Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች
- BBC
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59
Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ
- BBC
Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች
- BBC
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች
- BBC
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 23 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 23 SECONDS1:23
Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBCሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?
- BBC
Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBC
ጭምቅ ሃሳብ
- የእስራኤል ጦር ከፍተኛ የሐማስ አመራርን ገደልኩ አለ
- በጋዛ ከተገደሉት ከ40 በመቶ በላይ የሚሆኑት ህጻናት ናቸው- የዓለም ጤና ድርጅት
- ተመድ ወደ ጋዛ እርዳታ እንዲገባ ተማጽኖውን አቀረበ
- አሜሪካ በሶሪያ ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ
- 20 ቀናትን ያስቆጠረው የእስራኤል-ጋዛ ጦርነት
- አሜሪካ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል “የተኩሰ አቁም እንዲደረግ አልደግፍም” አለች
- አሜሪካ በሶሪያ የሚገኙ ወታደራዊ ተቋማትን በአየር ደበደበች
- የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በጋዛ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረስ ድምጽ ሊሰጥ ነው
- በጋዛ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ7ሺህ አለፈ
- ‘በጋዛ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ የለም’- ተመድ
- የእስራኤል ጦር በጋዛ ‘ዒላማ በተደረጉ ቦታዎች’ የታንክ ወረራ ፈጸመ
- ተመድ በነዳጅ እጥረት ምክንያት የጋዛ ስራው ሊቆም ይችላል አለ
- ሶሪያ 8 ወታደሮቼ በእስራኤል ተገደሉብኝ አለች
- የዮርዳኖስ ንግሥት ራኒያ ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙሃንን ተቹ
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 9:429:42እስራኤል በጋዛ ላይ የምታካሂደውን ዘመቻ አጠንክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች
Israeli Defence Forces (IDFCopyright: Israeli Defence Forces (IDFየእስራኤል ኤፍ16 ቦምብ ጣይ ጀትImage caption: የእስራኤል ኤፍ16 ቦምብ ጣይ ጀትየእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት የአገራቸው ሠራዊት በጦርነቱ የሚያካሂደው ዘመቻ ያለበት ደረጃ “መቀየሩን” በመግለጽ፣ “ተጨማሪ መረጃ አስኪሰጥ ድረስ” ዘመቻው ይቀጥላል ብለዋል።አርብ ምሽት ሠራዊቱ በወሰደው እርምጃ “የጋዛ ምድር ተንቀጥቅጣለች” በማለት የመከላከያ ሚኒስትሩ ለአንድ ቴሌዥን ጣቢያ ተናግረዋል።“ከመሬት ላይ እና በአየር ጥቃት ፈጽመናል። በሁሉም ደረጃ የሚገኙ ሽብርተኞች ላይ በያሉበት ጥቃት ፈጽመናል።ለሠራዊታችን የተሰጠው መመሪያ ግልጽ ነው፡ ተጨማሪ መግለጫ አስከሚሰጥ ድረስ ዘመቻው ይቀጥላል” ብለዋል።ከአርብ ምሽት ጀምሮ በተጠናከረ ሁኔታ የእስራኤል ጦር ኃይል በጋዛ ላይ የሚያካሂደው ጥቃት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ ወደ ተወሰኑ የጋዛ ክፍሎች የእስራኤል ወታደሮች ዘልቀው መግባታቸው ተነግሯል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ

- የታተመዉ 9:419:41ከአርብ ሌሊት የእስራኤል ድብደባ በኋላ ጋዛ ላይ ከፍተኛ ውድመት ደረሰ
AFPCopyright: AFPእስራኤል ሌሊቱን ካካሄደችው ከፍተኛ ድብደባ በኋላ ጋዛ ላይ የደረሰውን ውድመት የሚያሳዩ ምስሎች እየወጡ ነው።እነዚህ ምስሎች በጋዛ ከተማ ከሚገኘው አል-ሻቲ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ አቅራቢያ የተነሱ ናቸው።እዚህ ገጽ ላይ ለማሳየት እጅግ አሰቃቂ ከሆኑ ምስሎች በአንዱ አንድ ጎልማስ የታዳጊ ልጅ አስክሬን ታቅፎ ሲያለቅስ ያሳያል።ምሽቱን እስራኤል ባደረሰችው ከባድ ጥቃት ምክንያት በሰው ላይ የደረሰው ጉዳት እስካሁን ግልጽ አይደለም። እስራኤል የስልክ ማማዎችን ዒላማ በማድረጓ የግንኙነት መስመሮች በጋዛ ተቋርጠዋል።የእስራኤል ሲም ካርዶች ያሏቸው ሰዎች ስልክ ብቻ እንደሚሰሩ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
AFPCopyright: AFP
AFPCopyright: AFP
AFPCopyright: AFPArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:545:54የእስራኤል ጦር አሁንም ድረስ በጋዛ እንዳለ ተገለጸ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ ጦራቸው እስከ ቅዳሜ ረፋድ በጋዛ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።ቃል አቀባዩ ቅዳሜ ረፋድ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን በመግለጫቸው የሚከተሉትን ተናግረዋል።
- የእስራኤል መከላከያ ኃይል ወደ ሰሜናዊ ጋዛ የገባ ሲሆን የምድር ጦሩ በአየር ኃይሉ እና በባሕር ኃይሉ ድጋፍ ጥቃቶችን አድርሷል።
- እስራኤል በዚህ ዘመቻ የሐማስ ከፍተኛ አዛዥን ገድላለች።
- ዛሬ ምግብ፣ ውሃ፣ መድሃኒት የጫኑ የሰብዓዊ ድርጅቶች ተሸከርካሪዎች ወደ ጋዛ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል
- ሄዝቦላ ወደ እስራኤል ሚሳኤል መተኮሱን ተከትሎ የእስራኤል ጦር የአጸፋ እርምጃ ወስዷል።
- እስካሁን ድረስ 311 የእስራኤል ወታደሮች መገደላቸውን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።
- በሐማስ የታገቱትን ነጻ አውጥቶ ለቤታቸው ማብቃት የጦሩ ዋነኛ ዓላማ ነው።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 4:444:44ከከባድ የቦምብ ድብደባ ምሽት በኋላ በጋዛ “ትምርስ” ሆኗል
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበጋዛ የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ሩሽዲ አቡአሉፍ ሰሜናዊ የጋዛ ሰርጥ ምሽቱን እስካሁን ታይቶ በማይታቅ መጠን ከፍተኛ ድብደባ አስተናግዳለች ብሏል።በዚህም ሰሜናዊ ጋዛ ሙሉ በሙሉ ትርምስ ውስጥ ገብታለች ብሏል።የእስራኤል ጦር ከአርብ ለቅዳሜ ንጋት የሚያካሂደውን ዘመቻ አስፋፍቶ 150 የሐማስ ዒላማዎችን መደብደቡን ገልጿል።ትናንት ምሽት የነበረው ጥቃት በአየር ኃይል፣ በታንክ እና በእግረኛ ኃይል የታጀበ ስለመሆኑ ተገልጿል።የእስራኤል አየር ኃይል የዘመቻዎች ኃላፊ ብርጋዲዬር ጀነራል ጊላድ ኬኢናን እንዳሉት ወደ 100 የሚጠጉ ተዋጊ ጀቶች በጋዛ ሰርጥ የሐማስ ዒላማዎችን ሲደበድቡ አድረዋል።የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ የሆነው አል ቃሳም ብርጌድም በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ ከእስራኤል የምድር ኃይል ጋር እየተዋጋ ስለመሆኑ መግለጫ ሰጥቷል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:073:07100 ተዋጊ ጀቶች ጋዛን ሲደበድቡ ማደራቸውን ተገለጸ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል ባለስልጣናት አርብ ሌሊት ወደ 100 የሚጠጉ ተዋጊ ጀቶች በጋዛ ድብደባ ሲፈጽሙ ማደራቸውን አስታወቁ።የእስራኤል አየር ኃይል የዘመቻዎች ኃላፊ ብርጋዲዬር ጀነራል ጊላድ ኬኢናን እንዳሉት ወደ 100 የሚጠጉ ተዋጊ ጀቶች በጋዛ ሰርጥ የሐማስ ዒላማዎችን ሲደበድቡ አድረዋል።የእስራኤል ጦር የአየር ኃይሉን የዘመቻዎች ኃላፊን ጠቅሶ ባወጣው መግለጫ የአየር ጥቃቶቹ ዓላማ “የሐማስ እጅ ያረፈበትን እያንዳንዱ ነገር ማውደም ነው”።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:542:54በጋዛ የስልክ እና የኢንተርኔት አግልግሎት ተቋረጠ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበጋዛ የእስራኤል የተጠናከረው ድብደባ እንደቀጠለ ነውImage caption: በጋዛ የእስራኤል የተጠናከረው ድብደባ እንደቀጠለ ነውበጋዛ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ የግንኙነት መስመሮች ተቋርጠዋል።እንደ የፍልስጤም ቴሌኮሚኒኬሽን ኩባንያ ከሆነ የእስራኤል ጦር የስልክ ማማዎችን እና መስመሮችን መልሶ መላልሶ በመደብደቡ በጋዛ የስልክ እና የኢንተርኔት አግልግሎት ተቋርጧል።በግንኙነት መስመር መቋረጥ ምክንያት የሰብዓዊ ድርጅቶችና መገናኛ ብዙሃን በጋዛ ካሉ ሠራተኞቻቸው ጋር መገናኘት አለመቻላቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:532:53ሐማስ በሰሜናዊ ጋዛ ከእስራኤል ጦር ጋር እየተዋጋው ነው አለ
AFPCopyright: AFPየእስራኤል ጦር አባላት በሐማስ ጥቃት የወደመ ቤት ሲቃኙImage caption: የእስራኤል ጦር አባላት በሐማስ ጥቃት የወደመ ቤት ሲቃኙየሐማስ ወታደራዊ ክንፍ የሆነው አል ቃሳም ብርጌድ በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ ከእስራኤል የምድር ኃይል ጋር እየተዋጋው ነው አለ።ቡድኑ በጋዛ ቤኢት ሃኑን እንዲሁም ቡሬጂ በተባሉ አካባቢዎች ውጊያ እየገጠመ መሆኑን ከመግለጽ ውጭ የሰጠው ተጨማሪ መረጃ የለም።ሐማስ በጋዛ ከእስራኤል እግረኛ ጦር ጋር የተኩስ ልውውጥ እያደረጉ ነው ያለው እስራኤል ዘመቻዎቿን ማስፋቷን ከገለጸች በኋላ ነው።የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ለኒው ዮርክ ታይምስ እግረኛ ወታደሮች እና ታንኮች በጋዛ ሰርጥ ይገኛሉ ሲሉ ተናግረዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:411:41ቤተ-እስራኤላዊው አቨራ መንግሥቱ እና ለዓመታት በሐማስ እገታ ሥር ያሉ ሌሎች እስራኤላውያንበቅርቡ ሐማስ ከፈጸመው ጥቃት ጋር ተያይዞ ከታገቱት እስራኤላውያን በተጨማሪ ኢትዮጵያዊ-እስራኤላዊው አቨራ መንግሥቱ እና የቦዴያን አረብ-እስራኤላዊው ሒሻም አል-ሳይድ ለበርካታ ዓመታት በሐማስ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:321:32እስራኤል የሐማስ የአየር ዘመቻ ኃላፊን ገደልኩ አለችየእስራኤል መከላከያ ኃይል የሐማስ ቡድን የአየር ላይ ጥቃቶች አዛዥ የሆነውን ኃላፊ ገደልኩ አለች።ግለሰቡ መስከረም 26 በተፈጸመው ጥቃት የሐማስ ተዋጊዎች በአየር እስራኤል ዘልቀው እንዲገቡ እቅድ መንደፉ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም አሴም አቡ ራካብ የተባለው ግለሰብ በድሮኖች የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት ሲያቀናጅ ነበር ተብሏል።የእስራኤል ጦር አቡ ራካብ ገደልኩ ያለው ጦሩ ለሊቱን ባካሄደው የአየር ድብደባ ነው።እስራኤል ከፍተኛ የሐማስ አባልን ከደልኩ ስትል ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። ትናንት የእስራኤል ጦር የቡድኑን የድኅንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊን መግደሉን አስታውቆ ነበር።ጦሩ ገደልኩት ያለው ሻዲ ባሩድ የተባለው ግለሰብ፣ የሐማስ የደኅንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እንደነበረ እና በእስራኤል ላይ የተከፈተውን ድንገተኛ ጥቃት ዕቅድ ካወጡት መካከል አንዱ ነው ብሏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:301:30አሜሪካ በሌባኖስ ያሉ ዜጎቿ ከአገር እንዲወጡ አዘዘች
EPACopyright: EPAአሜሪካን የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ በቤይሩት ተካሂዶ ነበር።Image caption: አሜሪካን የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ በቤይሩት ተካሂዶ ነበር።አሜሪካ በሌባኖስ ያሉ ዜጎቿ በተቻላቸው ፍጥነት ከአገሪቱ እንዲወጡ አሳሰበች።የአሜሪካ መንግሥት በአካባቢው ያለውን የደኅንነት ሁኔታ መገመት አስቸጋሪ ስለሆነ የመንገደኞች አውሮፕላን አገልግሎት እስካለ ድረስ ዜጎች ከሌባኖስ እንዲወጡ ጠይቋል።ከሐማስ ጥቃት በኋላ መቀመጫውን ሌባኖስ ባደረገው የሺያ ሙስሊም ሚሊሻ ቡድን በሆነው ሄዝቦላ እና በእስራኤል ጦር መካከል የሚደረገው የተኩስ ልውውጥ በየዕለቱ እየጨመረ ይገኛል።ይህን ተከትሎ እስራኤል ሠራዊቷን እና ብረት ለበስ ወታደራዊ ተሸርካሪዎቿን ወደ ሌባኖስ ድንበር አስጠግታለች።በሌባኖስ ያለው ሁኔታ ያሳሰበው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መንግሥት ቀውስ በሚፈጠር ግዜ ዜጎችን ማውጣት ስለመቻሉ ምንም ማረጋገጫ ስለሌለ አሜሪካውያን ሁኔታዎች በፈቀዱ ወቅት ከሌባኖስ እንዲወጡ አሳስቧል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 13:53 27 ጥቅምት 202313:53 27 ጥቅምት 2023ጋዛ በከባድ ፍንዳታ እየተናጠች ባለበት የእስራኤል እግረኛ ሠራዊት ዘመቻውን እያሰፋ ነው
AFPCopyright: AFPምሽት ላይ ጋዛን ያናወጠው ፍንዳታImage caption: ምሽት ላይ ጋዛን ያናወጠው ፍንዳታአርብ ምሽት ጋዛ ሰርጥን ያናወጡ ከባድ ፍንዳታዎችን ተከትሎ የእስራኤል እግረኛ ሠራዊት የሚያካሂደውን “ዘመቻ እያሰፋ” መሆኑን የጦሩ ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ ተናገሩ።ለዚህ ጥቃት ምላሽ ነው በማለት ሐማስ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሱን መግለጹን የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ኤኤፍፒ ዘግቧል።በተጨማሪም የእስራኤል ሠራዊትን በጋዛ ላይ “ተከታታይ ጥቃቶችን” እየፈጸመ መሆኑ ለኤኤፍፒ ገልጿል።ሠራዊቱ በጋዛ ላይ የሚያካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ እያስፋፋ መሆኑን መግለጹን ተከትሎ፣ የጋዛ ከተማ ነዋሪዎች ወደ ደቡብ የጋዛ ክፍል ለቀው እንዲወጡ አዟል።ረቡዕ ሌሊት የእስራኤል ታንኮች ወደ ሰሜናዊ ጋዛ ክፍል ዘልቀው በመግባት የተመረጡ እርምጃዎችን ወስደው እንደወጡ መገለጹ ይታወቃል።ይህም ጥቃት ሠራዊቱ በጋዛ ላይ ለሚያካሂደው የቀጣይ ምዕራፍ ዘመቻ አመቺ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የታለመ መሆኑን የእስራኤል ጦር ኃይሎች ባለሥልጣናት ተናግረዋል።ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ድንገተኛ ጥቃትን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት ነገ ቅዳሜ ሦስተኛ ሳምነቱን የሚይዝ ሲሆን፣ እስራኤል እግረኛ ሠራዊቷን ወደ ጋዛ ለማስገባት እየተዘጋጀች መሆኑ ሲነገር ቀይቷል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 10:25 27 ጥቅምት 202310:25 27 ጥቅምት 2023ዛሬ አርብ የተከሰቱ ዋና ዋና ነገሮች በአጭሩ
ReutersCopyright: Reutersቴል አቪቭ ውስጥ በሚገኝ የመኖሪያ ሕንጻ ላይ የተፈጸመ የሮኬት ጥቃትImage caption: ቴል አቪቭ ውስጥ በሚገኝ የመኖሪያ ሕንጻ ላይ የተፈጸመ የሮኬት ጥቃትበእስራኤል እና በጋዛ መካከል የሚካሄደው ጦርነት ዛሬ አርብ 20ኛ ቀኑን ይዟል። በግጭቱ ከሁለቱም ወገን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል። በዛሬው ዕለት ምን ዋና ዋና ነገሮች ተከሰቱ?
- የሕክምና ሠራተኞች እንዳሉት በእስራኤሏ ከተማ ቴል አቪቭ ውስጥ በሚገኝ የመኖሪያ ሕንጻ ላይ በተፈጸመ የሮኬት ጥቃት ሦስት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
- መስከረም 26/2016 ዓ.ም. በተቀሰቀሰው ግጭት አስከ ዛሬ ድረስ ጋዛ ውስጥ 7,028 ሰዎች የተገደሉ መሆናቸውን የዓለም ጤና ድርጅት የገለጸ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ ወደ 3,000 የሚጠጉት ልጆች ናቸው።
- ከሦስት ሳምንት በፊት ሐማስ በደቡባዊ እስራኤል ላይ በፈጸመው ድንገተኛ ጥቃት ቢያንስ 1,400 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ 229 የሚሆኑት ደግሞ በታጣቂው ቡድን ታግተው ተወስደዋል ተብሎ ይታሰባል።
- ውሃ፣ ምግብ እና ሕክምና አቅርቦቶችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከሕክምና ቡድን ጋር በመሆን ወደ ጋዛ እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል፣ ነገር ግን የረድኤት ድርጅቶች ከዚህ የበለጠ እርዳታ እንደሚያስፍልግ ጥሪያቸውን ማቅረብ ቀጥለዋል።
- ጦርነቱ ከተጀመረበት ዕለት አንስቶ ወደ ጋዛ ነዳጅ እንዲገባ አልተፈቀደም፣ የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ ማኅበር ለቢቢሲ እንደገለጸው ለአምቡላንሶች የሚያስፈልገው ነዳጅ እያለቀ ሲሆን፣ ሕይወት አድን ማሽኖች ብቻ ናቸው እየሰሩ ያሉት።
- የመንግሥታቱ ድርጅት የፍልስጤም የስደተኞች ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ተኩስ አቁም እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፣ ግጭቱ ከቀጠለ ሥራውን ከአምስት ቀናት በላይ ሊቀጥል እንደማይችል አሳውቋል። ደርጅቱ ቢያንስ 57 ሠራተኞቹ ጋዛ ውስጥ ተገደለውበታል።
- አሜሪካ ሶሪያ ውስጥ የኢራን እና የምትደግፋቸው ሚሊሻዎቸ የሚጠቀሙባቸውን ወታደራዊ ተቋማትን በአውሮፕላን ደብድባለች። ይህም በቅርቡ ሶሪያ እና ኢራን ውስጥ በሚገኙ ወታሮቿ ላይ ለተፈጸሙ ጥቃቶች ምላሽ መሆኑን አሳውቃለች።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 8:46 27 ጥቅምት 20238:46 27 ጥቅምት 2023አሜሪካ በሶሪያ ላይ የፈጸመችው የአየር ጥቃት ከእስራኤል-ጋዛው ጦርነት ጋር ግንኙነት የለውም አለች
ReutersCopyright: Reutersየአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲንImage caption: የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲንአሜሪካ በምስራቃዊ ሶሪያ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ወታደራዊ ተቋማት ላይ የፈጸመችው የአየር ድብደባ ከእስራኤል- ጋዛ ጦርነት ጋር ግንኙነት እንደሌለው አስታወቀች።በኢራቅ እና በሶሪያ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር አባላት ላይ በኢራን የሚደገፉ የሚሊሻ ቡድኖች እየሰነዘሩት ላለው ጥቃት ምላሽ እንደሆነም የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ተናግረዋል።አገራቸው የፈጸመቻቸው እነዚህ ጥቃቶች “በእስራኤል እና በሃማስ መካከል እየተካሄደ ካለው ግጭት የማይገናኙ እና የማይያዙ ናቸው” ሲሉም በመግለጫቸው አክለዋል።የመከላከያ ሚኒስትሩ ሁሉም መንግሥታትም ሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ ሃይሎች ወደ ቀጣናዊ ግጭት ሊያሸጋግር የሚችል እርምጃም እንዳይወስዱም አሳስበዋል።በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር አርብ ንጋት ላይ የአሜሪካ ኤፍ-16 የጦር ጄቶች ከኢራቅ ጋር በምትሰዋነው በአቡከማል ከተማ አቅራቢያ የአየር ጥቃት ፈጽመዋል።በዚህ የአየር ጥቃት ኢራን የጦር መሳሪያ እና ተተኳሽ ለማከማችት የምትጠቀምበት ስፍራ ወድሟል ተብሏል። በጥቃቱ የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 7:58 27 ጥቅምት 20237:58 27 ጥቅምት 2023በጋዛ ከተገደሉት ከ40 በመቶ በላይ የሚሆኑት ህጻናት ናቸው- የዓለም ጤና ድርጅት
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ባለው የማያባራ የአየር ጥቃት ከተገደሉት ከ40 በመቶ በላይ የሚሆኑት ህጻናት መሆናቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።በጋዛ ሰርጥ እስካሁን 7 ሺህ 28 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴርን ዋቢ ያደረገው ተቋሙ በአየር ጥቃቱ ስለተገደሉት ሰዎች ዝርዝር መረጃ እንደደረሰው ገልጿል።በተጨማሪም ሌት ተቀን እየተፈጸመ ባለው የአየር ጥቃት 18 ሺህ 482 የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከነዚህም አብዛኛዎቹ ህጻናት መሆናቸውን ነው ተቋሙ በዛሬው ዕለት ያስታወቀው።በጋዛ ካሉ 35 ሆስፒታሎች ውስጥ 23ቱ አሁንም በከፊል አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ጠቁሞ ሌሎቹ እንዲሁም የማህበረሰብ ክሊኒኮች ተዘግተዋል ብሏል።በጋዛ ውስጥ 1 ሺህ ያህል ፍልስጥኤማውያን የኩላሊት እጥበት (ዲያሊሲስ) እንደሚያስፈልጋቸው፣ 30 ያለጊዜያቸው የተወለዱ ህጻናት በማሞቂያ ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ እና 2 ሺህ የካንሰር ህሙማን አስቸኳይ ህክምና ያስፈልጋቸዋል ብሏል።ሆኖም የነዳጅ እጥረት ክፉኛ ባጋጠማት ጋዛ ሆስፒታሎች አገልግሎታቸውን በጄኔሬተር እንዲሰጡ ለማድረግ ነዳጅ እንዲገባ መፈቀድ እንዳለበትም ነው ያስታወቀው።በሆስፒታሎች ውስጥ ያለውን አሳዛኝ ሁኔታ ያብራሩት የዓለም ጤና ድርጅት ባለስልጣን በጠና የተጎዱ ህሙማን ያለ ማደንዘዣ ቀዶ ህክምና በመተላለፊያዎች ላይ እንደሚደረግላቸው፣ “የተቆራረጡ የህጻናት አካላት” በየስፍራው የሚታዩበት እና የሞት ጥላ ያንዣበበት መሆኑንም ገልጸዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 7:12 27 ጥቅምት 20237:12 27 ጥቅምት 2023ቤተሰቡ በእስራኤል አየር ጥቃት የተገደሉበት የአልጀዚራው ጋዜጠኛየጋዛ ሰፈሮችን ወደ ፍርስራሽ ክምርነት የቀየሩት የእስራኤል አየር ጥቃቶችን በድፍረት ሲዘግቡ ከነበሩት አንዱ ዋኤል አልዳህዱ ነው። ዓለም ትኩረቱን ሁሉ በጋዛ ሰርጥ ላይ ባደረገበት ወቅት አልዳህዱ ከጋዛ ተሰሚ ድምጾች አንዱ ሆኗል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 7:09 27 ጥቅምት 20237:09 27 ጥቅምት 202320 ቀናትን ያስቆጠረው የእስራኤል-ጋዛ ጦርነት
ReutersCopyright: Reutersበደቡባዊ ጋዛ ኻን ዮኒስ ከተማ በተፈጸመው የአየር ጥቃት ቤተሳበቸውን ያጡ ፍልስጥኤማውያን እናቶች ሐዘናቸውን እየገለጹImage caption: በደቡባዊ ጋዛ ኻን ዮኒስ ከተማ በተፈጸመው የአየር ጥቃት ቤተሳበቸውን ያጡ ፍልስጥኤማውያን እናቶች ሐዘናቸውን እየገለጹበእስራኤል- ጋዛ የተቀሰቀሰው ጦርነት 20 ቀናት ሞላው።ሐማስ በእስራኤል ላይ በፈጸመው መብረቃዊ ጥቃት ከ1 ሺህ 400 በላይ እስራኤላውያን ተገድለዋል፤ ከ200 በላይ ሰዎች ታግተዋል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የማያባራ ጥቃት እየፈጸመች ሲሆን ከ7 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ተገድለዋል፤ ከነዚህም አብዛኞዎቹ ህጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም በፍርስራሽ ስር ተቀብረዋል።በተጨማሪም እስራኤል ጋዛን በሙሉ ከበባ በማስገባት ነዳጅ፣ ውሃ፣ ኤሌክትሪክ አቅርቦት እንዲቋረጥ አድርጋለች።የባለፉትን 20 ቀናት በምስል እንቃኛቸው፦
ReutersCopyright: Reutersበኻን ዮኒስ ከተማ በእስራኤል አየር ጥቃት በፈራረሱ ክምሮች ውስጥ አስከሬን እየፈለጉ ያሉ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችImage caption: በኻን ዮኒስ ከተማ በእስራኤል አየር ጥቃት በፈራረሱ ክምሮች ውስጥ አስከሬን እየፈለጉ ያሉ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤል ታንኮች በሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ በወታደራዊ ልምምድ ላይImage caption: የእስራኤል ታንኮች በሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ በወታደራዊ ልምምድ ላይ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበግብጽ ራፋህ የድንበር ማቋረጫ በኩል ወደ ጋዛ ሰርጥ ለመግባት በመጠባበቅ ላይ ያሉ እርዳታ የጫኑ መኪናዎችImage caption: በግብጽ ራፋህ የድንበር ማቋረጫ በኩል ወደ ጋዛ ሰርጥ ለመግባት በመጠባበቅ ላይ ያሉ እርዳታ የጫኑ መኪናዎችArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:32 27 ጥቅምት 20236:32 27 ጥቅምት 2023አሜሪካ በሶሪያ ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየአሜሪካ በምሥራቃዊ ሶሪያ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ወታደራዊ ተቋማት ላይ የአየር ደብድባ መፈጸሟን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ።የአሜሪካ ጥቃት የእስራኤል እና ሐማስ ግጭትን በመካከለኛው ምሥራቅ ያሉ አገራትን የሚያሳትፍ ግጭት እንዲሆን ሊያደርግ ይችላል በሚል ስጋት ነው የዋጋ ጭማሪው የተከሰተው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።በዚህም ምክንያት የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በ1.16 ዶላር በመጨመር 89.09 ዶላር እየተሸጠ ነው።በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭቱ የሚስፋፋ ከሆነ ነዳጅ አምራች ከሆኑ የአካባቢው አገራት በሚወጣው የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለት ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል።የአሜሪካ መከላከያ አርብ ንጋት ላይ በአየር የደበደባቸው ወታደራዊ ተቋማት በኢራን እና የኢራን ተባባሪ በሆኑ ቡድኖች ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ ተቋማት ናቸው ተብሏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:32 27 ጥቅምት 20236:32 27 ጥቅምት 2023ተመድ ወደ ጋዛ እርዳታ እንዲገባ ተማጽኖውን አቀረበ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበከበባ ላይ ባለችው የጋዛ ሰርጥ ተጨማሪ እርዳታ እንዲገባ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተማጽኖውን አቀረበ።”ጋዛ ታንቃ ነው ያለችው” እንዲሁም ህዝቦቿ “የተጣሉ፣ የተገለሉ እና የተተው እንደሆነ እየተሰማቸው ነው” ሲሉም የተባባሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች ኤጀንሲ ኮሚሽነር ጄነራል ፊሊፕ ላዛራኒ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።በርካታ ነዋሪዎች ምግብ እና ውሃ እየተመናመነባቸው፣ በሽታዎች እያንዣበበቡ እንደሆነ እንዲሁም ጋዛ በከፍተኛ የጤና አደጋ አፋፍ ላይ እንደምትገኝም ገልጸዋል።በጋዛ ውስጥ ሰዎች እየረገፉ እንዲሁም መሰረታዊ አገልግሎቶች እየፈራረሱ መሆናቸውንም ኮሚሽነሩ አጽንኦት በመስጠትም ነው የተናገሩት።የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ የአቅርቦት መስመሮችን ለመክፈት ከፍተኛ ድርድር ቢደረግም እስካሁን እንዲገቡ የተፈቀደላቸው “በጣት የሚቆጠሩ እርዳታ የጫኑ መኪናዎች መሆናቸውን”ም ገልጸዋል።”ብዙዎቻችን እነዚህ እርዳታ የጫኑ አሽከርካሪዎች ሲገቡ የተስፋ ጭላንጭል አይተን ነበር። ነገር ግን ከፍርፋሪ ያለፈ አልነበረም፤ በጋዛ ላይ ያለውንም ትኩረት የከፋፋለ ነው” ሲሉም ተደምጠዋል።አሁን ያለው አሰራር መቀየር እንዳለበት ገልጸው እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባም የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ስምምነት ሊደረስ ይገባል ብለዋል።”ይህንን መጠየቅ እንደ ትልቅ ጥያቄ መታየት የለበትም” ብለዋል ኮሚሽነሩ።”በርካቶች በችጋር ላይ ያሉበትን ሁኔታ በቀጥታ እያየን ባለንበት ወቅት ሰብዓዊ እርዳታ ላይ ጥያቄ መነሳቱ ህመም የሚፈጥር ነው” ሲሉም አክለዋል። ተመድ ምንም አይነት ሰብዓዊ እርዳታዎችን ላልተገባ አካልም እንደማያዞርም ተናግረዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:46 27 ጥቅምት 20234:46 27 ጥቅምት 2023አሜሪካ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል “የተኩሰ አቁም እንዲደረግ አልደግፍም” አለች
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል በጋዛ ሰርጥ እያካሄደች ባለችው ጥቃት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ተፈናቅሏል።Image caption: እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እያካሄደች ባለችው ጥቃት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ተፈናቅሏል።አሜሪካ ሐማስ መልሶ እንዲደራጅ ዕድል የሚሰጥ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ አልደግፍም አለች።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ሲናገሩ አገራቸው ሐማስ “እረፍት አድርጎ፣ እራሱን አደራጅቶ እስራኤል ላይ የሽብር ዘመቻዎችን እንዲቀጥል” የሚፈቅድ የተኩስ አቁም ስምምነትን አትደግፍም ብለዋል።ማቲው ሚለር መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ሐማስ እስራኤል ከፈጸመውን ጭካኔ የተሞላበት ድንገተኛ ጥቃት በተጨማሪ ቡድኑ “ሰላማዊ እስራኤላውያንን ዒላማ ያደረጉ ሮኬቶችን በየዕለቱ ያስወነጭፋል” ሲሉ ተናግረዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ሐማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ሳይደረስ አግቼ የያዝኳቸውን ታጋቾች አለቅም ብሏል።በሞስኮ ጉብኝት እያደረጉ ያሉ ከፍተኛ የሐማስ አመራሮች እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እያደረገች ያለው የአየር ደብደባ ሳይቆም ሐማስ የያዛቸውን ሰዎች እንደማይለቅ ለሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።ማቲው ሚለር የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ ሲባል ሁለቱ አካላት ተኩስ እንዲያቆሙ ግን አሜሪካ ፍላጎት እንዳላት አመልክተዋል።የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ አርብ ጥቅምት 16/2016 ዓ.ም. በጋዛ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ በሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ድምጽ ይሰጣል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:41 27 ጥቅምት 20234:41 27 ጥቅምት 2023ኤርትራ በዳህላክ የእስራኤል ወታደራዊ ጣቢያ ላይ ጥቃት ተፈጸመ መባሉን ሐሰት ነው አለችበመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ መገናኛ ብዙኃን በኤርትራ የሚገኝ የእስራኤል ወታደራዊ የቅኝት ጣቢያ ላይ ጥቃት ተፈጸመበት ሲሉ ያወጡት ዘገባ ሐሰት ነው ስትል አስተባበለች።ተጨማሪ ያንብቡ