Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. እስራኤል ሌሊቱን ባካሄደችው ጥቃት በርካታ የሐማስ ተዋጊዎችን መግደሏን ገለጸች
  2. አሜሪካ ወደ እስራኤልም ሆነ ወደ ጋዛ ወታደር የመላክ ፍላጎት የላትም፡ ካማላ ሐሪስ
  3. እስራኤል ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ ጋዛ ማሰማራቷን አስታወቀች
  4. እስራኤል ዲፕሎማቶቿን ከቱርክ ጠራች
  5. ሐማስ በጋዛ ካሉ የእስራኤል ወታደሮች ጋር ግጭቶች መከሰታቸውን አስታወቀ
  6. የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን እስራኤልን በጦር ወንጀሎች ከሰሱ
  7. በጋዛ ሰርጥ የተገደሉ ሰዎች ከስምንት ሺህ አለፈ
  8. ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርገው የእግረኛ ጦር የዘመቻው ቀጣይ ደረጃ እንደሆነ ተናገሩ
  9. እስራኤል “እርምጃ እንድንወስድ ልታስገድደን ትችላለች ” የኢራን ፕሬዚዳንት
  10. የፍልስጥኤም ድጋፍ በዓለም ዙሪያ
  11. የእስራኤል እግረኛ ጦር የታጋቾችን የመለቀቅ ጥረት ያወሳስበዋል- ኳታር
  12. እስራኤል የጋዛ ሰርጥ ወረራን ጀምራለች?

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 4:354:35እስራኤል ሌሊቱን ባካሄደችው ጥቃት በርካታ የሐማስ ተዋጊዎችን መግደሏን ገለጸችበአየር ጥቃት የወደመ የጋዛ ሰርጥ አካባቢGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበአየር ጥቃት የወደመ የጋዛ ሰርጥ አካባቢImage caption: በአየር ጥቃት የወደመ የጋዛ ሰርጥ አካባቢካለፈው አርብ ጀምራ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ የምታካሂደውን ዘመቻ በማስፋት እግረኛ ሠራዊቷን ያሰማራችው እስራኤል በርካታ የሐማስ ተዋጊዎችን መግደሏን ገልጻለች።የእስራኤል መከላከያ ኃይል “ሠራዊቱ ጋዛ ውስጥ በሕንጻዎች እና በዋሻዎች ውስጥ በመደበቅ ወታደሮቻችንን ለማጥቃት ከሞከሩ አሸባሪዎች ጋር በተካሄደ ግጭት ብዙዎቹ ተገድለዋል” ብሏል።የጦር ሠራዊቱ በመግለጫው ላይ በአንድ ጥቃት መሬት ላይ ባሉ የእስራኤል ወታደሮች ጠቋሚነት “ከ20 በላይ የሐማስ አሸባሪ ተዋጊዎች በውስጡ ነበሩበት” ባለው ሕንጻ ላይ በጦር አውሮፕላን ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል።በተጨማሪም አል-አህዛር ከተባለው ዩኒቨርስቲ አቅራቢያ ፀረ ታንክ ሚሳኤል የሚወነጨፍበት ወታደራዊ ኬላ በጦር አውሮፕላን መመታቱን አመልክቷል።እሁድ ሌሊት ጋዛ ውስጥ ከባድ የአየር ድብደባ ሲያካሂድ ያደረገው የእስራኤል አየር ኃይል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 600 ኢላማዎችን ጋዛ ውስጥ መምታቱን ሰኞ ጠዋት ገልጿል።እስራኤል ወታደሮቿን ወደ ጋዛ አስገብታ ጥቃት እያካሄደች በላበት በአሁኑ ወቅት የአየር ድብደባውም ቀጥሏል። በዚህም ሠራዊቱ ሐኪሞች ለቀው እንዲወጡ ካዘዘበት የአል-ቁዱስ ሆስፒታል አቅራቢያ የአየር ድብደባ እየተካሄደ መሆኑን የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ ማኅበር አስታውቋል።Article share tools
  2. የታተመዉ 2:512:51ሒዝቦላህ የእስራኤልን ድሮን መትቶ መጣሉን አስታወቀበዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በአስራኤል ጥቃት የተገደለ የሒዝቦላህ አዛዥ ቀበር ላይ የተገኙ የቡድኑ ተዋጊዎችGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በአስራኤል ጥቃት የተገደለ የሒዝቦላህ አዛዥ ቀበር ላይ የተገኙ የቡድኑ ተዋጊዎችImage caption: በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በአስራኤል ጥቃት የተገደለ የሒዝቦላህ አዛዥ ቀበር ላይ የተገኙ የቡድኑ ተዋጊዎችበደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኘው ታጣቂ ቡድን ሒዝቦላህ አንድ የእስራኤል ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) መትቶ መጣሉን አስታወቀ።ይህም በአካባቢው ወታደራዊ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ ሒዝቦላህ እንዲህ አይነቱን እርምጃ መውሰዱን ሲገልጽ የመጀመሪያው ነው።ሒዝቦላህ እንዳለው ድሮኑ የተመታው ሊባኖስ ከእስራኤል ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አካባቢ ኻይም በተባለ ስፍራ እሁድ ዕለት ነው። የተመታው ድሮንም በእስራኤል ግዛት ውስጥ ሲወድቅ መታየቱን ገልጿል።በአሜሪካ እና በዩናይትድ ኪንግደም በሽብርተኛ ቡድንነት የተፈረጀው ሒዝቦላህ፣ ሐማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ፈጽሞ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ባለፉት ሦስት ሳምንታት 46 ተዋጊዎቹ እንደተገደሉበት እና 43 መቁሰላቸውን ገልጿል።ባለፉት ሳምንታት ሒዝቦላህ ከሊባኖስ በኩል ወደ እስራኤል የሮኬት ጥቃቶችን የፈጸመ ሲሆን፣ እስራኤልም በአየር እና በከባድ መሳሪያዎች አጸፋ ስትመለስ ቆይታለች።Article share tools
  3. የታተመዉ 1:351:35የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ያደርጋልየጋዛ ነዋሪዎችReutersCopyright: Reutersተኩስ ቆሞ በችግር ላይ ላሉት የጋዛ ነዋሪዎች እርዳታ እንደቀርብ የፀጥታው ምክር ቤት በተደጋጋሚ ቢሰበሰብም ውጤት አልተገኘምImage caption: ተኩስ ቆሞ በችግር ላይ ላሉት የጋዛ ነዋሪዎች እርዳታ እንደቀርብ የፀጥታው ምክር ቤት በተደጋጋሚ ቢሰበሰብም ውጤት አልተገኘምእስራኤል በጋዛ ላይ የምታካሂደው ጥቃት ተጠናክሮ በቀጠለበት በአሁኑ ጊዜ የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ጋዛ ውስጥ ባለው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ቀውስ ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬ ሊያደርግ ነው።እስራኤል ካለፈው ሳምንት ማብቂያ ጀምሮ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ የምታካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ አጠናክራ የቀጠለች ሲሆን፣ የግዛቲቱ ነዋሪዎች ያሉበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑ እየተነገረ ነው።በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ጥያቄ ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 19/2016 ዓ.ም. በሚካሄደው የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ለፍልስጤማውያን ስደተኞች እርዳታ የሚያቀርበው የመንግሥታቱ ድርጅት አካል ስላለሁ ሁኔታ ማብራሪያ ይሰጣል ተብሏል።ባለፈው ቅዳሜ የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ ተኩስ እንዲቆም በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የቀረበውን ጥያቄ ከመፍቀድ ይልቅ እስራኤል በጋዛ ውስጥ የምታካሂደው ዘመቻ መጠናከሩ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ባለፉት ሦስት ሳምንታት ውስጥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ተኩስ እንዲቆም ለማድረግ በሚያስችል የውሳኔ ሃሳብ ላይ አራት ጊዜ ቢሰበሰብም ውጤት ሳያስገኝ ቀርቷል።ለዚህም ምክንያቱ አሜሪካ ወይም ሩሲያ በቀረቡት ሃሳቦች ላይ ድምጽን በድምጽ የመሻር ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ውድቅ በማድረጋቸው ነው።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማሳያ የሚሆን ማስጃን በመጥቀስ እንዳለው፣ በሰሜን ጋዛ የሚካሄደው የአየር ጥቃት የመኖሪያ አካባቢዎችን በማውደም ላይ ያነጣጠረ ይመስላል ብሏል።Article share tools
  4. የታተመዉ 1:001:00እስራኤል ሐማስን ማስወገድ ከቻለች በጋዛ ላይ ምን የያዘችው ዕቅድ አለ?የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ “መካከለኛው ምሥራቅን እንቀይረዋለን” ሲሉ ዝተዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን “ከእንግዲህ ወደ ኋላ ማለት የለም” ብለዋል። ፍልስጤማውያን መሄጃ ባይኖራቸውም ከሰሜናዊ ጋዛ ዘወር በሉ፣ ከባድ ጥቃት ልናደርስ ነው እየተባሉ ይሸበራሉ፤ ይመከራሉ። ይህ ጦርነት መጨረሻው ምን ይሆን?ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  5. የታተመዉ 0:240:24አሜሪካ ወደ እስራኤልም ሆነ ወደ ጋዛ ወታደር የመላክ ፍላጎት የላትም፡ ካማላ ሐሪስምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሐሪስEPA/EFECopyright: EPA/EFEየአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሐሪስImage caption: የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሐሪስመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ እየተካሄደ ካለው ግጭት ጋር በተያያዘ አሜሪካ ወደ እስራኤል ወይም ወደ ጋዛ ወታደሮቿን ለመላክ ፍላጎት እንደሌላት ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሐሪስ ገለጹ።ምክትል ፕሬዝዳንቷ ‘60 ሚነትስ’ ከተባለው የቴሌቪዥን ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ “ወደ አስራኤልም ሆነ ጋዛ ሰርጥ ወታደሮቻችንን የማሰማራት ፍላጎት ወይም ዕቅድ ፈጽሞ የለንም” በማለት ፈርጠም ብለው ተናግረዋል።ነገር ግን አሜሪካ ለእስራኤል የምክር፣ የቁሳቁስ እና የዲፕሎማሲ ድጋፍ እየሰጠች መሆኑን ገልጸዋል።“ጥያቄ በማይቀርብበት ሁኔታ እስራኤል እራሷን የመከላከል መብት አላት። ይህ ተብሎ ግን ሐማስን እና ፍልስጤማውያንን አንድ አድርጎ የመመልከት ሁኔታ መኖር የለበትም” ብለዋል ሐሪስ።“የፍልስጤማውያንን ደኅንነት የሚያስጠብቁ፣ የእራሳቸውን ዕድል የመወሰን እና ክብራቸውን የሚያስጠብቁ እርምጃዎች እንዲወሰዱ እንፈልጋለን፤ በተጨማሪም የጦርነት መመሪያዎች መከበር እንዳለባቸው ግልጽ አድርገናል፤ እንዲሁም ሰብአዊ እርዳታ እንዲገባም መደረግ አለበት።”ምክትል ፕሬዝዳንት ሐሪስ አክለውም፣ አሜሪካ ግጭቱ እንዳይባባስ የማድረግ ፍላጎት እንዳላት በማመልከት ኢራን እጇን እንዳታስገባ አስጠንቅቀዋል።Article share tools
  6. የታተመዉ 9:10 29 ጥቅምት 20239:10 29 ጥቅምት 2023እስራኤል ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ ጋዛ ማሰማራቷን አስታወቀችየእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪReutersCopyright: Reutersየእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪImage caption: የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪከተቀሰቀሰ ሦስተኛ ሳምነቱን ያሳለፈው የእስራኤል-ጋዛ ጦርነት ወደሌላ ደረጃ ተሸጋግሯል። ለሦስት ሳምንታት ያህል እስራኤል በጋዛ ላይ ስታካሂደው የቆየው የአየር ድብደባ የቀጠለ ሲሆን፣ እግረኛ ወታደሮች እና ከባድ መሳሪያዎች ወደ ጋዛ ዘልቀው ገብተዋል። የዛሬ እሁድ ጥቅምት 18/2016 ዓ.ም. ዋና ዋና ክስተቶች. . .
    • የቅዳሜ ሌሊት የእስራኤል ጥቃት
    ከቅዳሜ ሌሊት ጀምሮ ተጨማሪ እስራኤል ወታደሮች ወደ ጋዛ ሰርጥ መግባታቸውን ቁጥሩን ሳይገልጹ የጦሩ ቃል አቀባይ ሬር አድሚራል ዳንኤል ሃጋሪ አስታውቀዋል።በተጨማሪም ቅዳሜ ሌሊቱን የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች ጋዛ ውስጥ የሚገኙ 450 የሐማስ ይዞታዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።
    • የጋዛ የእርዳታ ማዕከላት ሁኔታ
    በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የእርዳታ አቅርቦት የተቀመጠባቸውን መጋዘኖች ሰብረው በመግባት ዱቄት እና የንጽህና መገልገያዎችን መውሰዳቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት የፍልስጤም ስደተኞች ድርጅት አስታውቋል።ድርጅቱም ጨምሮ ጋዛ ሰርጥ ውስጥ መደበኛው የሕዝብ ሥርዓት መጣስ እየጀመረ መሆኑን አመልክቷል።ጋዛ ውስጥ ከአንድ ቀን በላይ ሙሉ ለሙሉ ተቋርጠው የነበሩት የግንኙነት መስመሮች ወደ አገልግሎት እየተመሱ ሲሆን፣ ስልክ እና ኢንተርኔት መሥራት እየጀመሩ ነው።የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ ማኅበር ሰሜናዊ የጋዛ ክፍል የውጊያ ቀጠና በመሆኑ ከአል-ቁዱስ ሆስፒታል ለቆ እንዲወጣ በእስራኤል ባለሥልጣናት እንደተነገረው ገልጿል።
    • እስራኤላውያን ታጋቾች
    ጋዛ ውስጥ እስራኤል የጀመረችው የእግረኛ ሠራዊት ዘመቻ ያሳሰባቸው የታገቱ ሰዎች ቤተሰቦች ስጋታቸውን መግለጻቸውን ተከትሎ የእስራኤል የመከላከያ ኃይሎች ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ፣ ታጋቾችን ወደ ቤተሰባቸው መመለስ የጦሩ ቀዳሚ ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል።በሐማስ ከእስራኤል ተወስደው ጋዛ ውስጥ የሚገኙ ታጋቾች ቤተሰቦች፣ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ጋር ዛሬ እሁድ ለመገናኘት ቀጠሮ ተይዞላቸዋል።Article share tools
  7. የታተመዉ 7:13 29 ጥቅምት 20237:13 29 ጥቅምት 2023ፍልስጥኤማውያን በፍርስራሽ ክምሮች ውስጥ ቤተሰቦቻቸውን እየፈለጉ ነውበኻን ዮኒስ የደረሰው የአየር ጥቃትReutersCopyright: Reutersፍልስጥኤማውያን በአየር ጥቃት ከፈራረሱ ክምሮች ስር ቤተሰቦቻቸውን እየፈለጉ ነው። የኻን ዮኒስ ከተማ ህንጻዎች በአየር ጥቃት ወድመዋል።ኻን ዮኒስ እስራኤል ከሰሜን ጋዛ እንዲወጡ የሰጠችውን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ በርካቶች የተሰዱዳባት ከተማ ናት። አንዳንድ ፎቶዎች በጣም አሰቃቂ ናቸው።በኻን ዮኒስ የሚገኘው የናስር ሆስፒታል የተገደሉ ሰዎችን አስክሬን መሬት ላይ ተደርድረው የሚያሳይ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ቢያንስ ሶስቱ ህጻናት ናቸው።በጋዛ ፍርስራሽ ስር በመቶዎች የሚቆጠሩ ህጻናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ተቀብረው እንደሚገኙ የዓለም ጤና ድርጅት በቅርቡ አስታውቋል።በትናንትናው ዕለትም የእስራኤል ጦር የሰሜን ጋዛ ነዋሪዎችን ወደ ደቡብ እንዲሸሹ ያስጠነቀቀ ሲሆን ሰብዓዊ ጥረቶችም ይጨምራሉ ብሏል።እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገቻት የጋዛ ሰርጥ የማያባራ የአየር ጥቃት እየፈጸመች ትገኛለች። በዚህም ከ8 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን ከጋዛ ጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያስረዳል።በኻን ዮኒስ የደረሰው የአየር ጥቃትReutersCopyright: Reutersበኻን ዮኒስ የደረሰው የአየር ጥቃትReutersCopyright: Reutersበኻን ዮኒስ የደረሰው የአየር ጥቃትReutersCopyright: ReutersArticle share tools
  8. የታተመዉ 6:09 29 ጥቅምት 20236:09 29 ጥቅምት 2023የጋዛ ነዋሪዎች የእርዳታ መጋዘኖችን ሰብረው በመግባት ዱቄት እና ሌሎች ፍጆታዎችን መውሰዳቸውን ተመድ አስታወቀፍልስጥኤማውያን እርዳታ ሲወስዱAFPCopyright: AFPበሙሉ ከበባ ላይ ባለችው የጋዛ ሰርጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መጋዘኖችን እና ማከፋፈያ ማዕከሎችን ሰብረው በመግባት ዱቄት እና ሌሎች መሰረታዊ ፍጆታዎችን መውሰዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት አስታወቀ።”ከሶስት ሳምንታት ጦርነት እና በሙሉ ከበባ ውስጥ ባለችው ጋዛ ህዝባዊ ስርዓቱ መፍረስ መጀመሩን የሚያሳይ አሳሳቢ ምልክት ነው” ሲል የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች የእርዳታ ኤጀንሲ በመግለጫው አስፍሯል።”ነዋሪዎች ፈርተዋል፣ ተበሳጭተዋል እንዲሁም ተስፋ ቆርጠዋል። ውጥረቱ እና ፍርሃቱ በስልክ እና ኢንተርኔት መቋረጡ ተባብሷል” ብሏል።በዛሬው ዕለት የወጣው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶቹ የትኞቹ መጋዘኖቹ እንደተሰበሩም ግልጽ አላደረገም።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ኃላፊ ማርቲን ግሪፊዝ ወደ ጋዛ የሚገባው እርዳታ ጠብታ እንደሆነ ጠቅሰዋል።እስራኤል ጋዛን በሙሉ ከበባ ውስጥ ያስገባቻት ሲሆን ነዳጅ፣ መብራት እና ውሃ የተቋረጠ ሲሆን የማያባራ የአየር ጥቃትም እያስተናገደች ትገኛለች።Article share tools
  9. የታተመዉ 5:50 29 ጥቅምት 20235:50 29 ጥቅምት 2023ሐማስ በጋዛ ካሉ የእስራኤል ወታደሮች ጋር ውጊያዎች ማካሄዱን አስታወቀየእስራኤል እግረኛ ጦርIsrael Defense ForcesCopyright: Israel Defense Forcesየሐማስ ወታደራዊ ክንፍ የሆነው ኢዘዲን አል ቃሳም ብርጌድ ከእስራኤል ወታደሮች ጋር በስተሰሜን ምዕራብ ጋዛ የትጥቅ ግጭቶች ማካሄዱን በቴሌግራም ገጹ አስፍሯል።የእስራኤል መከላከያ ወታደሮቹ ወደ ጋዛ ሰርጥ እንደገቡ ያስታወቀ ሲሆን የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የጦር አዛዦችም በመላው ጋዛ መሰማራታቸውንም አክለዋል።በትናንትናው ዕለትም በሰሜን ምዕራብ ጋዛ ውጊያዎች እንደነበረ ይሄው ቴሌግራም ገጽ አስፍሯል። የእስራኤል መከላከያ ያወጣው ቪዲዮ ላይ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ሰሜን ምዕራብ ጋዛ አቅራቢያ የሚታዩ ሲሆን ስፍራው በእስራኤል ውስጥ መሆኑን ቢቢሲ አረጋግጧል።ይኸው የአል ቃሳም ቴሌግራም ከጋዛ ከተማ በስተምስራቅ ከሰፈሩ የእስራኤል ወታደሮች ጋር የትጥቅ ግጭት መኖሩን ዘግቧል።Article share tools
  10. የታተመዉ 5:17 29 ጥቅምት 20235:17 29 ጥቅምት 2023የእስራኤል እግረኛ ጦር የታጋቾችን የመለቀቅ ጥረት ያወሳስበዋል- ኳታርየእስራኤል ወታደሮችIsrael Defence ForceCopyright: Israel Defence Forceእስራኤል እግረኛ ጦሯን ወደ ጋዛ ማስገባቷን ተከትሎ በሐማስ የተወሰዱ ታጋቾችን ለማስለቀቅ የሚደረገውን ጥረት እንዳወሳሰበው የኳታር መንግሥት አስታወቀ።”ሁኔታዎች መባባሳቸው ጉዳዩን የበለጠ ፈታኝ ያደርገዋል” ሲሉም የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ማጅድ አል አንሳሪ ተናግረዋል።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው ሐማስን ድል መንሳት እና ታጋቾቹን ማስለቀቅ “ምንም ተቃርኖ” የሌለው ጉዳይ ነው ሲሉም ቀደም ሲል ተናግረው ነበር።እስራኤል 229 ሰዎች በሐማስ ታግተው መወሰዳቸውን ገልጻለች።Article share tools
  11. የታተመዉ 5:12 29 ጥቅምት 20235:12 29 ጥቅምት 2023እስራኤል የጋዛ ሰርጥ ወረራን ጀምራለች?እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እያደረገችውን የማያባራ የአየር ጥቃት አጠናክራ ቀጥላለች። ከአየር ጥቃት በተጨማሪም እግረኛ ጦሯን ወደ ጋዛ ሰርጥ አስገብታለች። የእስራኤል ወታደሮች በሰሜናዊቷ ጋዛ ቤት ሃኖን ተከማችተዋል። ወደ ደቡባዊ ጋዛም በተወሰነ መልኩ እየገፉ ይመስላል። እስራኤል እና ጋዛን በምታዋስነው የድንበር ከተማ ስዴሮትም የነበረው የቢቢሲ ጋዜጠኛ በባለፉት ቀናት የከባድ መሳሪያ ተኩሱ ተጠናክሮ መቀጠሉን ታዝቧል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  12. የታተመዉ 3:53 29 ጥቅምት 20233:53 29 ጥቅምት 2023የፍልስጥኤም ድጋፍ በዓለም ዙሪያበተለያዩ አገራት የፍልስጥኤም የአጋርነት ሰልፎች ተደርገዋል።በለንደን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፋቸውን በአደባባይ በመውጣት ያሳዪ ሲሆን የፍልስጥኤም ሰንደቅ አላማ እያውለበለቡ ፍልስጥኤም ነጻ እንድትሆንም ጠይቀዋል።በቱርኳ ኢስታንቡል በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን የተገኙ ሲሆን እስራኤልንም ወራሪ ሲሉ የጠሯት ሲሆን በጋዛ ላይ እየደረሰ ላለው ግድያም ምዕራባውያንን ተጠያቂ አድርገዋል።የፕሬዚዳንቱንም ንግግር ተከትሎ እስራኤል ዲፕሎማቶቿን ከቱርክ በመጥራት ምላሽ ሰጥታለች።በለንደን ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍEPACopyright: EPAበለንደን ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍImage caption: በለንደን ለፍልስጥኤም የተደረገው የድጋፍ ሰልፍበቱርክ በተደረገው የፍልስጥኤም የድጋፍ ሰልፍ ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን እስራኤልን በጦር ወንጀል ከሰዋልReutersCopyright: Reutersበቱርክ በተደረገው የፍልስጥኤም የድጋፍ ሰልፍ ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን እስራኤልን በጦር ወንጀል ከሰዋልImage caption: በቱርክ በተደረገው የፍልስጥኤም የድጋፍ ሰልፍ ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን እስራኤልን በጦር ወንጀል ከሰዋልበዌስት ባንክ በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ቤተሰቦቻቸው በእስራኤል የታሰሩባቸው ፍልስጥኤማውያን እንዲፈቱ እንዲሁም ለጋዛ ያላቸውንም አጋርነት ገልጸዋልGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበዌስት ባንክ በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ቤተሰቦቻቸው በእስራኤል የታሰሩባቸው ፍልስጥኤማውያን እንዲፈቱ እንዲሁም ለጋዛ ያላቸውንም አጋርነት ገልጸዋልImage caption: በዌስት ባንክ በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ቤተሰቦቻቸው በእስራኤል የታሰሩባቸው ፍልስጥኤማውያን እንዲፈቱ እንዲሁም ለጋዛ ያላቸውንም አጋርነት ገልጸዋልየፍልስጥኤም ደጋፊዎች በማሌዥያዋ ኳዋላላምፑር በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የፍልስጥኤምን ሰንደቅ አላማ አውለብልበዋልReutersCopyright: Reutersየፍልስጥኤም ደጋፊዎች በማሌዥያዋ ኳዋላላምፑር በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የፍልስጥኤምን ሰንደቅ አላማ አውለብልበዋልImage caption: የፍልስጥኤም ደጋፊዎች በማሌዥያዋ ኳዋላላምፑር በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የፍልስጥኤምን ሰንደቅ አላማ አውለብልበዋልበአውስትራሊያዋ ፐርዝ በርካታ የፍልስጥኤም አጋሮች ድጋፋቸውን በአደባባይ ገልጸዋልGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበአውስትራሊያዋ ፐርዝ በርካታ የፍልስጥኤም አጋሮች ድጋፋቸውን በአደባባይ ገልጸዋልImage caption: በአውስትራሊያዋ ፐርዝ በርካታ የፍልስጥኤም አጋሮች ድጋፋቸውን በአደባባይ ገልጸዋልArticle share tools
  13. የታተመዉ 3:18 29 ጥቅምት 20233:18 29 ጥቅምት 2023እስራኤል “እርምጃ እንድንወስድ ልታስገድደን ትችላለች ” የኢራን ፕሬዚዳንትየኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሒም ራይሲReutersCopyright: Reutersእስራኤል እያደረገችው ያለው ተግባር ቀይ መስር አልፏል፤ እርምጃ እንድንወስድ የሚያስገድደን” ሁኔታ ውስጥ እያስገባችን ነው ሲሉም የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሒም ራይሲ ተናግረዋል።ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያሉት እስራኤል እግረኛ ጦሯን ወደ ጋዛ ሰርጥ ባስገባችበት እና የጦር አዛዦችም በመላው ጋዛ ሰርጥ ተሰማርተዋል ባሉበት ወቅት ነው።”አሜሪካ ምንም እንዳናደርግ እየጠየቀችን ነው። ነገር ግን በተቃራኒው ለእስራኤል ከፍተኛ ድጋፍ እየሰጠች ነው። አሜሪካ ለአክሲስ ኦፍ ሬዚስታንስ መልዕክት የላከች ሲሆን ነገር ግን በጦር ሜዳውም ግልጽ ምላሽ አግኝታለች” ብለዋል።አክሲስ ኦፍ ሬዚስታንስ በመካከለኛው ምስራቅ ሐማስን ጨምሮ በኢራን የሚደገፉ ቡድኖችን የሚያመለክት ነው።አሜሪካ ሰፋ ያለ ቀጠናዊ ግጭት እንዳይከሰት በሚል ኢራን በእሰራኤል እና ሐማስ ጦርነት ተሳታፊ እንዳትሆንም የአሜሪካ ባለስልጣናት እያስጠነቀቁ ይገኛሉ።በሊባኖስ የሚገኘው እና በኢራን የሚደገፈው የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን ባለፉት ሳምንታት ከእስራኤል ጋር ተኩስ ተለዋውጧል።Article share tools
  14. የታተመዉ 2:49 29 ጥቅምት 20232:49 29 ጥቅምት 2023በእስራኤል- ጋዛ የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮችየፈራረሰችው ጋዛGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል ጋዛ ጦርነት ሶስት ሳምንት አለፈው። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርገው የእግረኛ ጦር የዘመቻው ቀጣይ ደረጃ መሆኑን ገልጸው ረዥም እና ፈታኝ እንደሚሆንም ተናግረዋል።በቅርቡ የተከሰቱ ጉዳዮችን እንዳስ፦
    • በጋዛ ሰርጥ ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና የኢንተርኔት ግንኙነት እየተመለሰ ነው። አርብ አመሻሽ ላይ የስልክ እና ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ የነበረ ሲሆን ጋዛም ከአለም ተቆራርጣም ነበር። በዚህም ወቅት በጦርነቱ የከፋውን የአየር ጥቃትም አስተናግዳለች።
    • ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የእስራኤል ጦር ወደ ጋዛ ሰርጥ መግባቱን ለማመላከት “የጥፋት ምሽግ” ገብቷል ያሉ ሲሆን የጦር አዛዦችም በመላው ጋዛ ሰርጥ መሰማራታቸውን ገልጸዋል። ታጋቾቹን ማስመለስ የጦሩ አላማ ቢሆንም ዋናው ተቀዳሚ ጉዳይ ሐማስን “ማጥፋት” ነው ብለዋል።
    • የእስራኤል መከላከያ ኃይል ግብጽ እና አሜሪካ ወደ ጋዛ የሚደረገውን ዕርዳታ እንደሚያስተባብሩ ቢጠቅስም ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል። የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ድርጅት ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲረግብ ጥሪ አቅርቧል። የሰው ህይወት እየረገፈ እንደሆነ እና ህዝቡም ለከፋ ስቃይ መጋለጡንም ገልጿል።
    • የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን እስራኤልን በጦር ወንጀሎች ከሰዋል። ኔንታንያሁ ዲፕሎማቶቻቸውን ከቱርክ በማስወጣት ምላሽ ሰጥተዋል።
    • ሐማስ በእስራኤል ላይ በፈጸመው ጥቃት 1 ሺህ 400 እስራኤላውያን ተገድለዋል፤ 229 ሰዎች ታግተዋል። እስራኤል የማያባራ ጥቃት በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመች ሲሆን ከ8 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከነዚህም አብዛኛዎቹ ህጻናት እና ሴቶች ናቸው። እስራኤል ጋዛ ሰርጥን በሙሉ ከበባ በማስገባት ነዳጅ፣ ውሃ እና የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲቋረጥ አድርጋለች።
    Article share tools
  15. የታተመዉ 1:48 29 ጥቅምት 20231:48 29 ጥቅምት 2023እስራኤል ዲፕሎማቶቿን ከቱርክ ጠራችእስራኤልና ቱርክ ከፍተኛ ወደሚባል የዲፕሎማሲ ፍጥጫ እየገቡ ነው። ትናንት እስራኤል አምባሳደሯን ጨምሮ ሁሉም ዲፕሎማቶቿን ከቱርክ ጠርታለች። ቴላቪቭ እርምጃውን የወሰደችው የቱርኩ ፕሬዝዳንት እስራኤልን ‘እንደ ጦር ወንጀለኛ እያደረጋት ነው’ ብለው መናገራቸውን ተከትሎ ነው። የቱርኩ ፕሬዝዳንት ይህን ያሉት በኢስታንቡል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ለፍልስጥኤም ያለውን አጋርነት ለመግለጽ አደባባይ በወጣበት ጊዜ ባደረጉት ንግግር ነው።