October 25, 2023 – Konjit Sitotaw
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃዲያ ዞን ምሥራቅ ባዳዋቾ ወረዳ የሕክምናና ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ካቋረጡ ኹለት ሳምንት ኾኗቸዋል።
የሕክምናና ትምህርት ተቋማት ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ የመቱት፣ የኹለት ወራት ደመወዛችን አልተከፈለንም በማለት ነው።
የአካባቢው ነዋሪዎች ሾኔ ሆስፒታልና ሌሎች የጤና ተቋማት አገልግሎት በማቋረጣቸው፣ ሕዝቡ ተወካዮቹን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ ዝግጅት እያደረገ መኾኑን መስማቱን ዘገባው ጠቅሷል።
የአካባቢው ባለሥልጣናት ትናንት ዕሁድ አድማ ከመቱት የሾኔ ሆስፒታል ሠራተኞች ጋር ያደርጉት ውይይት ለውጥ አላመጣም ተብሏል።