
ከ 1 ሰአት በፊት
በአሜሪካዋ ሊዊስተን ከተማ፣ ሜይን ቢያንስ 16 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ።
አንድ ግለሰብ ተኩስ ከፍቶ ነው ሰዎቹ የተገደሉት።
ትላንት በቦሊንግ መጫወቻና ሬስቶራንት አቅራቢያ ተኩሱ መከፈቱ የተገለጸ ሲሆን፣ ተኩሱን የከፈተው ሰው ፍለጋ እየተካሄደ ይገኛል።
የሊዊስተን ነዋሪዎችና በአቅራቢያው ሊዝበን የሚኖሩ ሰዎችን ከለላ እንዲያገኙ ተነግሯቸዋል።
ፖሊስ ተጠርጣሪው የ40 ዓመቱ ሮበርት ካርድ እንደሆነ ገልጿል። ግለሰቡ “የታጠቀና አደገኛ ነው” ተብሏል።
የሟቾችን ቁጥር ባልሥልጣናት ባያረጋግጡም የቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ሲቢኤስ እንዳለው ቁጥሩ ቢያንስ 16 መድረሱን ከፖሊሶች ባገኘው መረጃ ተመርኩዞ ዘግቧል።
አንዳንድ ያልተረጋገጡ ዘገባዎች ቢያንስ 50 ሰዎች ተጎድተዋል።
የሜይን የሕዝብ ደኅንነት ክፍል “ብዙ ጉዳት የደረሰባቸው አሉ” ብሏል።
በሊዊስተን 38,000 ሰዎች ገደማ ይኖራሉ።
ፖሊሶች ሁለት ቦታ ተኩስ እንደተከፈተ ሪፖርት ደርሷቸዋል። አንደኛው ሺሜንጊስ የተባለ ሬስቶራንት ሲሆን ሁለተኛው ስፔርታይም ሪክሬሽን የተባለ የቦሊንግ መጫወቻ ነው።
በመካከላቸው የ6.5 ኪሎሜትር ርቀት አለ።
ራይሊ ዱሞንት የተባለች እናት የ11 ዓመት ልጇ ቦሊንግ ውድድር ላይ ሳለች ተኩስ መስማቷን ለኤቢሲ ኒውስ ገልጻለች።
የቀድሞ ፖሊስ ባልደረባ የነበረው አባቷ ቤተሰቡን ወደ አንድ ጥግ እንደሰበሰበም ተናግራለች።
“ልጄን በሰውነቴ ስሸፍናት እናቴ ደግሞ የኔን ሰውነት እየከለለች ነበር” ብላለች።
- ሩሲያ ‘ግዙፍ’ የኒውክሌር ጥቃት ልምምድ ማድረጓን አስታወቀችከ 4 ሰአት በፊት
- እስራኤል ‘አሸባሪ አገር’ ናት ያለችው አየርላንዳዊት ከሥራ ተባረረችከ 4 ሰአት በፊት
- በአውሮፓ ሃገራት ጥቁሮች ላይ ያነጣጠረ ዘረኝነት “በአሳፋሪ” ሁኔታ እየጨመረ ነውከ 4 ሰአት በፊት
ለሊዊስተን የከተማ ምክር ቤት ውድድር የሚያደርጉት ቢሊ ጄን ኮኪ ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ ከአንድ መሰናዶ ሲወጡ ነው ተኩሱን የሰሙት።
“ሄሊኮፕተር ሰማሁ። ይሄን ሁሉ ግርግር በሕይወቴ አላየሁም። ከኛ ግዛትና ከሌሎችም ፖሊስ መጥቷል” ብለዋል።
መላ ከተማው ዝግ እንደተደረገና እንዲህ ዓይነት የከፋ ክስተት እንደሚያሳዝን አክከዋል።
የሜይን ፖሊስ በማኅበራዊ ገጹ ተኩስ መከፈቱን አስታውቋል።
የአንደርሶጊን ግዛት ፖሊስ የተጠርጣሪውን ምሥል ይፋ አድርጓል።
አንድ ቡናማ ሹራብ የለበሰ ግለሰብ መሣሪያ ታጥቆ ወደ ሕንጻ ሲገባ ነው ምሥሉ የሚያሳየው።
ግለሰቡ በአሜሪካ መከላያ ሥልጠና የወሰደ የጦር መሣሪያ አስተማሪ እንደሆነ አሶሽየትድ ፕረስ ዘግቧል።
ዘንድሮ የአእምሮ ሕክምና ማእከል እንደነበርም ተገልጿል። ተኩስ ለመክፈት ያስፈራራ እንደነበርም ተጠቁሟል።
የአንድ ነጭ መኪና ምሥል የወጣ ሲሆን፣ ነዋሪዎች የሚያውቁትን መረጃ ለፖሊስ እንዲያጋሩም ተጠይቋል።
የሜይን ሕክምና ማእከል እንዳለው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ከሌሎች ሆስፒታሎች ጋር በመተባበር እያከመ ነው።
በአካባቢው ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው እንደሚውሉም ተገልጿል።
የአገር ውስጥ ብሔራዊ ደኅንነት ተቋም ጸሐፊ አሌሀንድሮ ማዮርካስ ጉዳዩን እየተከታተሉት እንደሆነ ገልጸዋል።
ከሜይን አገረ ገዢ ጋር ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በስምክ እንደተነጋገሩ የዋይት ሀውስ መረጃ ይጠቁማል።
