
ከ 4 ሰአት በፊት
የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት የባሕር ኃይል መሪ ሾመ።
ምክር ቤቱ አድሚራል ሊሳ ፍራንቼቲ የባሕር ኃይሉን እንደሚሩ በአብላጫ ድምጽ ሾሟል።
የናቫል ኦፕሬሽንስ አለቃ ሆነው ያገለገሉት ሊሳ ባሕር ኃይሉን በመምራት የመጀመሪያዋ ሴት ይሆናሉ።
የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት 95 ለ1 በሆነ ድምፅ ሹመቱን በማፅደቅ ክፍት የቆየውን ከፍተኛውን ወታደራዊ ወንበር እንዲመሩ መርጧቸዋል።
የ59 ዓመቷ ጉምቱ የባሕር ኃይል በዩኤስ 6ኛው ፍሊት እና በደቡብ ኮሪያው ባሕር ኃይል ያገለገሉ ሲሆን አየር ኃይል ተሸካሚ የባሕር ጦር አዛዥም ሆነው ሠርተዋል።
በፕሬዝደንት ጆ ባይደን ለሹመት የታጩት ሊሳ የፔንታገን ወታደራዊ ክንፍ እንዲመሩ በዕጩነት የቀረቡ የመጀመሪያዋ ሴትም ሆነዋል።
ምንም እንኳ የዩኤስ ድንበር ጥበቃ መሪ አድሚራል ሊንዳ ፋጋን ሴት ቢሆኑም ይህ ክፍል በሃገር ውስጥ ደኅንነት እንጂ በመከላከያ ሚኒስቴር የሚመራ አይደለም።
- በአማራ እና በኦሮሚያ የሚካሄዱት ግጭቶች እንዳሳሰቧቸው ምዕራባውያን አገራት ገለጹ2 ህዳር 2023
- “ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጠብ ከሚያጭሩ ድርጊቶች መቆጠብ አለባቸው” አንቶኒ ብሊንከንከ 5 ሰአት በፊት
- በረራ ላይ ሳለ ካፕቴኑን በሽጉጥ እመታለሁ ሲል የዛተው አሜሪካዊ አብራሪ ተከሰሰ2 ህዳር 2023
![አድሚራል ሊሳ ፍራንቼቲ [በግራ በኩል] ደቡብ ኮሪያ በተካሄደ የሜዳሊያ ሽልማት ላይ](https://i0.wp.com/ichef.bbci.co.uk/news/640/cpsprodpb/00d9/live/0b638240-7a05-11ee-a503-4588075e3427.jpg?w=800&ssl=1)
ከአድሚራል ሊሳ ሹመት በተጨማሪ ጄኔራል ዴቪድ አልቪን የአሜሪካ አየር ኃይል ቺፍ ኦፍ ስታፍ፤ ሌተናንት ጄኔራል ክሪስ ማሆኒ ደግሞ ማሪን ኮር ረዳት አዛዥ ሆነው ተሹመዋል።
ላለፉት ዘጠኝ ወራት አንድ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል በፔንታገን ፅንስ ማቋረጥ ፖሊሲ ምክንያት ከ400 በላይ ወታደራዊ ሹመቶችን ሲያግዱ ቆይተዋል።
ሪፐብሊካኑ ቶሚ ተበርቫይል የሚቃወሙት የፔንታገን ፖሊሲ የሠራዊቱ አባላት ፅንስ ማቋረጥ ከፈለጉ ከአንድ ግዛት ወደሌላ ተጉዘው የሚመለሱበትን ወጭ ይሸፈናል ይላል።
ነገር ግን ረቡዕ ምሽት ሌሎች ሪፐብሊካኖች ለመጀመሪያ ጊዜ ከሰውየው ሐሳብ ወጥተው ሹመቱን ለማፅደቅ የድጋፍ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
ወታደራዊ ባለሥልጣናት እና ሕግ አውጭዎች በመካከለኛው ምስራቅ እና በዩክሬን ግጭት ባለበት በአሁኑ ሰዓት የሪፐብሊካኑ ተቃውሞ የዩኤስን ብሔራዊ ጥቅም ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነው ሲሉ ተችተዋል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስቲን የተወሰኑ ክፍት ወንበሮች በመሞላታቸው “ደስተኛ” መሆናቸውን ገልጠው “ከፍተኛ ወታራዊ ሥልጣኖች ባልታሰብ ሁኔታ ሳይሟሉ መቅረታቸው የሠራዊቱን ዝግጁነት የጎዳው ነው” ብለዋል።
“እኒህ ሰዎች ለበርካታ አስርት ዓመታት ሃገራቸውን በታማኝነት ሲያገለግሉ የቆዩ ምጡቅ መሪዎች ናቸው። በአሁኑ ወቅት ያጋጠመንን ለብሔራዊ ደኅንነት ስጋት የሆነ ፈታኝ ሁኔታ በብቃት እንደሚወጡ አምናለሁ” ሲሉ በመግለጫቸው አክለዋል።
“ነገር ግን አሁንም ከ370 በላይ ብቃት ያላቸው መሪዎች ሹመታቸው ያለአግባብ ዘግይቶባቸዋል።”