October 25, 2023 – Konjit Sitotaw 

ኢዜማ ገዥው ብልጽግና ፓርቲ ለአመራሮቹ ሥልጠና የተጠቀመው የመንግሥት ገንዘብ በኦዲት እንዲጣራ ለፌደራል ዋና ኦዲተር በጻፈው ደብዳቤ ጠይቋል።

ኢዜማ፣ የፌደራል ዋና ኦዲተር ገዥው ፓርቲ ለአመራሮቹ ሥልጠና ያዋለው የመንግሥት ገንዘብ ከፓርቲው ሒሳብ ተቀንሶ ወደ መንግሥት ካዝና ተመላሽ እንዲደረግም በደብዳቤው ጠይቋል። ኢዜማ፣ ገዥው ፓርቲ አባላቱን ከሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች በተለየ በመንግሥት በጀት ማሰልጠኑ ከፍተኛ ጥፋትና የሕግ ጥሰት ነው ብሏል።

ኢዜማ፣ ከመስከረም 29 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ክልሎች ለ10 ቀናት ያህል የገዥው ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ለተሳተፉበት ሥልጠና የወጣው በመቶ ሚሊዮኖች የሚገመት ወጪ ከግብር ከፋዩ ሕዝብ የተሰበሰበ ስለመኾኑ መረጃ አግኝቻለኹ በማለት ባለፈው ሳምንት መክሰሱ ይታወሳል፡፡

ገዥው ፓርቲ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ፣ ለኢዜማ ውንጀላ ይፋዊ ምላሽ አልሰጠም።