Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. በእስራኤል ላይ የምንፈጽመው ጥቃት ይቀጥላል፡ የየመን ሁቲ ታጣቂዎች
  2. እስራኤል በጋዛ ባካሄድኩት ዘመቻ “በርካታ አሸባሪዎችን ገደልኩ” አለች
  3. በጋዛ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ8 ሺህ በላይ ሆነ
  4. ኔታንያሁ የተኩስ አቁም ጥሪን ውድቅ በማድረግ “ለጦርነት ጊዜው ነው” አሉ
  5. በጦርነቱ ከተገደሉት 31 ጋዜጠኞች መካከል 26ቱ ፍልስጥኤማውያን ናቸው
  6. የእስራኤል መከላከያ የጋዛ ሰርጥ ላይ ከሁሉም አቅጣጫ ጥቃት እያደረስኩ ነው አለ
  7. አሜሪካ የጋዛ የተኩስ አቁም ጥሪን ውድቅ አደረገች
  8. የእስራኤል እግረኛ ጦር ጥቃት ወደ ጋዛ ማዕከላዊ ክፍል እየገፋ መሆኑ ተነገረ
  9. እስራኤል ሌሊቱን ባካሄደችው ጥቃት በርካታ የሐማስ ተዋጊዎችን መግደሏን ገለጸች
  10. አሜሪካ ወደ እስራኤልም ሆነ ወደ ጋዛ ወታደር የመላክ ፍላጎት የላትም፡ ካማላ ሐሪስ
  11. እስራኤል ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ ጋዛ ማሰማራቷን አስታወቀች
  12. እስራኤል ዲፕሎማቶቿን ከቱርክ ጠራች
  13. ሐማስ በጋዛ ካሉ የእስራኤል ወታደሮች ጋር ግጭቶች መከሰታቸውን አስታወቀ
  14. እስራኤል “እርምጃ እንድንወስድ ልታስገድደን ትችላለች ” የኢራን ፕሬዚዳንት
  15. የእስራኤል እግረኛ ጦር የታጋቾችን የመለቀቅ ጥረት ያወሳስበዋል- ኳታር
  16. እስራኤል የጋዛ ሰርጥ ወረራን ጀምራለች?

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 11:5611:56በጋዛ የስደተኞች መጠለያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከ50 ያላነሱ ሰዎች ተገደሉጃባሊያ መጠለያReutersCopyright: Reutersጃባሊያ መጠለያImage caption: ጃባሊያ መጠለያጃባሊያ ተብሎ በሚጠራው የስደተኞች መጠያ ጣቢያ ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት ከ50 ያላሱ ሰዎች መገደላቸው የጤና ተቋማት አስታወቁ።በሰሜን ጋዛ በሚገኘው መጠለያ ጣቢያ ላይ የደረሰውን ከፍተኛ ውድመት የሚያሳዩ ምስሎች እየወጡ ነው።የሮይተርስ ጋዜጠኛ ባጋረው ምስል ሰዎች ወደ ፍርስራሽነት በተቀየሩት ሕንጻዎች ስር በሕይወት የተረፉ ሰዎችን እና አስክሬኖችን ሲያወጡ አሳይቷል።ጃባሊያ መጠለያReutersCopyright: Reutersጃባሊያ መጠለያImage caption: ጃባሊያ መጠለያበሐማስ የሚተዳደረው ጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከመጠለያ ጣቢያው በቅርብ ርቀት የሚገኝ የኢንዶኔዢያ ሆስፒታል ዳይሬክተር በጥቃቱ ከ50 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን ገልጸዋል።ጃባሊያ መጠለያ ጣቢያ በጋዛ ከሚገኙት 8 መጠለያ ጣቢያዎች በርካታ ሰዎችን በመያዝ ቀዳሚው ሲሆን፣ የተባበሩት መንግሥታት ሐምሌ 2015 ዓ.ም. ላይ በመጠለያ ጣቢያው የተጠለሉ 116ሺህ ፍልስጤማውያን መዝግቦ ነበር።የእስራኤል መከላከያ ኃይል ጥቃቱን በተመለከተ እስካሁን ያለው ነገር የለም።Article share tools
  2. የታተመዉ 10:3610:36በእስራኤል ላይ የምንፈጽመው ጥቃት ይቀጥላል፡ የየመን ሁቲ ታጣቂዎችየሁቲ ጦር ቃል አቀባይTelegram/Yahya SareeCopyright: Telegram/Yahya Sareeየየመን ሁቲ አማጺያን “በርካታ ቁጥር ያለው” ተወንጫፊ ባሊስቲክ ሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ወደ እስራኤል ማስፈንጨፋቸውን አስታወቁ።የሁቲ አማጺያን ዛሬ ማክሰኞ ከደቡብ-ምሥራቅ እስራኤል በመቶ ኪሎ ሜትሮች ርቃ ከምትገኘው የመን ከዒላማቸው ጋር እየተላተሙ ጉዳት የሚያደርሱ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ማስወንጨፋቸውን አስታውቀው ነበር።ቀደም ሲል እስራኤል ኤላት የተሰኘችውን የጎብኚዎች መዳረሻ የሆነችውን ከተማዋን ዒላማ ያደረጉ ድሮኖችን ቀይ ባሕር ላይ መትታ መጣሏን አስታውቃለች።በኤላት የአየር ጥቃት ስጋት መኖሩን ተከትሎ የማስጠንቀቂያ ድምጾች በተከማዋ ተስተጋብተው ነበር።የሁቲ ጦር ቃል አቀባይ ያህያ ሳሬ በቴሌቪዥን በተሰራጨ መግለጫ፣ እራኤልን ዒላማ ያደረገው ይህ ጥቃት ሦስተኛው መሆኑን እና ተጨማሪ ጥቃቶች እንደሚሰነሩ ጨምረው ተናግረዋል።የሁቲ ኃይል “የእስራኤል ጥቃት እስኪቆም ድረስ ልዩ የሆኑ ዘመቻዎችን ማካሄዳቸውን ይቀጥላሉ” ብለዋል ቃል አቀባዩ።በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማጺያን የየመን መዲና ሰነዓን ጨምሮ በርካታ የአገሪቱ አካባቢዎችን የሚቆጣጠሩ ሲሆን፣ አስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከሳዑዲ መራሹ ኃይል ጋር ጦርነት ውስጥ መቆየታቸው ይታወሳል።ባለፈው ሳምንት በሁለት የግብፅ ከተሞች ውስጥ ላጋጠሙ ፍንዳታዎች እስራኤል ይህን ቡድን ተጠያቂ አድርጋ ነበር።ለእስራኤል ተብለው የሁቲ አማጺያን የተተኮሱት ኢራን ሰራሽ ድሮኖች በሁለቱ የግብፅ ከተሞች ላይ ፍንዳታ መፍጠራቸውን እስራኤል ገልጻለች።Article share tools
  3. የታተመዉ 9:339:33እስራኤል በጋዛ ባካሄድኩት ዘመቻ “በርካታ አሸባሪዎችን ገደልኩ” አለችየእስራኤል እግረኛ ጦር በጋዛIDFCopyright: IDFየእስራኤል እግረኛ ጦር በጋዛImage caption: የእስራኤል እግረኛ ጦር በጋዛየእስራኤል ጦር በጋዛ ባካሄደው ዘመቻ በርካታ የሐማስ ተዋጊዎችን መግደሉን አስታወቀ።ጦሩ ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ባወጣው ሪፖርት “በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ የአሸባሪው ሐማስ ወታደራዊ የቅኝት ጣቢያን” መምታቱን አስታውቋል።የእስራኤል እግረኛ ጦር ባካሄደው ዘመቻ “በርካታ አሸባሪዎችን” መግደሉን፣ ፀረ ታንክ ሚሳኤል የሚያስወነጭፉ ቡድኖችን መደምሰሱን፣ ሚሳኤል ማስወንጨፊያ እና የወታደራዊ ቅኝት ጣቢያዎችን ማውደሙን እንዲሁም በርካታ መሳሪዎች እና ቦምቦችን መማረኩን አስታውቋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ሐማስ በበኩሉ በጋዛ በተደረገ ውጊያ አንድ የእስራኤል ወታደር መግደሉን እና ታንክ ማጋየቱን አስታውቋል።ሐማስ በሰሜን ምዕራብ ጋዛ ዘልቀው ለመግባት የሞከሩ ሁለት የእስራኤል ጦር ተሸከርካሪዎችን ማውደሙን ጨምሮ ገልጿል።Article share tools
  4. የታተመዉ 7:587:58የእስራኤል አየር መንገድ ከኢራን አየር ክልል ለመራቅ የበረራ አቅጣጫውን ቀየረፎቶ ፋይል የእስራኤል አየር መንገድ አውሮፕላንAFPCopyright: AFPየእስራኤል አየር መንገድ አውሮፕላን [ፎቶ ፋይል]Image caption: የእስራኤል አየር መንገድ አውሮፕላን [ፎቶ ፋይል]የእስራኤል አየር መንገድ የሆነው ኤል ኤአይ ሐማስን በመደገፍ ከምትታወቀው ኢራን የአየር ክልል ለመራቅ ሲል የበረራ አቅጣጫውን ቀየረ።አሶሺዬትድ ፕሬስ እንደዘገበው የአየር መንገዱ የመንገደኞች አውሮፕላን ወደ ታይላንድ በነበረው በረራ የተለመወደውን የበረራ አቅጣጫውን በመቀየሩ የበረራ ጊዜው በሰዓታት ተራዝሟል።አየር መንገዱ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ከኢራን በቅርብ ርቀት በምትገኘው በኦማን የአየር ክልል አድርጎ ነበር ወደ መዳረሻው ይበር የነበረው።ይሁን እንጂ አውሮፕላኑ በቅድሚያ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ከበረራ በኋላ፣ በቀይ ባሕር በኩል አድርጎ ወደ አፍሪካ ቀንድ ከዚያም ወደ ሕንድ ውቅያኖስ ፊቱን አዙሮ ወደ መዳረሻው አቅንቷል።Article share tools
  5. የታተመዉ 7:517:51በጋዛ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ8 ሺህ በላይ ሆነበእስራኤል አየር ኃይል ጥቃት የደረሰበት ካህን ዩኒስ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ገጽታReutersCopyright: Reutersበእስራኤል አየር ኃይል ጥቃት የደረሰበት ኻህን ዩኒስ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ገጽታImage caption: በእስራኤል አየር ኃይል ጥቃት የደረሰበት ኻህን ዩኒስ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ገጽታበእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት ምክንያት በጋዛ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ8ሺህ በላይ ማለፉ ተገለጸ።በሐማስ የሚተዳደረው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር ከመስከረም 26 ጀምሮ በጋዛ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 8525 ደርሷል ብሏል።እንደ ጤና ሚኒስቴሩ ከሆነ ከሟቾቹ መካከል 3542 ያህሉ ሕጻናት ሲሆኑ፣ 2187 ሴቶች ናቸው ብሏል። 130 የሚሆኑት ደግሞ የጤና ባለሙያዎች መሆናቸው ተገልጿል።ሐማስ ከጥቂት ቀናት በፊት በእስራኤል የአየር፣ የምድር እና የባሕር ላይ ጥቃቶች የተገደሉ ናቸው ያላቸው የ7ሺህ ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጎ ነበር።Article share tools
  6. የታተመዉ 7:487:48ሐማስ “ከፍልስጤማውያን ጀርባር ተደብቋል” ስትል እስራኤል ከሰሰችየእስራኤል ቡልዶዘር በጋዛIDFCopyright: IDFየእስራኤል ቡልዶዘር በጋዛImage caption: የእስራኤል ቡልዶዘር በጋዛየእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ “ሐማስ ከፍልስጤማውያን ጀርባ ተደብቋል” ሲሉ ለቢቢሲ ተናገሩ።ቃል አቀባዩ ፒተር ለርነር እንዳሉት ሐማስ ሰላማዊ ሰዎች በሚኖሩበት አካባቢ መሽጓል።“የሚፈነዱ ሰው አልባ አውሮፕላኖቹን ጨምር በሰዎች መኖሪያ ቤት ጣሪያ ላይ አከማችቷል። . . . ሮኬቶችን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋማት እያስወነጨፈ ነው” በማለት ቃል አቀባዩ ቡድኑን ወቅሰዋል።በሁለቱም በኩል በግጭቱ ምክንያት ጉዳዩ የማይመለከታቸው ሰላማዊ ሰዎች እየተጎዱ መሆኑን የገለጹት ፒተር ለርነር፤ ሐማስ መወገድ ካለበት ምክንያቶች መካከል አንዱ በሰላማዊ ሰዎች ስር መሸሸጉ አንዱ ነው ብለዋል።ቃል አቀባዩ ጨምረውም ሐማስ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከሰነዘረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከ7ሺህ በላይ ሮኬቶችን ከጋዛ ማስወንጨፉን ተናግረዋል።ይህ ቃል አቀባይ ከዚህ ቀደም ሐማስ በጋዛ የሚገኙ ሆስፒታሎችን እንደ ጦር ማዘዣ ጣቢያ እና የመሰባሰቢያ ቀጠና አድርጎ እየተጠቀመ ነው ብለው ነበር።Article share tools
  7. የታተመዉ 5:345:34የተባበሩት መንግሥታት 64 ሰራተኞቹ በጋዛ እንደተገደሉበት አስታወቀየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች ኤጀንሲ 64 ሰራተኞቹ በጋዛ እንደተገደሉበት አስታወቀ።በትናንትናው ዕለትም አንድ የተመድ ሰራተኛ ከስምንት ልጆቹ እና ከባለቤቱ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እያሉ መገደላቸውን ቃለ አቀባይዋ ጁሊየት ቶውማ ለቢቢሲ ተናግረዋል።በጋዛ ሰርጥ የተባበሩት መንግሥታት የሚያስተዳድራቸው 450 መጠለያዎች ያሉ ሲሆን እነዚህም መጨናነቃቸውን ቃለ አቀባይዋ ተናግረዋል።እነዚህ መጠለያዎች 670 ሺህ ፍልስጥኤማውያንን እያስተናገደ ነው ተብሏል።“እንደ እከክ እና ተቅማጥ የመሳሰሉ በሽታዎች እየተዛመቱ መሆናቸውንም ሪፖርቶች ደርሰውናል” ብለዋል።“የሰብዓዊ ተኩስ አቁም መደረግ አለበት። ጥበቃ ሊደረግላቸው የሚገቡ አብያተ ክርስቲያናት፣ መስጂዶች እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋማት ተመትተዋል። የትኛውም የጋዛ ስፍራ ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም። ጋዛ በፍጥነት ወደ ገሐነም ተቀይራለች” በማለትም ተናግረዋል።እስራኤል ሐማስ ላደረሰው መብረቃዊ ጥቃት ምላሽ ነው በሚል በጋዛ ላይ የማያባራ የአየር እና የመሬት ጥቃት እየፈጸመች ትገኛለች።ሐማስ ባደረሰው ጥቃት 1 ሺህ 400 ሰዎች ተገድለዋል እንዲሁም ከ200 በላይ ሰዎች ታግተዋል። በእስራኤል ጥቃት ከ8 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን የተገደሉ ሲሆን፣ ከእነዚህም አብዛኛዎቹ ሕጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።እስራኤል ጋዛን በሙሉ ከበባ ውስጥ ያስገባቻት ሲሆን በዚህም የነዳጅ፣ የመብራት እና የውሃ አቅርቦት እንዲቋረጥ አድርጋለች።Article share tools
  8. የታተመዉ 4:544:54አሜሪካ የጋዛ የተኩስ አቁም ጥሪን ውድቅ አደረገችበእስራኤል እና የፍልስጥኤም ቡድን ሐማስ መካከል የተኩስ አቁም እንዲኖር የሚጠይቁ ዓለም አቀፍ ጥሪዎችን አሜሪካ ውድቅ አደረገች። “ይህ ትክክለኛው ምላሸ አይደለም” በማለት የአሜሪካ የብሔራዊ ደኅንነት ቃለ አቀባይ ጆን ኪርቢ በትናንትናው ዕለት ምላሽ ሰጥተዋል። በምትኩ በጋዛ ውስጥ ዕርዳታ እንዲገባ ለመርዳት ጦርነቱ “በጊዜያዊነት ገታ እንዲደረግ” ጠቁመዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  9. የታተመዉ 4:534:53የእስራኤል መከላከያ የጋዛ ሰርጥ ላይ ከሁሉም አቅጣጫ ጥቃት እያደረስኩ ነው አለየጋዛ ጥቃትReutersCopyright: Reutersእስራኤል ለሶስት ሳምንታት ከቀጠለችው የማያባራ የአየር ጥቃት በተጨማሪ እግረኛ ጦሯ ከፍተኛ ጥቃት እያደረሰ መሆኑን አስታውቃለች።በትናንትናው ዕለትም 300 የሚጠጉ ኢላማዎችን በአየር ጥቃት እና በእግረኛ ጦሯ መምታቱን የእስራኤል መከላከያ ኃይል ገልጿል።የእስራኤል ጦር ሁሉንም የጋዛ ሰርጥ አካባቢዎችን እየመታ መሆኑንም የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ቃለ አቀባይ ሌተናል ኮሎኔል ጆናታን ተናግረዋል።”ዋናው ትኩረታችን ሰሜናዊው ጋዛ ሐማስ ማዕከል ያደረገው ስፍራ ነው። ነገር ግን ሌሎች የጋዛ አካባቢዎችን መምታታችንን እንቀጥላለን።አዛዦቻቸውንን እያደንን ነው። መሰረተ ልማቶቻቸውን እያጠቃን ነው፤ አስፈላጊ ዒላማ ሲገኝ እንመታዋለን” ሲሉም ነው የተናገሩት።እስራኤል የንጹሐን ዜጎችን ግድያ ለማስቀረት የተቻላትን ሁሉ እያደረገች እንደሆነ የገለጹት ቃለ አቀባዩ ሐማስ የጋዛ ዋና ሆስፒታል አል ሺፋን ሽፋ “የአሸባሪዎች መደበቂያ” አድርጎታል ሲሉም ከሰዋል።እስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ የሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያንን ከዋዲ ጋዛ ወንዝ በስተደቡበ በኩል እንዲሸሹ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።ሆኖም እስራኤል በሰሜን ጋዛ ብቻ ሳይሆን ደቡብ ጋዛም ላይ የማያባራ የአየር ጥቃት መፈጸሟን በመቀጠሏ የተባበሩት መንግሥታት በጋዛ “ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ የለም” ብሏል።ሰኞ ዕለት የእስራኤል መከላከያ ኃይል ሰሜን ጋዛን የወረሩ ሲሆን በስፍራውም ከ600 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ይኖራሉ ተብሏል።የእስራኤል መከላከያ ታንኮች ወደ ሰሜን ጋዛም ሲገባ የደቡብ መተላለፊያውን መንገድ ለአጭር ጊዜ ቆርጠውት እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል።Article share tools
  10. የታተመዉ 4:514:51ሌሊቱን ጋዛ ውስጥ ከሐማስ ኃይሎች ጋር ‘ከፍተኛ’ ውጊያ ሲካሄድ እንደነበር እስራኤል ገለጸችታንክIDFCopyright: IDFከቀናት በፊት ወደ ጋዛ የገባው የእስራኤል እግረኛ ጦር ጋዛ ውስጥ በሐማስ ይዞታዎች ላይ የሚያካሂደውን ጥቃት ሌሊቱን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ ‘ትላልቅ’ ውጊያዎች መካሄዳቸው አመልክቷል።እስራኤል እንዳለችው ጋዛ ውስጥ ከሐማስ ተዋጊዎች ጋር “የጎላ የተኩስ ልውውጥ” መካሄዱን እና ወታደሮቿ በሰሜን ጋዛ ውስጥ የሚያካሂዱትን ዘመቻ “በዝግታ እና ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ” እያሰፉ ናቸው።ፒተር ለርነር የተባሉ የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጋዛ ውስጥ “ከፍተኛ መጠን ያለው የተኩስ ልውውጥ” በእስራኤል እና በሐማስ ኃይሎች መካከል ሌሊቱን ተካሂዷል።ሌላኛው የሠራዊቱ ቃል አቀባይ ሌተናል ኮሎኔል ጆናታን ኮንሪከስ የእስራኤል ኃይሎች በአየር እና በምድር ዘመቻውን እያካሄዱ ያሉት በከፍተኛ የተኩስ ኃይል እና በመረጃ ተደግፈው መሆኑን ገልጸዋል።ቃል አቀባዩ አክለውም ጦሩ ጥቃቱን “የሐማስ ዋነኛ ማዕከል ነው” ባሉት ሰሜናዊ የጋዛ ሰርጥ ላይ በማተኮር “በሁሉም የጋዛ ሰርጥ ክፍሎች ላይ እየፈጸመ ነው” ብለዋል።ሌሊቱን የእስራኤል ወታደሮች ከሐማስ ኃይሎች ጋር ጋዛ ውስጥ መዋጋታቸውን እና በሐማስ የፀረ ታንክ ሚሳኤል እና የመትረየስ ጥቃት ተሰንዝሮበት እንደነበር ሠራዊቱ ገልጿል።በተመሳሳይ የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ አል-ቃሳም ብርጌድ በቴሌግራም ላይ ተመሳሳይ መረጃ አጋርቷል። በዚህም የቡድኑ ተዋጊዎች ሰሜናዊ ጋዛ ውስጥ ሦስት የእስራኤል የጦር ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጿል።መረጃው አክሎም ተሽከርካሪዎቹ ወደ ጋዛ ዘልቀው ለመግባት አል-ታዋም በተባለው አካባቢ ሲንቀሳቀሱ ፀረ ታንክ ሚሳኤል ተተኩሶባቸዋል ብሏል።ቀደም ብሎ ባጋራው መረጃ በደቡባዊ ጋዛ ኬሬም መተላለፊያ አቅራቢያ በእስራኤል እግረኛ ጦር ላይ የሞርታር ጥቃት እንደፈጸመ ሐማስ ገልጾ ነበር።Article share tools
  11. የታተመዉ 1:571:57ፑቲን በአገራቸው ለተፈጠረው ጸረ-አይሁድ እንቅስቃሴ ምዕራባዊያንን ተጠያቂ አደረጉእሁድ ዕለት ከእስራኤል ቴልአቪቭ የተነሳው አውሮፕላን በሩሲያ አየር ማረፊያ በሚደርስበት ወቅት ጸረ- ሴማዊ ተቃውሞዎች መነሳታቸውን ተከትሎ ሩሲያ በዩክሬን እና በምዕራባውያን የተቀነባበረ ነው ስትል ወቀሰች። አሜሪካ በምላሹ “የማይረባ” በማለት አጣጥላዋለች። የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቴሌቭዥን በተካሄደ ስብሰባ ላይ እንደገለጹት ክስተቱ “ሁከትን” ለማስፋፋት የተደረገ ሙከራ ነው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  12. የታተመዉ 1:111:11የፍልስጥኤም ደጋፊዎች የካናዳ መንግሥታዊ ቢሮዎችን ያዙየፍልስጥኤም ደጋፊዎችReutersCopyright: Reutersበመላው ካናዳ ያሉ ሰብዓዊ ተሟጋቾች በጋዛ የተኩስ አቁም ጥሪ እንዲደረግ ለመጠየቅ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት የሆኑ ቢሮዎችን ይዘዋል።የፓርላማ አባላቱ የተኩስ አቁም ጥሪ እንዲያቀርቡ ጫና ለማድረግም ነው ተሟጋቾቹ በነዚህ የመንግሥት ባለስልጣናት ቢሮዎች የተቀመጡት።ተሟጋቾቹ ሰኞ እለት ከያዟቸው ቢሮዎች መካከል የመከላከያ ሚኒስትሩ ቢል ብሌየር እና የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክሪስቲያ ፍሪላንድ ይገኙበታል።ተቃውሞው የተካሄደው በመላ ሃገሪቱ ባሉ 12 ከተሞች በሚገኙ 17 የመንግሥት መስሪያ ቤቶች መሆኑንም የሞንትሪያል ጋዜጣ ዘግቧል።”የካናዳ መንግሥት በጋዛ ላይ የተኩስ አቁም ጥሪ እንዲያደርግ እንዲሁም በጋዛ ሰርጥ ላይ ለ16 ዓመታት የቀጠለው እገዳ እና ከበባ እንዲቆም እንዲሁም ካናዳ ለእስራኤል የምታሳየውን አጋርነት እንድታቆም ለመጠየቅ ነው” ሲሉም አንድ ተቃዋሚ ለሮይተርስ ተናግረዋል።ተቃዋሚዎቹ በጋዛ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ጭፍጨፋ እንዲቆም እና ነጻ ፍልስጥኤምን የሚጠይቁ መፈክሮችን ይዘዋል።Article share tools
  13. የታተመዉ 1:011:01የዩኬ ባለሥልጣን ‘በጋዛ ተኩስ አቁም ይደረግ’ በማለታቸው ከሥራ ተባረሩበዩናይትድ ኪንግደም አንድ የሚኒስትር ረዳት እና የተወካዮች ምክር ቤት አባል ከሥራ ተባረሩ። ፖል ብሪስቶ ሥራቸውን ያጡት በጋዛ ተኩስ አቁም ይደረግ ብለው በይፋ መናገራቸውን ተከትሎ ነው። ፖል ብሪስቶ ባለፈው ሳምንት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪሺ ሱናክ በጻፉት ደብዳቤ ነበር በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረግ የጠየቁት። “ዘላቂ ተኩስ አቁም ቢደረግ በጋዛ የሰብአዊ ረድኤት ለማድረግ ያግዛል፤ የሚሞቱ ንጹሐንም ቁጥር ይገታል’ ብለው ነበር በደብዳቤያቸው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  14. የታተመዉ 0:390:39በጦርነቱ ከተገደሉት 31 ጋዜጠኞች መካከል 26ቱ ፍልስጥኤማውያን ናቸውየጋዛ ጥቃትReutersCopyright: Reutersበእስራኤል- ጋዛ የተፈጠረውን ቀውስ በመዘገብ ላይ የነበሩ 31 ጋዜጠኞች የተገደሉ ሲሆን ከነዚህም ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው የፍልስጥኤማውያን መሆኑን የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪው ሲፒጄ መረጃ ያሳያል።26 ፍልስጥኤማውያን፣ 4 እስራኤላውያን እና 1 የሊባኖስ ዜጋ የዘገባ ስራቸውን በማከናወን ላይ እያሉ መገደላቸውን ነው ተቋሙ ያስታወቀው።ተጨማሪ ስምንት ጋዜጠኞች የቆሰሉ ሲሆን ዘጠኝ ደግሞ እንደጠፉ ወይም ታስረው ሊሆን እንደሚችል ነው ሲፒጄ በመግለጫው አስፍሯል።በተለይም በጋዛ የሚዘግቡ ጋዜጠኞች በከፍተኛ ፈተናው ውስጥ እንደሆኑም አስፍሯል።”እስራኤል በመሬት ላይ እየፈጸመች ያለችውን ከባድ ጥቃት፣ አውዳሚ የአየር ድብደባዎች፣ እንዲሁም የመገናኛ ዘዴዎች እና የኤሌክትሪክ አቅርቦት በሚቆራረጥበት ሁኔታ እየዘገቡ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ አደጋም ተደቅኖባቸዋል” ብሏል።ከተገደሉት መካከል ታዋቂው ፍልስጥኤማዊ ፊልም ሰሪ ሮሽዲ ሳራጅ፣ በቤይሩት የሮይተርስ የቪዲዮ ባለሙያ ኢሳም አብዳላህ ይገኙበታል ።እስራኤል በሊባኖስ ላይ በፈጸመችው የከባድ መሳሪያ ጥቃትም በቤይሩት የነበረው የሮይተርስ ጋዜጠኛ እንደተገደለ ሲፒጄ አትቷል።የእስራኤል መከላከያ ጉዳዩን እየመረመርኩ ነው ብሏል። የእስራኤል መከላከያ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ለሚሰሩ ጋዜጠኞቻቸው ደህንነት ዋስትና እንደማይሰጥም ለሮይተርስ እና አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግሯል።መከላከያው ይህንን የተናገረው ሰራተኞቻቸው በእስራኤል ጥቃት ጉዳት እንዳማይደርስባቸው የዜና ወኪሎቹ መጠየቃቸውን ተከትሎም እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።Article share tools
  15. የታተመዉ 0:370:37እግረኛ ጦሯን ወደ ጋዛ ያሰማራችው እስራኤል የምትፈልገውን ግብ ማሳካት ትችላለች?የእስራኤል አመራሮች ሐማስ ከምድረ ገጽ እንደሚጠፋ እና ጋዛ የቀድሞው ይዞታዋ እንደማይቀጥል ዝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ “ሁሉም የሐማስ አባል ሟች ነው” ብለዋል። ሐማስ በፈጸመው ድንገተኛ ጥቃት 1,400 እስራኤላውያን በሐማስ ተገድለዋል። በአጸፋው እስራኤል በጋዛ ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ከ8 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል። ከቀናት በፊት ደግሞ እስራኤልም እግረኛ ወታደሮቿን በማሰማራት ጋዛ ላይ ወረራ ፈጽማለች።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  16. የታተመዉ 12:59 30 ጥቅምት 202312:59 30 ጥቅምት 2023እስራኤል በሐማስ ታግታ የነበረች ወታደሯን ነጻ ማውጣቷን አስታወቀችከእገታ ነጻ የወጣችው ወታደር (ከመሃል) ከቤተሰቦቿ ጋርISACopyright: ISAከእገታ ነጻ የወጣችው ወታደር (ከመሃል) ከቤተሰቦቿ ጋርImage caption: ከእገታ ነጻ የወጣችው ወታደር (ከመሃል) ከቤተሰቦቿ ጋርእስራኤል በሐማስ ታግታ ተወስዳ የነበረች ሴት ወታደሯን ማስለቀቅ መቻሏን ዛሬ ሰኞ ምሽት በተሰጠ መግለጫ አስታወቀች።የእስራኤል መከላከያ ኃይል እና የእስራኤል ደኅንነት ባለሥልጣን በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ ነው በሐማስ ቁጥጥር ስር የነበረችውን ወታደር ነጻ መውጣት መቻሉን ያስታወቁት።ኦሪ ሜጊዲሽ የተባለችው ወታደር መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ሐማስ ከፈጸመው ጥቃት ጋር በተያያዘ ከታገቱ ሰዎች መካከል አንዷ ስትሆን፣ የእስራኤል እግረኛ ጦር ትናንት ሌሊት ባካሄደው ዘመቻ ነው ነጻ ሊያወጣት የቻለው ተብሏል።የወታደሯን ነጻ መውጣት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ በኤክስ (ትዊተር) ላይ “እንኳን ወደ ቤትሽ ተመለስሽ” በማለት የቪዲዮ መልዕክት አስተላልፈዋል።የወታደሯ መለቀቅም ታጋቾችን ለማስለቀቅ የአገራቸውን ቁርጠኝነት በመግለጽ፣ ሐማስ ላይም እስራኤል የቡድኑን አባላቱ ዒላማ ማድጓን እንደምትቀጥል ዝተዋል።“የወታደሯ ጤና በደህና ሁኔታ ላይ ነው ያለው፣ ከቤተሰቦቿ ጋርም ተገናኝታለች። ጦሩ እና የደኅንነት ተቋሙ ሁሉንም ታጋቾች ለማስለቀቅ የሚያስፍልጉ ሁሉንም ነገሮች ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ” ብሏል በጋራ የወጣው መግለጫ።Article share tools
  17. የታተመዉ 12:11 30 ጥቅምት 202312:11 30 ጥቅምት 2023ኔታንያሁ ሐማስ የለቀቀውን የታጋቾች ቪድዮ “ጭካኔ የተሞላ የሥነ ልቦና ፕሮፓጋንዳ” አሉትቤንያሚን ኔታኒያሁReutersCopyright: Reutersየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ በሐማስ የተለቀቀው ታጋቾችን የሚያሳይ ቪድዮ “ጭካኔ የተሞላበት ሥነ ልቦና ላይ ያነጣጠረ ፕሮፓጋንዳ ነው” በማለት አወገዙ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁጣቸውን የገለጹት ጋዛ ውስጥ ተይዘው የሚገኙ ሦስት ታጋቾችን የሚያሳይ ቪድዮ በሐማስ መለቀቁን ተከትሎ ነው።ኔታኒያሁ የታጋቾቹን ስም በመጥራትም መልዕክት አስተላልፈዋል። “የጦር ወንጀል በሚፈጽመው ሐማስ የታገታችሁት ኤሌና ትሩፓኖቭ፣ ዳንኤል አሎኒ እና ሪሞን ኪርሽት አቅፌያችኋለሁ” ብለዋል።ከአንድ ደቂቃ ትንሽ በሚረዝመው እና ቢቢሲ በማያጋራው ቪድዮ ላይ፣ ሦስቱ ታጋቾች ግድግዳ ጥግ ተቀምጠው ወደ ካሜራ እያዩ ሲናገሩ ይታያል።ሐማስ ከሦስት ሳምንት በፊት በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት በፈጸመበት ጊዜ ከ230 በላይ ሰዎችን አግቶ ወደ ጋዛ መውሰዱን የእስራኤል መንግሥት አስታውቋል።ባለፈው ሳምንት የተወሰኑ ሰዎችን በቀይ መስቀል በኩል የለቀቀ ሲሆን፣ የቀሩትን ለመልቀቅ እስራኤል በጋዛ ላይ የምታካሂደውን ዘመቻ እንድታቆም ጠይቋል።Article share tools
  18. የታተመዉ 9:17 30 ጥቅምት 20239:17 30 ጥቅምት 2023የእስራኤል እግረኛ ጦር ጥቃት ወደ ጋዛ ማዕከላዊ ክፍል እየገፋ መሆኑ ተነገረየእስራኤል ታንክGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል ሠራዊት የሚፈጽመው ጥቃት ወደ ጋዛ ማዕከላዊ ክፍል ዘልቆ እየገባ ሲሆን፣ ታንኮቹም በጋዛ ቁልፍ መንገዶች ላይ መታየታቸው ተዘገበ።በጋዛ ሰርጥ ከሰሜን ወደ ደቡብ በሚወስደው ዋና አውራ ጎዳና ላይ የእስራኤል ታንኮች ታይተዋል።ይህም ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ወደ ጋዛ ዘልቀው የገቡት የእስራኤል እግረኛ ወታደሮች በአሁኑ ጊዜ የበለጠ ወደ ጋዛ ከተማ መጠጋት መጀመራቸውን ያሳያል።ወደ ጋዛ እየተጓዘ የነበረ መኪና ላይ የእስራኤል ታንክ እንደተኮሰበት የተዘገበ ሲሆን፣ በዋዲ ጋዛ ደቡብ በኩል የእስራኤል ኃይል ለመጀመሪያ ጊዜ ጎዳና ላይ መታየቱ ነው።ይህ ዋዲ ጋዛ የሚባለው ቦታ የእስራኤል መከላከያ ኃይል የጋዛ ነዋሪዎች ወደ ደቡብ እንዲወጡ ካስጠነቀቀ በኋላ የሚጓጓዙበት መስመር ነው።የእስራኤል ኃይሎች ጋዛ ከተማ ላይ አነጣጥረው ዘመቻቸውን አጠናክረው እየቀጠሉ ነው።አሁንም ግን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በፍርሃት እና ቤታቸውን ለቀው ላለመውጣት በመወሰን በሰሜናዊ የጋዛ ክፍል ለመቆየት መርጠዋል።የእስራኤል መከላከያ ግን መስመሩን ሙሉ በሙሉ ሊቆርጠው ይችላል።ከሰሜን ወደ ደቡብ የሚወስዱት ሁለት መንገዶች ብቻ ናቸው። አንደኛው ዛሬ ታንክ የታየበት ሳላህ-አል-ዲን የሚባለው ዋነኛ መንገድ ነው።ሁለተኛው አነስተኛ መንገድ በባሕር ዳርቻ አቅራቢያ ያለ ሲሆን የእስራኤል የጦር መርከብ ዒላማ ያደረገው ነው።ዋዲ ጋዛ ከጋዛ ያነሰ ሰው ነው የሚኖርበት። እስራኤል የጋዛ ሰርጥን ለሁለት ለመክፈል የምትጠቀመው ይህንን ቦታ ሊሆን ይችላል ተብሏል።Article share tools
  19. የታተመዉ 6:40 30 ጥቅምት 20236:40 30 ጥቅምት 2023በመቶዎች የሚቆጠሩ ህሙማን በሆስፒታል ውስጥ ናቸው፤ መውጣትም አይችሉም- ተመድየፍልስጤም ቀይ ጨረቃ በአል ቁድስ ሆስፒታል የተገኘ በሚል ይህንን ፎቶ አጋርቷልReutersCopyright: Reutersየፍልስጤም ቀይ ጨረቃ በአል ቁድስ ሆስፒታል የተገኘ በሚል ይህንን ፎቶ አጋርቷልImage caption: የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ በአል ቁድስ ሆስፒታል የተገኘ በሚል ይህንን ፎቶ አጋርቷልበመቶዎች የሚቆጠሩ ታካሚዎች በሰሜን ጋዛ በሚገኙ ሆስፒታሎች ውስጥ በመሆናቸው ወደ ደቡብ ጋዛ መሸሽ አልቻሉም ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ ኃላፊ ተናግሩ።የድርጅቱ ባልደረባ የሆኑት ቶም ዋይት በሰሜን ጋዛ ከሚገኙት እንደ አል ቁድስ ካሉ ሆስፒታሎች፤ ህሙማንን ማንቀሳቀስ አይቻልም ሲሉ ዶክተሮች እና ሌሎች በጎ አድራጎት ድርጅቶች የተናገሩትን ስጋት አስተጋብተዋል።የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ እንደገለፀው እስራኤል ሆስፒታሉን ለቀው እንዲወጡ አዛለች። የሆስፒታሉ አካባቢ የአየር ደብደባ ዒላማ መሆኑም ተጠቅሷል።”በሰሜን ጋዛ ያሉ ብዙ ሰዎች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትምህርት ቤቶች እና በሆስፒታሎች መጠለል ይፈልጋሉ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ህመምተኞች እና መንቀሳቀስ የማይችሉ ህሙማን በአንዱ ሆስፒታል ይገኛሉ” ሲሉ ዋይት ተናግረዋል።በሰሜን ጋዛ የሚኖሩ በርካታ ሰዎችም “አቅም ስለሌላቸው መንቀሳቀስ አይችሉም” ብለዋል።ሰዎቹ “በጣም ተርበዋል፣ በጣም ተጠምተዋል እንዲሁም በጣም ፈርተዋል” ብዙዎች በዳቦ እና “እኛ ስንችል በምንሰጠቻው የታሸጉ ምግቦች እየኖሩ ነው” ብለዋል።Article share tools
  20. የታተመዉ 6:38 30 ጥቅምት 20236:38 30 ጥቅምት 2023የእስራኤል ጦር ከሰሜን ወደ ደቡብ ጋዛ የሚወስደውን ቁልፍ መንገድ መዝጋቱን የዐይን እማኞች ተናገሩእስራኤል ጦር ወደ ጋዛ በመግባት በታንክ እና በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ከሰሜን ወደ ደቡብ የጋዛ ሰርጥ የሚወስደውን ቁልፍ መንገድ መዝጋታቸውን ፍልስጤማዊያን የዐይን እማኞች ተናገሩ።ታንኮቹ በካርኒ-ኔትዛሪም አቅራቢያ በሚገኘው ሳላ-አል-ዲን መንገድ ላይ መሆናቸው ተነግሯል። ይህም በግዛቲቱ ትልቁ ከተማ ላይ የሚደረገው ዘመቻ አካል ሊሆን ይችላል የሚል ግምትን ፈጥሯል።በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ አንድ ቪዲዮ እየተሰራጨ ይገኛል። በቪዲዮው አንድ መኪና ወደ ታንክ ተጠግቶ ለመታጠፍ ሲሞክር ተኩስ ተከፍቶበት ተሽከርካሪው ሲወድም ያሳያል።አንድ ግለሰብ “እሱም፣ መላው ቤተሰቡም አልቀዋል” እያለ በፍጥነት ሌሎች መኪኖች ዞረው እንዲመለሱ ሲነገር ይደመጣል።የእስራኤል ጦር ባለፉት 24 ሰዓታት በጋዛ የእግረኛ ጦር ዘመቻውን ማስፋፋቱን አስታውቋል። ጦሩ “በደርዘን የሚቆጠሩ አሸባሪዎችን በተሳካ ሁኔታ ማጥፋት ችያለሁ” ብሏል።ጦሩ በጋዛ የትኛው ክፍል እንደሚገኝ ከማሳወቅ ተቆጥቧል።በጉዳዩ ዙሪያ ጥያቄ የቀረበላቸው የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ “ለፀጥታ ኃይሎቻችን ቅድሚያ እንሰጣል” ብለዋል።”በጋዛ ሰርጥ የትጥቅ እና የእግረኛ ክፍላችንን በማሳተፍ ዘመቻችንን አስፋፍተናል” ብለዋል።ሃጋሪ ስለ ዘመቻው አጠቃላይ ሁኔታ ሲናገሩም፤ የምድር እና የአየር ጥቃት ለመሰንዘር ወደ ጋዛ ተጨማሪ “እግረኛ ወታደሮችን፣ ታንኮችን እና የመድፍ ኃይልን” እንደሚልኩ ተናግረዋል።