
ከ 2 ሰአት በፊት
በዩክሬን ለልደት ስጦታ ተብሎ የተበረከተ የእጅ ቦምብ ፈንድቶ የአገሪቱ ጦር አዛዥ የቅርብ አማካሪ የሆኑ ግለሰብን ገደለ።
የ39 ዓመቱ ሻለቃ ሄናዲይ ቻስታይኮቭ ከልደት በዓል ድግስ መልስ ከጓደኞቹ የተበረከቱለትን ስጦታዎች እየከፈተ ሳለ ነበር ፍንዳታው ያጋጠመው።
በፍንዳታው ሻለቃ ሄናዲይ ሕይወቱ ሲያልፍ የ13 ዓመት ልጁ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል ተብሏል።
የዩክሬን የአገር ውስጥ ሚኒስትር ኢሆር ክላይሜንኮ ታዳጊው የቦምቡን ቀለበት ሲነካካ የዩክሬን ጦር አባሉ ከልጁ ተቀብሎ ቀለበቱን መሳቡ ለፍንዳታው ምክንያት ሆኗል ብለዋል።
የጦር አባሉ ሞት በዩክሬን ፖለቲከኞች ዘንድ መነጋገሪያ ሲሆን፣ ማርያና ቤዙላህ የተባሉ የምክር ቤት አባል የሻለቃው ሞት የተከሰተው በቸልተኝነት ነው ካሉ በኋላ፤ “ቻስታይኮቭ ቸልተኛ በመሆኑ በራሱ የልደት በዓል ላይ ይሞታል ብዬ አስቤ አላውቅም። . . . የእጅ ቦምቦች በስጦታ የሚበረከቱ አይደሉም” ሲሉ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ፍንዳታው ያጋጠመው በቸልተኝነት ሳይሆን የጦር አባሉን ለመግደል በታቀደ ሴራ ነው የሚሉም አልጠፉም።
- በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት ቀናት ከባድ ውጊያዎች መካሄዳቸውን ነዋሪዎች ተናገሩከ 2 ሰአት በፊት
- የትግራይ ክልል የ12ተኛ ክፍል ውጤት ከአገር አቀፉ ውጤት ለምን የተለየ ሊሆን ቻለ?ከ 7 ሰአት በፊት
- በሶማሌ ክልል ጎርፍ 24 ሰዎችን ሲገድል፣ 23 ሺህ አባወራዎችን አፈናቀለ7 ህዳር 2023
የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትሩ ኢሆር ክላይሜንኮ ግን “እጅግ አሳዛኝ” ያሉት ክስተትን የተመለከተ ሙሉ ምርመራ ይደረጋል ያሉ ሲሆን፣ የምርመራ ውጤቱ ይፋ እስኪሆን ድረስ ሰዎች መላ ምቶችን ከመሰንዘር እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
ፖሊስ ከዩክሬን ዋና ከተማ ኪዬቭ በቅርብ ርቀት ባለችው ከተማ ፍንዳታው የደረሰበት ምክንያት “ተቀጣጣይ ነገርን በአግባቡ ባለመያዝ ነው” ብሏል።
ፖሊስ ፍንዳታው ካጋጠመበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ሌሎች አምስት ቦምቦችን ያገኘ ሲሆን፣ እነዚህ የእጅ ቦምቦች በተመሳሳይ በስጦት መልክ የተበረከቱ ናቸው ተብሏል።
ለጦር ሠራዊቱ አባል ሞት ምክንያት የሆነው ቦምብ በስጦት መልክ ከሰጠው እና በስም ካልተጠቀውስ ኮሌኔል መኖሪያ ቤት እንዲሁ ፖሊስ ብርበራ አድርጎ ሁለት ቦምቦችን አግኝቷል።
የአገሪቱ ጦር አዛዥ ጄኔራል ቫሌሪ ዛሉዘሃኝ የአማካሪያቸውን ሞት ሲሰሙ እጅጉን ማዘናቸውን ገልጸው፤ አማካሪያቸው ሩሲያ በአገራቸው ላይ መጠነ ሰፊ ወረራ ከከፈተች ጊዜ አንስቶ ትልቅ አበርክቶ ማድረጉን ገልጸዋል።
