Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች
- BBC
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59
Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ
- BBC
Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች
- BBC
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች
- BBC
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC
ጭምቅ ሃሳብ
- የእስራኤል ጦር ጋዛ ከተማን ሙሉ በሙሉ መክበቡን አስታወቀ
- የተመድ ባለሥልጣን በጋዛ ‘ደኅንነቱ የተጠበቀ’ ቦታ የለም አሉ
- አንቶኒ ብሊንከን እስራኤል ገቡ
- ሐማስ ከዋሻዎች እየወጣ ጥቃት ሰንዝሮ እየሸሸ ነው ስትል እስራኤል ገለጸች
- ሄዝቦላህ የእስራኤልን ድሮን አውድሟል መባሉን የአገሪቱ መከላከያ አስተባበለ
- ፕሬዚዳንት ባይደን የጋዛ ጦርነት ‘በጊዜያዊነት እንዲቆም’ ጥሪ አቀረቡ
- ፖፕ ፍራንሲስ የሁለት አገራት ምስረታ ለግጭቱ ዋነኛ መፍትሔ እንደሆነ ተናገሩ
- የኢራኑ አያቶላ አረብ አገራት ምግብ እና ነዳጅ ለእስራኤል እንዳይልኩ አሳሰቡ
- እስራኤል በጃባሊያ መጠለያ ጣቢያ ባደረስኩት ጥቃት የሐማስ መሪን ገደልኩ አለች
- እስራኤል ሚሳኤል ተሸካሚ መርከቦቿን ወደ ቀይ ባሕር አስጠጋች
- በጋዛ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዳግም ተቋረጠ
- እስራኤል እስካሁን ድረስ 11ሺህ ዒላማዎችን መምታቷን አስታወቀች
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 9:449:44ቱርክ የእስራኤል አምባሳደሯን ጠራች
ReutersCopyright: Reutersቱርክ በእስራኤል የሚገኙ አምባሳደሯን መጥራቷን የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።ሚኒስቴሩ አምባሳደሩ የተጠሩት እስራኤል በጋዛ እየወሰደች ስላለችው ድብደባ እና በጋዛ ስለተፈጠረው ሰብዓዊ ቀውስ ምክክር ለማድረግ ነው ተብሏል።ከእስራኤል-ጋዛ ጦርነት በኋላ ቴል አቪቭ እና አንካራ ከፍተኛ ወደሚባል የዲፕሎማሲ ፍጥጫ እየገቡ ነው።ከጥቂት ቀናት በፊት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃን እስራኤልን “የጦር ወንጀለኛ” ብለው መናገራቸውን ተከትሎ እስራኤል በቱርክ ያላትን አምባሳደሯን ጨምሮ ሁሉም ዲፕሎማቶቿን ጠርታለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ

- የታተመዉ 9:359:35የአሜሪካ ባለስልጣን በሰሜን ጋዛ 400ሺህ ያክል ሰዎች መኖራቸውን ገለጹ
ReutersCopyright: Reutersየአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ በሰሜናዊ ጋዛ 400ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መኖራቸውን ተናገሩ።ባለፉት ሳምንታት የእስራኤል ጦር ነዋሪዎች ከሰሜን ጋዛ ወጥተው ደኅንነቱ የተጠበቀ ነው ወደምትለው ደቡባዊ ጋዛ እንዲያመሩ ስታሳስብ ቆይታለች።የእስራኤል-ጋዛ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጊዜ አንስቶ እስራኤል በተለይ በሰሜን ጋዛ የማያባራ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ስትፈጽም ቆይታለች።ሳተርፊልድ ዛሬ በጆርዳን መዲና አማን ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፤ 800ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ወደ ደቡባ ጋዛ መሸሻቸውን ገልጸው ከ350-400ሺህ የሚሆኑት ግን አሁንም በሰሜን ጋዛ ይገኛሉ ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 9:299:29የእስራኤል ጦር በጋዛ ትልቁ አውራ ጎዳና ላይ ለሦስት ሰዓታት ለትራፊክ ክፍት ነው አለየእስራኤል ጦር በጋዛ ከሚገኙ ሁለት ግዙፍ ዋና መንገዶች መካከል አንዱ የሆነው ሳላህ አል-ዲን ለሦስት ሰዓታት ያክል ለትራፊክ ክፍት ሆኖ ይቆያል አለ።ጦሩ በኤክስ ገጹ ላይ ነዋሪዎች ከሰሜናዊ ጋዛ ወደ ደቡብ ጋዛ እንዲሄዱ የሚያስችለው መንገድ ዛሬ ከሰዓት ለትራፊክ ክፍት ነው ብሏል።እስራኤል ሰሜናዊ ጋዛ ላይ ወታደራዊ እርምጃ ስለምወስድ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ደቡባዊ የጋዛ ሰርጥ እንዲያመሩ ስታሳስብ ቆይታለች።ይሁን እንጂ የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ ሰብዓዊ ድርጅቶች የትኛውም የጋዛ ክፍል ደኅንነቱ የተጠበቀ አይደለም ይላሉ።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:466:46ብሊንከን ከሌባኖስ እና ኳታር መሪዎች ጋር ተገናኙ
ReutersCopyright: Reutersብሊንከን ከኳታሩ ጠቅላይ ሚንስትር ጋርImage caption: ብሊንከን ከኳታሩ ጠቅላይ ሚንስትር ጋርየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ከሌባኖስ እና ኳታር ጠቅላይ ሚንስትሮች ጋር ተገናኙ።ብሊንከን መሪዎቹን እያነጋገሩ ያሉት በጆርዳን ነው።ብሊንከን ቀደም ሲል ከሌባኖስ ግዚያዊ ጠቅላይ ሚንስትር ናጂብ ሚካቲ ጋር ተገናኝተዋል።
ReutersCopyright: Reutersብሊንከን ከሌባኖሱ ግዚያዊ ጠቅላይ ሚንስትር ጋርImage caption: ብሊንከን ከሌባኖሱ ግዚያዊ ጠቅላይ ሚንስትር ጋርየግዚያ ጠቅላይ ሚንስትሩ ጸ/ቤት ከብሊንከን በነበራቸው ውይይት ሌባኖስ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ስለመጠየቋ አስታውቋል።አንቶኒ ብሊንከን ከጆርዳን፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ግብጽ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ጋርም እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:085:08ብሊንከን ዛሬ በጋዛ ጉዳይ ከበርካታ የአረብ አገራት መሪዎች ጋር ሊነጋገሩ ነው
AFPCopyright: AFPየአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን በእስራኤል ሐማስ ጦርነት ዙሪያ ከበርካታ የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት መሪዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል።የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ከሌባኖስ፣ ኳታር እና ጆርዳን መሪዎች ጋር እንደሚገናኙ ይጠበቃል።ብሊንከን በአሁኑ ወቅት ጆርዳን የሚገኙ ሲሆን ከጆርዳን ንጉሥ አብዱላህ ሁለተኛ ጋር እና ከኳታር ጠቅላይ ሚንስትር ጋር እንደሚገናኙ ይጠበቃል።ብሊንከን ቀደም ሲል ከሌባኖስ ግዚያዊ ጠቅላይ ሚንስትር ናጂብ ሚካቲ ጋር ተገናኝተዋል።አንቶኒ ብሊንከን ከጆርዳን፣ ሌባኖስ፣ ኳታር፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ግብጽ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ጋርም እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:065:06“አንዳንድ ጊዜ ከካሜራ ጀርባ ቆሜ አለቅሳለሁ” የጋዛው ጋዜጠኛእስራኤል በሙሉ ከበባ ባስገባቻት ጋዛ ኤሌክትሪክ፣ ውሃ ተቋርጧል። የነዳጅ እና ምግብ አቅርቦት እየተመናመነ ነው። የጋዛው ጋዜጠኛ ማህሙድ ባሳም ስልኩ እንደ ድሮው አይጠራም። ስልኩን በየቀኑ ቻርጅ አያደርግም። ቻርጅ ባደረገበት ቀን የስልክ ጥሪዎች ተከታትለው ይመጣሉ። ምግብ ሲያገኝ ይበላል፤ ካላገኘም ጦሙን ያድራል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:574:57እስራኤል የሐማስ መሪ መኖሪያ ቤትን በሚሳኤል መታች
AFPCopyright: AFPየሐማስ የፖለቲካ መሪ ኢስማኢል ሃኒዬImage caption: የሐማስ የፖለቲካ መሪ ኢስማኢል ሃኒዬሮይተርስ የዜና ወኪል ለሐማስ ቅርበት ያላቸውን መገናኛ ብዙሃንን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ እስራኤል የሐማስ የፖለቲካ መሪ መኖሪያ ቤትን በሚሳኤል መትታለች።ኢስማኢል ሃኒዬ እአአ 2009 ላይ ከጋዛ ሰርጥ ወጥቶ ቋሚ መኖሪያውን በቱርክ እና ኳታር አድርጓል። ጥቃቱ ሲፈጸምም ኢስማኢል ሃኒዬ ከጋዛ ውጭ ስለመሆኑ ሪፖርቶች ጠቁመዋል።በጋዛ በሚገኘው ኢስማኢል ሃኒዬ መኖሪያ ቤት ላይ በደረሰው ጥቃት በቤተሰብ አባላቱ ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ እስካሁን የተባለ ነገር የለም።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:373:37የእስራኤል ጦር የውሃ ታንከሮችን፣ ጄነሬተሮችን፣ የሶላር ሳህኖችን ዒላማ ማድረጉ ተገለጸየእስራኤል ጦር ሌሊቱን በጋዛ ባደረገው ድብደባ የውሃ ማከማቻ ታንከሮችን፣ የኤሌክትሪክ ኃይሉ የሚያመነጩ ጄነሬተሮችን እና ሶላር ሳህኖችን ዒላማ ማድረጉ ተገለጸ።አናዱሉ፣ ቲአርቲ ዎርልድ እና አል ጀዚራ እንደዘገቡት በምዕራብ ጋዛ ለሚገኘው ናሰር የሕጻናት ሆስፒታል ከጸሐይ ብርሃን የኤሌክሪክ ኃይል አቅርቦት ይሰጡ የነበሩ የሶላር ሳህኖች በአየር ድብደባ እንዲወድሙ ተደርገዋል።የምስራቅ ራፋህ ነዋሪዎች የውሃ ማከማቻ ታንከርም እንዲሁ በእስራኤል ድብደባ ተመትቷል።በጋዛ ከተማ የአል-ዋፋ ሆስፒታል ዋነኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭ የሆነ ጄኔሬተርም ተመትቶ ከጥቅም ውጭ መሆኑ ተዘግቧል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:232:23የፔንታገን ቃል አቀባይ፡ “ግጭቱ ወደ ቀጠናው እንዳይሻገር ተደርጓል”
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየፔንታገን ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀነራል ፓትሪክ ኤስ ራይደር አሁን ባለው ሁኔታ የእስራኤል እና ሐማስ ግጭት ወደ ቀጠናው እንዳይስፋፋ ማድረግ መቻሉን ገለጹ።ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ “አሁን ግጭቱ የእስራኤልና ሐማስ ብቻ ነው” ብለዋል።የሄዝቦላህ መሪ ሐሰን ናስረላህ ከግጭቱ መነሳት በኋላ የመጀመሪያ ንግግራቸውን ትላንት ማድረጋቸውን ተከትሎ ጥያቄ የቀረበላቸው ቃል አቀባዩ፣ ግጭቱ ቀጠናዊ እንዳይሆን ማድረግ “የመንግሥታችንና መከላከያችን ዋነኛ ትኩረት ነው” በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።ሁለት ተዋጊ አውሮፕላ ተሸካሚ መርከቦችን አሜሪካ ያስጠጋችው በዚህ ምክንያት እንደሆነም አክለዋል።“ቀጠናዊ ግጭት ተቀልብሷል ብለን እናምናለን። ከኢራን ጋር መጋጨት አንሻም። በቀጠናው ግጭት እንዲስፋፋ አንፈልግም። ግጭቱን አስቁሞ መረጋጋት ማስፈን ነው ግባችን” ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:202:20ሊባኖስን የሚያንቀጠቅጠው፣ የእስራኤል ስጋት ሒዝቦላህ፡ መሪው ሐሰን ናስራላህ ማን ናቸው?ሐሰን ናስራላህ ከአውሮፓውያኑ 1992 ጀምሮ ሊባኖስ ውስጥ የሚገኘውን ሒዝቦላህን በመምራት አስካሁን ቆይተዋል። ከአገሪቱ ሠራዊት ጎን የታጣቀ ኃይል ያለው ቡድኑ በአሁኑ ጊዜ ሊባኖስ ውስጥ ካሉ የፖለቲካ ኃይሎች ሁሉ ከፍተኛ ተጽእኖ አለው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:311:31የተመድ ባለሥልጣን በጋዛ ‘ደኅንነቱ የተጠበቀ’ ቦታ የለም አሉ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየተባበሩት መንግሥታት ባለሥልጣን በጋዛ አሁን ላይ “ደኅንነቱ የተጠበቀ አንዳችም ቦታ የለም” አሉ።የተመድ ሕንጻዎች ለበርካታ የተፈናቀሉ ሰዎች መጠለያ ሆነዋል።የተመድ ባለሥልጣኑ ቶማስ ዋይት ተቋሙ ለተፈናቃዮች ከለላ መስጠት ከአቅሙ በላይ እንደሚሆን ተናግረዋል።በተመድ ከለላ የሚሹ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደኅንነታቸው የተጠበቀ እንደማይሆን ገልጸዋል።የተመድ የፍልስጥኤማውያን ተፈናቃዮች ተቋም ያስጠለላቸውን 600,000ተፈናቃዮች ደኅንነት ከዚህ በኋላ ለማረጋገጥ እንደሚቸገር ገልጿል።የተመድ የጋዛ ቅርንጫፎች “ከአገልግሎት ውጭ ሆነዋል” ብለዋል ባለሥልጣኑ።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን የቀረበውን ሰብአዊ ጊዜያዊ ተኩስ አቁም እንደማይቀበሉ ገልጸዋል።ብሊንከን አሁን በዮርዳኖስ የሚገኙ ሲሆን፣ ከአረብ አገራት መሪዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:271:27ኤል ጋዚ ለፍልስጥኤማውያን ድጋፉን በመግለጹ ክለቡ ውሉን አቋረጠ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesአንዋር ኤል ጋዚImage caption: አንዋር ኤል ጋዚየክንፍ ተጫዋቹ አንዋር ኤል ጋዚ በማሕበራዊ ሚዲያ ገጹ ለፍልስጥኤማውያን ድጋፉን በመግለጹ ክለቡ ውሉን ሰረዘ።የጀርመኑ ሜንዝ የ28 ዓመቱ ተጫዋች ውል የሰረዘው ተጫዋቹ ለፍልስጥኤማውያን ድጋፍ የሚገለጽ መግለጫው እና ማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ባጋራቸው ይዘቶች ነው ብሏል።ኤል ጋዚ ከክለቡ ጋር የነበረው ውል መሰረዙን ተከትሎ “ለብቻችንንም ቢሆን ትክክል ለሆነው ነገር ጸንተን መቆም አለብን” ብሏል።ተጫዋቹ በጋዛ የሰላማዊ ሰዎች ግድያ እንዲቆም ሲጠይቅ ነበር።የኔዘርላንድስ ዜግነት ያለው ኤል-ጋዚ ከዚህ ቀደም በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለአስቶን ቪላ እና ኤቨርተን ተጫውቷል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:261:26የእስራኤል ባለሥልጣን ሐማስ ከሆስፒታል ስር ማዘዣ ጣቢያ አለው አሉየጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ አማካሪ ማርክ ሬጌቭ ሐማስ ከሆስፒታል ስር የማዘዣ ጣቢያ እንዳለው እስራኤል መረጃው አላት አሉ።ይህ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሐማስ ማዘዣ ጣቢያ በጋዛ ትልቁ በሆነው አል-ሺፋ ሆስፒታል ስር የሚገኝ መሆኑን ቻናል 4 ለተባለ የዩኬ የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።ሬጌቭ የጠላት ኃይል በሰላማዊ ሰዎች መሠረተ ልማት ስር መሰል ግንባታ ካላው መሠረተ ልማቱ “ዒላማ ሊደረግ ይችላል” ብለዋል።እስራኤል በጋዛ በትልቁ ሆስፒታል ፊት ለፊት ጥቃት አድርሳ አምቡላንስ አውድማ 13 ሰዎች ስለመግደሏ ሪፖርት ተደርጓል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:241:24ዶ/ር ቴድሮስ ሆስፒታል አቅራቢያ ፍንዳታ ማጋጠሙ ‘እጅግ አስደንግጦኛል’ አሉ
ReutersCopyright: Reutersየዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ፊት ለፊት ፍንዳታ ማጋጠሙ ‘እጅግ አስደንግጦኛል’ አሉ።ዋና ዳይሬክተሩ በሪፖርቱ እጅግ መደናገጣቸውን ገለጸው በፍንዳታው ምክንያት ሰዎች መሞታቸውን፣ መጎዳታቸውን እና በሆስፒታል ንብረት ላይ ውድመት ማጋጠሙን ገልጸዋል።“ታማሚዎች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ የሕክምና ጠቋማት እና አምቡላንሶች በየትኛውን ጊዜ ሊጠበቁ ይገባል። ሁልግዜም። አሁኑኑ የተኩስ አቁም ይደረግ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።ቀደም ሲል በሐማስ የሚተዳደረው ጤና ሚንስቴር አል-ሺፋ ሆስፒታል ፊት ለፊት ባጋጠመው ፍንዳታ 13 ሰዎች መገደላቸውን አስታውቆ ነበር።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:091:09የእስራኤል ጦር አምቡላንስ መምታቱን ገለጸ
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤል አየር ኃይል በጋዛ አምቡላንስ መምታቱን ገለጸ።ጦሩ አምቡላንሱን የመታው ተሸከርካሪው “በሐማስ ሽብርተኛ ቡድን ሴል” ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን በማረጋገጤ ነው ብሏል።የእስራኤል ጦር አምቡላንስን በመጠቀም ሐማስ አባላቱን እና ጦር መሳሪያዎችን እያዘዋወረ ስለመሆኑ መረጃው አለኝ ብሏል።በጋዛ ከተማ ትልቁ ከሆነው አል-ሺፋ ሆስፒታል ፊት ለፊት ከፍተኛ ፍንዳታ ስለማጋጠሙ ተዘግቧል።ቢቢሲ ያረጋገጣቸው ምስሎች በፍንዳታው የወደመ አምቡላንስ እንዲሁም ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ከሆስፒታሉ ፊት ለፊት ወድቀው ያሳያሉ።እስራኤል አሁንም ሰዎች ለደኅንነታቸው ሲሉ ወደ ደቡብ ጋዛ እንዲሸሹ ማስጠንቀቂያ መስጠቷን ቀጥላለች።“ይህ ቀጠና የውጊያ አካባቢ በመሆኑ ሰላማዊ ሰዎች ለራሳቸው ደኅንነት ሲሉ ወደ ደቡብ አቅጣጫ እንዲሄዱ በተደጋጋሚ ጥሪ አቅርበናል” ብሏል ጦሩ በመግለጫው።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 11:18 3 ህዳር 202311:18 3 ህዳር 2023ኔታኒያሁ ጊዜያዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ የቀረቡ ጥያቄዎችን ወደቅ አደረጉ
ReutersCopyright: Reutersጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁImage caption: ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁየእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ከሐማስ ጋር አየተደረገ ባለው ግጭት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እየቀረቡ ያሉትን ጥሪዎች ውድቀ አደረጉ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቴሌቪዥን በተላለፈ ንግግራቸው፣ ሐማሰ በእስራኤል ላይ ጥቃት በሰነዘረበት ወቅት የታገቱ ሰዎች በሙሉ አስከሚለቀቁ ድረስ በሚቀርቡት የተኩሰ አቁም ጥሪያዎች እንደማይስማሙ ገልጽ አድርገዋል።ኔታኒያሁ ይህንን የተናገሩት ዛሬ አርብ እስራኤልን የጎበኙት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ወደ ጋዛ ሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ ግጭቱ ጋብ እንዲል በድጋሚ ጥሪ ካቀረቡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ነው። ብሊንከን ተኩስ ማቆም ከተደረገ “ታጋቾች እንዲለቀቁ አመቺ ሁኔታን ሊፈጥር ይችላል” ብለው ነበር።ብሊንከን ግጭቱ በጊዜያዊነት እንዴት ጋብ እንደሚል “ውይይት የሚደረግበት ይሆናል” በማለት፣ ይህ ግን እንዴት መሆን አለበት በሚለው ዙሪያ እስራኤል “ተገቢ የሆኑ ጥያቄዎች አሏት” ሲሉ ተናግረዋል።ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ “እስራኤል የታገቱብንን ሰዎች ማስመለስን የማይጨምር ጊዜያዊ ተኩስ አቁምን እንደማትቀበል አሳውቀናል” ብለዋል።መደበኛ የተኩስ አቁም በአብዛኛው ተፋላሚ ወገኖች ንግግር እንዲያደርጉ የሚያስችል ረጅም ጊዜን የሚጠይቅ ሲሆን፣ ለሰብአዊ እርዳታ ግጭትን ማቆም ግን ለሰዓታት የሚቆይ ሊሆን ይችላል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 10:55 3 ህዳር 202310:55 3 ህዳር 2023የሒዝቦላህ መሪ ሐማሰ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት አደነቁ
ReutersCopyright: Reutersየመሪውን ንግግር ለመሰማት አደባባይ የወጡት የሒዝቦላህ ደጋፊዎችImage caption: የመሪውን ንግግር ለመሰማት አደባባይ የወጡት የሒዝቦላህ ደጋፊዎችበሊባኖስ ውስጥ በወታደራዊ እና በፖለቲካዊ አቅሙ ኃያል የሆነው የእስላማዊው ቡድን ሒዝቦላህ መሪ ሐሰን ናስራላህ በእስራኤል እና በጋዛ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየታቸውን ሰጡ።ናስራላህ ከምስጢራዊ ስፍራ በሰጡት እና በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤየሩት ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አደባባይ ወጥተው በተከታተሉት ንግግራቸው፣ ሐማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ፈጸሞ 1,400 ሰዎችነ የገደለበተን አርምጃ አድንቀዋል።አንደ ሒዝቦላህ ሁሉ አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በምዕራባውያን አገራት ሽብርተኛ ድርጅት የተባለው ሐማስ፣ የወሰደው እርምጃ “ትክክለኛ፣ ብልህ እና ፍትሃዊ” ነው በማለት፣ በእስራኤል ላይ ላይ የተፈጸመው ጥቃት “100% የፍልስጤማውያን ነው” በማለት ገልጸውታል።ናስራላህ በንግግራቸው አሜሪካ በጋዛ ውስጥ ለሚካሄደው ጦርነት ተጠያቂ ናት በማለት በቁጣ ተችተዋል።በተጨማሪም በየመን እና በኢራቅ ያሉ በኢራን የሚደገፉ ኃይሎችን አመስግነዋል። በየመን የሚገኙት ሁቲ አማጺያን በእስራኤል ላይ ድሮኖችን ያስወነጨፉ ሲሆን፣ የኢራቅ ሺዓ ሚሊሻዎች ደግሞ በኢራቅ እና በሶሪያ በሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃት ማድረሳቸው ይታወቃል።ኢራን ዋነኛውን ኃያል ቡድን ሒዝቦልህን ጨምሮ በኢራቅ ያሉ ሚሊሻዎችን፣ የሶሪያውን መሪ ባሻር አል-አሳድን፣ የሁቱ አማጺያንን እና ሐማስን የካተተውን እንቅስቃሴ ትደግፋለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 9:51 3 ህዳር 20239:51 3 ህዳር 2023የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ “ተሰማርቷል እንዲሁም ዝግጁ ነው” ተባለ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል ጦር በሰሜናዊ የሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።የእስራኤል ጦር ቃለ አቀባይ ኮሎኔል ሪቻርድ ሄክት የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በድንበር አቅራቢያ “ተሰማርቷል እንዲሁም ዝግጁ ነው” ብለዋል።አክለውም ጦሯቸው “ለመከላከል ዝግጁ” መሆኑንም ተናግረዋል። “ለሊባኖሳውያን የወደፊት ዕጣ ፈንታችሁን ለሐማስ አትሰው እያልን ነው” ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።የሄዝቦላህ መሪ ሐሰን ናስራላህ የእስራኤልና ሐማስ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ንግግር ያደርጋሉ በተባለበትም ወቅት ነው ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት።የሊባኖሱ የሺዓ ሙስሊም ቡድን መሪ እስከዛሬ ድረስ ለተከታዮቻቸው በአደባባይ ያሉት ነገር የለም። ሄዝቦላህ በቀጣይ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ሐሰን ናስራላህ ዛሬ በሚያደርጉት ንግግራቸው እንደሚጠቁሙ ይጠበቃል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:47 3 ህዳር 20238:47 3 ህዳር 2023ከአየር ጥቃቶቹ በፊት ስድስት ሚሊዮን አጭር የጽሁፍ መልዕክቶች ማስጠንቀቂያ ተልኳል- እስራኤል
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የአየር ጥቃት ከመጀመሯ በፊት የማስጠንቀቂያ በራሪ ወረቀቶች መበተኗን ፕሬዚዳንቷ አይዛክ ሄርዞግ ለጋዜጠኞች አሳይተዋል።ስድስት ሚሊዮን አጭር የጽሁፍ መልዕክት እንደተላከ፣ አራት ሚሊዮን ስልክ እንደተደወለ እና 1.2 ሚሊዮን በራሪ ወረቀቶች ተበትነዋል ብለዋል።ፕሬዚዳንቱ ተበትኗል ብለው እያሳዩ የነበረውን በራሪ ጽሑፍ ላይ የተጻፈውን ማስጠንቀቂያ ቢቢሲ ማንበብ አልቻለም።እስራኤል በጃባሊያ መጠለያ በፈጸመችው የአየር ጥቃት በርካታ ሰላማዊ ዜጎች የተገደሉ ሲሆን በዚህም ጥቃት ለሰላማዊ ዜጎች ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል በማለት አገራቸው አለም አቀፉን ህግ በማክበር ነው የምትሰራው ብለዋል።እስራኤል በተከታታይ ቀናት በጃባሊያ መጠለያ የፈጸመቻቸው የአየር ጥቃቶችን የተበባሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ “ግልጽ የሆነ የዓለም አቀፍ ህግ ጥሰት ነው” ሲሉ አውግዘውታል።አንቶኒዮ ጉተሬዝ ባለፈው ሳምንት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባደረጉት ንግግር ሁለቱንም አካላት በስም ባይጠቅሱም ሐማስ ሰላማዊ ዜጎችን ሸፋን በማድረግ እንዲሁም እስራኤል ከአንድ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን በአስገዳጅ ሁኔታ ማፈናቀሏን ጠቅሰዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 7:41 3 ህዳር 20237:41 3 ህዳር 2023በጋዛ- እስራኤል የተከሰቱ የቅርብ ጉዳዮች
ReutersCopyright: Reutersበጋዛ- እስራኤል የተከሰተው ቀውስ አንድ ወር ሊሞላው የቀሩት ጥቂት ቀናት ናቸው።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የአየር እና የምድር ጥቃቶችን እንዲሁም ከባህር በሚወነጨፉ ሚሳኤሎች የምትፈጽመውን ጥቃት አጠናክራ መቀጠሏን ጦሯ አስታውቋል።
- የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን እስራኤል ገብተዋል። ሐማስ የፈጸመውን መብረቃዊ ጥቃት ተከትሎም ኃላፊው ለሶስተኛ ጊዜ ነው እስራኤልን ሲጎበኙ። የአሜሪካው ባለስልጣን ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር የተገናኙ ሲሆን በጋዛ ሰርጥ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ “ተጨባጭ እርምጃዎች” ላይ እንደሚያተኩሩም ተገልጿል።
- የእስራኤል ጦር የጋዛ ከተማን ሙሉ በሙሉ መክበቡን አስታውቋል።
- በግብጽ በኩል ያለው የራፋህ የድንበር ማቋረጫ ከረቡዕ ጀምሮ ለሶስተኛ ጊዜ ተከፍቷል። ማቋረጫው የተከፈተው ጥምር ዜግነት ያላቸውን ዜጎች ለማስወጣት ነው።
- እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እየፈጸመችው ባለው የአየር ጥቃቶች ከ9 ሺህ ሰዎች በላይ መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
- ከጋዛ ወደ እስራኤል ለስራ ሄደው የነበረ በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን የስራ ፈቃዳቸው ተሰርዞ ወደ ጋዛ እንዲመለሱ መደረጋቸውን የእስራኤል መንግሥት አስታውቋል።
- በዌስት ባንክ በተፈጸመው ጥቃት ስምንት ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጤም የህክምና ምንጮች ለሮይተርስ ተናግረዋል።
- በጋዛ ሴቶችና ህጻናት ጨምሮ 242 ግለሰቦች በሐማስ ታግተዋል።