https://www.bbc.com/amharic/live/news-67184520
Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች
- BBC
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59
Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ
- BBC
Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች
- BBC
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች
- BBC
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 23 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 23 SECONDS1:23
Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBCሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?
- BBC
Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBC
ጭምቅ ሃሳብ
- ሶሪያ 8 ወታደሮቼ በእስራኤል ተገደሉብኝ አለች
- የዮርዳኖስ ንግሥት ራኒያ ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙሃንን ተቹ
- የሶሪያ ወታደራዊ ኢላማዋችን ማጥቃቷን እስራኤል አስታወቀች
- የተመድ ዋና ፀሐፊ ሥልጣን እንዲለቁ እስራኤል ጠየቀች
- ተመድ በነዳጅ ችግር ምክንያት ጋዛ ውስጥ ሥራ ሊያቆም ነው
- እስራኤል ታጋቾች ያሉበትን ለጠቆመ ወሮታ እከፍላለሁ ስትል በራሪ ወረቀት በተነች
- እስራኤል ሁለት ተጨማሪ ታጋቾች ከጋዛ መለቀቃቸውን አረጋገጠች
- የእስራኤል መከላከያ በጋዛ ባለፉት 24 ሰዓታት 400 ኢላማዎችን መምታቱን አስታወቀ
- የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ማክሮን እስራኤል ገቡ
- የተባበሩት መንግሥታት 35 ሰራተኞቹ በጋዛ እንደተገደሉበት ገለጸ
- በፍልስጤማዊያን ጉዳይ የተጠራው የካይሮ የሰላም ጉባኤ ያለ ውጤት ተበተነ
- ሐማስ፣ እስራኤል እና ምዕራባውያንን የተቹት የሳዑዲው ልዑል ለምን አነጋጋሪ ሆኑ?
- የተመድ ኤጀንሲዎች በጋዛ ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ
- እስራኤል በዌስት ባንክ የስደተኞች መጠለያ ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች
- እርዳታ የጫኑ የመጀመሪያዎቹ ተሸከርካሪዎች ጋዛ ገቡ
- እስራኤል በጋዛ ላይ የምታካሂደው ‘ወታደራዊ ዘመቻ’ ወራት ሊወስድ እንደሚችል አስታወቀች
- እስራኤል የጋዛን ጦርነት ካላቆመች ቀጠናው ከቁጥጥር ውጭ ሊወጣ እንደሚችል ኢራን አስጠነቀቀች
- ሆስፒታሎቿ በቁስለኞች እና በአስከሬን በተጨናነቁባት ጋዛ የአየር ጥቃቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል
- ግጭቱ ከጀመረ ቢያንስ 22 ጋዜጠኞች መገደላቸው ተገለጸ
- ፍልስጥኤምን የሚደግፉ ሰልፎች በተለያዩ አገራት ተካሄዱ
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 5:375:37በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በእስራኤል መካከል ያለው ውዝግብ እየተካረረ ነው
EPACopyright: EPAአንቶኒዮ ጉተሬዝImage caption: አንቶኒዮ ጉተሬዝማክሰኞ ምሽት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በእስራኤል እና በጋዛ ጦርነት ላይ ለመወያየት በተቀመጠው ስብሰባ ምክንያት በድርጅቱ እና በቴል አቪቭ መካከል ውዝግብ ተፈጠሯል።የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ከ1400 በላይ ሰዎች የተገደሉበት የሐማስ ጥቃት “ዝም ተብሎ የተፈጠረ” አይደለም ሲሉ እስራኤል “ለ56 ዓመታት በፍልስጥኤም ያደረገችውን ወረራ” በማመልከት ተናግረዋል።አስተያየቱን ተከትሎ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሊ ኮኸን “ለእንዲህ ዓይነቱ እልቂት ምንም ምክንያት መቅረብ የለበትም” ሲሉ ቁጣ አዘል ምላሽ ሰጥተዋል።”በየትኛው ዓለም ነው የምትኖረው?” ሲሉ ለጉተሬዝ ጥያቄ አቅርበዋል። ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኃላፊ ጋር የሚያደርጉትን ስብሰባ እንደሰረዙም አክለው ገልጸዋል።በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የእስራኤል አምባሳደር የሆኑት ጊላድ ኤርዳን “የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ለመምራት ብቁ አይደሉም” በማለት ጉተሬዝ ስልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል።ጉተሬዝ በኋላ ላይ በኤክስ ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ “የፍልስጥኤም ሕዝብ ቅሬታ በሐማስ ዘግናኝ ጥቃት ሊረጋግጥ አይችልም። . . . አስከፊዎቹ ጥቃቶች ደግሞ በጅምላ ፍልስጥኤማዊያንን በመቅጣት ሊያረጋግጥ አይችልም” ብለዋል።አሁን ደግሞ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለስልጣናት ቪዛ እንደምትከለክል እስራኤል አስታውቃለች። ኤርዳን ለእስራኤሉ ሬዲዮ ሃሳባቸውን የሰጡት ኤርዳን የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሐፊ ማርቲን ግሪፍትስ ቪዛ መከልከላቸውን ተናግረዋል። “እነሱን የምናስተምርበት ጊዜ ደርሷል” ሲሉ ኤርዳን ገልጸዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:553:55የእስራኤል የአየር ጥቃት ያደረሰው ጉዳትእስራኤል በጋዛ ሰርጥ በሚገኘው ዃን ዩኒስ ትናትን ምሽት ያደረሰችውን ጥቃት የሚያሳይ ምስል ደርሶናል።ቴል አቪቭ በጥቃቱ ዒላማ ያደረገችው የሐማስ መሠረተ ልማቶችን መሆኑን አስታውቃለች።
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤል የአየር ጥቃት ያደረሰው ጉዳትImage caption: የእስራኤል የአየር ጥቃት ያደረሰው ጉዳት
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤል የአየር ጥቃት ያደረሰው ጉዳትImage caption: የእስራኤል የአየር ጥቃት ያደረሰው ጉዳት
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤል የአየር ጥቃት ያደረሰው ጉዳትImage caption: የእስራኤል የአየር ጥቃት ያደረሰው ጉዳትArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:273:27ሶሪያ 8 ወታደሮቼ በእስራኤል ተገደሉብኝ አለች
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesሶሪያ 8 ወታደሮቿ በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደላቸውን አስታወቀች።ዳራ በተባለው የሶሪያ ግዛት በተፈጸመው የአየር ጥቃት ተጨማሪ 7 ወታደሮች መቁሰላቸው ተገልጿል።የሶሪያ መንግሥት የዜና ወኪል ሳና እንዳለው ጥቃቱ የተፈጸመው ትናንት ረቡዕ ከእኩለ ለሊት በኋላ ነው።የእስራኤል ጦር የአየር ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጦ፤ በሶሪያ የአየር ጥቃት ዒላማ አድርጌ የነበረው ወታደራዊ መሠረተ ልማቶችን ነው ብሏል።እስራኤል ጥቃቱን የፈጸመችው ከሶሪያ ሮኬቶች ከተተኮሱባት በኋላ ሮኬት እና ሞርታር ማስወንጨፊያዎችን መምታቷን አስታውቃለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:223:22በጋዛ በአንድ ሌሊት 80 ሰዎች መገደላቸውን በሐማስ የሚመራው መንግሥት አስታወቀእስራኤል ትላንት ምሽት በጋዛ ሰርጥ በሰነዘረችው የአየር ጥቃት በትንሹ 80 ሰዎች መገደላቸውን በሐማስ የሚመራው መንግሥት አስታወቀ።የመንግሥት የሚዲያ ፅህፈት ቤት ያወጣውን መግለጫ ጠቅሶ እስራኤል ባደረሰችው ጥቃት ከ80 በላይ ሰዎች መገደላቸውን እና በመቶዎች የሚቆጠሩት መቁሰላቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።ጥቅምት 7 የሐማስ ታጥቂዎች ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ የሚገኘው የታጣቂ ቡድን ዒላማ አድርጋ የአየር ድብደባ እየፈጸመች ነው።ከዚያ ወዲህ በጋዛ ከ5,800 በላይ ሰዎች መገደላቸውን በሐማስ የሚመራው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:142:14የጋዛ ሆስፒታሎች የህክምና ክፍሎቻቸውን መዝጋት ጀመሩ
EPACopyright: EPAለሆስፒታሎች እርዳታ ቢደርስም እስካሁን ነዳጅ አላገኙምImage caption: ለሆስፒታሎች እርዳታ ቢደርስም እስካሁን ነዳጅ አላገኙምበጋዛ የሚገኙ ሆስፒታሎች የሚያስፈልጋቸውን ነዳጅ ማግኘት ባለመቻላቸው ከድንገተኛ ክፍሎቻቸው በስተቀር ሁሉንም የህክምና ክፍሎቻቸውን ዘጉ።”ያላቸውን ነዳጅ ለመቆጠብ በማሰብ በሆስፒታሉ ውስጥ ያሉ አብዛኞቹ ክፍሎች መዘጋታቸውን” የቢቢሲው ባልደረባ ሩሽዲ አቡአሉፍ ተናግሯል።እንደ የኩላሊት እጥበት ያሉ ህክምናዎች ላይ ትኩረት መደረጉን በመግለጽ “የህይወት በማዳን ላይ ብቻ ያተኮሩ ሆነዋል” ሲል ገልጿል።በጣም አስከፊ ሁኔታ መኖሩንም አክሏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:361:36አውስትራሊያ ወታደሮቿን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ላከችአውስትራሊያ ተጨማሪ ወታደራዊ ኃይሏን ወደ መካከለኛው ምስራቅ እያሰማራች ነው።የአገሪቱ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪቻርድ ማርለስ እንዳሉት ለጥንቃቄ በሚል ሁለት አውሮፕላኖች እና ወታደሮችን ወደ ቀጠናው ልከዋል።ማርለስ ምን ያህል ወታደሮች እንደሚላኩ ባይናገሩም “ትልቅ ቁጥር” መሆኑን ግን አረጋግጠዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:321:32የዮርዳኖስ ንግሥት ራኒያ ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙሃንን ተቹ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesንግሥት ራኒያ ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙሃንን ተቹImage caption: ንግሥት ራኒያ ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙሃንን ተቹየዮርዳኖስ ንግሥት ራኒያ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ከእስራኤል እና ከጋዛ ጦርነት ጋር በተያያዘ የፍልስጤም እና የአይሁድ ማህበረሰቦችን ጉዳይ በአንድ ዓይን አይዘግቡትም ሲሉ ተችተዋል።ማክሰኞ ከአማን በተለቀቀው የሲኤንኤን ቃለ ምልልስ ላይ “ዛሬ ዓለም ላይ የሚታየው በአንድ ዓይን ያለመዘገብ ነገር አሳዛኝ ነው። ጥቅምት 7 የተፈፀመውን ጥቃት በተመለከተ ጠንከር ያለ ውግዘት ቢታይም አሁን እየሆነ ስላለው ነገር የሚሰማው ውግዘት በጣም ትንሽ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።“አፋጣኝ የተኩስ ማቆም ጥሪ ለምን አልተደረገም? ዛሬም በሰው ልጆች ላይ አስደንጋጭ ስቃይ ሲደርስ እያየን ነው። ታዲያ ለምንድነው ትርክቱ ሁሌም ወደ እስራኤላውያን የሚያዘነብለው?”“ቤተሰብን፣ ሙሉ ቤተሰብን በጠመንጃ መግደል ስህተት እንደሆነ እየተነገረን ነው። ቤተሰቡን በአየር ጥቃት መግደል ግን ምንም አይደለም…. ይህ ለአረቡ ዓለም አስደንጋጭ ነው” ብለዋል።“በዘመናዊው ታሪክ ውስጥ እንዲህ ዓይነት የሰው ልጆች መከራ ሲደርስ ይህ የመጀመሪያው ነው። ዓለም ግን የተኩስ አቁም ጥሪ እንኳን አያደርግም። ዝምታው በዝቷል”ሲሉ አክለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:301:30በምስል፡ የጋዛ ነዋሪዎች ጉዳት የደረሰባቸውን ለማዳን እየሞከሩ ነው
Anadolu via Getty ImagesCopyright: Anadolu via Getty Imagesየጋዛዋ ዃን ዩኒስ ከተማ በእስራኤል ተደጋጋሚ የአየር ጥቃት ደርሶባታልImage caption: የጋዛዋ ዃን ዩኒስ ከተማ በእስራኤል ተደጋጋሚ የአየር ጥቃት ደርሶባታልየጋዛ ነዋሪዎች በእስራኤል የአየር ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸውን ሕይወት ለማትረፍ እየሞከሩ ነው።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ ተጨማሪ ነዳጅ ካላገኘ የእርዳታ ሥራው እንደሚቋረጥ አስታውቋል።አንድ የእስራኤል ቃል አቀባይ በበኩላቸው ሐማስ ነዳጅ እያከማቸ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesነዋሪዎች እና የእርዳታ ሠራተኞች ከፈረሰ ህንጻ ስራ ጉዳት የደረሰባቸውን ለማዳን እየተረባረቡ ነውImage caption: ነዋሪዎች እና የእርዳታ ሠራተኞች ከፈረሰ ህንጻ ስራ ጉዳት የደረሰባቸውን ለማዳን እየተረባረቡ ነው
ReutersCopyright: Reutersሕይወታቸው ያለፉት የቀበር ስነ ስርዓትም በመከናወን ላይ ይገኛልImage caption: ሕይወታቸው ያለፉት የቀበር ስነ ስርዓትም በመከናወን ላይ ይገኛል
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል ጋዛን በከበባ ውስጥ ካስገባች ሁለት ሳምንታት አለፉImage caption: እስራኤል ጋዛን በከበባ ውስጥ ካስገባች ሁለት ሳምንታት አለፉArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:420:42አሜሪካ እስራኤልን ለመከላከል ምን ልታደርግ ትችላለች?አሜሪካ እና እስራኤል፣ እስራኤል እና አሜሪካ፤ አንቺ ትብስ አንተ ትብስ መባባለቸው ሁለት አገር መሆናቸውን ያስረሳል። ወዳጅነታቸው ጥብቅ ነው። ጆ ባይደን በድርጊትም በንግግርም ይህን አሳይተዋል፤ ገልጸውታልም። በድርጊት የጦር ጄት የሚሸከሙ መርከቦችን ወደ ሜዲትራኒያን ባሕር በማስጠጋት፣ በቃል ደግሞ ቴል አቪቭ ተገኝተው ደግሞ እስራኤልን “በማንኛውም ሁኔታ ከጎንሽ ነን” በተደጋጋሚ ብለዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:410:41የሶሪያ ወታደራዊ ኢላማዋችን ማጥቃቷን እስራኤል አስታወቀችረቡዕ ማለዳ ላይ የእስራኤል ተዋጊ ጄቶች የሶሪያ ጦር ወታደራዊ መሠረተ ልማቶችን እና የሞርታር ማስወንጨፊያዎችን ማጥቃታቸውን የእስራኤል ጦር አስታወቀ።እርምጃው ማክሰኞ እስራኤል ላይ ለተሰነዘረው ጥቃት ምላሽ ነው ሲልም ጦሩ አክሏል።በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮች ይፋ አልተደረጉም።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:410:41እስራኤል በጄኒን የድሮን ጥቃት ሰነዘረች
EPACopyright: EPAእሑድ በተካሄደ የእስራኤል የአየር ጥቃት ጄኒን ውስጥ ሁለት ወጣቶች ተገድለዋልImage caption: እሑድ በተካሄደ የእስራኤል የአየር ጥቃት ጄኒን ውስጥ ሁለት ወጣቶች ተገድለዋልየእስራኤል መከላከያ ሰራዊት “ከአጭር ጊዜ በፊት” በዌስት ባንክ ጄኒን ከተማ አቅራቢያ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በተፈጠረ ግጭት የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መፈጸሙን በማህበራዊ ሚዲያ አስታወቀ።በጄኒን ሰዎች “ከታጠቁ አሸባሪዎች” ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሁለት ተይዘዋል ሲል አክሏል።ግጭቱ የተቀሰቀሰው እስራኤል በጄኒን የስደተኞች ካምፕ አካባቢ ጥበቃ እያደረገች ባለችበት ወቅት የፍልስጥኤም ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው በእስራኤል ወታደሮች ላይ ቦንቦችን ከወረወሩ በኋላ መሆኑን ቴል አቪቭ አስታውቃለች።እስራኤል በመግለጫዋ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃቱ እና በተኩስ ልውውጡ የደረሰው ጉዳት ተለይቷል ብላለች።የእስራኤል ወታደሮች ላይ ጉዳት አለመድረሱም ታውቋል።እስራኤል “የአሸባሪዎች ግቢ” ባለችውና በጄኒን በሚገኘ መስጊድ ላይ እሑድ ዕለት የአየር ጥቃት ሰነዘራ ነበር።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 12:21 24 ጥቅምት 202312:21 24 ጥቅምት 2023የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሥልጣን እንዲለቁ እስራኤል ጠየቀች
ReutersCopyright: Reutersየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሥልጣናቸውን በፍቃዳቸው እንዲለቁ እስራኤል ጠየቀች።በድርጀቱ የእስራኤል አምባሳደር ጊላድ ኤርዳን ዋና ፀሐፊው “ሐማስ ጥቃቱን የከፈተው ያለ ምክንያት አይደለም” ማለታቸውን ተከትሎ ነው ጉቴሬዝ ሥልጣን እንዲለቁ የጠየቁት።አምባሳደሩ አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀ ቡድን በእስራኤላውያን ላይ ያደረሰውን ጥቃት ትክክለኛነት ለማሳየት ከሚጥሩት ጋር ምንም አይነት ንግግር ማድረግ አያስፈልግም ብለዋል።ዛሬ [ማክሰኞ] በኒው ዮርክ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ጉቴሬዝ “የፍልስጤም ሕዝብ ለ56 ዓመታት በአፋኝ በሆነ ግዞት ውስጥ ቆይቷል። መሬታቸው በፍጥነት በሰፈራ ሲከፋፈል እና በአመጽ ሲታመስ ተመልክተዋል። ምጣኔ ሃብታቸው ደቋል። ሕዝባቸው ተፈናቅሎ ቤታቸው ፈርሷል። ለስቃያቸው ፖለቲካዊ መፍትሄ ይገኛል በሚል የነበራቸው ተስፋ መሻታቸው ምላሽ አላገኝም” ሲሉ ተናግረዋል።
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበዚህ የአንቶኒዮ ጉተሬዝ ንግግር ደስተኛ ያልሆኑት የእስራኤል አምባሳደር ጊላድ ኤርዳን በኤክስ (ትዊተር) ገጻቸው ላይ ዋና ፀሐፊው ጉቴሬዝ በአስቸኳይ ከመንግሥታቱ ድርጅት ሥልጣናቸው እንዲነሱ ጠይቀዋል።አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚህ ንግግራቸው ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ሳያወግዙ አላለፉም።“የፍልስጥኤማውያን ሕመም ሐማስ ላደረሰው አሰቃቂ ጥቃት ምክያት ሊሆን አይችልም፤ እንዲሁም ይህም ጥቃት በፍልስጥኤም ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን የጅምላ ቅጣትን ትክክል አያደርገውመ” ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 11:00 24 ጥቅምት 202311:00 24 ጥቅምት 2023የተባበሩት መንግሥታት በነዳጅ ችግር ምክንያት ጋዛ ውስጥ ሥራ ሊያቆም ነው
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበጋዛ እንደ ጤና ተቋማት ያሉ መሠረተ ልማቶች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።Image caption: በጋዛ እንደ ጤና ተቋማት ያሉ መሠረተ ልማቶች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የነዳጅ አቅርቦት ካላገኘ በጋዛ ውስጥ የሚያከናውነውን የሰብአዊ እርዳታ ተግባር ከነገ ረቡዕ ጀምሮ እንደሚያቋርጥ ገለጸ።በፍልስጥኤም ውስጥ የስደተኞች ጉዳይን የሚከታተለው የድርጅቱ ተቋም ዛሬ ማክሰኞ እንዳስጠነቀቀው በሰብአዊ ቀውስ ውስጥ በምትገኘው ጋዛ ሰርጥ ውስጥ ሥራውን ለማቆም ከጫፍ ደርሷል።የድርጅቱ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ሬዲዮ 4 እንደተናገሩት “በአስቸኳይ ነዳጅ ማግኘት ካልቻልን፣ ከነገ ረቡዕ ምሽት ጀምሮ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ የምናካሂደውን ሥራ እንቆማለን” ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 10:58 24 ጥቅምት 202310:58 24 ጥቅምት 2023ድንበር ተሻጋሪ ግጭቶችን በመሸሽ የሊባኖስ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቀሉ
EPACopyright: EPAመቀመጫውን ሊባኖስ ባደረገው ሒዝቦላህ እና በእስራኤል መካከል የሚደረገው ግጭት መባባሱን ተከትሎ ድንበር ላይ ያሉ የሊባኖስ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀል ጀመሩ።የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንደሚለው ከሁለት ሳምንታት ገደማ በፊት በሐማስ እና በእስራኤል መካከል ግጭት ከተከሰተ ወዲህ ወደ 20ሺህ የሚጠጉ የሊባኖስ ዜጎች ከደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል ተፈናቅለዋል።ድንበር ላይ የሚገኙ የሊባኖስ መንደሮች፣ መደብሮች እና መንገዶች ጭር ብለው ታይተዋል።ታይሬ በምትባለው ከተማ መሄጃ የሌላቸው ነዋሪዎች ወደ መጠለያነት በተቀየሩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ።ስለ ሒዝቦላህ ተጨማሪ ለማንበብ ይህን ይጫኑ፡ ሊባኖስ የሚገኘው የእስራኤል ጠላት ሒዝቦላህ ማን ነው?Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:11 24 ጥቅምት 20238:11 24 ጥቅምት 2023እስራኤል ታጋቾች ያሉበትን ለጠቆመ ወሮታ እከፍላለሁ ስትል በራሪ ወረቀት በተነች
BBCCopyright: BBCእስራኤል የበተነችው በራሪ ወረቀትImage caption: እስራኤል የበተነችው በራሪ ወረቀትእስራኤል በሐማስ የታገቱ ሰዎች መገኛን ለጠቆመ ወሮታ እከፍላለሁ ስትል በራሪ ወረቀቶችን በጋዛ ላይ በተነች።የእስራኤል ጦር በሰሜናዊ ጋዛ በበተነው በራሪ ወረቀት፣ ታጋቾች የሚገኙበትን ትክክለኛ መረጃ ለጠቆመ ወሮታ እና የደኅንነት ጥበቃ እሰጣለሁ ብላለች።“ፍላጎትዎ በሰላም መኖር እና ለልጅዎ የተሻለ ሕይወትን የሚመኙ ከሆነ ሰብዓዊነት ያለው ተግባር በመፈጸም በአካባቢዎ የታገቱ ሰዎች ያሉበትን ቦታ ይጠቁሙ” ይላል እስራኤል በአረብኛ ቋንቋ የበተነችው በራሪ ወረቀት።እስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ በበተነችው ወረቀት ጥቆማ የሚሰጡ ሰዎች ማንነትን በምሥጢር እንደምትይዝ እና የገንዘብ ሽልማትም እንደምትሰጥ ቃል ገብታለች።
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል የበተነችው በራሪ ወረቀት በአንዳንዶች በተቃውሞ ተቀዶ ተጥሏል።Image caption: እስራኤል የበተነችው በራሪ ወረቀት በአንዳንዶች በተቃውሞ ተቀዶ ተጥሏል።እስራኤል ይህን ትበል እንጂ የሰሜናዊ ጋዛ ነዋሪዎች በራሪ ወረቀቶቹን እየቀደዱ ሲበትኑ መመልከቱን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።አቡ ራማዳን የተባለ ሰው በራሪ ወረቀቱን ቀዶ በመበተን፤ “. . . የፈለጋችሁትን አድርጉ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በጋዛ ያለን ሰዎች አንንበረከክም። ከፈለጋችሁ በቦምብ ደብድቡን። ሕይወታችንን እና መኖሪያችንን ጥለን አንሰደድም” ሲል ከበውት የነበሩት ሰዎች በጭብጨባ ድጋፋቸውን ገልጸውለታል ብሏል ሮይተርስ በዘገባው።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:09 24 ጥቅምት 20238:09 24 ጥቅምት 2023ሐማስ ባለፉት 24 ሰዓታት ከ700 በላይ ሰዎች ተገድለዋል አለ
ReutersCopyright: Reutersበጋዛ በእስራኤል አየር ጥቃት የወደመ ነዳጅ ማደያImage caption: በጋዛ በእስራኤል አየር ጥቃት የወደመ ነዳጅ ማደያበሐማስ የሚተዳደረው የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ከ700 ያላነሱ ሰዎች ጋዛ ውስጥ ተገድለዋል አለ።የጤና ሚኒስቴሩ የሐማስ እና የእስራኤል ግጭት ከጀመረ ወዲህ የሟቾች ቁጥር ወደ 5 ሺህ 791 ደርሷል።ከ700 ያላሱት ሰዎች ባለፉት 24 ሰዓታት የመገደላቸው ዜና የተሰማው የእስራኤል ጦር ትናንት ከ400 ያላነሱ ዒላማዎችን ጋዛ ውስጥ በአየር መደብደቡን ካሳወቀ በኋላ ነው።የእስራል ጦር የዒላማ ያደረኩት ሐማስ የሚጠቀምባቸውን መሠረተ ልማቶችን ነው ይላል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:14 24 ጥቅምት 20236:14 24 ጥቅምት 2023″በቁርዓን እናምናለን፤ አንጎዳችሁም” በሐማስ ታግተው ከተለቀቁት
EPACopyright: EPAጋዛ ውስጥ ታግተው ከነበሩት አንዷ ዮቼቭድ ሊቭሺትዝ አጋቾቻቸው “በቁርዓን እናምናለን” አንጎዳችሁም እንዳሏቸው ተናገሩ።በትናንትናው ምሽት የተለቀቁት የ85 ዓመቷ የዕድሜ ባለጸጋ በሞተር ሳይክል በማይመች ሁኔታም እንደተወሰዱና መተንፈስም ተቸግረው እንደነበር ገልጸዋል።በሐማስ ታጋቾች ሲወሰዱም ጌጣጌጦች እና ሰዓታቸው እንደተወሰደባቸው እንዲሁም መመታታቸውንም የገለጹት የዕድሜ ባለጸጋዋ “ሲዖል ውስጥ ነበርኩ” ብለዋል።ከሞተር ብስክሌቱ ከወረዱ በኋላ ሰላምታ የሰጧቸው ሰዎች ” በቁርዓን እናምናለን” ሲሉም ጉዳት እንደማያደርሱባቸው ነግረውኛል ብለዋል።እሳቸው እና ሌሎች 24 ሰዎች ወደ ዋሻዎች መወሰዳቸውን በአስተርጓሚ ልጃቸው በኩል ተናግረዋል።የዋሻዎቹ መተላለፊያዎች “እርጥበት የተሞላበት መሬት” መሆኑን መግለጻቸውንም ነው ልጃቸው የተናገረችው።ከሁለት ወይም ከሶስት ሰዓታት ገደማ በኋላ ከኪቡትዝ ኒር ኦዝ አካባቢ የመጡ አምስት ሰዎችን ወደተለየ ክፍል ወሰዷቸው ብለዋል።በስፍራው ጠባቂዎች፣ የድንገተኛ አደጋ የጤና ባለሙያ እንዲሁም ዶክተር መኖራቸውንም ገልጸዋል።እሳቸው እና ሌሎች ታጋቾች ንጽህናው በተጠበቀ መልኩ መያዛቸውንም አስረድተዋል።በዋሻዎች ውስጥ እያሉም ነጭ አይብ እና ኩከምበር እንዲመገቡ ይሰጣቸው እንደነበርም ነው በዚህ ወቅት ያስረዱት።የሐማስ ታጣቂዎችም እየተመገቡት የነበረው ተመሳሳይ ምግብም እንደነበርም ገልጸዋል። በጋዛ ስር ባሉ ዋሻዎች ውስጥ ፍራሽ ላይ ያድሩ እንደነበር እና ዶክተሩም በየሁለት እና ሶስት ቀናት ልዩነት ይጎበኘን ነበር ብለዋል።ወደ ጋዛ በሚወስደው የሞተር ሳይክል ጉዞ ላይ አደጋ የደረሰበት ታጋች ህክምና እንዳገኘም ገልጸዋል።የድንገተኛ አደጋ የጤና ባለሙያውም የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒቶች እንዳመጣላቸውም ነው የተናገሩትሐማስ ሁለቱን አረጋውያን ሴቶች ለመልቀቅ የወሰነው በሰብዓዊነት እና በጤና ምክንያት እንደሆነም አስታውቋል።የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ ግለሰቦቹን ለአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ድርጅት ተወካዮች ሰኞ ዕለት አስረክቧል።ታጋቾቹ የተለቀቁት በግብጽ እና ኳታር አሸማጋይነት ነው። እስራኤል ሁለቱን ታጋቾች ለማስመለስ ግብጽ በማሸማገሉ ረገድ ላደረገችው ጥረት እንዲሁም ቀይ መስቀል ስላበረከተው አስተዋጽኦ አመስግናለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:40 24 ጥቅምት 20234:40 24 ጥቅምት 2023በጋዛ ባለፉት 24 ሰዓታት ከተፈጸሙ የአየር ጥቃት የተገኙ ምስሎች
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር በጋዛ ሰርጥ ባለፉት 24 ሰዓታት 400 ኢላማዎችን መምታቱን አስታውቋል።በዚህም የሐማስ ተዋጊዎች የሚገኙባቸው ዋሻዎች እና የቡድኑ የቅኝት ማማዎች ተመትተዋል ብሏል።ከስፍራው የተገኙ ምስሎች ህንጻዎች መውደማቸውን እና የቆሰሉ ፍልስጥኤማውያንንም አሳይተዋል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመችው ባለችው ጥቃት ከ5 ሺህ ፍልስጥኤማውያን በላይ መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
Getty ImagesCopyright: Getty Images
Getty ImagesCopyright: Getty ImagesArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:20 24 ጥቅምት 20234:20 24 ጥቅምት 2023የተባበሩት መንግሥታት 35 ሠራተኞቹ በጋዛ እንደተገደሉበት ገለጸ
ReutersCopyright: Reutersየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 35 ሠራተኞች ጋዛ ሰርጥ ውስጥ እንደተገደሉበት አስታወቀ።የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች ኤጀንሲ ስድስት ሠራተኞች ባለፉት 24 ሰዓታት መገደላቸውን ገልጾ፣ በአጠቃላይም በባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ 35 የድርጅቱ ሠራተኞች ተገድለዋል ብሏል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ “በህልፈታቸው አዝነናል እናም በዚህ ወቅት የተቸገሩትን ለመርዳት እየጣሩ ካሉ የሥራ ባልደረቦቻችን ጋር አብረን እንቆማለን” ሲሉም በኤክስ (ትዊተር) ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እያደረገችው ያለው ወታደራዊ ዘመቻ ወራት ሊፈጅ እንደሚችል አስታውቃ፣ የአየር ጥቃቷንም አጠናክራ ቀጥላለች።በእነዚህ ጥቃቶች ከተገደሉት አብዛኞቹ ሕጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን ከጋዛ የጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።ከተገደሉት መካከል 2,055 ሕጻናት፣ 1,119 ሴቶች፣ 217አረጋውያን እንደሚገኙበት ተገልጿል። በአጠቃላይ የተገደሉ ሰዎች ከ5 ሺህ አልፏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:27 24 ጥቅምት 20233:27 24 ጥቅምት 2023የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ማክሮን እስራኤል ገቡ
ReutersCopyright: Reutersየፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ እስራኤል አቅንተዋል።ቤን ጉሪዮን አለም አቀፍ ማረፊያ በዛሬው ዕለት የደረሱት ፕሬዚዳንቱ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሏል።የፕሬዚዳንቱ የጉብኝቱ አላማ አገራቸው ለእስራኤል ያላትን አጋርነት ለማሳየት፣ በሐማስ ቁጥጥር ስር ያሉ ታጋቾችን እንዲፈቱ ለማገዝ እና ግጭቱ እንዳይባባስ ለማድረግ መሆኑን አማካሪዎቻቸው ለሮይተርስ ተናግረዋል።ማክሮን በዚህ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁ በተጨማሪ ከእስራኤሉ ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ እና ከሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጋር ይመክራሉ ተብሏል።