
28 ጥቅምት 2023
የቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በጋዜጠኛነት ተቀጠሩ።
ጂቢ ኒውስ በተባለው የቴሌቭዥን ጣቢያ ነው የተቀጠሩት።
ጆንሰን በቴሌቪዥን ጣቢያው የፕሮግራም አቅራቢ፣ አዘጋጅና ተንታኝ ይሆናሉ።
በቀጣይ ዓመት የአሜሪካና የዩኬ ምርጫ በመዘገብ “ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ” ተብሏል።
“የእንግሊዝን ኃይል የሚያሳይ መሰናዶ” ያቀርባሉም ብሏል ጂኒ ኒውስ።
በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዩች ምልከታቸውን ለማጋራት ቃል ገብተዋል።
በዴይሊ ሜይል ላይም አምደኛ የሆኑት ቦሪስ ጆንሰን ሥራቸውን በአውሮፓውያኑ አዲስ ዓመት ይጀምራሉ።
ቦሪስ ጆንሰን በኤክስ ገጻቸው ላይ “ጂቢ ኒውስን እንደምቀላቀል ስነግራችሁ በደስታ ነው” ብለው ቪድዮ አጋርተዋል።
“በሩሲያ፣ ቻይና፣ ዩክሬንና ሌሎችም ጉዳዮች እውነተኛ ዕይታዬን አቀርባለሁ” ብለዋል።
“እንግሊዝ በዓለም ስላላት ዕምቅ አቅምና ፈተናዎቻችንም እናገራለሁ” ሲሉ አክለዋል።
- ቤተ-እስራኤላዊው አቨራ መንግሥቱ እና ለዓመታት በሐማስ እገታ ሥር ያሉ ሌሎች እስራኤላውያን28 ጥቅምት 2023
- “ስኬታማ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የምሆን ይመስለኛል…” አኖልድ ሽዋዝኒገር28 ጥቅምት 2023
- በአሜሪካ 18 ሰዎች በመግደል ሲፈለግ የነበረው ሞቶ መገኘቱ ተገለጸ28 ጥቅምት 2023
ቦሪስ ከሥልጣን እንዲወርዱ ከፍተኛ ጫና መፈጠሩን ተከትሎ ነው አምና የወረዱት። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ያሳዩት አመራር አሁንም ምርመራ እየተደረገበት ነው።
በዩኬ የቀድሞ መሪዎች ሥልጣን በለቀቁ በሁለት ዓመታት ስለሚይዙት ሥራ የሚያማክሩት አገራዊ ኮሚቴ አለ።
ይህ ኮሚቴ ቦሪስ ጆንሰብ ጂቢ ኒውስ መግባታቸው ከመንግሥት መርህ ጋር የሚጻረር ስላልሆነ ፈቅዷል።
ሥልጣን ላይ ሳሉ ያገኟቸውን መረጃዎች ያለአግባብ እንዳይጠቀሙ መርሆች ተቀምጠዋል። በተጨማሪም ጂቢ ኒውስን ወክለው መንግሥት ላይ ጫና እንዳያደርጉም ጥንቃቄ ይደረጋል።
ይህ የሚሆነው ሥልጣን ከለቀቁበት ጊዜ በኋላ ላሉት ሁለት ዓመታት ነው።
ቦሪስ ከሥልጣን በለቀቁ በአምስት ወራት ውስጥ በተለያዩ መሰናዶዎች ንግግር በማድረግና የግል የሕይወት ታሪካቸውን ለመጻፍ በመስማማት 4.8 ሚሊዮን ፓውንድ አግኝተዋል።
ጂቢ ኒውስ ከዚህ በፊት ታዋቂው ኮሜድያን ጆን ክሊስን ቀጥሯል።
ጣቢያው ቦሪስ ጆንሰንን ከቀጠረ በኋላ የተመልካቾቹ ቁጥር ከፍ እንደሚል ይጠበቃል።
