የተቃዋሚው የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ ሊቀመንበር ተሠማ ኤሊያስ ለደኅንነቴ ስለሰጋኹ ከአገር ወጥቻለኹ በማለት ማምሻውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሠፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።
አቶ ተሠማ፣ የክልሉ መንግሥት “ያለ ወንጀል የእስር ማዘዣ” እንዳወጣባቸውና “በክልሉ ከፍተኛ አመራር አቀነባባሪነት” ለሕይወታቸው የሚያሰጋ እንቅስቃሴ እየተደረገ ስለመኹኑ “ተጨባጭ መረጃ” እንዳገኙ ገልጸዋል። የፓርቲው ሊቀመንበር፣ በሕይወቴ ላይ ተደቅኗል ባሉት የደኅንነት ስጋት ሳቢያ ቀደም ሲል ለፓርቲው ትግል ሲሉ ያልተጠቀሙበትን የውጭ ትምህርት ዕድል አኹን ለመጠቀም ከአገር መውጣታቸውንም አብራርተዋል።
Post

የተቃዋሚው የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ ሊቀመንበር ተሠማ ኤሊያስ ለደኅንነቴ ስለሰጋኹ ከአገር ወጥቻለኹ
በማለት ማምሻውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሠፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።
ተሠማ፣ የክልሉ መንግሥት “ያለ ወንጀል የእስር …..ማዘዣ” እንዳወጣባቸውና “በክልሉ ከፍተኛ አመራር
አቀነባባሪነት” ለሕይወታቸው የሚያሰጋ እንቅስቃሴ እየተደረገ ስለመኹኑ “ተጨባጭ መረጃ” እንዳገኙ
ገልጸዋል። የፓርቲው ሊቀመንበር፣ በሕይወቴ ላይ ተደቅኗል ባሉት የደኅንነት ስጋት ሳቢያ ቀደም ሲል
ለፓርቲው ትግል ሲሉ ያልተጠቀሙበትን የውጭ ትምህርት ዕድል አኹን ለመጠቀም ከአገር
መውጣታቸውንም አብራርተዋል። የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት አመራሮች “በጣም አደገኛ የሕዝብ ጠላት
ኾነዋል” በማለት የከሰሱት ተሠማ፣ አመራሮቹን ወደ ሥልጣን ያመጣቸው ፌደራል መንግሥት የክልሉ
አመራሮች ንጹሃን ዜጎችን ያለጥፋታቸው ማሠርን ጨምሮ በሕዝብ ላይ የሚፈጽሙትን በደል በዝምታ
ተመልክቷል በማለት ወቅሰዋል። የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ፣ የክልሉ ፖሊስ በርካታ አመራሮቹን
እንዳሠረበት ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ወዲህ ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል። ምርጫ ቦርድም፣ ፖሊስ
የፓርቲውን አመራሮች ያሠረበትን ምክንያት እንዲያብራራ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ደብዳቤ መላኩን
ፓርቲው በቅርቡ መግለጡ ይታወሳል። [ዋዜማ]
Translate post
የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት አመራሮች “በጣም አደገኛ የሕዝብ ጠላት ኾነዋል” በማለት የከሰሱት ተሠማ፣ አመራሮቹን ወደ ሥልጣን ያመጣቸው ፌደራል መንግሥት የክልሉ አመራሮች ንጹሃን ዜጎችን ያለጥፋታቸው ማሠርን ጨምሮ በሕዝብ ላይ የሚፈጽሙትን በደል በዝምታ ተመልክቷል በማለት ወቅሰዋል።
የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ፣ የክልሉ ፖሊስ በርካታ አመራሮቹን እንዳሠረበት ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ወዲህ ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል። ምርጫ ቦርድም፣ ፖሊስ የፓርቲውን አመራሮች ያሠረበትን ምክንያት እንዲያብራራ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ደብዳቤ መላኩን ፓርቲው በቅርቡ መግለጡ ይታወሳል። [ዋዜማ]
