Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. ሄዝቦላህ የእስራኤልን ድሮን አውድሟል መባሉን የአገሪቱ መከላከያ አስተባበለ
  2. ፕሬዚዳንት ባይደን የጋዛ ጦርነት ‘በጊዜያዊነት እንዲቆም’ ጥሪ አቀረቡ
  3. ፖፕ ፍራንሲስ የሁለት አገራት ምስረታ ለግጭቱ ዋነኛ መፍትሔ እንደሆነ ተናገሩ
  4. የኢራኑ አያቶላ አረብ አገራት ምግብ እና ነዳጅ ለእስራኤል እንዳይልኩ አሳሰቡ
  5. እስራኤል በጃባሊያ መጠለያ ጣቢያ ባደረስኩት ጥቃት የሐማስ መሪን ገደልኩ አለች
  6. እስራኤል ሚሳኤል ተሸካሚ መርከቦቿን ወደ ቀይ ባሕር አስጠጋች
  7. በጋዛ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዳግም ተቋረጠ
  8. እስራኤል እስካሁን ድረስ 11ሺህ ዒላማዎችን መምታቷን አስታወቀች
  9. በእስራኤል ላይ የምንፈጽመው ጥቃት ይቀጥላል፡ የየመን ሁቲ ታጣቂዎች
  10. እስራኤል በጋዛ ባካሄድኩት ዘመቻ “በርካታ አሸባሪዎችን ገደልኩ” አለች
  11. በጋዛ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ8 ሺህ በላይ ሆነ
  12. ኔታንያሁ የተኩስ አቁም ጥሪን ውድቅ በማድረግ “ለጦርነት ጊዜው ነው” አሉ
  13. በጦርነቱ ከተገደሉት 31 ጋዜጠኞች መካከል 26ቱ ፍልስጥኤማውያን ናቸው
  14. የእስራኤል መከላከያ የጋዛ ሰርጥ ላይ ከሁሉም አቅጣጫ ጥቃት እያደረስኩ ነው አለ
  15. አሜሪካ የጋዛ የተኩስ አቁም ጥሪን ውድቅ አደረገች

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 4:474:47በጃባሊያ የስደተኞች ጣቢያ የተገደሉ ፍልስጥኤማውያን ቁጥር መጨመሩ ተገለጸጃባሊያ የስደተኞች ጣቢያGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየስደተኞች መጠለያ በሆነው ጃባሊያ ሰሜናዊ ክፍል እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ።በጋዛ የሚገኘውና በሐማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር የሟቾች ቁጥር መጨመሩን ገልጿል።በጃባሊያ ላይ እስራኤል ላለፉት ሁለት ቀናት ተከታታይ የአየር ጥቃት ፈጽማለች።እስራኤል በስደተኞች ማቆያው ከፈጸመችው ጥቀት በኋላ 1,000ሰዎች መገደላቸው፣ መጎዳታቸው ወይም የት እንዳሉ እንዳልታወቀ ተገልጿል።ምን ያህሉ ሰዎች እንደሞቱ፣ እንደተጎዱና እንደጠፉ ባይገለጽም ከዚህ ቀደም የሟቾች ቁጥር 195 እንደደረሰ ተገልጿል።ያሳለፍነው ማክሰኞ እና ረቡዕ በደረሱት ጥቃቶች ብዙ ሕንጻዎች ተጎድተዋል።የእስራኤል መከላከያ በበኩሉ የሐማስ ኮማንደርን ዒላማ እንዳደረገና ብዙ ተዋጊዎችን እንደገደለ አስታውቋል።Article share tools
  2. የታተመዉ 3:423:42የእስራኤል ጦር ከሐማስ ጋር ከባድ ውጊያ ማድረጉን እና በርካታ ታጣቂዎች መገደላቸውን አስታወቀየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በጋዛ ሰርጥ ከሐማስ ጋር ከባድ ውጊያ ማድረጉን እና በርካታ ታጣቂዎች መገደላቸውን አስታወቀ።እግረኛ ጦሩም በአየር እና ባህር ጥቃቶች በመታገዝ በሰሜናዊ ጋዛ የሚገኘውን የሐማስ መከላከያ ግንባር መስበራቸውንም የእስራኤል ወታደራዊ ቃለ አቀባይ ገልጸዋል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ በምታደርገው የማያባራ የአየር ጥቃት እና ከባድ መሳሪያ ድብደባ ከ8 ሺህ 700 በላይ ሰዎች ሲገደሉ በርካቶቹ ህጻናት መሆናቸውን ከጋዛ ጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያስረዳል።በትናንትናው ምሽት አል ቁድስ ሆስፒታል አቅራቢያን ጨምሮ ከፍተኛ ፍንዳታዎች እና የከባድ መሳሪያ ድብደባ ተኩሶች እየተሰሙ እንደነበር አለም አቀፉ የቀይ ጨረቃ ድርጅት አስታውቋል።የእስራኤል ባለስልጣናት ህሙማንና የጤና ባለሙያዎች ሆስፒታሉን ለቀው እንዲወጡ ያስጠነቀቁ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ በህሙማን ላይ የሞት አደጋ መፈረጅ ነው ብሎታል።የመከላከያ ኃይሉ ሐማስ ጸረ ታንክ ሚሳኤሎችን መተኮሱን፣ ፈንጂዎችን እና የእጅ ቦምቦችን በእስራኤል ወታደሮችን ላይ መወርወራቸውን አስረድቷል። ጦሩም በምላሹ በከባድ መሳሪያ፣ በታንክ እንዲሁም በአየር እና ከባህር በተወነጨፈ የሚሳኤል ጥቃት አድርሻለሁ ብሏል። እግረኛ ጦሩም ከሐማስ ታጣቂዎች ጋር ፊት ለፊት መዋጋታቸውንም አክሎ ገልጿል።Article share tools
  3. የታተመዉ 2:572:57ፖፕ ፍራንሲስ የሁለት አገራት ምስረታ ለግጭቱ ዋነኛ መፍትሔ እንደሆነ ተናገሩየሮማው ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስReutersCopyright: Reutersየሮማው ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ በፍልስጥዔም እና በእስራኤል መካከል ያለውን ግጭት ለመፍታት የሁለት አገራት ምስረታ እና በግልጽ የተደነገጉ ግዛቶች መሰመር መፍትሔ መሆኑን ተናገሩ።ፖፕ ፍራንሲስ ለጣሊያኑ ሚዲያ አርኤአይ እንደተናገሩት “ሁለት በግልጽ የተደነገጉ ግዛቶች” ሊኖሩ ይገባል ብለዋል። እየሩሳሌምም ልዩ ስፍራ ይሰጣት ሲሉ ተናግረዋል።”በቅድስት አገር ያለው ጦርነት ያስፈራኛል። እነዚህ ማህበረሰቦች ይህንን ታሪክ እንዴት ይቋጩታል?” ሲሉም ጠይቀዋል።ፖፕ ፍራንሲስ የጦርነቱ መፋፋም “የብዙ ነገሮች መጨረሻ እና የበርካታ ሰዎች እልቂትንም የሚያስከትል ነው” ሲሉም ነው አጽንኦት የሰጡት ።በጋዛ ውስጥ 560 የሚሆኑ በአብዛኛው ክርስቲያኖች እንዲሁም አንዳንድ ሙስሊሞች ያስጠለሉ ገዳማትን እየመሩ ያሉ ቄሶች እና መነኮሳት ጋር በየቀኑ በስልክ እንደሚነጋገሩም ፖፑ አስረድተዋል።”ለአሁኑ አምላክ ይመስገን የእስራኤል ወታደሮች ለእነዚህ ደብሮች ክብር ሰጥተዋቸዋል” ብለዋል።Article share tools
  4. የታተመዉ 1:161:16ፕሬዚዳንት ባይደን የጋዛ ጦርነት ‘በጊዜያዊነት እንዲቆም’ ጥሪ አቀረቡየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንReutersCopyright: Reutersየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ታጋቾችን ለማስለቀቅ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የሚደረገው ጦርነት ‘በጊዜያዊነት እንዲቆም’ ጥሪ አቀረቡ።በሚኒሶታ በነበረ አንድ ዝግጅት ላይ አንዲት ሴት የተኩስ አቁም ስምምነት ጥሪ እንዲያደርጉ ፕሬዚዳንቱን መጠየቋን ተከትሎም ነው ባይደን በጊዜያዊነት መቆም እንዳለበት የተናገሩት።”በእኔ አስተሳሰብ በጊዜያዊነት መቆም አለበት። መገታት ማለት እስረኞቹን ለማስወጣት ጊዜ መስጠት ማለት” ነው ሲሉም ተናግረዋል።ፕሬዚዳንቱ ጥሪ ያደረጉት ሰብዓዊ እርዳታ እንዲገባ እና በሐማስ የተወሰዱት 240 ታጋቾች እንዲፈቱ ነው ሲል ዋይት ሐውስ ማብራሪያ ሰጥቷል።ግለሰቧ “የተኩስ አቁም አሁን” እያለች በተደጋጋሚ ስትናገርም በደህንነት ታጅባ ከዝግጅቱ እንድትወጣ ተደርጋለች።ፕሬዚዳንት ባይደንም ሁኔታው ለእስራኤላውያንም ሆነ ለሙስሊሙ ዓለም “በሚገርም ሁኔታ የተወሳሳበ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።”የሁለት አገራት መፍትሄን ደግፌያለሁ። ከጅምሩም ነው የደገፍኩት። እውነታው ሐማስ አሸባሪ ድርጅት ነው። ፍጹም አሸባሪ ድርጅት” ብለዋል።Article share tools
  5. የታተመዉ 0:460:46ሄዝቦላህ የእስራኤልን ድሮን አውድሟል መባሉን የአገሪቱ መከላከያ አስተባበለሄዝቦላህGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበደቡባዊ ሊባኖስ ላይ እየበረረ የነበረን የእስራኤል ድሮን (ሰው አልባ አውሮፕላን) ሄዝቦላህ ማውደሙን አስታውቋል።ሄዝቦላህ ድሮኑን መትቸ ጥያለሁ ማለቱን ተከትሎ የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃለ አቀባይ በማስተባበል ምላሽ ሰጥተዋል።ቃለ አቀባዩ ዳንኤል ሐጋሪ ሰው አልባ አውሮፕላኑ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰበት በኤክስ ገጻቸው አስታውቀዋል።በድሮኑ (ሰው አልባ አውሮፕላኑ) ላይ የተኮሰው ቡድን ላይ ጦራቸው ጥቃት መፈጸሙን ቃለ አቀባዩ አክለው ተናግረዋል።በእስራኤል እና ሊባኖስ ድንበር ያለው ውጥረት በተጋጋለበት በዚህ ወቅት ሄዝቦላህ የእስራኤልን ድሮን መትቶ መጣሉን ሲያስታውቅ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።Article share tools
  6. የታተመዉ 0:440:44120 ሺህ እስራኤላውያን የጦር መሣሪያ ፍቃድ እንዲሰጣቸው የጠየቁት ለምንድነው?ባለፉት ጥቂት ሳምንታት 120 ሺህ የሚሆኑ እስራኤላውያን የጦር መሣሪያ ፍቃድ እንዲሰጣቸው አመልክተዋል። በዚህም ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሕጋዊ መንገድን ተከትሎ ለመታጠቅ በስፋት ማመልከቻ እያስገቡ ነው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  7. የታተመዉ 0:440:44“ይሄ የትንሿ ልጄ ፒጃማ ነው” 11 የቤተሰቡን አባላት በአንድ ጥቃት ያጣው የጋዛው አባትአንድ ወር ሊሞላው በተቃረበው ጦርነት ወደ ዘጠኝ ሺህ የተጠጉ ፍልስጤማውያን ጋዛ ውስጥ በእስራኤል የአየር ጥቃት ተገድለዋል። የኻሊል ግን ከሁሉ የተለየ ነው በቤቱ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሁሉንም ልጆቹን ጨምሮ 11 የቤተሰቡን አባላት በአንድ ጀንበር አጥቷል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  8. የታተመዉ 11:12 1 ህዳር 202311:12 1 ህዳር 2023ቢቢሲ ለጋዛ ነዋሪዎች ዜና እና መረጃዎች የሚቀርቡበት የሬዲዮ ስርጭት ሊጀምር ነውየቢቢሲ ዓለም አቀፍ አገልግሎት ለጋዛ ነዋሪዎች የአስቸኳይ ጊዜ የሬዲዮ ሥርጫት በአጭር ሞገድ ከመጪው አርብ ጀምሮ ማቅረብ ሊጀመር ነው።ይህ በጋዛ ላይ የሚያተኩረው የሬዲዮ ፕሮግራም በየዕለቱ ለጋዛ ነዋሪዎች ዜና የሚያቀርብ ሲሆን፣ በተጨማሪም ለደኅንነት የሚጠቅሙ ምክሮችን፣ ነዋሪዎች የምግብ፣ የውሃ እና የመጠለያ አቅርቦቶችን ሊያገኙባቸው ስለሚችሉባቸው ቦታዎች መረጃን ይሰጣል።በመጪው አርብ ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም. ቢቢሲ ለጋዛ ነዋሪዎች የሚጀምረው የሬዲዮ ስርጭት ለመጀመሪያ በቀን አንድ ፕሮግራም የሚኖረው ሲሆን፣ በጋዛ የሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ 11 ሰዓት የሚቀርብ ነው።በሳምንቱ አርብ ደግሞ ሁለተኛው ዕለታዊ ፕሮግራም የሚጀመር ይሆናል። የሬዲዮ ሥርጭቱ ካይሮ እና ለንደን በሚገኙት የቢቢሲ ቢሮዎች የሚዘጋጁ ናቸው።ለጋዛ የሚጀመረው አዲስ የሬዲዮ ሥርጭት በመካከለኛ ሞገድ 639 ኪሎ ኽርዝ የሚተላለፍ ይሆናል።Article share tools
  9. የታተመዉ 9:39 1 ህዳር 20239:39 1 ህዳር 2023የተወሰኑ ቁስለኞች እና የውጭ ዜጎች ከጋዛ በመውጣት ወደ ግብፅ ገቡወደ ግብፅ ሲጠባበቁ ከነበሩ ቁስለኞች መካከልReutersCopyright: Reutersወደ ግብፅ ሲጠባበቁ ከነበሩ ቁስለኞች መካከልImage caption: ወደ ግብፅ ሲጠባበቁ ከነበሩ ቁስለኞች መካከልከጋዛ ወደ ግብፅ በሚያስገባው የራፋህ መተላለፊያ ቢያንስ 20 ጉዳት የደረሰባቸው ሰላማዊ ሰዎች ሕክምና ማግኘት እንዲችሉ ወደ ግብፅ መሻገራቸውን ቢቢሲ አረጋገጠ።ከተወሰነ የእርዳታ አቅርቦት በስተቀር ለሰዎችም ሆነ ለሌሎችን ነገሮች ዝግ ሆኖ በሰነበተው የራፋህ መተላለፊያ፣ ከተጎዱ ሰዎች በተጨማሪ 110 የሚሆኑ ጥምር ዜግነት ያላቸው ሰዎች ከጋዛ ወደ ግብፅ ገብተዋል።በዚህም ጦርነቱ ተጀምሮ የጋዛ መግቢያ መውጫ ከተዘጋ ከሦስት ሳምንት በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ ሰላማዊ ሰዎች ግዛቲቱን ለቀው እንዲወጡ ሲፈቀድ ይህ የመጀመሪያው ነው።ዛሬ ረቡዕ ረፋድ ላይ የራፋህ የድንበር መተላለፊያ ሲከፈት የእርዳታ አቅርቦት የጫኑ 20 ተሽከርካሪዎች ወደ ጋዛ እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል።በሌላ ዜና የእስራኤል አየር ኃይል ጃባሊያ በተባለው የስደተኞች ካምፕ ላይ ማክሰኞ በፈጸመው ጥቃት በሐማስ ቁጥጥር ስር ካሉ ታጋቾች ሰባቱ መገደላቸውን በሐማስ የሚመራው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።አንድ ወር ሊሞላው በተቃረበው ጦርነት ውስጥ እስራኤል እያካሄደች ባለው ድብደባ አስከ ዛሬ ረቡዕ ከሰዓት ድረስ የተገደሉት ሰዎች 8,796 መድረሱን የጤና ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል።እስራኤል ውስጥ ደግሞ ማክሰኞ ዕለት ጋዛ ውስጥ በሚካሄደው ዘመቻ ላይ ተሰማርተው ከተገደሉ 11 ወታደሮች መካከል የተወሰኑት የቀብር ሥነ ሥርዓት ረቡዕ ተከናውኗል።Article share tools
  10. የታተመዉ 7:54 1 ህዳር 20237:54 1 ህዳር 2023ጋዛ ውስጥ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 8,796 መድረሱ ተነገረበሐማስ የሚመራው የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ከመስከረም መጨረሻ ጀምሮ አስካሁን ድረስ ባለው ጊዜ 8,796 ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀ።ይህ አሃዝ ማክሰኞ ዕለት 8,525 የነበረ ሲሆን፣ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በ271 ጨምሮ ነው 8,796 የደረሰው።አስካሁን ጋዛ ውስጥ ከተገደሉት ሰዎች መካከልም 3,648 የሚሆኑት ሕጻናት መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴሩ አስታውቋል።እስራኤል በሐማስ ድንገተኛ ጥቃት ተፈጽሞባት ከ1,400 በላይ ሰዎች ከተገደሉባት እና ከ220 የሚበልጡ ታግተው ወደ ጋዛ ከተወሰዱ በኋላ ነው ጥቃት ማካሄድ የጀመረችው።ሳይቋረጥ ለሳምንታት በጋዛ ላይ የአየር ድብደባ ስትፈጽም የነበረችው እስራአል፣ ባለፉት ቀናት እግረኛ ሠራዊቷን ወደ ጋዛ አሰማርታለች።Article share tools
  11. የታተመዉ 7:10 1 ህዳር 20237:10 1 ህዳር 2023በምስል፡ ከጋዛ ወደ ግብፅ በመሻገር ሕክምና ለማግኘት የሚጠብቁ ሰዎችከጋዛ ወደ ግብፅ በሚያስወጣው ራፋህ መተላለፊያ በኩል ለመሻገር በአሁኑ ወቅት የሚጠባበቁ ሕክምና የሚፈልጉ ሰዎች ሁኔታን የሚያሳዩ ምስሎችተጎጂዎች ጋዛን ለመልቀቅ ሲጠባበቁReutersCopyright: Reutersተጎጂዎች ጋዛን ለመልቀቅ ሲጠባበቁReutersCopyright: Reutersተጎጂዎች ጋዛን ለመልቀቅ ሲጠባበቁReutersCopyright: ReutersArticle share tools
  12. የታተመዉ 6:28 1 ህዳር 20236:28 1 ህዳር 2023ጋዛ ውስጥ 11 የእስራኤል ወታደሮች መገደላቸውን ኔታንያሁ ተናገሩየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁPrime Minister Benjamin Netanyahu / @netanyahu on XCopyright: Prime Minister Benjamin Netanyahu / @netanyahu on Xየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁImage caption: የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁየእስራኤል ጦር ሠራዊት ጋዛ ውስጥ የእግረኛ ሠራዊት ዘመቻ ማካሄድ ከጀመረ በኋላ 11 ወታደሮች እንደተገደሉበት ተገለጸ።ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ማክሰኞ ዕለት ጋዛ በውስጥ በተደረገ ውጊያ 11 ወታደሮቻቸው መሞታቸው ከተረጋገጠ በኋላ በሰጡት አስተያየት ወታደሮቹ “በፍትሃዊ ጦርነት” ውስጥ መሞታቸውን ገልጸዋል።ኔታኒያሁ “አስቸጋሪ ጦርነት ውስጥ ነን። ረዥም ጦርነት ይሆናል። ጠቃሚ ስኬቶች አስመዝግበናል። ነገር ግን አሳዛኝ ኪሳራዎችም ገጥመውናል” በማለት በወታደሮቹ ላይ ስለደረሰው ጉዳት ተናግረዋል።“እናውቃለን፣ ሁሉም ወታደሮቻችን በጣም ጠቃሚዎቻችን ናቸው። የቤተሰብ አባላት መላው የእስራኤል ሕዝብ ከእናንተ ጋር ነው። በዚህ ታላቅ የሐዘን ወቅት ሁላችንም ከእናንተ ጋር ነን” ብለዋል።”ለአገራችን ሲሉ ወታደሮቻችን በፍትሃዊ ጦርነት ወድቀዋል። ለእናንተ ለእስራኤል ዜጎች ቃል የምገባላችሁ ተልዕኮውን በድል እስክንወጣ ድረስ እንቀጥላለን፣ እስክናሸንፍ ድረስ እንቀጥላለን” ሲሉ ተናግረዋል።Article share tools
  13. የታተመዉ 6:02 1 ህዳር 20236:02 1 ህዳር 2023በግብጽ ጊዜያዊ ሆስፒታል መቋቋሙን ተከትሎ ቁስለኞች እና የውጭ ዜጎች ጋዛን ሊለቁ ነውድንበር ለማቋረጥ የሚጠባበቁ ሰዎችReutersCopyright: Reutersድንበር ለማቋረጥ የሚጠባበቁ ሰዎችImage caption: ድንበር ለማቋረጥ የሚጠባበቁ ሰዎችበርካታ ልጆች እና ቤተሰቦቻቸው በራፋህ ማቋረጫ በኩል ድንበሩ ይከፈታል በሚል በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።በቅርቡ ድንበሩን ለማቋረጥ ተፈቅዶላቸው የሚወጡ ሰዎች እንደሚኖሩ ይጠበቃል።አምቡላንስም ሆነ የተጎዱ ሰዎች ወደ ግብፅ ሲሻገሩ እስካሁን አልታየም። ነገር ግን ለህክምና የሚጓጓዙ ሰዎች ወደ ግብጽ ለመሻገር የተለየ ስምምነት እንደሚኖርም ይጠበቃል።ከአካባቢው ባለስልጣናት ለመረዳት እንደተቻለው 88 የሚሆኑ በጽኑ የተጎዱ ሰዎች ወደ ግብጽ እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል።ግብጽ ከድንበር 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ጊዜያዊ ሆስፒታል እንደገነባች ተሰምቷል።ሮይተርስ የዜና ወኪል ከእስራኤል እና ከሐማስ ጋር ግንኙነቷን ያስጠበቀችው ኳታር ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ከጋዛ ወጥተው ሕክምና እንዲያገኙ ያስቻለው ስምመነት እንዲደረስ ማሸማገሏ ተሰምቷል።Article share tools
  14. የታተመዉ 6:00 1 ህዳር 20236:00 1 ህዳር 2023የኢራኑ አያቶላ አረብ አገራት ምግብ እና ነዳጅ ለእስራኤል እንዳይልኩ አሳሰቡየኢራኑ የሃይማኖት መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒAFPCopyright: AFPየኢራኑ ሃይማኖታዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒ ሙስሊም አገራት ነዳጅ እና ምግብ ለእስራኤል ከመላክ እንዲቆጠቡ ጥሪ አቀረቡ።ተጽእኖ ፈጣሪው ሃይማኖታዊ መሪ እስራኤል በጋዛ የምታደርገው ድብደባ እስኪቆም ድረስ አገራቱ ምርቶቻቸውን ከመላክ መቆጠብ አለባቸው ብለዋል።“በጋዛ ያለው ድብደባ በአስቸኳይ መቆም አለበት . . . ለጽዮናዊ አምባገነን መንግሥት ምግብ እና ነዳጅ የሚወስደው መንገድ መዘጋት አለበት” ሰለማለታቸው የኢራን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።የሐማስ ድንገተኛ ጥቃትን ተከትሎ እስራኤል በኢራን የሚደገፈውን እና ጋዛን የሚያስተዳድረውን ቡድን ከምድረ ገጽ አጠፋለሁ ብላ ከተነሳች በኋላ ጠንካራ ክንዷን በጋዛ እያሳረፍች ትገኛለች።ባለፉት ሦሰት ሳምንታት ከ8ሺህ የማያንሱ ሰዎች ጋዛ ውስጥ ስለመገዳለቸው ተዘግቧል።Article share tools
  15. የታተመዉ 4:06 1 ህዳር 20234:06 1 ህዳር 2023እስራኤል ሚሳኤል ተሸካሚ መርከቦቿን ወደ ቀይ ባሕር አስጠጋችየእስራኤል ሚሳኤል ተሸካሚ መርከብIDFCopyright: IDFየእስራኤል ሚሳኤል ተሸካሚ መርከብImage caption: የእስራኤል ሚሳኤል ተሸካሚ መርከብከእስራኤል በስተደቡብ አቅጣጫ በመቶዎች ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኘው የየመኑ የሁቲ አማጽያን ቡድን ትናንት እስራኤልን ሦስት ጊዜ በሚሳኤል እና በሰው አልባ አውሮፕላኖች ማጥቃቱን ገልጾ፤ ጥቃቱ እንደሚቀጥልም አስታውቆ ነበር።የእስራኤል ጦር በበኩሉ “በአካባቢው ያለውን የመከላከል ጥረት ለማጠናከር” የሚሳኤል መርከቦቹን ትናንት ወደ ቀይ ባሕር ማሰማራቱን አስታውቋል።ከእስራኤልዋ ኢላት ከተማ በስተደቡብ በሚገኘው ቀይ ባህር ላይ የተሰነዘረውን “የአየር ጥቃት በሚገባ ማክሸፉን” ጦሩ ዛሬ ማለዳ አስታውቋል።Article share tools
  16. የታተመዉ 3:49 1 ህዳር 20233:49 1 ህዳር 2023በእስራኤልና ሐማስ ጦርነት የቻይና ፍላጎት እና ሚና ምንድን ነው?ቻይና እየተባባሰ ለመጣው የእስራኤልና ሐማስ ጦርነት መፍትሄ ለመስጠት የሰላም አደራዳሪ የመሆን ፍላጎት አሳይታለች። ለመሆኑ በእስራኤልና ሐማስ ጦርነት የቻይና ሚና ምንድን ነው?ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  17. የታተመዉ 3:48 1 ህዳር 20233:48 1 ህዳር 2023ለብዙዎቹ የጋዛ ነዋሪዎች ‘ቴሌኮሙኒኬሽን ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል’በጋዛ ሰርጥ የኢንተርኔት እና የስልክ ኔትወርኮች መቋረጣቸውን የጋዛ ትልቁ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ ፓልቴል አስታውቋል። በዚህም ባለፈው አንድ ሳምንት ለሁለተኛ ጊዜ አገልግሎት ተቋርጧል።የዓለም አቀፍ የበይነ መረብ መቆጣጠሪያው ኔትብሎክስ “በዋናው አገልግሎት አቅራቢ ፓልቴል ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ ጋዛ አዲስ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ውስጥ ነች” ሲል አረጋግጧል።አብዛኛዎቹ የጋዛ ነዋሪዎች “ሙሉ ለሙሉ የቴሌኮሙኒኬሽን መቋረጥ ያጋጥማቸዋል” ሲል ኤክስ ላይ አስፍሯል።Article share tools
  18. የታተመዉ 3:27 1 ህዳር 20233:27 1 ህዳር 2023እስራኤል እስካሁን ድረስ 11ሺህ ዒላማዎችን መምታቷን አስታወቀችየእስራኤል ጦር በጋዛIDFCopyright: IDFየእስራኤል ጦር በጋዛImage caption: የእስራኤል ጦር በጋዛየእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ እስራኤል 11 ሺህ ዒላማዎችን መምታቷን አስታወቀች።የእስራኤል መከላከያ ኃይል ከመስከም 26 ጀምሮ በጋዛ “የአሸባሪ ድርጅቶች” ይዞታ የሆኑ ዒላማዎችን መምታቱን ገልጿል።ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ እስካሁን ከ8ሺህ የማያንሱ ሰዎች በእስራኤል ጥቃቶች በጋዛ ተገድለዋል።Article share tools
  19. የታተመዉ 3:17 1 ህዳር 20233:17 1 ህዳር 2023በአሜሪካ ፀረ ሴማዊነት “ታሪካዊ” ከሚባል ደረጃ ላይ መድረሱን የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ተናገሩበእስራኤል እና በጋዛ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በአሜሪካ ፀረ ሴማዊነት በታሪካዊ ከፍተኛ በሚባል ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ክሪስቶፈር ራይ አስጠነቀቁ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  20. የታተመዉ 1:29 1 ህዳር 20231:29 1 ህዳር 2023በሐማስ የተያዙ ታጋቾች ጉዳይ ‘በጣም አሳሳቢ’ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸሐማስ ጥቅምት 7 በደቡብ እስራኤል ተካሄደን የሙዚቃ ድግስ አጥቅቷልGetty ImagesCopyright: Getty Imagesሐማስ ጥቅምት 7 በደቡብ እስራኤል ተካሄደን የሙዚቃ ድግስ አጥቅቷልImage caption: ሐማስ ጥቅምት 7 በደቡብ እስራኤል ተካሄደን የሙዚቃ ድግስ አጥቅቷልየዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ሐማስ መስከረም 26 እስራኤል ላይ ጥቃት በፈፀመበት ወቅት አፍኖ የወሰዳቸው ታጋቾች ሁኔታ “በጣም ያሳስበናል” ሲሉ ገልጸዋል።ቴድሮስ በኤክስ ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ በተለይም የህጻናት፣ የሴቶች፣ የአረጋውያን እና አፋጣኝ የህክምና ክትትል የሚሹ ሰዎች ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል።”የዓለም ጤና ድርጅት በድጋሚ ሁሉም ታጋቾች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ይጠይቃል” ሲሉ ጨምረው አስፍረዋል።