ቀጥታ

የእስራኤል ጦር ጋዛ ከተማን ሙሉ በሙሉ መክበቡን አስታወቀ

Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. የእስራኤል ጦር ጋዛ ከተማን ሙሉ በሙሉ መክበቡን አስታወቀ
  2. አንቶኒ ብሊንከን እስራኤል ገቡ
  3. ሐማስ ከዋሻዎች እየወጣ ጥቃት ሰንዝሮ እየሸሸ ነው ስትል እስራኤል ገለጸች
  4. ሄዝቦላህ የእስራኤልን ድሮን አውድሟል መባሉን የአገሪቱ መከላከያ አስተባበለ
  5. ፕሬዚዳንት ባይደን የጋዛ ጦርነት ‘በጊዜያዊነት እንዲቆም’ ጥሪ አቀረቡ
  6. ፖፕ ፍራንሲስ የሁለት አገራት ምስረታ ለግጭቱ ዋነኛ መፍትሔ እንደሆነ ተናገሩ
  7. የኢራኑ አያቶላ አረብ አገራት ምግብ እና ነዳጅ ለእስራኤል እንዳይልኩ አሳሰቡ
  8. እስራኤል በጃባሊያ መጠለያ ጣቢያ ባደረስኩት ጥቃት የሐማስ መሪን ገደልኩ አለች
  9. እስራኤል ሚሳኤል ተሸካሚ መርከቦቿን ወደ ቀይ ባሕር አስጠጋች
  10. በጋዛ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዳግም ተቋረጠ
  11. እስራኤል እስካሁን ድረስ 11ሺህ ዒላማዎችን መምታቷን አስታወቀች

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 5:365:36እስራኤል ድብደባዋን በአስቸኳይ እንድታቆም ጆርዳን ጥያቄዋን ለአሜሪካ ልታቀርብ ነውየጆርዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አይማን ሳፋዲReutersCopyright: Reutersየጆርዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አይማን ሳፋዲImage caption: የጆርዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አይማን ሳፋዲየጆርዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ከአሜሪካው አቻቸው ጋር ሲገናኙ እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን ድብደባ በአስቸኳይ እንድታቆም እንደሚጠይቁ ተገለጸ።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ቅዳሜ ወደ ጆርዳን ተጉዘው ከውጪ ጉዳይ ሚንስትር አይማን ሳፋዲ ጋር ይነጋገራሉ።በሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ውይይት ላይ አይማን ሳፋዲ የእስራኤል እርምጃን አጥብቀው እንደሚያወግዙ ይጠበቃል።የጆርዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሚንስትሩ ከብሊንከን ጋር ሲገናኙ እስራኤል ሰላማዊ ሰዎችን በቦምብ በመደብደብ እና ከበባ ውስጥ በመክተት የጦር ወንጀል እየፈጸመች እንደሆነ በመግለጽ የአገራቸውን ጠንካራ አቋም ያንጸባርቃሉ።ብሊንከን ከሐማስ ጥቃት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በቀጠናው የሚገኙ መሪዎችን ለማነጋገር ዛሬ ረፋድ ቴል አቪቭ ደርሰዋል።ይህ የብሊንከን የጉዞ ዋነኛ ትኩረት ሐማስ በዚህ ጦርነት የሚሸነፍ ከሆነ የጋዛ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል እንዲሁም ግጭቱ በቀጠናው ወዳሉ አገራት እንዳይስፋፋ መግታት ስለሚቻልበት ሁኔታ ለመምከር ነው።Article share tools
  2. የታተመዉ 5:285:28ሐማስ ከዋሻዎች እየወጣ ጥቃት ሰንዝሮ እየሸሸ ነው ስትል እስራኤል ገለጸችየእስራኤል ጦር የሐማስ ጠንካራ ይዞታ የሆነውን የጋዛ ከተማን መክበቡን ገልጾ የሐማስ ተዋጊዎች ከዋሻዎች እየወጡ ጥቃት እየከፈቱ ነው ብሏል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  3. የታተመዉ 3:203:20የሄዝቦላ መሪ ሐሰን ናስራላህ የቡድኑን ቀጣይ እርምጃን የሚጠቁም ንግግራቸው ዛሬ ሊያደርጉ ነውየሄዝቦላህ መሪ ሐሰን ናስራላህ የእስራኤልና ሐማስ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ንግግር ያደርጋሉ ተባል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  4. የታተመዉ 3:203:20የእስራኤል-ሐማስ ግጭት ወደ አካባቢው አገራት ሊስፋፋ እንደሚችል አረብ ኤምሬትስ ገለጸችየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚንስትር የእስራኤል-ሐማስ ግጭት ወደ አካባቢው አገራት ሊስፋፋ እንደሚችል ስጋታቸውን ገለጹ።ሚንስትሩ አካባቢው ሁኔታ “ሊፈነዳ ከጫፍ ደርሷል” ብለዋል።“ግጭቱ በቀጠናው የመቀጣጠሉ እና የመስፋፋቱ ነገር እሙን ነው። አክራሪ ቡድኖችም አጋጣሚውን በመጠቀም ርዮተ ዓለም ከማስፋፋት ባለፈ ወደ ግጭት ዑደት ውስጥ ሊከቱን ይችላሉ” ሲሉ ኑራ አል-ካቢ በአቡ ዳቢ በተካሄደ የፖሊሲ ኮንፈረንስ ላይ ተናግረዋል።በአሜሪካ አሸማጋይነት ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያው ግንኘቷን በ2020 የጀመረችው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፤ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም እንዲደረገ “ያለመታከት” እየሠራች መሆኗን አል-ካቢ ገልጸዋል።“ጥረቶች ሁሉ ሲቪሎችን መጠበቅ እና ግጭቱን በፍጥነት ማስቆም ላይ ያተኩራሉ” ብለዋል።Article share tools
  5. የታተመዉ 3:173:17አንቶኒ ብሊንከን እስራኤል ገቡአንቶኒ ብሊንከንReutersCopyright: Reutersከእስራኤል ባለስልጣናት ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ የሚጠበቁት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንክን ቴል አቪቭ ገብተዋል።ብሊንከን በሲቪሎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት በሚቀንስበት ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርገው ይመክራሉ ተብሏል።ሐማስ መስከረም 26 ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ወደ እስራኤል ሲያቀኑ የአሁነኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።በሲቪሎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እስራኤል “ጠንካራ እርምጃ” የምትወስድበትን መንገድ እንደሚያፈላልጉ ከአሜሪካ ከመነሳታቸው በፊት አሳውቀዋል።ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንም ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚሆን ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቅርበዋል።ብሊንከን ወደ ጆርዳን እንደሚያቀኑ ይጠበቃል።እስራኤል የጋዛ ከተማን ሙሉ በሙሉ መክበቧን እና ከሐማስ ታጣቂዎች ጋር ፊት ለፊት እየተዋጋች መሆኗን አሳውቃለች።Article share tools
  6. የታተመዉ 1:391:39ታይላንድ በሐማስ የተያዙ 23 ዜጎቿን ለማስፈታት ከኢራን ጋር እየተነጋገረች ነውታይላንድ ዜጎቿን ለማስፈታት ኢራንን ጨምሮ ከሌሎች ከሐማስ ጋር ግንኙነት መፍጠር ከሚችሉ መንግስታት ጋር እየተነጋገረች መሆኗን አስታወቀች።ሐማስ መስከረም 26 በእስራኤል ላይ ጥቃት ሰንዝሮ አግቶ ከወሰዳቸው ከ240 በላይ ሰዎች መካከል ቢያንስ 23ቱ የታይላንድ ዜጎች ናቸው።የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓርንፕሬይ ባሂዳ-ኑካራ ለሐማስ ቅርበት ያላት ኢራን በድርድሩ ላይ እገዛ ለማድረግ ቃል ገብታለች ብለዋል።ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት ወደ 30 ሺህ የሚጠጉ ታይላንዳውያን በእስራኤል እርሻዎች ላይ ይሠሩ ነበር ተብሏል። በሐማስ ጥቃት በርካታ የታይላንድ ዜጎች ተገድለዋል።Article share tools
  7. የታተመዉ 1:391:39አሜሪካ ታጋቾችን ለመፈለግ በጋዛ ድሮን ማብረሯ ተገለጸየአሜሪካ የስለላ ድሮን (ፋይል ፎቶ)APCopyright: APየአሜሪካ የስለላ ድሮን (ፋይል ፎቶ)Image caption: የአሜሪካ የስለላ ድሮን (ፋይል ፎቶ)ሐማስ መስከረም 26 እስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ሰንዝሮ ሰዎችን አግቶ ወደ ጋዛ ከወሰደ በኋላ አሜሪካ ታጋቾችን ፍለጋ በጋዛ በሰው አልባ አውሮፕላን የታገዘ ቅኝት ስታደርግ መቆየቷ ተዘገበ።ሮይተርስ የዜና ወኪል ሁለት የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው አሜሪካ የታጋቾችን ቦታ ለመለየት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የቅኝት ድሮኖችን በጋዛ ስታበር ቆይታለች።ስሜ አይጠቀስ ያሉት የአገሪቱ ባለስልጣን አሜሪካ ከአንድ ሳምንት በላይ ድሮኖቹን ስታበር ቆይታለች።ሐማስ ከእስራኤል ካገታቸው መካከል 10 የሚሆኑት አሜሪካውያን መሆናቸው ተገልጿል።Article share tools
  8. የታተመዉ 1:221:22“በ24 ዓመቴ በፍጹም መሞት አልፈልግም”፡ ከራፋህ ድንበር መሻገር ያልቻለችው ወጣትለሦስተኛ ጊዜ ነው ድንበር ለመሻገር የሞከሩት። አሁን ግን ተስፋ አላቸው። ድንበሩ በቅርቡ እንደሚከፈት ተነግሯል። ይሄ ቤተሰብ በራፋህ በኩል እንዲወጣ በዮርዳኖስ ኤምባሲ ተነግሯታል።ታላ አቡ ናህላ እናቷ የዮርዳኖስ ዜጋ ናቸው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  9. የታተመዉ 1:221:22ሐማስ ከዋሻዎች እየወጣ ጥቃት ሰንዝሮ እየሸሸ ነው ስትል እስራኤል ገለጸችሐማስGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል ጦር የሐማስ ጠንካራ ይዞታ የሆነውን የጋዛ ከተማን መክበቡን ገልጾ የሐማስ ተዋጊዎች ከዋሻዎች እየወጡ ጥቃት እየከፈቱ ነው ብሏል።ጦሩ ከሐማስ ተዋጊዎች ጋር በቅርብ ርቀት ጦርነት መግጠሙንና የሐማስ ተዋጊዎች ከዋሻዎች በመውጣት ጥቃት ሰንዝረው እየሸሹ መሆኑን ጠቁሟል።Article share tools
  10. የታተመዉ 0:550:55በምስል፡ በመላው ዓለም ሰልፎች ተካሂዱበተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የእስራኤል-ሐማስ ጦርነትን በተመለከተ ሰልፎች ተካሄዱ።ሰልፎቹ በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚጠይቁ አልያም ለእስራኤል አጋርነትን የሚገልጹ ናቸው።ፈረንሳይ ፓሪስEPACopyright: EPAፈረንሳይ ፓሪስImage caption: ፈረንሳይ ፓሪስበፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰልፈኞች ለፍልስጤማውያን አጋርነታቸውን ለመግለጽ አደባባይ ወጥተዋል።ደቡብ ኮሪያEPACopyright: EPAደቡብ ኮሪያImage caption: ደቡብ ኮሪያበደቡብ ኮሪያ ሶል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ የሚጠይቅ ሰልፍ ተካሂዷል።በሮማኒያ እና በስዊትዘርላንድ ደግሞ ለእስራኤል አጋርነትን የሚገልጹ ሰልፎች ተካሂደዋል።በሮማኒያ የተካሄደው ሰልፍEPACopyright: EPAበሮማኒያ የተካሄደው ሰልፍImage caption: በሮማኒያ የተካሄደው ሰልፍስዊትዘርላንድ ዙሪክEPACopyright: EPAስዊትዘርላንድ ዙሪክImage caption: ስዊትዘርላንድ ዙሪክArticle share tools
  11. የታተመዉ 0:410:41የእስራኤል ጦር ጋዛ ከተማን ሙሉ በሙሉ መክበቡን አስታወቀጋዛGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል ጦር ጋዛ ከተማን ሙሉ በሙሉ መክበቡን እና በከተማዋ ሐማስ ወታደራዊ ቅኝት የሚያደርግባቸውን መመልከቻዎች፣ ማዘዣ ጣቢያዎች እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን እያጠቃ እንደሆነ አስታወቀ።ቀደም ሲል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ጦራቸው ወደ ጋዛ ከተማ የሚያደርገውን ግስጋሴ ማጠናከሩን ገልጸው ነበር።ጠቅላይ ሚንሰትሩ “አስደናቂ ስኬት አስመዝግበን የጋዛ ከተማ ዙሪያን አልፈን ወደፊት እየገሰገስን ነው” ብለዋል።Article share tools
  12. የታተመዉ 12:49 2 ህዳር 202312:49 2 ህዳር 2023ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ጦራቸው ወደ ጋዛ ከተማ እየገሰገሰ መሆኑን ገለጹጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁReutersCopyright: Reutersጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁImage caption: ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ጦራቸው ወደ ጋዛ ከተማ የሚያደርገውን ግስጋሴ ማጠናከሩን ገለጹ።ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት የወጣው መግለጫ ጋዛ ውስጥ በሚካሄደው “ጦርነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ነን” ብሏል።ኔታኒያሁ ዝርዝር ከመረጃ ከመስጠት በተቆጠቡበት መግለጫ “አስደናቂ ስኬት አስመዝግበን የጋዛ ከተማ ዙሪያን አልፈን ወደፊት እየገሰገስን ነው” ብለዋል።ቀደም ሲል ሲወጡ የነበሩ ሪፖርቶች በእስራኤል እና በሐማስ መካከል በጋዛ ከተማ ዙሪያ ጠንካራ ውጊያ እየተደረገ መሆኑ ተዘግቦ ነበር።ጋዛ ውስጥ ያለው የቢቢሲ ሪፖርተርም ሁለቱ ኃይሎች በሰሜናዊ የጋዛ ሰርጥ ቢያንስ በአምስት አካባቢዎች ውጊያ እያደረጉ ነው ሲል ዘግቦ ነበር።Article share tools
  13. የታተመዉ 11:13 2 ህዳር 202311:13 2 ህዳር 2023በሐማስ የታገቱ ሰዎች ቁጥር 242 መድረሱን እስራኤል አስታወቀችበሐማስ ከታገቱት መካከል አንዷ እስራኤላዊት አዛውንት ዲታዝ ሂይማን ይገኙበታልFamily HandoutCopyright: Family Handoutበሐማስ ከታገቱት መካከል አንዷ እስራኤላዊት አዛውንት ዲታዝ ሂይማን ይገኙበታልImage caption: በሐማስ ከታገቱት መካከል አንዷ እስራኤላዊት አዛውንት ዲታዝ ሂይማን ይገኙበታልእስራኤል በሐማስ የታገቱ ሰዎች ቁጥር 242 መድረሱን አስታወቀች።ሐማስ እስራኤል ላይ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ድንገተኛ ጥቃት ሰንዝሮ በውል ያልታወቁ ሰዎችን አፍኖ መውሰዱ ይታወሳል።እስራኤል አድራሻቸው የጠፋ ሰዎችን ጉዳይ ስትመርምር የቆየች ሲሆን፣ አሁን ላይ በሐማስ እጅ የገቡ ሰዎች ቁጥር 242 መሆኑን አረጋግጫለሁ ያለች ሲሆን ከታጋቾቹ መካከል ሕጻናት እና አዛውንቶች ይገኙበታል ተብሏል።ሐማስ ከእስራኤል ያገታቸውን የተለያዩ ዜግነት ያላቸውን ሰዎች በጋዛ በተለያዩ ስፍራዎች እንደደበቀ የገለጸ ሲሆን፣ ቩድኑ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ድብደባ እስካሁን ድረስ 57 የሚሆኑ ታጋቾች ተገድለዋል ብሏል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የታይላንድ መንግሥት በሐማስ ታግተው የሚገኙ ዜጎቹን ለማስለቀቅ ከቡድኑ ጋር ድርድር እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል።የታይላንድ መንግሥት እንዳለው ከሆነ “በትክክለኛው ጊዜ” ዜጎቹ እንደሚለቀቁ ከሐማስ ማረጋገጫ አግኝቷል።Article share tools
  14. የታተመዉ 9:58 2 ህዳር 20239:58 2 ህዳር 2023ባህሬን በእስራኤል ያሉትን አምባሳደሯን ጠራችተቃውሞReutersCopyright: Reutersበቅርቡ ከእስራኤል ጋር ወዳጅነቷን ያደሰችው ባህሬን እስራኤል በጋዛ ውስጥ እያካሄደችው ካለው ዘመቻ ጋር በተያያዘ በቴል አቪቭ የሚገኙትን አምባሳደሯን ጠርታለች።ከዚህ በተጨማሪም የባህሬን ፓርላማ እስራኤል በጋዛ እየፈጸመች ባለችው ጥቃት ምክንያት ከአገሪቱ ጋር ያላትን ምጣኔ ሃብታዊ ግንኙነትም እንዲቋረጥ ትዕዛዝ አሳልፏል።በባህሬን የነበሩት የእስራኤል አምባሳደርም ወደ አገራቸው ስለመመላሳቸው ተገልጿል።ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአሜሪካ አሸማጋይነት ባህሬን፣ ሞሮኮ፣ ሱዳን እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ከእስራኤል ጋር ግንኙነታቸውን በማደስ የንግድ እና ወታደራዊ ትብብር ስምምነት መፈጸማቸው ይታወሳል።Article share tools
  15. የታተመዉ 8:43 2 ህዳር 20238:43 2 ህዳር 2023አስካሁን ከ9 ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀበጃባሊያ በተባበሩት መንግሥታት በሚተዳደር ትምህርት ቤት ላይ ከተፈጸመ የአየር ጥቃት በኋላReutersCopyright: Reutersበጃባሊያ በተባበሩት መንግሥታት በሚተዳደር ትምህርት ቤት ላይ ከተፈጸመ የአየር ጥቃት በኋላImage caption: በጃባሊያ በተባበሩት መንግሥታት በሚተዳደር ትምህርት ቤት ላይ ከተፈጸመ የአየር ጥቃት በኋላአንድ ወር ሊሞላው በተቃረበው የእስራኤል እና የሐማስ ጦርነት በጋዛ ላይ ያለማቋረጥ በተካሄደው የእስራኤል የአየር ድብደባ የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር ከ9,000 በመብለጡን በሐማስ የሚመራው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ በጋዛ ሰርጥ ላይ እየተፈጸመ ባለው ጥቃት የተገደሉ ሰዎች አሃዝ ከዕለት ዕለት እያሻቀበ ሲሆን፣ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በወጣው አዲስ ቁጥር መሠረት 9,061 ሰዎች ተገድለዋል።ከተገደሉት ውስጥም ከአንድ ሦስተኛው የሚልቁት ወይም 3,760ዎቹ ሕጻናት መሆናቸውን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አመልክቶ፣ ከ32,000 የሚልቁ የጋዛ ነዋሪዎች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸዋል።ለዚህ ጦርነት መቀስቀስ ምክንያት በሆነው የሐማስ ጥቃት 1,400 በላይ እስራኤላውያን የተገደሉ ሲሆን፣ 242 የሚሆኑት ደግሞ በቡድኑ ታግተው ወደ ጋዛ መወሰዳቸውን የእስራኤል መንግሥት አስታውቋል።Article share tools
  16. የታተመዉ 6:25 2 ህዳር 20236:25 2 ህዳር 2023በጋዛ – እስራኤል የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮችየጋዛ ጥቃትShutterstockCopyright: Shutterstockእስራኤል በጋዛ ሰርጥ የምታደርገውን ጥቃት በአየር፣ በመሬት እና በባህር በተቀናጀ መልኩ አጠናክራ መቀጠሏን ገልጻለች።ትናንት ምሽትም ከሐማስ ጋር ከባድ ውጊያ እንደተካሄደም የእስራኤል ጦር አስታውቋል።በቅርቡ የተከሰቱ ጉዳዮችን እንዳስ፦
    • የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እያካሄዱት በነበረው የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ላይ አንዲት ሴት የፕሬዚዳንቱን ንግግር አቋርጣ በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ተደጋጋሚ ጥሪ አቅርባለች። ይህንንም ተከትሎ ፕሬዚዳንቱ ታጋቾችን ለማስለቀቅ በጊዜያዊነት እንዲቆም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። “በእኔ አስተሳሰብ በጊዜያዊነት መቆም አለበት። መገታት ማለት እስረኞቹን ለማስወጣት ጊዜ መስጠት ማለት” ነው ሲሉም ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ ጥሪ ያደረጉት ሰብዓዊ እርዳታ እንዲገባ እና በሐማስ የተወሰዱት 240 ታጋቾች እንዲፈቱ ነው ሲል ዋይት ሐውስ ማብራሪያ ሰጥቷል።
    • ከ400 በላይ የውጭ አገራት ዜጎች እና የተጎዱ ፍልስጤማውያን ከሶስት ሳምንታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋዛን ለቀው እንዲወጡ ተፈቅዶላቸዋል። ከነዚህም መካከል የእንግሊዝ እና የአሜሪካ ዜጎች ይገኙበታል።
    • በግብጽ በኩል ያለው የራፋህ ድንበር ማቋረጫ ተዘግቶ የቆየ ሲሆን ለጋዛ እርዳታ ለማስገባትም ተከፍቶ ነበር።
    • የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ ላይ ያደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ ተዋጊ ጄቶች በጃባሊያ የሚገኘውን የሐማስ ማዘዣ እና መቆጣጠሪያ ህንጻ ላይ ጥቃት ማድረሱን ጠቅሶ “በጥቃቱ ሁለት የሐማስ አሸባሪዎች ተወግደዋል” ሲልም ለቢቢሲ ተናግሯል።
    • በጃባሊያ ላይ እስራኤል ላለፉት ሁለት ቀናት ተከታታይ የአየር ጥቃት ፈጽማለች። እስራኤል በስደተኞች ማቆያው ከፈጸመችው ጥቀት በኋላ 1,000ሰዎች መገደላቸው፣ መጎዳታቸው ወይም የት እንዳሉ እንዳልታወቀ የጋዛ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
    • የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ጽህፈት ቤት እስራኤል በጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ ላይ የፈጸመቻቸውን የአየር ጥቃቶች አውግዞ፣ የሞቱ ሰላማዊ ሰዎችም አኃዝም በእስራኤል የተፈጸመ “የጦርነት ወንጀል” ሊሆን እንደሚችልም ጠቅሷል።
    • የእስራኤል መከላከያ 162ኛ ዲቪዥን አዛዥ ጄነራል ኢትዚክ ኮኸን ጦሩ ወደ ጋዛ በጥልቀት እየገባ እንደሆነ ተናግረዋል።
    Article share tools
  17. የታተመዉ 4:47 2 ህዳር 20234:47 2 ህዳር 2023በጃባሊያ የስደተኞች ጣቢያ የተገደሉ ፍልስጥኤማውያን ቁጥር መጨመሩ ተገለጸጃባሊያ የስደተኞች ጣቢያGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየስደተኞች መጠለያ በሆነው ጃባሊያ ሰሜናዊ ክፍል እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ።በጋዛ የሚገኘውና በሐማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር የሟቾች ቁጥር መጨመሩን ገልጿል።በጃባሊያ ላይ እስራኤል ላለፉት ሁለት ቀናት ተከታታይ የአየር ጥቃት ፈጽማለች።እስራኤል በስደተኞች ማቆያው ከፈጸመችው ጥቀት በኋላ 1,000ሰዎች መገደላቸው፣ መጎዳታቸው ወይም የት እንዳሉ እንዳልታወቀ ተገልጿል።ምን ያህሉ ሰዎች እንደሞቱ፣ እንደተጎዱና እንደጠፉ ባይገለጽም ከዚህ ቀደም የሟቾች ቁጥር 195 እንደደረሰ ተገልጿል።ያሳለፍነው ማክሰኞ እና ረቡዕ በደረሱት ጥቃቶች ብዙ ሕንጻዎች ተጎድተዋል።የእስራኤል መከላከያ በበኩሉ የሐማስ ኮማንደርን ዒላማ እንዳደረገና ብዙ ተዋጊዎችን እንደገደለ አስታውቋል።Article share tools
  18. የታተመዉ 3:42 2 ህዳር 20233:42 2 ህዳር 2023የእስራኤል ጦር ከሐማስ ጋር ከባድ ውጊያ ማድረጉን እና በርካታ ታጣቂዎች መገደላቸውን አስታወቀየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በጋዛ ሰርጥ ከሐማስ ጋር ከባድ ውጊያ ማድረጉን እና በርካታ ታጣቂዎች መገደላቸውን አስታወቀ።እግረኛ ጦሩም በአየር እና ባህር ጥቃቶች በመታገዝ በሰሜናዊ ጋዛ የሚገኘውን የሐማስ መከላከያ ግንባር መስበራቸውንም የእስራኤል ወታደራዊ ቃለ አቀባይ ገልጸዋል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ በምታደርገው የማያባራ የአየር ጥቃት እና ከባድ መሳሪያ ድብደባ ከ8 ሺህ 700 በላይ ሰዎች ሲገደሉ በርካቶቹ ህጻናት መሆናቸውን ከጋዛ ጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያስረዳል።በትናንትናው ምሽት አል ቁድስ ሆስፒታል አቅራቢያን ጨምሮ ከፍተኛ ፍንዳታዎች እና የከባድ መሳሪያ ድብደባ ተኩሶች እየተሰሙ እንደነበር አለም አቀፉ የቀይ ጨረቃ ድርጅት አስታውቋል።የእስራኤል ባለስልጣናት ህሙማንና የጤና ባለሙያዎች ሆስፒታሉን ለቀው እንዲወጡ ያስጠነቀቁ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ በህሙማን ላይ የሞት አደጋ መፈረጅ ነው ብሎታል።የመከላከያ ኃይሉ ሐማስ ጸረ ታንክ ሚሳኤሎችን መተኮሱን፣ ፈንጂዎችን እና የእጅ ቦምቦችን በእስራኤል ወታደሮችን ላይ መወርወራቸውን አስረድቷል። ጦሩም በምላሹ በከባድ መሳሪያ፣ በታንክ እንዲሁም በአየር እና ከባህር በተወነጨፈ የሚሳኤል ጥቃት አድርሻለሁ ብሏል። እግረኛ ጦሩም ከሐማስ ታጣቂዎች ጋር ፊት ለፊት መዋጋታቸውንም አክሎ ገልጿል።Article share tools
  19. የታተመዉ 2:57 2 ህዳር 20232:57 2 ህዳር 2023ፖፕ ፍራንሲስ የሁለት አገራት ምስረታ ለግጭቱ ዋነኛ መፍትሔ እንደሆነ ተናገሩየሮማው ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስReutersCopyright: Reutersየሮማው ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ በፍልስጥዔም እና በእስራኤል መካከል ያለውን ግጭት ለመፍታት የሁለት አገራት ምስረታ እና በግልጽ የተደነገጉ ግዛቶች መሰመር መፍትሔ መሆኑን ተናገሩ።ፖፕ ፍራንሲስ ለጣሊያኑ ሚዲያ አርኤአይ እንደተናገሩት “ሁለት በግልጽ የተደነገጉ ግዛቶች” ሊኖሩ ይገባል ብለዋል። እየሩሳሌምም ልዩ ስፍራ ይሰጣት ሲሉ ተናግረዋል።”በቅድስት አገር ያለው ጦርነት ያስፈራኛል። እነዚህ ማህበረሰቦች ይህንን ታሪክ እንዴት ይቋጩታል?” ሲሉም ጠይቀዋል።ፖፕ ፍራንሲስ የጦርነቱ መፋፋም “የብዙ ነገሮች መጨረሻ እና የበርካታ ሰዎች እልቂትንም የሚያስከትል ነው” ሲሉም ነው አጽንኦት የሰጡት ።በጋዛ ውስጥ 560 የሚሆኑ በአብዛኛው ክርስቲያኖች እንዲሁም አንዳንድ ሙስሊሞች ያስጠለሉ ገዳማትን እየመሩ ያሉ ቄሶች እና መነኮሳት ጋር በየቀኑ በስልክ እንደሚነጋገሩም ፖፑ አስረድተዋል።”ለአሁኑ አምላክ ይመስገን የእስራኤል ወታደሮች ለእነዚህ ደብሮች ክብር ሰጥተዋቸዋል” ብለዋል።Article share tools
  20. የታተመዉ 1:16 2 ህዳር 20231:16 2 ህዳር 2023ፕሬዚዳንት ባይደን የጋዛ ጦርነት ‘በጊዜያዊነት እንዲቆም’ ጥሪ አቀረቡየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንReutersCopyright: Reutersየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ታጋቾችን ለማስለቀቅ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የሚደረገው ጦርነት ‘በጊዜያዊነት እንዲቆም’ ጥሪ አቀረቡ።በሚኒሶታ በነበረ አንድ ዝግጅት ላይ አንዲት ሴት የተኩስ አቁም ስምምነት ጥሪ እንዲያደርጉ ፕሬዚዳንቱን መጠየቋን ተከትሎም ነው ባይደን በጊዜያዊነት መቆም እንዳለበት የተናገሩት።”በእኔ አስተሳሰብ በጊዜያዊነት መቆም አለበት። መገታት ማለት እስረኞቹን ለማስወጣት ጊዜ መስጠት ማለት” ነው ሲሉም ተናግረዋል።ፕሬዚዳንቱ ጥሪ ያደረጉት ሰብዓዊ እርዳታ እንዲገባ እና በሐማስ የተወሰዱት 240 ታጋቾች እንዲፈቱ ነው ሲል ዋይት ሐውስ ማብራሪያ ሰጥቷል።ግለሰቧ “የተኩስ አቁም አሁን” እያለች በተደጋጋሚ ስትናገርም በደህንነት ታጅባ ከዝግጅቱ እንድትወጣ ተደርጋለች።ፕሬዚዳንት ባይደንም ሁኔታው ለእስራኤላውያንም ሆነ ለሙስሊሙ ዓለም “በሚገርም ሁኔታ የተወሳሳበ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።”የሁለት አገራት መፍትሄን ደግፌያለሁ። ከጅምሩም ነው የደገፍኩት። እውነታው ሐማስ አሸባሪ ድርጅት ነው። ፍጹም አሸባሪ ድርጅት” ብለዋል።