November 5, 2023 

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ ሚኒሶታ ሀገረ ስብከት ተዘዋወሩ !

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰሜን አሜሪካ ወደሚገኘው የሚኒሶታ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ተዘዋውረው እንዲያገለግሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጥቅምት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ተፈርሞ የወጣ የብፁዕነታቸውን የዝውውር ደብዳቤ ተመልክቷል።

ለብፁዕነታቸው መልካም የአገልግሎት ጊዜን እንመኛለን።

ምንጭ = ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል