማ ፍልስጤማውያን ለደኅንነታቸው ሲሉ ትተውት እንዲወጡ የተጠየቀ ነው። የእስራኤል ወታደሮች ወደ “በበርካታ ሜትሮች” ጥሰው እንደገቡም ተገልጿል።• የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ እንዳለው “ከወራሪው ኃይል ጋር ተዋግቷል።” ሁለት ቡልዶዘሮች እና ታንክ እንዳወደሙም ገልጸዋል። እስራኤላዊ ወታደሮች መኪናቸውን ትተው በእግራቸው ወደ ምሥራቃዊ አቅጣጫ ሸሽተዋል።ሰኞ:• የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ ዳንኤል ሐጋሪ እንዳሉት፣ እስራኤል በአንድ ምሽት ብዙ ወረር በጋዛ ላይ ፈጽማለች።• ቃል አቀባዩ አክለውም “ምሽት ላይ ዘመቻው ሲካሄድ በታንክ እና በእግረኞች ነው። አሸባሪዎችን የገደሉት እነዚህ ዘመቻዎች ለቀጣይ የጦርነቱ ክፍል የተደረገ ዝግጅትን ኢላማ አድርገዋል። የታገቱ ሰዎችን ለማግኘት እና የደኅንነት መረጃ ለማግኘትም ጠልቀን ወደ ውስጥ ገብተዋል” ብለዋል።ይህ የእስራኤል ወታደሮች ወደ ጋዛ ዘልቀው የገቡበት የመጀመሪያው ጊዜ አይደለም። በግጭቱ የመጀመሪያው ሳምንት እስራኤል ወታደሮቿ እና ታንኮች ወደ ጋዛ ሰርጥ ሐማስን ለመዋጋት እና ወደ እስራኤል የሚወነጨፉ ሚሳኤሎችን ለማግኘት እንደገቡ ገልጻለች።Article share tools
  19. የታተመዉ 9:06 23 ጥቅምት 20239:06 23 ጥቅምት 2023በጋዛ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ5 ሺህ አለፈበጋዛ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ5,000 ማለፉን የፍልስጤማ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።በጋዛ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 5,087የደረሰ ሲሆን፣ ከትላንትናው የሟቾች ቁጥር በ436ጨምሯል።ከተገደሉት መካከል 2,055ሕጻናት፣ 1,119ሴቶች፣ 217አረጋውያን እንደሚገኙበት ተገልጿል።ከ15,273በላይ ሰዎች ተጎድተዋል።Article share tools
  20. የታተመዉ 9:03 23 ጥቅምት 20239:03 23 ጥቅምት 2023ሕይወት በጋዛ፡ ከቤት ተፈናቅሎ መጠለያ ፍለጋ መንከራተትመስከረም 26/2016 ዓ.ም. የተፈጸመባትን ጥቃት ተከትሎ ባለፉት ሁለት ሳምንታት እስራኤል እያካሄደችው ባለው የአየር ጥቃት ምክንያት ጋዛ ውስጥ ከሚገኙ ነዋሪዎች መካከል ከ600 ሺህ በላይ ሰዎች ከቤታቸው ተፈናቅለዋል። ከእነዚህ መካከል ቢቢሲ ሁለቱን በማግኘት አሁን ስላሉበት ሁኔታ ጠይቋቸዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools