
ከ 4 ሰአት በፊት
አሜሪካዊያን ጥንዶች የማደጎ ልጃቸውን በማሰቃየታቸውና ኢሰብአዊ ድርጊት በመፈጸማቸው በኡጋንዳ ፍርድ ቤት የ28,000 ዶላር ቅጣት ተጣለባቸው።
የአስር ዓመት የማደጎ ልጃቸው ላይ “ኢሰብአዊ የጭካኔ ድርጊት” መፈጸማቸውን በፍርድ ቤት አምነዋል።
ኒኮላስ ስፔንሰርና ሜኬንዚ ስፔንሰር የተባሉት ጥንዶች ከዚህም የባሱ ክሶች ቀርበበውባቸው የነበረ ሲሆን ይህንን ቅጣት ለመቀበል በመስማማታቸው ሌሎቹ ክሶች ውድቅ ተደርገዋል።
ጥንዶቹ የማደጎ ልጃቸውን በእንጨት ላይ እንዲተኛ አድርገው ቀዝቃዛ ምግብ ይሰጡት ነበር።
ሞግዚታቸው ልዩ የጤና ክትትልና እንክብካቤ የሚያሻው ልጅ “ያልተገባ ኢሰብአዊ ድርጊት” እንደተፈጸመበት ለፖሊስ ጠቁማለች።
በደቡብ ካሮላይና የተወለደው የማደጎ ልጅ ከጥንዶቹ ጋር ሁለት ዓመት የኖረ ሲሆን፣ ጥንዶቹ አምና ነው በቁጥጥር ሥር የዋሉት።
ጥንዶቹ ካመኗቸው ሌሎች ክሶች መካከል ሰውን ማዋረድ፣ በኡጋንዳ በሕገ ወጥ መንገድ መሥራት እና በኡጋንዳ ያለ ፈቃድ መቆየት ይገኙበታል።
በእነዚህ ክሶች ሁለት ወር በእስር እንዲቆዩ ተወስኗል። ይህንንም በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ በእስር በመቆየት ሁለት ወሩን አሳልፈዋል።
የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ አሊስ ኮሚሀጊ ለተጎዳው ልጅ ካሳ 28,000 ዶላር እንዲከፍሉ ወስነዋል።
“ልጁ እርዳታ እና እንክብካቤ ነበር የሚሻው። አባቱን አጥቷል። እናቱ ጥላው ሄዳለች። ተከሳሾቹ ግን ልጁን መያዝ አልቻሉም” ብለዋል ዳኛዋ።
- “ይሄ የትንሿ ልጄ ፒጃማ ነው” 11 የቤተሰቡን አባላት በአንድ ጥቃት ያጣው የጋዛው አባትከ 5 ሰአት በፊት
- 120 ሺህ እስራኤላውያን የጦር መሣሪያ ፍቃድ እንዲሰጣቸው የጠየቁት ለምንድነው?ከ 5 ሰአት በፊት
- ዝናቸው ከኬንያ እስከ ኒው ዮርክ የተሻገረው የ84 ዓመቱ የ1ኛ ክፍል ተማሪ1 ህዳር 2023
የጥንዶቹ ጠበቃ ዴቪድ ምፓንጋ እንዳለው፣ ልጁ የአእምሮ ጤና እክል የገጠመው ሲሆን ጥንዶቹ ሊንከባከቡት ያልቻሉት ከዚህ ቀደም ልምድ ስለሌላቸው ነው።
ጥንዶቹ በኡጋንዳ ሦስት የማደጎ ልጆች አሏቸው። እአአ በ2017 ለበጎ ፈቃድ ሥራ ኡጋንዳ መኖር ጀምረዋል።
የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የሕፃናት መብት ተሟጋቾችን አስቆጥቷል። ውሳኔውን ፍትሕ ላይ መቀለድ ነው ሲሉ ተችተዋል።
የመብት ተሟጋች ፕሮስቪያ ናጁኡምባ ጥንዶቹ ልጁን “ማሰቃየታቸውን” በማመናቸው ለጥፋታቸው ሳይቀጡ “እንዲልፉ” ተደርጓል በማለት አስተያየታቸውን ለኤኤፍፒ ሰጥተዋል።
ችልድረን ፊኒክስ የተባለ ተቋም የመሠረቱት ዳረን ናማቶቭ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ልጆች ለማደጎ ሲሰጡ ተገቢው የጥንዶች የጀርባ ታሪክ ጥናት መደረግ አለበት።
በኡጋንዳ ዓለም አቀፍ የልጆች ማደጎ አወዛጋቢ ነው።
ልጆችን በሕገ ወጥ መንገድ ለማዘዋወር መንገድ ይከፍታል የተባለ የኡጋንዳ የሕግ ክፍል ላይ ዘንድሮ ማሻሻያ ተደርጓል።