
ከ 9 ሰአት በፊት
አንድ ከፍተኛ የሃማስ መሪ ቡድናቸው በእስራኤል ሰላማዊ ሰዎች አልገደሉም አሉ።
ዒላማ የተደረጉት ወታደሮች ብቻ ናቸው ብለዋል።
ሙሳ አቡ ማርዙክ ለቢቢሲ እንደተናገሩት “የሐማስ ጥቃት ሴቶች፣ ህጻናት እና ሲቪሎች ላይ አላነጣጠረም” ብለዋል።
አስተያየታቸው የሐማስ ታጣቂዎች ሲቪል ወጣቶች እና ህጻናት ላይ ሲተኩሱ ከሚያሳየው የቪዲዮ ማስረጃ ጋር በእጅጉ የሚቃረን ነው።
መስከረም 26 በደረሰው ጥቃት ከ1 ሺህ 400 በላይ ሰዎች መገደላቸው እና አብዛኛዎቹ ሰላማዊ ሰዎች መሆናቸውን እስራኤል አስታውቃለች።
በዩናይትድ ኪንግደም በፀረ-ሽብርተኝነት ህጎች ንብረታቸው ላይ እገዳ የተጣለባቸውና የቡድኑ ምክትል የፖለቲካ መሪ የሆኑት ማርዙክ ቅዳሜ ዕለት ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ከመስከረም 26ቱ ጥቃት በኋላ ለቢቢሲ ቃላቸውን የሰጡ ከፍተኛው የቡድኑ አባል ናቸው።
ማርዙክን በጋዛ ላይ እየተካሄደ ስላለው ጦርነት በተለይም በግዛቱ ውስጥ ስለተያዙት ብዛት ያላቸው ታጋቾች አጽንዖት በመስጠት ጥያቄዎች ከቢቢሲ ቀርቦላቸው ነበር።
እስራኤል ጋዛን በቦምብ እየደበደበች ባለችበት ወቅት ታጋቾችን ነፃ መውጣት አይቻልም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። በሐማስ የሚመራው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እስራኤል ባለፈው ወር አጠናክራ በቀጠለችው የማያባራ ጥቃት ከ10 ሺህ ሰዎች ተገድለዋል ብሏል።
“እኛ እንፈታቸዋለን። ግን ውጊያው መቆም አለበት” ብሏል።
- በሶማሌ ክልል ጎርፍ 24 ሰዎችን ሲገድል፣ 23 ሺህ አባወራዎችን አፈናቀለ7 ህዳር 2023
- ደቡብ አፍሪካ ሁሉንም ዲፕሎማቶቿን ከእስራኤል ጠራች7 ህዳር 2023
- ቱርክን ወደ ኦቶማን ዘመን ዝናዋ ለመመለስ የሚጥሩት ኤርዶዋን ምን እያደረጉ ነው?7 ህዳር 2023
ማርዙክ በሐማስ የታገቱ ስምንት የሩሲያ-እስራኤል ጥምር ዜግነት ያላቸውን በተመለከተ ለመወያየት በቅርቡ ወደ ሞስኮ ተጉዘው ነበር።
በጋዛ የሚገኙ የሐማስ አባላት ከሩሲያ የመጡ ሁለት ሴት ታጋቾችን ቢያገኙም በግጭቱ ምክንያት መልቀቅ እንዳልቻሉ ተናግረዋል።
ታጋቾችን መፍታት የሚችሉት “እስራኤላውያን ጦርነቱን አቁማ ለቀይ መስቀል አሳልፈን መስጠት ከቻልን ነው” ብሏል።
ስለመስከረም 26ቱ ጥቃት ከቢቢሲ ጥያቄዎች የቀረቡላቸው ማርዙክ፤ የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ የሆነው የአል ቃሳም ብርጌድስ መሪ የሆነው ሞሐመድ ኤል-ዲፍ አባላቱ ሰላማዊ ዜጎች እንዳይነኩ ማዘዙን ተናግሯል ።
“ኤል-ዲፍ ለታጋዮቹ ‘ሴትን አትግደሉ፣ ህጻናትን አትግደሉ እና በዕድሜ የገፉትን አትግደሉ” በማለት በግልጽ ተናግረዋል።
ሆኖም የተጠባባቂ ወታደሮች “ዒላማ ተደርገዋል” ብሏል። የተገደሉት “ከጦሩ ጋር የሚሠሩ … ወይም ወታደሮች” ብቻ ዒላማ እንደሆኑ ተናግረዋል።
ሴቶች፣ ህጻናት እና ሲቪሎች “መተዋቸውን” ተናግሯል።
ከሐማስ ተዋጊዎች ካሜራ የተገኙ ቪዲዮዎችን መሠረት በማድረግ መሳሪያ ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች በመኪናቸው ውስጥ እና በቤታቸው በጥይት ስለመገደላቸው ቢቢሲ የሐማስን ከፍተኛ ኃላፊ አበክሮ ጠይቋል።
በቃለ መጠይቁ ወቅት አንዳንድ ጊዜ ወደ ብስጭት ቢያመሩም ማርዙክ ምላሻቸው የተጠና ሲሆን ለጥያቄውም በቀጥታ ምላሽ አልሰጡም።
የሐማስ የፖለቲካ ክንፍ ለጥቃቱ ነበረውን ዝግጁነት ያውቅ እንደሆነ ለቀረበለት ጥያቄ ምክትል መሪው “ወታደራዊው ክንፍ ከፖለቲካ አመራሩ ጋር መመካከር የለበትም፣ አያስፈልገውም” ብሏል።
በኳታር የሚገኘው የፖለቲካው ክንፍ ብዙ ጊዜ በጋዛ ከሚገኘው ወታደራዊው ክንፍ የራቀ እንደሆነ አድርጎ ይገልጻል።
የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት በሁለቱ መካከል ምንም አይት ልዩነት ሳያስቀምጥ በ 2021 የሐማስን የፖለቲካ ክንፍ እንደ አሸባሪ ድርጅት ፈርጇል። “ሐማስ የተለያዩ ክፍሎች እንዳሉት አድርጎ ማቅረብ የማይመስል ነው። ሐማስ ውስብስብ ቢሆንም አንድ አሸባሪ ድርጅት ነው” ሲል ገልጾታል።
ማርዙክ በአሜሪካ ግምጃ ቤት በልዩ ሁኔታ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሸባሪ ተብለው ተፈርጇል። የሐማስን እንቅስቃሴዎች በማስተባበር እና በገንዘብ በመደገፍም ክስ ተመስርቶበታል።
የእገታው ቀውስ
ወደ ጋዛ እርዳታ እንዲገባ እና ሐማስ ከወሰደባቸው 240 ታጋቾች መካከል ጥቂቶቹን ለማውጣት በጋዛ “ሰብዓዊ ተኩስ አቁም” እንዲደርስ አሜሪካን ያቀረበችውን ጥያቄ እስራኤል ውድቅ ካደረገች በኋላ ነው ቃለ መጠይቁ የተደረገው ።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የትኛውም ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ከመድረሱ በፊት ታጋቾች መፈታት አለባቸው ብለዋል።
ማርዙክ “እንግዶች” በማለት የጠራቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ሐማስ አለመያዙን ወይም ብዙዎች የት እንዳሉ እንደማያውቅ ተናግረዋል። ለዚህ ምክንያት ያሉት ታጋቾቹ “በተለያዩ አንጃዎች” በመያዛቸው ነው።
የፍልስጤም እስላማዊ ጂሃድን ጨምሮ በጋዛ ውስጥ ከሐማስ ጋር በቅርበት የሚሠሩ ነገር ግን ራሳቸውን የቻሉ በርካታ ቡድኖች አሉ።
መረጃውን ለማጠናቀር የተኩስ አቁም ያስፈልግ ነበር በማለት ጠቅሰው ጋዛ በቦምብ ድብደባ ውስጥ ባለችበት በዚህ ሰዓት ሌሎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች እንዳሉ ተናግረዋል።
ከእስራኤል ጋር ያለው ግጭት ሁኔታ ላይ ማርዙክ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን በታጋቾቹ ዙሪያ በሚደረገው ድርድርም ቀዳሚ ተሳታፊ ሊሆኑ ይችላል።