November 4, 2023 – Konjit Sitotaw 

ብርሃኑ ነጋ ደንግጧል።

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 69 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት አስመዘገቡ ሲሉ የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል። በቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል ማትሪክን የወሰዱ ተማሪዎች በሙሉ በወደቁበት እና በቁጥር የሚሆኑ ተማሪዎች ባለፉት በዚህ ወቅት በጦርነት ውስጥ ባለፈችው ትግራይ ከመቶ 69 የሆኑ ተማሪዎች አለፉ ተብሎ መታወጁ ጥያቄ አስነስቷል። በጦርነት  የተጎዱ ስለሆኑ እንደ ልዩ ጥቅም ታይቶ ከሆነ በዝምታ ማለፉ ይሻላል ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች ።

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር ዓቀፍ ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 69 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮን ጠቅሶ የዘገበው የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የትምሕርት ሚኒስቴርን አስተያየት አላካታተም። በሃገር አቀፍ ደረጃ በተሰጠ ፈተና የፌዴራሉ ትምሕርት ሚኒስቴር መግለጫ መስጠት ሲገባው የትምሕርት ቢሮው መግለጫ መስጠቱ ሌላኛው ጥያቄ ያስነሳ ጉዳይ ነው።

የቢሮው ኃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ በክልሉ ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር ዓቀፍ የፈተና ውጤት ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት ላይ ይፋ መሆኑን አስታውሰዋል።

በዚህም መሠረት ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 69 ነጥብ 96 በመቶ የሚሆኑት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣታቸውን ገልጸዋል።

ከተመዘገበው ውጤት 657 ከፍተኛው ነጥብ መሆኑንም አመልክተዋል። የአገር አቀፍ ፈተናን በተመለከተ የሚመለከተው የትምሕርት ሚኒስቴር ሆኖ ሳለ የትምሕርት ቢሮው ሃላፊ በፌስቡክ ገፃቸው ይፋ ማድረጋቸው በምን ምክኛት እንደሆነ ያላብራራው ዜናውን የዘገበው የመንግስት ሚዲያ ፋና  የትምሕርት ሚኒስቴርን አስተያየት አላካታተም። በሃገር አቀፍ ደረጃ በተሰጠ ፈተና የፌዴራሉ ትምሕርት ሚኒስቴር መግለጫ መስጠት ሲገባው የትምሕርት ቢሮው መግለጫ መስጠቱ ሌላኛው ጥያቄ ያስነሳ ጉዳይ ነው።