October 27, 2023 – Konjit Sitotaw
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ መቀሌ ውስጥ የተጠራው የክልል ባለሥልጣናት ስብሰባ “ሕገወጥ” ነው ሲሉ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
ጌታቸው፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ስብሰባው መደበኛ ባልኾነ ኹኔታ የተጠራና “ሕገወጥ” መኾኑን አውቀው ሃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው በማለት ማሳሰባቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ጌታቸው፣ “ሕገወጥ” ያሉትን ስብሰባ ማን እንደጠራው ይግለጡ አይግለጡ ግን ዘገባው አልጠቀሰም።
ሕወሃት በመጭው ቅዳሜና ዕሁድ የማዕከላዊ ኮሚቴና ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ እንደሚያካሂድ ገልጦ፣ በስብሰባው ዓላማ ዙሪያ የሚናፈሱ ወሬዎች ግን ሐሰት ናቸው የሚል መግለጫ ትናንት ምሽት አውጥቶ ነበር።
