እያወራን ያለነው ስለ ትምሕርት ሚኒስቴር ነው ! ብርሃኑ ነጋ በገዛ ፈቃዱ ስልጣን መልቀቅ አለበት ። አብይ በፋኖ ትግል መውደቁ አይቀርም።

ትውልድን መግደል፣ አድልዎና ፖለቲካዊ ሻጥር በትምሕርቱ ላይ እየተፈጸመ ነው። የፕሪቶሪያው ውል በጦርነት ስነ ልቦና የተጎዱ ተማሪዎች ልዩ ጥቅምን አካቶ የያዘ ከሆነ ይነገረን፤ አድልዎ ተደርጓል ብለው የቤተመንግስት ሰፈር ሰዎችም እንዳያስቡ ግልፅና ዝርዝር ማብራሪያ ይሰጣቸው። በትግራይ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 73.09% የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች እና 51.38% የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች በአጠቃላይ 66.96% ተማሪዎች 50% በላይ ውጤት በማምጣት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ማግኘታቸውን ተነግሯል።በአገር ደረጃ 3% የማይሞላ ተማሪ አልፏል ተብሎ በክልል ደረጃ ይህን ይህል አልፏል ሲባል የትምሕርት ሚኒስትሩ መክሸፋቸውን በደንብ እያሳየን ነው።
ከመቶ 69. ተማሪዎች ማለፋቸው ምንም ችግር የለውም፤ በጦርነት ለተጎዱ አከባቢዎች ቅድሚያ መሰጠቱም በፍፁም የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም ይባል ። በትግራይ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኃላም በደም አፋሳሹ ጦርነት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ርቀው መቆየታቸው የሚዘነጋ አይደለም። ትውልድ መግደሉና አድሎአዊ አሰራሩ ታሳቢ በማድረግ ከመነሻ እስከመድረሻው ስትገሰግስ ግን ጥያቄ የሚያስነሱ በርካታ ጉዳዮች አሉ። ፈተናው አገር አቀፍ እንጂ ክልል አቀፍ አይደለም። ትምሕርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ የት ሄደው ነው ?
የክልሉ ትምሕርት ቢሮ ሃላፊ ያውም በፌስቡክ ገፃቸው ይህን ጉዳይ ሊያውጁ የቻሉት ? ትምሕርት ሚኒስትሩ አልዋጥልህ ብሏቸው ነው መግለጫ ያልሰጡት ? ያው የተለመደው የአብይ ትዕዛዝ እንደተጠበቀ ሆኖ ማለት ነው። የትምሕርት ሚኒስቴር ስልጣን ምንድነው ? ቀድሞ የትምሕርት ቢሮው መናገሩ ለምን አስፈለገው ? ፈተናው በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል እንደተሰተው በትግራይስ እንዴት ነበር የተሰጠው ? በጦርነት ስነ ልቦና ውስጥ ያለፉ ተማሪዎች ምን ያህል ዝግጅት አድርገው ነው እንዲህ በገፍ ሊያልፉ የቻሉት ? በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር ዓቀፍ ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 69 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮን ጠቅሶ የዘገበው የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የትምሕርት ሚኒስቴርን አስተያየት አላካታተም። በሃገር አቀፍ ደረጃ በተሰጠ ፈተና የፌዴራሉ ትምሕርት ሚኒስቴር መግለጫ መስጠት ሲገባው የትምሕርት ቢሮው መግለጫ መስጠቱ ጥያቄ ያስነሳ ጉዳይ ነው። በምንስ አመክኞ ነው ካንድ ክልል ብቻ 69።9% ….. በሌሎች ክልሎች 1 % የማይሞላው ባለፈበት ሁኔታ ስትመዝነው ? የከሸፈው ሕወሓት ሳይሆን ብርሃኑ ነጋ ነው ! እንደ ሃገር ትውልድ እየተገደለ መድልዎ እየተፈፀመ ነው ። በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 69. 9% እንዲያልፉ የተደረገው ለነበረው ጦርነት ጉዳት ማካካሻ ተብሎ ከሆነ አማራ እና አፋር ክልሎችም በተመሳሳይ ይህ ማካካሻ ሊተገበር ይገባል። እያወራን ያለነው ስለ ትምሕርት ሚኒስቴር ነው ! ብርሃኑ ነጋ በገዛ ፈቃዱ ስልጣን መልቀቅ አለበት። አብይ በፋኖ ትግል መውደቁ አይቀርም። #MinilikSalsawi