በሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ደራ ወረዳ በታጠቁ ኃይሎች በደረሰ ጥቃት
* 3 አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸው እና
* ከ10 በላይ አገልጋይ ካህናት መገደላቸው ተገልጿል።
በምእመናን ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ እንደቀጠለ ገልጸው በደራ ወረዳ ሕገ ወጥ ታጣቂዎቹ ባደረሱት ጥያት ከ400 በላይ የኦርቶዶክሳውያን ቤቶች መቃጠላቸውም ነው የተገለጸው።
ታጣቂዎቹ ባደረሱት ጥቃት ከ8 ወረዳዎች በላይ የሚሆኑ የሚሆኑ በርካታ ዜጎች ከአካባቢያቸው ተሰደው ወደ አጎራባች ከተሞች እንደሚገኙ ፤ በከተማው የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያንን ደግሞ አግተው ገንዘብ እየጠየቁ መሆኑም ተመላክቷል።
ችግሩን ለመፍታት የሚመለከተው አካል ምንም አይነት ጥረት እያደረገ ባለመሆኑ የምእመናኑ የመኖር ህልውና በአደጋ ውስጥ እንደሚገኝ ለከባድ እንግልትም መዳረጋቸው ነው የተገለጸው።
በሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ደራ ወረዳ በታጠቁ ኃይሎች ኦርቶዶክሳውያን ላይ ተኮር በሆነ መልኩ በተፈጸመው ጥቃት በተለይም በገጠሩ ክፍል የሚገኙ አብዛኞቹ አብያተክርስቲያናት መዘጋጀታቸውን እና በደረሰው ጉዳት ቤተክርስቲያን አገልግሎት መስጠት መቆሙም ተገልጿል ሲል ማኅበረ ቅዱሳን ዘግቧል።