Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 23 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 23 SECONDS1:23

Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBCሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?

Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. አሜሪካ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል “የተኩሰ አቁም እንዲደረግ አልደግፍም” አለች
  2. አሜሪካ በሶሪያ የሚገኙ ወታደራዊ ተቋማትን በአየር ደበደበች
  3. የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በጋዛ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረስ ድምጽ ሊሰጥ ነው
  4. በጋዛ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ7ሺህ አለፈ
  5. ‘በጋዛ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ የለም’- ተመድ
  6. የእስራኤል ጦር በጋዛ ‘ዒላማ በተደረጉ ቦታዎች’ የታንክ ወረራ ፈጸመ
  7. ተመድ በነዳጅ እጥረት ምክንያት የጋዛ ስራው ሊቆም ይችላል አለ
  8. ሶሪያ 8 ወታደሮቼ በእስራኤል ተገደሉብኝ አለች
  9. የዮርዳኖስ ንግሥት ራኒያ ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙሃንን ተቹ

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 4:464:46አሜሪካ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል “የተኩሰ አቁም እንዲደረግ አልደግፍም” አለችእስራኤል በጋዛ ሰርጥ እያካሄደች ባለችው ጥቃት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ተፈናቅሏል።Getty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል በጋዛ ሰርጥ እያካሄደች ባለችው ጥቃት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ተፈናቅሏል።Image caption: እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እያካሄደች ባለችው ጥቃት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ተፈናቅሏል።አሜሪካ ሐማስ መልሶ እንዲደራጅ ዕድል የሚሰጥ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ አልደግፍም አለች።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ሲናገሩ አገራቸው ሐማስ “እረፍት አድርጎ፣ እራሱን አደራጅቶ እስራኤል ላይ የሽብር ዘመቻዎችን እንዲቀጥል” የሚፈቅድ የተኩስ አቁም ስምምነትን አትደግፍም ብለዋል።ማቲው ሚለር መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ሐማስ እስራኤል ከፈጸመውን ጭካኔ የተሞላበት ድንገተኛ ጥቃት በተጨማሪ ቡድኑ “ሰላማዊ እስራኤላውያንን ዒላማ ያደረጉ ሮኬቶችን በየዕለቱ ያስወነጭፋል” ሲሉ ተናግረዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ሐማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ሳይደረስ አግቼ የያዝኳቸውን ታጋቾች አለቅም ብሏል።በሞስኮ ጉብኝት እያደረጉ ያሉ ከፍተኛ የሐማስ አመራሮች እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እያደረገች ያለው የአየር ደብደባ ሳይቆም ሐማስ የያዛቸውን ሰዎች እንደማይለቅ ለሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።ማቲው ሚለር የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ ሲባል ሁለቱ አካላት ተኩስ እንዲያቆሙ ግን አሜሪካ ፍላጎት እንዳላት አመልክተዋል።የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ አርብ ጥቅምት 16/2016 ዓ.ም. በጋዛ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ በሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ድምጽ ይሰጣል።Article share tools
  2. የታተመዉ 4:414:41ኤርትራ በዳህላክ የእስራኤል ወታደራዊ ጣቢያ ላይ ጥቃት ተፈጸመ መባሉን ሐሰት ነው አለችበመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ መገናኛ ብዙኃን በኤርትራ የሚገኝ የእስራኤል ወታደራዊ የቅኝት ጣቢያ ላይ ጥቃት ተፈጸመበት ሲሉ ያወጡት ዘገባ ሐሰት ነው ስትል አስተባበለች።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  3. የታተመዉ 4:074:07የተኩስ አቁም እስኪደረሰ ታጋቾች እንደማይለቀቁ የሐማስ ተወካይ ተናገሩሞስኮን በመጎብኘት ላይ የሚገኙ የሐማስ የልዑካን ቡድን አባል ከእስራኤል የተወሰዱ ታጋቾች የተኩስ አቁም ስምምነት እስኪደረስ ድረስ እንደማይለቀቁ መናገራቸውን አንድ የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ዘገበ።የሩሲያው ኮመርሳንት ጋዜጣ አቡ ሐሚድን ጠቅሶ እንደዘገበው ሐማስ ታጋቾችን በሙሉ ለማግኘት ጊዜ ይፈልጋል ብለዋል።”አብዛኛዎቹ ሲቪሎች የሆኑ በርካታ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ውለዋል። በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ፈልገን እስከምናገኛቸው ጊዜ እንፈልጋለን” ሲሉ ሐሚድ ተናግረዋል።እስካሁን አራት ታጋቾች “በሰብአዊ ምክንያቶች” በሐማስ ተለቀዋል። እናት እና ሴት ልጃቸው ጁዲት እና ናታሊ ራናን ጥቅምት 20 ሲለቀቁ፤ የ85 ዓመቷ ዮቼቭድ ሊፍሺትዝ እና የ79 ዓመቷ ኑሪት ኩፐር ሰኞ ተለቀዋል።Article share tools
  4. የታተመዉ 3:573:57አሜሪካ የኢራን ናቸው ያለቻቸውን በሶሪያ የሚገኙ ወታደራዊ ተቋማትን በአየር ደበደበችአሜሪካ በምሥራቃዊ ሶሪያ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ወታደራዊ ተቋማት ላይ የአየር ደብድባ መፈጸሟን አስታወቀች።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  5. የታተመዉ 3:283:28በምስል፡ የተጎዱ ፍልስጥኤማውያን ወደ ሆስፒታል እየገቡ ነውማስጠንቀቂያ፡ እነዚህ ምስሎች ስሜት የሚረብሹ ሊሆኑ ይችላሉ።እስራኤል ባለፉት 24 ሰዓት በጋዛ ሰርጥ ያደረገችውን ድብደባ ተከትሎ የተጎዱ ፍልስጤማውያን ወደ ጤና ተቋማት እየገቡ ነው።ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በደቡባዊ ጋዛ ዃን ዩኒስ ከተማ ወደሚገኝ ሆስፒታል ሲወሰዱ የሚያሳዩ ምስሎችን የተለያዩ የዜና አውታሮች ይፋ አድርገዋል።ማምሻወንም እስራኤል ሌላ ዙር የአየር ድብደባ በከተማይቱ ላይ መፈጸሟ ተዘግቧል። የእስራኤል ጦር ሲቪሎች ለደኅንነታቸው ሲሉ ከሰሜኑ የሰርጡ ክፍል ወደ ደቡብ እንዲሸሹ ጠይቋል።የአየር ድብደባው እና ወረራው ደቡብ ጋዛን ጨምሮ በመላው ጋዛ ሰርጥ ቀጥሏል።የተጎዱ ፍልስጥኤማውያን ወደ ሆስፒታል እየገቡ ነውGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየተጎዱ ፍልስጥኤማውያን ወደ ሆስፒታል እየገቡ ነውGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየተጎዱ ፍልስጥኤማውያን ወደ ሆስፒታል እየገቡ ነውGetty ImagesCopyright: Getty ImagesArticle share tools
  6. የታተመዉ 3:223:22እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በርካታ የሐማስ ዒላማዎችን መደብደቧን አስታወቀችየእስራኤል ጦር ባለፉት 24 ሰዓታት በጋዛ ሰርጥ በደርዘን የሚቆጠሩ የሐማስ ዒላማዎችን መደብደቡን የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።የምድር ጦሩ በተዋጊ ጄቶች እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ታግዞ በሹጃ’ያ አካባቢ ዒላማዎችን ደብድቧል። በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ሌሎች ቦታዎችም መመታታቸውን መግለጫው ገልጿል።ዒላማ የተደረጉትም የፀረ ታንክ ሚሳኤል ማስወንጨፊያ ቦታዎች፣ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያዎች፣ መቆጣጠሪያ ማዕከላት እና የሃማስ ተዋጊዎች ይገኙበታል የተባሉ ቦታዎች መሆናቸውን ጦሩ አስታውቋል።ዘመቻው እንደተጠናቀቀ ወታደሮቹ አካባቢውን ለቀው የወጡ ሲሆን በእስራኤል ሠራዊት ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰም አክሏል።Article share tools
  7. የታተመዉ 1:591:59የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በጋዛ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረስ ድምጽ ሊሰጥ ነውፋይል ፎቶ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤGetty ImagesCopyright: Getty Imagesፋይል ፎቶ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤImage caption: ፋይል ፎቶ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤየተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ አርብ ጥቅምት 16/2016 ዓ.ም. በጋዛ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ድምጽ ሊሰጥ ነው።የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ትናንት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የእስራኤል እና ፍልስጥኤም አምባሳደሮች ጦርነቱ በዜጎቻቸው ላይ ያደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ለጉባኤው ንግግር አድርገዋል።ድምጽ የሚሰጥበት የውሳኔ ሃሳብ አስቸኳይ የተኩስ አቁም ተደርጎ ያልተገደበ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግ፣ ተዋጊዎች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕግጋቶች እንዲከበሩ ጠይቀዋል።Article share tools
  8. የታተመዉ 1:461:46በጋዛ የካቶሊክ መነኮሳት፡ “ሕዝባችንን ጥለን ወደ የትም አንሄድም”ማሪያ ዴል ፒላሰር እና ማሪያ ዴል ፔርፔቶ ሶኮሮ ቫርጋስ ይባላሉ። መንታ መነኮሳት ናቸው። አሁን በጋዛ ነው የሚገኙት። የፔሩ ዜግነት አላቸው። የሆሊ ፋሚሊ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ናቸው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  9. ሁለት ታንዛኒያውያን እና አንድ ደቡብ አፍሪካዊ በሐማስ ታግተዋል- እስራኤልበጋዛ ድንበር ላይ የምትገኘው ካቡትዝ ጥቃት አስተናግዳለችEPACopyright: EPAበጋዛ ድንበር ላይ የምትገኘው ካቡትዝ ጥቃት አስተናግዳለችImage caption: በጋዛ ድንበር ላይ የምትገኘው ካቡትዝ ጥቃት አስተናግዳለችመስከረም 26/2016 ዓ.ም. በእስራኤል ከተፈጸመው ጥቃት በኋላ በሃማስ ከተያዙት 224 ታጋቾች መካከል ሁለት ታንዛኒያውያን እና አንድ ደቡብ አፍሪካዊ እንደሚገኙበት የእስራኤል መንግስት አስታወቀ።ሦስቱም በእስራኤል መንግሥት በስም አልተጠቀሱም።በእስራኤል የታንዛኒያ አምባሳደር ሁለት ዜጎቻቸው መታገታቸውን አረጋግጠዋል። ቢቢሲ በእስራኤል ጠፋ የተባውን ታንዛኒያዊ ጆሹዋ ሞልን አባት አናጋሯል። ታንዛኒያዊ ጥቃት በደረሰባት በኪቡዝ የግብርና ተማሪ ነበር።ስለልጁ እጣ ፈንታ ምንም አይነት መረጃ እንደሌለው ሐሙስ ለቢቢሲ ተናግሯል።ጥቃቱ ከመድረሱ ሁለት ቀናት ቀደም ብሎ ጀምሮ ከልጁ ጋር አለመነጋገራቸውን እና ቤተሰቡ ጭንቀት እንደገባው ተናግሯል ።”መብላትም ሆነ መተኛት አልቻልንም። ወደ ገበያ ስሄድ ሰዎች ለምን ክብደት እንደቀነስኩ ይጠይቁኛል” ሲል ገልጿል።ከታጋቾቹ መካከል አንዱ ደቡብ አፍሪካዊ ነው ስለመባሉ የአገሪቱ ባለስልጣናት የሰጡት አስተያየት የለም።በአጠቃላይ ከ25 አገራት የተውጣጡ የውጭ ዜጎች በሐማስ ቁጥጥር ስር መሆናቸውን እስራኤል ተናገራለች።ከተያዙት 224 ታጋቾች 135 ያህሉ የውጭ ዜጎች ሲሆኑ 54ቱ ታይላንዳዊያን መሆናቸው ታውቋል።ታጋቾቹ የተወሰዱት የሐማስ ታጣቂዎች ከጋዛ ወደ እስራኤል ገብተው ቢያንስ 1,400 ሰዎችን ከገደሉ በኋላ ነው።እስራኤል በወሰደችው የአየር የአጸፋ ጥቃት 6500 የሚጠጉ ሰዎችን መግደሏን በሐማስ የሚመራው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።Article share tools
  10. የታተመዉ 1:001:00ባይደን ኢራንን በቀጥታ አስጠነቀቁፕሬዝዳንት ባይደንGetty ImagesCopyright: Getty Imagesፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኢራንን በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮችን ዒላማ እንዳታደርግ ኢራንን በቀጥታ ማስጠንቀቃቸውን ዋይት ሃውስ ገለጸ። ለኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ በቀጥታ ከተላለፉ ጥቂት ማስጠንቀቂያዎች አንዱ ነው ተብሏል።የዋይት ሃውስ የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ በሰጡት አጭር መግለጫ ላይ “ቀጥተኛ መልዕክት ተላልፏል” ብለዋል።ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ግን አልሰጡም።በአከባቢው ጥቃቶች መበራከታቸውን ተከትሎ 900 የሚጠጉ ተጨማሪ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ አካባቢው በማቅናት የአየር ኃይሉን ጥበቃ እንደሚያጠናክሩ ፔንታጎን ተናግሯል።ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ ወታደሮች በኢራቅ ቢያንስ 12 ጊዜ፤ በሶሪያ ደግሞ አራት ጊዜ ጥቃት ደርሶባቸዋል ሲል ፔንታጎን ገልጿል።ባይደን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮቿ ዒላማ መደረጋቸው ከቀጠለ ምላሽ እንደምትሰጥ አያቶላህን አስጠንቅቀው ነበር።መልዕክቱ ስለተላለፈበት መንገድ ግን ተጨማሪ ማብራሪያ አልተሰጠም።Article share tools
  11. የታተመዉ 0:590:59የግጭቱ ሰለባ ሆነው ሞታቸው ያልታመነላቸው የ4 ዓመቶቹ የፍልስጥኤም እና የእስራኤል ሕጻናትየእስራኤል-ጋዛ ጦርነት ‘ሀ’ ተብሎ ሲጀመር ነው ሁለቱም ሕጻናት የተቀጠፉት። ሁለቱም አራት ዓመታቸው ነበር። አንዱ ፍልስጥኤማዊ ሌላኛው እስራኤላዊ። ብዙዎች በእነዚህ ሕጻናት ግድያ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲያዝኑ አልታዩም፤ እንዲያውም አልተገደሉም ብለው የሚሞግቱም ነበሩ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  12. የታተመዉ 0:570:57በእየሩሳሌም የታገቱ 224 ሰዎችን ለማሰብ 224 መብራቶች በሩመብራት የማብራት ስነ-ስርዓትEPACopyright: EPAትናንት ሐሙስ ምሽት በሐማስ የታገቱ 224 ሰዎችን ለማሰብ 224 መብራቶች በእየሩሳሌም ሰማይ ላይ በርተው ታይተዋል።“የብርሃን ተስፋ” በሚል መርህ በተዘጋጀው መብራት የማብራት ስነ-ስርዓት ላይ የታጋቾች ማንነትን የሚያሳዩ ስም እና ፎቶግራፎች ቀርበዋል።መብራት የማብራት ስነ-ስርዓትEPACopyright: EPAሐማስ ከእስራኤል አግቶ በቁጥጥሩ ስር ከሚገኙት ታጋቾች መካከል 50 የሚሆኑት እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እየፈጸመችው ባለችው የአየር ጥቃት መገደላቸውን ትናንት ማስታወቁ ይታወሳል።መብራት የማብራት ስነ-ስርዓትEPACopyright: EPAArticle share tools
  13. የታተመዉ 0:390:39አሜሪካ በሶሪያ የሚገኙ ወታደራዊ መሠረተ ልማቶችን በአየር ደበደበችየአሜሪካ ጦር ጀትUS Department of DefenseCopyright: US Department of Defenseአሜሪካ በሶሪያ የሚገኙ ሁለት ወታደራዊ መሠረተ ልማቶችን በአየር ደብድባ ማውደሟን አስታወቀች።የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በአየር የተደበደቡት መሠረተ ልማቶች በኢራን እና የኢራን ተባባሪ በሆኑ ቡድኖች ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ ናቸው ብሏል።በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር አርብ ንጋት ላይ በተፈጸመው የአየር ድብደባ ኢራን ጦር መሳሪያ ለማከማችት የምትጠቀምበት ስፍራ ወድሟል ተብሏል።መከላከያ ሚንስትሩ ላሎድ ኦስቲን አሜሪካን ይህን እርምጃ የወሰደችው በኢራቅ እና ሶሪያ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠራዊት አባላትን ለመጠበቅ እና በቅርቡ በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች ላደረሱት ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ነው ብለዋል።መከላከያ ሚንስትሩ በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች በአሜሪካ ጦር ሠራዊት ላይ የሚያደርሱት ጥቃት የማይቆም ከሆነ አሜሪካ አሁንም ተመሳሳይ እርምጃዎችን መውሰዷን ትቀጥላለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል።የእስራኤል እና ሐማስ ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ በኢራቅ እና ሶሪያ በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠራዊት አባላት እና ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ 12 ጥቃቶች የተፈጸሙ ሲሆን በዚህም ከ20 የማያንሱ የአሜሪካ ሠራዊት አባላት ጉዳት እንደደረሰባቸው ፔንታጎን አስታውቋል።ኦስቲን ይህን የአየር ጥቃት በእስራኤል እና ሐማስ መካከል እየተደረገ ካለው ጦርነት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ያሉ ሲሆን የአየር ጥቃቱም ከእስራኤል ጋር በቅንጅት የተደረገ አይደለም ብለዋል።ይሁን እንጂ ይህ የአየር ጥቃት በመከላከለኛው ምስራቅ ያለውን ውጥረት ከፍ አድርጎታል።Article share tools
  14. የታተመዉ 13:30 26 ጥቅምት 202313:30 26 ጥቅምት 2023ፈረንሳይ በሐማስ ጥቃት የተገደሉት ዜጎቿ ቁጥር 35 ደርሷል አለችየፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሐማስ ጥቃት የተገደሉት የአገሪቱ ዜጎች ቁጥር 35 መስረሱን አስታወቀ።ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የተገደሉት ፈረንሳያውያን ቁጥር 31 እንደሆነ ሲገልጽ ቆይቷል።ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መገደላቸው እርግጥ ከሆኑት በተጨማሪ 9 ዜጎቹ አድራሻው አለመታወቁንም ገልጿል። ከእነዚህ መካከል በሐማስ እገታ ስር የሚገኙ እንዳሉም ታውቋል።የፈረንሳይ ዜጎችን “ከአገታት ለማስለቀቅ የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው” ብሏል ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ።አድራሻቸው ከጠፋው እና በሐማስ ከታገቱ ሰዎች ቤተሰብ ጋር የቅርብ ግንኙነት እያደረገ እንደሆነ የፈረንሳይ መንግሥት ጨምሮ ገልጿል።Article share tools
  15. የታተመዉ 12:30 26 ጥቅምት 202312:30 26 ጥቅምት 2023የአረብ አገራት በጋዛ ሰላማዊ ሰዎች ዒላማ መደረጋቸውን አወገዙጋዛEFECopyright: EFEበርካታ የአረብ አገራት በጋራ ባወጡት መግለጫ እስራኤል እየፈጸመችው ባለው አየር ጥቃት ሰላማዊ ሰዎችን በጋዛ ሰርጥ ዒላማ አድርጋለች በማለት አወገዙ።ባህሬን፣ ግብፅ፣ ዮርዳኖስ፣ ኩዌት፣ ሞሮኮ፣ ኦማን፣ ኳታር፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በጋዛ ሰርጥ የሰላማዊ ሰዎች ግድያን የተቃወሙ ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕግም ተጥሷል ብለዋል።አገራቱ በጋራ መግለጫቸው እራሳን የመከላከል መብት፤ ሕግ መጣሳን እና የፍልስጥኤማውያንን መብት መጣሳን ትክክል አይደርግም ብለዋል።አገራቱ በጋዛ ሰርጥ ያሉ ሰዎችን በጅምላ የመቅጣት እና በኃይል የማፈናቀል እርምጃ ያሉትን የእስራኤልን ጥቃት ጨምረው አውግዘዋል።Article share tools
  16. የታተመዉ 12:21 26 ጥቅምት 202312:21 26 ጥቅምት 2023የሐማስ ልዑክ ሞስኮ እንደሚገኝ ተዘገበየሩሲያ መንግሥት ባጋራው ምስል ላይ ሙሳ አቡ ማርዙክ ታይተዋል (ከግራ ወደቀኝ መጨረሻ)TelegramCopyright: Telegramየሩሲያ መንግሥት ባጋራው ምስል ላይ ሙሳ አቡ ማርዙክ ታይተዋል (ከግራ ወደቀኝ መጨረሻ)Image caption: የሩሲያ መንግሥት ባጋራው ምስል ላይ ሙሳ አቡ ማርዙክ ታይተዋል (ከግራ ወደቀኝ መጨረሻ)የሐማስ ልዑክ በሩሲያ መዲና ሞስኮ ጉብኝት እያደረገ እንደሚገኝ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ።የሩሲያ መንግሥት የዜና ወኪል የሆነውን ሪአ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው በሞስኮ በጉብኝት ላይ ከሚገኙት መካከል የሐማስ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ሙሳ አቡ ማርዙክ ይገኙበታል።ሩሲያ ከእስራኤል፣ ከኢራን፣ ከፍልስጥኤም መንግሥት እና ከሐማስ ጋር ግንኙነት ያላት ሲሆን፣ አሁን ለተፈጠረው ግጭት ምክንያቱ የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ውድቀት ነው ብላለች።የቡድኑ አባላት በሞስኮ በሚኖራቸው ቆይታ ሐማስ እስራኤል ላይ ጥቃት በፈጸመበት ወቅት ያገታቸው የሩሲያ ዜጎች በሚለቀቁበት ሁኔታ ላይ ንግግር ይደረጋል ሲል ሮይተርስ የዜና ወኪል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ዘግቧል።የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛኻሮቫ በበኩላቸው የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሊ ባግጂሪ ካኒ በአሁኑ ወቅት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሞስኮ እንደሚገኙ ተናግረዋል።Article share tools
  17. የታተመዉ 12:10 26 ጥቅምት 202312:10 26 ጥቅምት 2023እስራኤል የሐማስ የድኅንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊን ገደልኩ አለችየእስራኤል ጦር የሐማስ ቁልፍ መሪ የሆነውን ግለሰብ እያካሄደችው ባለው አየር ጥቃት መግደሏን ገለጸች።ጦሩ ገደልኩት ያለው ሻዲ ባሩድ የተባለው ግለሰብ፣ የሐማስ የደኅንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እንደነበረ እና በእስራኤል ላይ የተከፈተውን ድንገተኛ ጥቃት ዕቅድ ካወጡት መካከል አንዱ ነው ብሏል።የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ በአየር ጥቃት የተገደለው ሻዲ ባሩድ በጋዛ የሐማስ ከፍተኛ ባለሥልጣን ከሆነው ያሃያ ሲንዋር ጋር በቅርበት ይሠራ ነበር ብለዋል።ያሃያ ሲንዋር ጋዛ ከሚገኙ የሐማስ መሪዎች መካከል በእስራኤል በጥብቅ ከሚፈለጉ ቀዳሚው ነው።የሐማስ የደኅንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ መገደልን በተመለከተ የሐማስ የጦር ክንፍ የሆነው ቃሳም ብርጌድ አስካሁን የሰጠው ማረጋገጫ ሆነ ማስተባበያ የለም።Article share tools
  18. የታተመዉ 11:40 26 ጥቅምት 202311:40 26 ጥቅምት 2023ሐማስ ካገታቸው ሰዎች መካከል 50ዎቹ በእስራኤል ጥቃት ተገድለዋል አለሐማስ ከእስራኤል አግቶ በቁጥጥሩ ስር ከሚገኙት ታጋቾች መካከል 50 የሚሆኑት እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እየፈጸመችው ባለችው የአየር ጥቃት መገደላቸውን አስታወቀ።የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ ቃል አቀባይ በተዋጊዎቹ ተይዘው ከነበሩ ታጋቾች መካከል በእስራኤል የአየር ድብደባዎች 50 ያህሉ ተገድለዋል ብለዋል።አቡ ኦቤይድ የተባሉት የሐማስ የጦር ክንፍ ቃል አቀባይ 50 ታጋቾች ተገድለዋል ከማለት ውጪ ተጨማሪ ማብራሪያ አልሰጡም።ቢቢሲ የዚህን መረጃ ትክክለኛነት ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ አልቻለም።ሐማስ ቅዳሜ መስከረም 26/2106 ዓ.ም. ድንገተኛ ጥቃት ፈጽሞ አብዛኛዎቹ እስራኤላውያን የሆኑ፣ የበርካታ አገራት ዜጎች ያሉበት 224 ሰዎችን ማገቱን እስራኤል ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።Article share tools
  19. የታተመዉ 11:04 26 ጥቅምት 202311:04 26 ጥቅምት 2023እስራኤል ወደ ጋዛ ሰብራ የገባችው ‘ለቀጣዩ ዘመቻ ዝግጅት ነው’ አለችየእስራኤል ታንክEPACopyright: EPAየእስራኤል ጦር ወደ ተመረጡ የጋዛ አካባቢዎች ረቡዕ ሌሊት ሰብሮ በመግባት ጥቃት የፈጸመው ለቀጣዩ ዙር ውጊያ ዝግጅት ለማድረግ ነው ብሏል።እስራኤል ከሦስት ሳምንት ገደማ በፊት በሐማስ ድንገተኛ ጥቃት ከተከፈተባት በኋላ ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶችን በጋዛ ላይ ስትፈጽም ቆይታለች።ቴል አቪቭ የአየር ጥቃቱን እያደረሰች በምድር ኃይል በጋዛ በኩል ጥቃት ለመክፍት ዝግጅት ስታደርግ ቆይታለች።ረቡዕ ሌሊት እስራኤል “በተመረጡ ስፍራዎች” በታንክ የታገዘ ወረራ የፈጸመች ሲሆን፣ ይህ ግን ለቀጣዩ ጦርነት ዝግጅት እንጂ በምድር ኃይል የማደርገው ጥቃት አይደለም ብላለች።የእስራኤል ጦር ለሰዓታት በቆየው ዘመቻ በወታደሮቹ ላይ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስ “አሸባሪዎች ተወግደዋል” ብሏል።እስራኤል ጥቃት የፈጸመባትን የሐማስ ቡድንን ከጋዛ ለማጥፋት የዛተች ሲሆን፣ በጋዛ ድንበር ዙሪያ ከ300 ሺህ በላይ ሠራዊቷን እና ከባድ መሳሪያዎቿን በተጠንቀቅ አቁማለች።አንዳንድ አገራት እስራኤል ወደ ጋዛ ዘልቃ እንዳትገባ እየወተወቱ ቢሆንም፣ የእስራኤል ሠራዊት ግን በጋዛ ላይ ለሚፈጽመው የእግረኛ ሠራዊት ወረራ ዝግጅት እና የመጀመሪያ ደረጃ ዘመቻዎችን እኣካሄደ መሆኑን ገልጿል።Article share tools
  20. የታተመዉ 10:07 26 ጥቅምት 202310:07 26 ጥቅምት 2023ኤርዶዋን ምዕራባውያን ፊታቸውን ያዞሩት “የሚፈሰው የሙስሊም ደም” ስለሆነ ነው አሉየቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃንEPACopyright: EPAየቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃንImage caption: የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃንየቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን እስራኤል በጋዛ እየፈጸመች ባለው ጥቃት ምክንያት ምዕራባውያንን አጥብቀው ተቹ።ኤርዶዋን በጋዛ “እየፈሰሰ ያለው የሙስሊም ደም በመሆኑ” ምዕራባውያን መንግሥታት እርምጃ እየወሰዱ አይደለም ብለዋል።“ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ ለምን አይከበርም?” ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ጠይቀዋል። “ጥቅማቸውን የማያስከብር ከሆነ [ምዕራባውያኑ] ዞር ብለው አይመለከቱም። ለምን? ምክንያቱም እየፈሰሰ ያለው የሙስሊም ደም ስለሆነ ነው” ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ ወደ እስራኤል ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ የሰረዙ ሲሆን፣ ባለፈው ወር በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁን “እጅ መጨበጤ ይቆጨኛል” ብለዋል።ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ለቱርክ ፓርላማ ሲናገሩ እስራኤል በጋዛ “ጭፍጨፋ” እየፈጸመች ነው ያሉ ሲሆን፣ ፍልስጥኤማውያን ደግሞ “ለነጻነት” እየታገሉ ነው ብለዋል።“ሐማስ አሸባሪ አይደለም። ለዜጎች እና ለመሬታቸውን የሚታገል የነጻነት ድርጅት ነው” ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ተደምጠዋል።