
Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች
- BBC
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59
Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ
- BBC
Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች
- BBC
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች
- BBC
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 23 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 23 SECONDS1:23
Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBCሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?
- BBC
Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBC
ጭምቅ ሃሳብ
- በጋዛ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ7ሺህ አለፈ
- ‘በጋዛ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ የለም’- ተመድ
- የእስራኤል ጦር በጋዛ ‘ዒላማ በተደረጉ ቦታዎች’ የታንክ ወረራ ፈጸመ
- ተመድ በነዳጅ እጥረት ምክንያት የጋዛ ስራው ሊቆም ይችላል አለ
- ሶሪያ 8 ወታደሮቼ በእስራኤል ተገደሉብኝ አለች
- የዮርዳኖስ ንግሥት ራኒያ ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙሃንን ተቹ
- የሶሪያ ወታደራዊ ኢላማዋችን ማጥቃቷን እስራኤል አስታወቀች
- የተመድ ዋና ፀሐፊ ሥልጣን እንዲለቁ እስራኤል ጠየቀች
- ተመድ በነዳጅ ችግር ምክንያት ጋዛ ውስጥ ሥራ ሊያቆም ነው
- እስራኤል ታጋቾች ያሉበትን ለጠቆመ ወሮታ እከፍላለሁ ስትል በራሪ ወረቀት በተነች
- እስራኤል ሁለት ተጨማሪ ታጋቾች ከጋዛ መለቀቃቸውን አረጋገጠች
- የእስራኤል መከላከያ በጋዛ ባለፉት 24 ሰዓታት 400 ኢላማዎችን መምታቱን አስታወቀ
- የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ማክሮን እስራኤል ገቡ
- የተባበሩት መንግሥታት 35 ሰራተኞቹ በጋዛ እንደተገደሉበት ገለጸ
- በፍልስጤማዊያን ጉዳይ የተጠራው የካይሮ የሰላም ጉባኤ ያለ ውጤት ተበተነ
- ሐማስ፣ እስራኤል እና ምዕራባውያንን የተቹት የሳዑዲው ልዑል ለምን አነጋጋሪ ሆኑ?
- የተመድ ኤጀንሲዎች በጋዛ ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 13:3013:30ፈረንሳይ በሐማስ ጥቃት የተገደሉት ዜጎቿ ቁጥር 35 ደርሷል አለችየፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሐማስ ጥቃት የተገደሉት የአገሪቱ ዜጎች ቁጥር 35 መስረሱን አስታወቀ።ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የተገደሉት ፈረንሳያውያን ቁጥር 31 እንደሆነ ሲገልጽ ቆይቷል።ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መገደላቸው እርግጥ ከሆኑት በተጨማሪ 9 ዜጎቹ አድራሻው አለመታወቁንም ገልጿል። ከእነዚህ መካከል በሐማስ እገታ ስር የሚገኙ እንዳሉም ታውቋል።የፈረንሳይ ዜጎችን “ከአገታት ለማስለቀቅ የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው” ብሏል ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ።አድራሻቸው ከጠፋው እና በሐማስ ከታገቱ ሰዎች ቤተሰብ ጋር የቅርብ ግንኙነት እያደረገ እንደሆነ የፈረንሳይ መንግሥት ጨምሮ ገልጿል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 12:3012:30የአረብ አገራት በጋዛ ሰላማዊ ሰዎች ዒላማ መደረጋቸውን አወገዙ
EFECopyright: EFEበርካታ የአረብ አገራት በጋራ ባወጡት መግለጫ እስራኤል እየፈጸመችው ባለው አየር ጥቃት ሰላማዊ ሰዎችን በጋዛ ሰርጥ ዒላማ አድርጋለች በማለት አወገዙ።ባህሬን፣ ግብፅ፣ ዮርዳኖስ፣ ኩዌት፣ ሞሮኮ፣ ኦማን፣ ኳታር፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በጋዛ ሰርጥ የሰላማዊ ሰዎች ግድያን የተቃወሙ ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕግም ተጥሷል ብለዋል።አገራቱ በጋራ መግለጫቸው እራሳን የመከላከል መብት፤ ሕግ መጣሳን እና የፍልስጥኤማውያንን መብት መጣሳን ትክክል አይደርግም ብለዋል።አገራቱ በጋዛ ሰርጥ ያሉ ሰዎችን በጅምላ የመቅጣት እና በኃይል የማፈናቀል እርምጃ ያሉትን የእስራኤልን ጥቃት ጨምረው አውግዘዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 12:2112:21የሐማስ ልዑክ ሞስኮ እንደሚገኝ ተዘገበየሐማስ ልዑክ በሩሲያ መዲና ሞስኮ ጉብኝት እያደረገ እንደሚገኝ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ።የሩሲያ መንግሥት የዜና ወኪል የሆነውን ሪአ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው በሞስኮ በጉብኝት ላይ ከሚገኙት መካከል የሐማስ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቡ ማርዙክ ይገኙበታል።ሩሲያ ከእስራኤል፣ ከኢራን፣ ከፍልስጥኤም መንግሥት እና ከሐማስ ጋር ግንኙነት ያላት ሲሆን፣ አሁን ለተፈጠረው ግጭት ምክንያቱ የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ውድቀት ነው ብላለች።የቡድኑ አባላት በሞስኮ በሚኖራቸው ቆይታ ሐማስ እስራኤል ላይ ጥቃት በፈጸመበት ወቅት ያገታቸው የሩሲያ ዜጎች በሚለቀቁበት ሁኔታ ላይ ንግግር ይደረጋል ሲል ሮይተርስ የዜና ወኪል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ዘግቧል።የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛኻሮቫ በበኩላቸው የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሊ ባግጂሪ ካኒ በአሁኑ ወቅት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሞስኮ እንደሚገኙ ተናግረዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 12:1012:10እስራኤል የሐማስ የድኅንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊን ገደልኩ አለችየእስራኤል ጦር የሐማስ ቁልፍ መሪ የሆነውን ግለሰብ እያካሄደችው ባለው አየር ጥቃት መግደሏን ገለጸች።ጦሩ ገደልኩት ያለው ሻዲ ባሩድ የተባለው ግለሰብ፣ የሐማስ የደኅንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እንደነበረ እና በእስራኤል ላይ የተከፈተውን ድንገተኛ ጥቃት ዕቅድ ካወጡት መካከል አንዱ ነው ብሏል።የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ በአየር ጥቃት የተገደለው ሻዲ ባሩድ በጋዛ የሐማስ ከፍተኛ ባለሥልጣን ከሆነው ያሃያ ሲንዋር ጋር በቅርበት ይሠራ ነበር ብለዋል።ያሃያ ሲንዋር ጋዛ ከሚገኙ የሐማስ መሪዎች መካከል በእስራኤል በጥብቅ ከሚፈለጉ ቀዳሚው ነው።የሐማስ የደኅንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ መገደልን በተመለከተ የሐማስ የጦር ክንፍ የሆነው ቃሳም ብርጌድ አስካሁን የሰጠው ማረጋገጫ ሆነ ማስተባበያ የለም።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 11:4011:40ሐማስ ካገታቸው ሰዎች መካከል 50ዎቹ በእስራኤል ጥቃት ተገድለዋል አለሐማስ ከእስራኤል አግቶ በቁጥጥሩ ስር ከሚገኙት ታጋቾች መካከል 50 የሚሆኑት እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እየፈጸመችው ባለችው የአየር ጥቃት መገደላቸውን አስታወቀ።የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ ቃል አቀባይ በተዋጊዎቹ ተይዘው ከነበሩ ታጋቾች መካከል በእስራኤል የአየር ድብደባዎች 50 ያህሉ ተገድለዋል ብለዋል።አቡ ኦቤይድ የተባሉት የሐማስ የጦር ክንፍ ቃል አቀባይ 50 ታጋቾች ተገድለዋል ከማለት ውጪ ተጨማሪ ማብራሪያ አልሰጡም።ቢቢሲ የዚህን መረጃ ትክክለኛነት ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ አልቻለም።ሐማስ ቅዳሜ መስከረም 26/2106 ዓ.ም. ድንገተኛ ጥቃት ፈጽሞ አብዛኛዎቹ እስራኤላውያን የሆኑ፣ የበርካታ አገራት ዜጎች ያሉበት 224 ሰዎችን ማገቱን እስራኤል ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 11:0411:04እስራኤል ወደ ጋዛ ሰብራ የገባችው ‘ለቀጣዩ ዘመቻ ዝግጅት ነው’ አለች
EPACopyright: EPAየእስራኤል ጦር ወደ ተመረጡ የጋዛ አካባቢዎች ረቡዕ ሌሊት ሰብሮ በመግባት ጥቃት የፈጸመው ለቀጣዩ ዙር ውጊያ ዝግጅት ለማድረግ ነው ብሏል።እስራኤል ከሦስት ሳምንት ገደማ በፊት በሐማስ ድንገተኛ ጥቃት ከተከፈተባት በኋላ ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶችን በጋዛ ላይ ስትፈጽም ቆይታለች።ቴል አቪቭ የአየር ጥቃቱን እያደረሰች በምድር ኃይል በጋዛ በኩል ጥቃት ለመክፍት ዝግጅት ስታደርግ ቆይታለች።ረቡዕ ሌሊት እስራኤል “በተመረጡ ስፍራዎች” በታንክ የታገዘ ወረራ የፈጸመች ሲሆን፣ ይህ ግን ለቀጣዩ ጦርነት ዝግጅት እንጂ በምድር ኃይል የማደርገው ጥቃት አይደለም ብላለች።የእስራኤል ጦር ለሰዓታት በቆየው ዘመቻ በወታደሮቹ ላይ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስ “አሸባሪዎች ተወግደዋል” ብሏል።እስራኤል ጥቃት የፈጸመባትን የሐማስ ቡድንን ከጋዛ ለማጥፋት የዛተች ሲሆን፣ በጋዛ ድንበር ዙሪያ ከ300 ሺህ በላይ ሠራዊቷን እና ከባድ መሳሪያዎቿን በተጠንቀቅ አቁማለች።አንዳንድ አገራት እስራኤል ወደ ጋዛ ዘልቃ እንዳትገባ እየወተወቱ ቢሆንም፣ የእስራኤል ሠራዊት ግን በጋዛ ላይ ለሚፈጽመው የእግረኛ ሠራዊት ወረራ ዝግጅት እና የመጀመሪያ ደረጃ ዘመቻዎችን እኣካሄደ መሆኑን ገልጿል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 10:0710:07ኤርዶዋን ምዕራባውያን ፊታቸውን ያዞሩት “የሚፈሰው የሙስሊም ደም” ስለሆነ ነው አሉ
EPACopyright: EPAየቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃንImage caption: የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃንየቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን እስራኤል በጋዛ እየፈጸመች ባለው ጥቃት ምክንያት ምዕራባውያንን አጥብቀው ተቹ።ኤርዶዋን በጋዛ “እየፈሰሰ ያለው የሙስሊም ደም በመሆኑ” ምዕራባውያን መንግሥታት እርምጃ እየወሰዱ አይደለም ብለዋል።“ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ ለምን አይከበርም?” ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ጠይቀዋል። “ጥቅማቸውን የማያስከብር ከሆነ [ምዕራባውያኑ] ዞር ብለው አይመለከቱም። ለምን? ምክንያቱም እየፈሰሰ ያለው የሙስሊም ደም ስለሆነ ነው” ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ ወደ እስራኤል ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ የሰረዙ ሲሆን፣ ባለፈው ወር በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁን “እጅ መጨበጤ ይቆጨኛል” ብለዋል።ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ለቱርክ ፓርላማ ሲናገሩ እስራኤል በጋዛ “ጭፍጨፋ” እየፈጸመች ነው ያሉ ሲሆን፣ ፍልስጥኤማውያን ደግሞ “ለነጻነት” እየታገሉ ነው ብለዋል።“ሐማስ አሸባሪ አይደለም። ለዜጎች እና ለመሬታቸውን የሚታገል የነጻነት ድርጅት ነው” ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ተደምጠዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 10:0410:04ማዕከላዊ እስራኤልን ዒላማ ያደረጉ በርካታ ሮኬቶች ተተኮሱ
ReutersCopyright: Reutersከጋዛ የተወነጨፉ ሮኬቶች በአሽኬሎን ከተማ ሰማይ ላይ ይታዩ ነበር።Image caption: ከጋዛ የተወነጨፉ ሮኬቶች በአሽኬሎን ከተማ ሰማይ ላይ ይታዩ ነበር።ባለፉት ሰዓታት ማዕከላዊ እስራኤልን ዒላማ ያደረጉ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሮኬቶች ከጋዛ መተኮሳቸው ተዘገበ።ይህን ተከትሎ የአየር ጥቃት የማስጠንቀቂያ ደውሎች በአብዛኛው የእስራኤል ክፍል ተሰምቷል።የእስራኤል አየር መቃወሚያ ሥርዓትም በሐማስ ተተኩሰዋል የተባሉ አብዛኛዎቹን ሮኬቶች ስለማክሸፉም በስፋት ተዘግቧል።ከእስራኤል መዲና ቴል አቪቭ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ፔታህ ቲክቫ ውስጥ ሮኬት ወይም የሮኬት ፍንጣሪ ያወደመው ሕንጻ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሸከረከር ነበር።የአየር ጥቃት የማስጠንቀቂያ ደውሎች ከተሰሙ በኋላ የእስራኤል የአደጋ ጊዜ አገልግሎት በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ብሏል።ሐማስ እነዚህን ሮኬቶች የተኮስኩት እኔ ነኝ ብሏል።ቡድኑ ባለፉት ሦስት ሳምንታት በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል አስወንጭፏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:478:47ጋዛ ውስጥ እየተፈጸሙ ባሉ ጥቃቶች የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ7 ሺህ አለፈ
EPACopyright: EPAከሦስት ሳምንታት በፊት የሐማስን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ላይ እየፈጸመችው ባለው የአየር ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ7 ሺህ ማለፉ ተነገረ።በሐማስ የሚተዳደረው የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ከቅዳሜ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ወዲህ አስካ ዛሬ ሐመስ ድረስ ጋዛ ውስጥ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ7 ሺህ በላይ ሆኗል ብሏል።ከእነዚህ ሟቾች መካከል 2 ሺህ 900 የሚሆኑት ሕጻናት መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል።የእስራኤል ጦር ባለፉት 24 ሰዓታት በጋዛ የሚገኙ 250 የሐማስ መገኛዎችን ዒላማ ማድረጉን አስታውቋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:078:07ሚስቱ እና አራት ልጆቹ የተገደሉበት የጋዛ ነዋሪ
ReutersCopyright: Reutersየልጆቹ አባት የአንደኛውን ልጁን አስከሬን አቅፎImage caption: የልጆቹ አባት የአንደኛውን ልጁን አስከሬን አቅፎበሰሜናዊ ጋዛ ውስጥ በሚገኘው ጃባሊያ የስደተኞች ከምፕ ላይ በእስራኤል በተፈጸመ የአየር ጥቃት አንዲት እናት ከአራት ልጆቿ ጋር ተገድለዋል። የልጆቹ አባት ሆስፒታል ውስጥ የአንደኛውን ልጁን አስከሬን አቅፎ ይዞ ሲያለቅስ ይታያል።“ዕድሜው ገና ሁለት ወር ተኩል ነው እኮ፣ ምን አጥፍቶ ነው?” ብሎ ለሮይተርስ የተናገረው አባት፣ “ሰው ገድሏል? አቁስሏል? ሰው አግቷል? ቤታቸው ውስጥ የነበሩ ሁሉም ምንም የማያውቁ ልጆች ናቸው” በማለት ስተገደሉት ልጆቹ ተናግሯል።የእስራኤል ጦር ሠራዊት ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሰሜን ጋዛ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው በመውጣት ወደ ደቡብ እንዲሄዱ ሲያስጠነቅቅ ቆይቷል።ሚስቱ እና ልጆቹ የተገደሉበት አባትም “በታንክ በላዬ ላይ ቢሄዱብኝ እንኳን፣ ቤቴን ለቅቄ ወደየትም አልሄድም” ብሏል።“አሁንም በፈረሰው ቤቴ ላይ ድንኳን ሰርቼ እዚያው ነው የምኖረው።”Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:454:45በእስራኤል- ጋዛ የተከሰቱ የቅርብ ጉዳዮች
EPACopyright: EPAየጋዛ ጦርነት ሶስት ሳምንት ሊቀሩት ጥቂት ቀናትን ይዟል። በቅርብ ሰዓታት የነበሩ ጉዳዮችን እንዳስ
- የእስራኤል መከላከያ ኃይል በሰሜናዊ ጋዛ ‘ዒላማ በተደረጉ ቦታዎች ላይ የታንክ ወረራ መፈጸሙን አስታውቋል።
- በርካታ “የአሸባሪ መቀመጫዎች፣ መሰረተ ልማትና ተከላካይ መተናል” ብሏል። – ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጦራቸው በጋዛ ላይ የእግረኛ ወረራ ለመጀመር ዝግጅት ላይ መሆናቸውን በድጋሜ ቢናገሩም ወቅቱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
- የተባባሩት መንግሥታት በጋዛ ያለው ነዳጅ በሚቀጥሉት ሰዓታት ውስጥ ተሟጦ ሊያልቅ እንደሚችል ጠቁሞ በአሁኑ ወቅት ሆስፒታሎች ለድንገተኛ ህክምናዎች ብቻ አገልግሎት እየሰጡ ነው ብሏል።
- የአውሮፓ ህብረት አመራሮች በጋዛ አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ ይቻል ዘንድ ውጊያው ለአፍታ እንዲገታ ጥሪ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
- የአለም ጤና ድርጅት ሐማስ ሁሉንም ታጋቾች በህክምና ምክንያት እንዲለቅ ጠየቀ።
- የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በእስራኤልና ፍልስጥኤማውያን መካከል ግጭቱ ከተነሳበት በፊት ወደነበረው ወደቀድሞው ሁኔታ መመለስ አይቻልም ሲሉ ተደምጠዋል።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 3:573:57’በጋዛ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ የለም’- ተመድ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ የሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያንን ቀያቸውን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቋን ተከትሎ የተባባሩት መንግሥታት በጋዛ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ የለም የሚል ምላሽ ሰጠ።”ቀያቸውን ለቀው መሸሻ ላጡ ወይም መንቀሳቀስ ለማይችሉ ሰዎች ቅድመ ማስጠንቀቂያ መስጠት ምንም ለውጥ አያመጣም” ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ቢሮ የፍልስጥኤም አስተባባሪ ሊን ሄስቲንግስ ተናግረዋል።”መሸሻ መንገዶች በቦምብ ሲደበደቡ፣ በሰሜንም ሆነ በደቡብ ጋዛ ያሉ ፍልስጥኤማውያን በጦርነት ማዕከል ውስጥ በሆኑበት፤ በህይወት ለመቆየት መሰረታዊ ነገሮች ሲታጡ፤ ከጦርነቱ በኋላ ለመመለስ ዋስትና በሌለበት ሁኔታ በርካቶች ፈታኝ ምርጫዎች ብቻ ይቀራቸዋል” ብለዋል።”የትኛውም የጋዛ ቦታ ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም” ሲሉም አክለዋል። ጦርነቱ በአለም አቀፍ ህግ መመራት እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል።”ይህም ማለት ሲቪሎች ጥበቃ ሊደረግላቸው እና መቆየትም መረጡ ወይም መሸሽ መፈናቀል ለህይወት መቆያ የሆኑ መሰረታዊ አቅርቦቶች ሊሟላቸው ይገባል” ብለዋል። ታጋቾችንም በተመለከተ “ሁሉም ታጋቾች በአስቸኳይ እና ያለ ቅድመ ሁኔታ ሊለቀቁ ይገባል” ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:343:34ጋዛ ከጦርነቱ በፊት እና አሁን- ከሳተላይት የተገኙ ምስሎችየጋዛ ጦርነት ከተጀመረ ሶስት ሳምንታት ሊሞላው ጥቂት ቀናት ብቻ ነው የቀሩት።ሐማስ በእስራኤል ላይ የሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የማያባራ የአየር ጥቃት እየፈጸመች ትገኛለች።በዚህ አየር ጥቃት አንዳንድ የጋዛ ሰፈሮች ወደ ፍርስራሽ ክምርነት ተቀይረዋል።ጋዛ ከጦርነቱ በፊት እና አሁን ያለችበትን የሚያሳዩ የሳተላይት ምስሎችን ቢቢሲ አግኝቷል። ከታች ያለው የመጀመሪያው ምስል በሰሜናዊ ጋዛ የምትገኘው ቤይት ሃኑን መስከረም 29/ 2016 ዓ.ም የተወሰደ ነው።ሁለተኛው የሳተላይት ምስል ከመጀመሪያው ከአስራ አንድ ቀናት በኋላ የተወሰደ ነው።
BBCCopyright: BBCArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:352:35የእስራኤል ጦር በጋዛ ‘ዒላማ በተደረጉ ቦታዎች’ የታንክ ወረራ ፈጸመ
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤል መከላከያ ኃይል በሰሜናዊ በጋዛ ‘ዒላማ በተደረጉ ቦታዎች’ በታንክ ወረራ መፈጸሙን አስታወቀ።ይህ ወረራ የተፈጸመው “ለውጊያው ቀጣይ ክፍል ለመዘጋጀት” መሆኑን ገልጿል።“ብዙ የአሸባሪ መቀመጫዎች፣ መሠረተ ልማትና ታንክ ተከላካይ ሚሳኤል መተናል” ሲልም አክሏል።ወረራውን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል መከላከያ ኃይሉ ለቋል።“ወታደሮቹ ከዚያ ወጥተው አሁን ወደ እስራኤል ግዛት ተመልሰዋል” ብሏል።ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በቴሌቭዥን በተላለፈ ንግግራቸው የእስራኤል መከላከያ ኃይል በመሬት ወረራ ለመፈጸም እየተዘጋጁ መሆናቸው ገልጸዋል። መቼ እንደሚፈጸም ግን ይፋ አላደረጉም።እስራኤል 1.1 የጋዛ ነዋሪዎች ለደኅንነታቸው ሲሉ ለቀው እንዲወጡ ባለፈው ሳምንት መግለጿ ይታወሳል።ሆኖም ግን ከፍተኛ የተባበሩት መንግሥታት ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ በደቡባዊ ጋዛ ያለው ሁኔታ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት፣ ከጋዛ በስተሰሜን ካለው መኖሪያው ሸሽተው ከወጡ ፍልስጥኤማውያን መካከል የተወሰኑት ወደ ቤታቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:231:23ተመድ በነዳጅ እጥረት ምክንያት የጋዛ ስራው ሊቆም ይችላል አለ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ አስገብቻታለሁ ባለችው የጋዛ ሰርጥ ነዳጅ እንዳይገባ በመከልከሉ ምክንያት የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ችግር እንደገጠመው አስታወቀ።በነዳጅ እጥረት ምክንያት በጋዛ እየሰጠ ያለው የሰብዓዊ አገልግሎት በሰዓታት ውስጥ ሊቆም እንደሚችልም ገልጿል።ተቋሙ በጋዛ ውስጥ ምን አይነት የሰብዓዊ አገልግሎት መስጠት ይችላል በሚለውም ላይ በሚቀጥሉት ሰዓታት ውሳኔ ላይ እንደሚደርስም ነው ያስታወቀው።የተባባሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች ኤጀንሲ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ተቋሙ ምናልባትም አገልግሎቱን መቀነስ አለበት ብለዋል።”ተቋሙ አገልግሎቱን እንዲቀጥል የሚላክልን የነዳጅ አቅርቦት ይኖራል ብለን ተስፋ እያደረግን ነው። መጪዎቹ ሰዓታት ወሳኝ ናቸው” ሲሉም ነው ለቢቢሲ የተናገሩትነዳጅ ካልገባልን “ፈታኝ የሚባል ውሳኔ ላይ መድረስ አለብን ይህም በከፍተኛ ሁኔታ እርዳታ ለሚያስፈልገው የጋዛ ስርጥ ነዋሪ ሰብዓዊ ድጋፋችንን መቀነስ” ብለዋል።”ነዳጅ ወደ ጋዛ ካልገባ ውሳኔያችንን ዛሬ (ሐሙስ) የምናሳውቅ ይሆናል” ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:211:21እስራኤል ‘አሸባሪ አገር’ ናት ያለችው አየርላንዳዊት ከሥራ ተባረረችኮርኒ ኬሪ የተባለች አየርላንዳዊት እስራኤል “አሸባሪ አገር ናት” ብላ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በመጻፏ ከአየርላንድ የቴክኖሎጂ ተቋም ተባረረች። የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር ከሥራ የተባረረችው በፖለቲካዊ አቋሟ እንደሆነ ካመነች ጉዳዩን ወደ ሕግ አካል እንድትወስደው ነግረዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:570:57የእስራኤል እግረኛ ጦር ጋዛ ሲገባ ከሐማስ ምን ሊገጥመው ይችላል?እስራኤል ጋዛን በአየር ስትደበድብ ከሁለት ሳምንት በላይ ሆኗታል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿንም በጋዛ ድንበር አቅራቢያ አሰባስባ፣ በጋዛ ላይ ወረራ ለመፈጸም እየተዘገጀች ነው። እስራኤል ከሐማስ የተቃጣባትን መብረቃዊ ጥቃት ለመበቀል ነው የተነሳችው። ሐማስን ከምድረ ገጽ ሳላጠፋ አልመለስም ስትል ዝታለች።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 13:03 25 ጥቅምት 202313:03 25 ጥቅምት 2023በተመድ የእስራኤል አምባሳደር ጉቴሬዝ ከዋና ፀሐፊነታቸው እንዲለቁ በድጋሚ ጠየቁ
ReutersCopyright: Reutersአምባሳደር ጊላድ ኤርዳንImage caption: አምባሳደር ጊላድ ኤርዳንየተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ማክሰኞ ዕለት ባደረጉት ንግግር ዙሪያ ዛሬ [ረቡዕ] የሰጡትን ማብራሪያ ተከትሎ በድርጅቱ የእስራኤል አምባሳደር ጊላድ ኤርዳን በቁጣ በሰጡት ምላሽ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሥልጣን እንዲለቁ በድጋሚ ጠይቀዋል።“ዋና ፀሐፊው የተናገሩትን ቃል መልሰው አለማስተባበላቸው፣ እንዲሁም ይቅርታ ለመጠየቅ አለመቻላቸው ለመንግሥታቱ ድርጅት ውርደት ነው” ሲሉ አምባሳደሩ ቁጣቸውን ገልጸዋል።ኤርዳን የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ ጉቴሬዝን “እውነታን በማዛባት እና በመጠምዘዝ” ሐማስ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ለፈጸመው የጭካኔ ጥቃት እስራኤልን ከሰዋል ሲሉ ወቅሰዋል።“ሐማስ ለፈጸመው ድርጊት እስራኤልን ጥፋተኛ አድርገው ማቅረባቸውን ከተናገሯቸው ቃላት ሁሉም ሰው በደንብ ሊረዳው ይችላል፣ ወይም ወደዚህ ጭፍጨፋ የመራውን ‘የኋላ ታሪክ’ በተመለከተ ያላቸውን መረዳት ያሳያል።“የትኛውም ‘የኋላ ታሪክ’ በንጹሃን ላይ የሚፈጸምን ግድያ ማስረዳት እንደማይችል የማይረዳ ዋና ፀሐፊ፣ ዋና ፀሐፊ ሊሆን አይችልም” ሲሉ አምባሳደሩ ጉቴሬዝ ከኃላፊነታቸው እንዲለቁ በድጋሚ ጠይቀዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 10:59 25 ጥቅምት 202310:59 25 ጥቅምት 2023ጉቴሬዝ ንግግራቸው በፈጠረው ውዝግብ መደንገጣቸውን ተናገሩ
AFPCopyright: AFPዋና ፀሐፊው ዛሬ (ረቡዕ) ከሰዓት በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡImage caption: ዋና ፀሐፊው ዛሬ (ረቡዕ) ከሰዓት በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ማክሰኞ ዕለት በድርጅቱ የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ያደረጉት ንግግር በፈጠረው ውዝግብ እንዳስደነገጣቸው ተናገሩ።ጉቴሬዝ በንግግራቸው ውስጥ “የሐማስ ጥቃት እንዲሁ ያለምክንያት የተከሰተ አይደለም” በማለት “ፍልስጥኤማውያን ለ56 ዓመታት በማያፈናፍን ወረራ ውስጥ ቆይተዋል” ብለው ነበር።ይህንንም ተከትሎ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ባለሥልጣናት ተቆጠተው፣ ዋና ፀሐፊው ከዓለም አቀፉ ድርጅት ኃላፊነታቸው እንዲለቁ ከመጠየቅ በተጨማሪ ለተመድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ቪዛ አስከመከልከል ደርሰዋል።ኒው ዮርክ ውስጥ የፀጥታው ምክር ቤት ማክሰኞ ዕለት ያተካሄደውን ስብሰባ ጉቴሬዝ ሲከፍቱ ሐማስ የፈጸመውን “አሰቃቂ እና አጋጥሞ የማያውቅ” ያሉትን ጥቃት በጽኑ እንደሚያወግዙ በመግለጽ፣ ሆን ተብሎ የተፈጸመውን የሰላማዊ ሰዎች ግድያ፣ ጉዳት ወይም ማገት በምንም ሁኔታ ምክንያት የሚቀርብለት እንዳልሆነ ገልጸዋል።ውዝግቡ እየተባባሰ ባለበት እና አስራኤል ለመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊ ማርቲን ግሪፊትስ ቪዛ መከልከሏን ተከትሎ በሁኔታው መደንገጣቸውን አስታውቀዋል።ጉቴሬዝ ዛሬ ረቡዕ ከሰዓት በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ንግግራቸው “በሐማስ የተፈጸመውን የሽብር ተግባር ምክንያታዊ ያደረኩት ያህል” ከአላግባብ ትርጉም እንዲይዝ በመደረጉ መደንገጣቸውን ገልጸዋል።ጉቴሬዝ ንግግራቸው የሐማስን ጥቃት ትክክለኝነት የሚያሳይ ሳይሆን፣ በተቃራኒው የሚገልጽ ሃሳብ መሆኑን ተናግረው፣ በድጋሚም ሐማስ በእስራኤል ላይ “የፈጸመውን አሰቃቂ የሽብር ድርጊት” አውግዘዋል።ጨምረውም በፍልስጥኤማውያን በኩል ያለውን ምሬት በተመለከተ የተናገሩ ሲሆን፣ ነገር ግን የፍልስጥኤማውያኑ ቅሬታ “በሐማስ የተፈጸመውን አስቀያሚ ጥቃት ትክክል አያደርገውም” ብለዋል።በማክሰኞው ንግግራቸው ምክንያት የተፈጠረውን ውዥንብር ለማጥራት እና የተናገሩትን ግልጽ ለማድረግ የፈለጉት ለጥቃቱ ሰለባዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ካላቸው አክብሮት የመነጨ መሆኑን ጉቴሬዝ ተናግረዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:31 25 ጥቅምት 20238:31 25 ጥቅምት 2023ባለፉት 24 ሰዓታት ከ700 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፡ የጋዛ ጤና ሚኒስቴር
ReutersCopyright: Reutersጋዛ ውስጥ ከተገደሉ ሰዎች አስከሬን መካከል የሚታይ ሰውImage caption: ጋዛ ውስጥ ከተገደሉ ሰዎች አስከሬን መካከል የሚታይ ሰውባለፉት 24 ሰዓታት ጋዛ ውስጥ ከ700 በላይ ሰዎች መገደላቸውን በሐማስ የሚመራው የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።ባለሥልጣኑ ባወጣው መረጃ መሠረት በ24 ሰዓቱ ውስጥ 344 ሕጻናትን ጨምሮ 756 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን ገልጿል።ሚኒስቴሩ እንዳለው እስራኤል በጋዛ ላይ እያካሄደችው ባለው ያልተቋረጠ የአየር ጥቃት ምክንያት የተገደሉ ሰዎች አጠቃላይ አሃዝ ከ6,500 በላይ ደርሷል።ከመስከረም 26/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ጋዛ ውስጥ በተፈጸሙ የአየር ድብደባዎች ምክንያት ከተገደሉት 6,500 በላይ ሰዎች መካከል 2,704 የሚሆኑት ሕጻናት ናቸው።በቅርብ ቀናት አስራኤል እያካሄደች ያለው ተከታታይ የአየር ጥቃት በተለይ በደቡባዊው የጋዛ ክልል ላይ በእጅጉ የበረታ መሆኑን የጤና ባለሥልጣኑ ገልጿል።እስራኤል በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበትን ይህንን የአየር ጥቃት ጋዛ ላይ መፈጸም የጀመረችው፣ ሐማስ በደቡባዊ ክፍሏ ውስጥ በፈጸመው ጥቃት ከ1400 በላይ የሚሆኑ ዜጎቿ ከተገደሉ በኋላ ነው።