October 25, 2023 – Konjit Sitotaw
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያዊያን ካለፉት ግጭቶችና ጦርነቶች ስህተትን በመማር አብሮ መኖርን ብቸኛ አማራጭ እንዲያደርጉ ሰሞኑን ተማጽኖዋን አሰምታለች።
ቤተክርስቲያኗ ይህን ተማጽኖዋን ያሰማችው፣ 16ኛውን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባዔ በማስመልከት ባስተላለፈችው መዕልክት ነው።
ቤተክርስቲያኗ፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በትግራይ፣ አማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉምዝ፣ በቀድሞው ደቡብ፣ ሱማሌና ጋምቤላ ክልሎች እንዲኹም በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች በተካሄዱ ግጭቶችና ጦርነቶች የዜጎች ደም በከንቱ መፍሰሱ እንዳሳዘናት ገልጣለች።
በትግራይ ክልል በሰሜኑ ጦርነት ላለቁ ወገኖች ሐዘኗን የገለጠችው ቤተክርስቲያኗ፣ ባኹኑ ወቅት በአማራ ክልል በሚካሄው ግጭት ለሚሞቱ ሰዎችም ሐዘኔን እገልጣለኹ ብላለች።
