ዝንቅ ጥቅምት 17 የባህላዊ መድኃኒት ለቀማ ቀን

በጋዜጣዉ ሪፓርተር

ቀን: November 5, 2023

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በየም ዞን ጥቅምት 17 ቀን ጎህ ሲቀድ ማኅበረሰቡ በነቂስ በመውጣት ለአንድ ዓመት የሚሆን ለሰውና ለእንስሳት መድኃኒትነት የሚያገለግል ባህላዊ መድኃኒት የሚለቅምበት ዕለት ነው፡፡ ባህላዊ መድኃኒቱ በቦር ተራራ የሚለቀም ሲሆን፣ የዕፅዋት ቅርፊት፣ ቅጠላ ቅጠሎች፣ ስራ ስሮች በብዛት ይለቀማሉ። የቦር ተራራ ተፈጥሮአዊና መልክዓ ምድራዊ አቀማመጡም እጅግ የሚስብ ነው፡፡ ዘንድሮም ሕፃናት፣ ወጣትና ሽማግሌዎች እንደ ወትሮው ሁሉ በኅብረ ዜማቸው በመታገዝ የባህላዊ መድኃኒት ለቀማቸውን አከናውነዋል፡፡ የዞኑ መንግሥትም ባህላዊ መድኃኒቶች ያላቸውን ጥቅም በመረዳት፣ ከቀደምት አባቶቻቸው ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የአገር በቀል ዕውቀት ለትውልድ ለማስተላለፍና ማኅበረሰቡንም በአንድ ማዕከል የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴርንና አጋር አካላትን በማስተባበር የባህላዊ መድኃኒት ቅመማና አገልግሎት መስጫ ማዕከል ገንብቶ ጥቅምት 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡

ጥቅምት 17 የባህላዊ መድኃኒት ለቀማ ቀን | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

(ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር)