አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ7 የዩኒቨርሲቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ትናንት ጥቅምት 12/2016 ለ7 የዩኒቨርሲቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡
በዚሁ መሠረት ቦርዱ፦
1. ለፕሮፌሰር ዮናስ ጨቡዴ – በኦርጋኒከ ኮሚስተሪ
2. ለፕሮፌሰር አህመድ ሙስጠፋ – በኮምፒቲሽናል ኬሚስተሪ
3. ለፕሮፌሰር ኑርልኝ ተፈራ – በኬሚካል ኢነጂነሪንግ
4. ለፕሮፌሰር አምቢሳ ቀነዓ – በጄነራል ኢዱኬሽን
5. ለፕሮፌሰር ፈቃዱ ጋሻው – በፊዚክስ
6. ለፕሮፌሰር አበባው ይርጋ – በሀየር ኢዱኬሽን እንዲሁም
7. ለፕሮፌሰር ታደሰ በሪሶ – በአንትሮፖሎጂ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡
በተጨማሪም ቦርዱ፤ ለፕሮፈሰር ሚሊያርድ ደርበው፣ ለፕሮፌሰር አታላይ ዓለም እና ለፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ስለሞን የኢሜሪተስ ፕሮፌሰርነት ደረጃ ሰጥቷል፡፡