ጋዛ

5 ህዳር 2023, 08:04 EAT

የእስራኤል-ጋዛ ጦርነት የዓለም ትኩረትን ሰቅዞ ቢይዝም፣ መገናኛ ብዙኃን ክስተቱን ቀን ከሌሊት ዋነኛ አጀንዳቸው አድርገው ቢዘግቡትም፣ ስለ ጦርነቱ ሁሉም የጠራ እውነታ የለውም።

ነገሮች በፍጥነት እየተቀያየሩ ነው። ጦርነቱ ወደ ጎረቤት አገራት ሊስፋፋ ይችላል የሚለው ስጋት አሁንም አንዳለ ነው።

የእስራኤል እና የፍልስጤማውያን ግጭት ገና ጨርሶ ትክክለኛ መልኩን አልያዘም። ስለ ጦርነቱ ግን ጥቂት ቢሆኑም ሁሉም ሊስማማበት የሚችል እውነታዎችን ተረድተናል።

1. እስራኤላውያን ወታደራዊ እርምጃውን ይደግፋሉ

በጋዛ ያለው የሐማስ ኃይል እንዲሰበር እስራኤላውያን መንግሥታቸው የሚያደርገውን ወታደራዊ ዘመቻ እንደሚደግፉ እርግጥ ነው።

ምናልባትም የእስራኤላውያን ቁጭት እና በስጭት የመጣው ሐማስ በድንገተኛ ጥቃት 1400 ወገኖቻቸውን ገድሎ ከ240 በላይ የሚሆኑትን አፍኖ በመውሰዱ ሊሆን ይችላል።

ኖአም ቲቦን ጡረተኛ የእስራኤል ጦር አባል ሲሆኑ፣ የሐማስ ጥቃትን በሰሙ ወቅት ልጃቸውን ለመታደግ ከባለቤታቸው ጋር በመሆን መኪናቸውን እያሸከረከሩ ከጋዛ ድንበር ለመድረስ ጊዜ አላባከኑም።

ተልዕኳቸው ልጃቸውን ከእነ ሦስት ቤተሰቡ መታደግ ነበር።

ኖአም ጡረተኛ የ62 ዓመት የዕድሜ ባለጸገ ቢሆኑም በዚያ የትርምስ ዕለት በአካባቢው የነበሩት የእስራኤል ወታደሮችን አስተባበረው እና መርተው ከሐማስ ወታደሮች ጋር ለመዋጋት እርጅና አልገደባቸውም።

የተገደለ የእስራኤል ወታደር መሳሪያ ታጥቀው የልጃቸውን ቤተሰብ እና ሌሎች በርካቶችን ከሐማስ መታደግ ችለዋል።

“ጋዛ ገና ብዙ ትደማለች . . . ጎረቤቱ ሕጻናት እና ሴቶችን እንዲያርድ የትኛወም አገር አይፈቅድም። ለጋዛ ምንም ምህረት አያስፈልግም።”

በእስራኤል ጥቃቶች እየሞቱ ስላሉ ሰላማዊ ሰዎች ምን እንደሚያስቡ ጡረኛው ወታደር ሲጠየቁም “አለመታደል ሆኖ እየሞቱ ነው። አስቸጋሪ በሆነ ቀጠና ውስጥ ነው የምንኖረው። በሕይወት ለመኖር መፍጨርጨር አለብን . . . ጠንካራ መሆን አለብን። ሌላ ምንም አማራጭ የለንም” ሲሉ መልሰዋል።

በርካታ እስራኤላውያን ከኖአም ጋር የሚመሳሰል አቋም የያዙ ይመስላል። ኖአም የሰላማዊ ፍልስጤማውያን ሞት አሳዛኝ ቢሆንም እየሞቱ ያሉት ግን በሐማስ እርምጃ ምክንያት ነው ባይ ናቸው።

በእስራኤል በተፈጸመ ጥቃት ድንጋጤ ውስጥ ያሉ የጋዛ ነዋሪዎች
የምስሉ መግለጫ,በእስራኤል በተፈጸመ ጥቃት ድንጋጤ ውስጥ ያሉ የጋዛ ነዋሪዎች

2. የማያባራ የጋዛ ዋይታ

ሌላው የማይካደው እውነት እየፈሰሰ ያለው ደም መብዛቱ ነው።

የእስራኤል ጥቃት በጋዛ የማያባራ ዋይታን ፈጥሯል። በጣም ብዙ ደም ፈሷል።

በሐማስ የሚተዳደረው ጤና ሚኒስቴር እስካሁን ድረስ ከ9ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል። ከእነዚህ መካከል ደግሞ 65 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች እና ሕጻናት ናቸው።

ከሟች ወንዶች መካከል ምን ያህሉ ሰላማዊ፣ ምን ያህሉ የሐማስ ወይም የእስላማዊ ጂሃድ ተዋጊዎች እንደሆኑ መገመት ከባድ ነው።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና እስራኤል በሐማስ የሚተዳደረው የጤና ሚኒስቴር የሚያወጣውን አሃዝ አያምኑትም። ይህ ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደም በነበሩ ግጭቶ ሟች ፍልስጤማውያንን በተመለከተ ሚኒስቴሩ ያወጣቸው አሃዞች በዓለም አቀፍ ተቋማት ትክክለኛነታቸው ሲረጋገጥ ቆይቷል።

በአሁኑ ወቅት በዓለማችን እየተካሄዱ ባሉት ሁለት ጦርነቶች የሟቾችን ቁጥር ስናነጻጸር በዚህ ጦርነት ውስጥ አስደንጋጭ እውነታን እንመለከታለን።

የተባበሩት መንግሥታት 21 ወራት ባስቆጠረው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 9 ሺህ 700 ነው ይላል። በጋዛ ግን ገና በ1 ወሩ የሟቾች ቁጥር ከ9ሺህ ተሻግሯል።

ኔታኒያሁ
የምስሉ መግለጫ,ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ

3. ኔታኒያሁ የገቡበት አጣብቂኝ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፍተኛ ጫና ውስጥ መሆናቸው ግልጽ ነው።

በእስራኤል ድንበር አካባቢ የሚኖሩ ማኅበረሰቦች ለጥቃት ተጋላጭ በመሆናቸው ኃላፊነት አልወሰዱም። የእስራኤል መከላከያ እና ሚሊሻ ኃላፊዎች ግን ለክፍተቱ ኃላፊነት ወስደዋል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ባለፈው እሑድ የደኅንነት ክፍሉን የሚወቅስ ትዊት ጽፈው ወቀሳ ደርሶባቸዋል። ኋላ ላይ ደግሞ ትዊቱን አጥፍተው ይቅርታ ጠይቀዋል።

ጆርናል ፎሬን አፌርስ ላይ የቀድሞ የእስራኤል የስለላ ተቋም ኃላፊ፣ የሰላም ተደራዳሪ እና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ነጋዴ አንድ ጽሑፍ አጋርተዋል።

በጽሑፋቸው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በጦርነቱ እንዲሁም ተከትሎ በመጣው ቀውስ እና ጦርነት ውስጥ ምንም ድርሻ እንደሌላቸው ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታማኝ ደጋፊዎች አሏቸው።

ቤተሰቦቹን ለማዳን እስከ ኪቡትዝ ናሀል ኦዝ ድረስ የታገለው ጡረታ የወጣው ኖአም ቲቦን በበኩሉ ቤንያሚን ኔታንያሁን የሚያነጻጽረው እአአ በ1940 ከሥልጣን እንዲወርዱ ተገደው በዊንስተን ቸርችል ከተተኩት ናቪል ቻምበርሊን ጋር ነው።

“በታሪክ ትልቅ ውድቀት ነው” ይላል፤ “ለእስራኤል በታሪክ ትልቅ ውድቀት ነው። ወታደራዊ ውድቀት ነው። የስለላ ውድቀት ነው። የመንግሥት ውድቀት ነው። ብቸኛው ተጠያቂ እሱ ነው። በእስራኤል ታሪክ ለታላቁ ውድቀት ተጠያቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ነው።”

ከጋዛ ድንበር አቅራቢያ በሐማስ ጥቃት የወደመ መኖሪያ ቤት
የምስሉ መግለጫ,ከጋዛ ድንበር አቅራቢያ በሐማስ ጥቃት የወደመ መኖሪያ ቤት

4. ታሪክ ተቀይሯል

ነገሮች እንደ ቀድሞው አይደሉም።

የፍልስጤም ንቅናቄ በእአአ 2005 ገደማ ከተገባደደ በኋላ ነው ለውጦች የታዩት።

ቤንያሚን ኔታንያሁ እስከ ወዲያኛው ይቀጥላሉ የሚለው በእስራኤል እና በፍልስጤም ዘንድ አንዳች ለውጥ አምጥቷል።

ፍልስጤማውያን ለእስራኤላውያን ስጋት መሆን አቁመዋል የሚል ምልከታም ነበር።

ለዘመናት የቆየው ፍጥጫ መፈታት የሚችል ችግር ተደርጎ ነበር የተወሰደው።

“ከፋፍሎ መግዛት” ለዚህ አንድ መንገድ ተደርጎም ነበር።

ቤንያሚን ኔታንያሁ ከ2009 (እአአ) ጀምሮ ሥልጣን ላይ ናቸው።

እስራኤል የሰላም አጋር የላትም ብለው ይከራከራሉ።

የፍልስጤም አስተዳደር ግን የሐማስ ተቀናቃኝ ሆኖ ተነስቷል።

የፍልስጤም አስተዳደር ዕድሜው እንደገፋ እና ፕሬዝዳንት መህሙድ አባስ ከሥልጣን መወገድ እንዳለባቸው የሚናገሩም አሉ።

በ1990ዎቹ ከእስራኤል ጎን የፍልስጤማውያን አገር መመሥረትን ተቀብሎም ነበር።

ቤንያሚን ኔታንያሁ “ከፋፍለህ ግዛ” የሚለው አካሄዳቸው ሐማስ በጋዛ ኃይሉን እንዲያጠናክር ማድረግ እና የፍልስጤምን አስተዳደር ችላ ማለትን ይጨምራል።

ቤንያሚን ኔታንያሁ ፍልስጤማውያን የራሳቸው አገር እንዲኖራቸው እንደማይፈልጉ ግን ይታወቃል።

ይህ ዌስት ባንክን እና ምሥራቅ ኢየሩሳሌምን መስጠት ይጠይቃል። እነዚህ ቦታዎች ደግሞ የአይሁዳውያን እንደሆኑ የእስራኤል ቀኝ ዘመሞች ያምናሉ።

በ2019 ሊኩድ የተሰኘው ፓርቲያቸው ውስጥ ባደረጉት ንግግር ፍልስጤም አገር መሆኗን የሚቃወሙ የፓርቲው አባላት የገንዘብ ምንጭ አማራጭ ማምጣት እንዳለባቸው መናገራቸውን አስታውቀዋል።

ለጋዛ ገንዘብ ፈሰስ የሚደረገው ከኳታር ነው።

በሐማስ እና በጋዛ መካከል ያለውን ትስስር ማጠንከር የፍልስጤም አስተዳደር ዌስት ባንክ ውስጥ ያለውን ትስስር ማጠንከር ፍልስጤም አገር እንዳትሆን እንደሚረዳ በንግግራቸው መጥቀሳቸውም ተገልጿል።

5. አፈሙዝ መፍትሄ አይሆንም

ጋዛ ውስጥ በተገደለ የእስራኤል ወታደር ቀብር ላይ የታደመች ሴት
የምስሉ መግለጫ,ጋዛ ውስጥ በተገደለ የእስራኤል ወታደር ቀብር ላይ የታደመች ሴት

በአሜሪካውያን እየተደገፈች እየተዋጋች ያለችው እስራኤል፤ ደመኛ ጠላቷ ሐማስ ሥልጣን ላይ እንዲቆይ የሚፈቅድ ስምምነት ውስጥ እንደማትገባ ግልጽ ነው።

ይህ አለ ማለት ደም መፋሰሱ ይባባሳል የማለት ያህል ነው – በእስራኤል በኩል።

ሐማስ ቢወገድ እንኳ እነርሱን ተከትሎ ጋዛን ማን ያስተዳድራል የሚለውም ሌላ ጥያቄ ነው። እስካሁንም ምላሽ አላገኘም።

ከዮርዳኖስ ወንዝ እስከ ሜዲትራኒያን ባሕር ያለውን መሬት በአረቦችን እና አይሁዳውያንን ለ100 ዓመታት ሲያዋጋ ቆይቷል።

ወታደራዊ መፍትሄ ይኖራል ተብሎ እንደማይታመንም ታሪክ ምስክር ነው።

በ1990ዎቹ የኦስሎ የሰላም ስምምነት ይህንን ግጭት ለመፍተት ያለመ ነበር። ፍልስጤም ከእስራኤል ጎን አገር ሆና ዋና መዲናዋ በምሥራቅ ኢየሩሳሌም እንዲሆን ነበር አላማው።

ድርድሩ ሲጀመር እና ሲቋረጥ ቆይቶ በባራክ ኦባማ ጊዜ በድጋሚ ተጀምሯል።

ከአሥር ዓመታት በፊት ይህም አልሳካ ብሎ ግጭት በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል።

ከእስራኤል ጎን የፍልስጥኤምን አገር መመሥረት ከተጨማሪ ደም መፋሰስ እንደሚያድን ፕሬዝዳንት ባይደን እና ሌሎችም ተናግረዋል።

አሁን በሁለቱም ወገን ያሉት መሪዎች ይህ እንዲሆን አያስችሉም።

በሁለቱም ወገን ያሉ አክራሪዎች ሐሳቡን አይቀበሉም። በ1990ዎቹ የሆነውም ይሄው ነው።

አንዳንዶች የፈጣሪን ፈቃድ እየፈጸሙ እንደሆነ ያምናሉ።

ከሃይማኖት ነጻ የሆነ አካሄድ ለመከተል ከባድ የሆነውም ለዚያ ነው።

ከዚህ ቀደም የነበሩ የተዛቡ አመለካከቶችን ነቅሎ ለመጣል እና ሁለቱ ወገኖችን ወደ አንድ ጠረጴዛ ለማምጣት የአሁኑ ጦርነት ያስከተለውን ድንጋጤን ፈጥሮ ካልሆነ ሌላ የሚመጣ ነገር ላይኖር ይችላል።

ግጭቱን ለማቆም በሁለቱም ወገኖች ስምምነት ያለው መፍትሄ ካልተገኘ ፍልስጤማውያን እና እስራኤላውያን ከትውልድ ትውልድ በጦርነት መዝለቃቸው አይቀርም።