
ብልጽግና የአለም አቀፍ ማጅራት መቺዎች ስብስብ ነው የምንለው ወደን አይደለም፤ የአብይ ሚኒስትሮች ጠባቂዎቻቸውን እየላኩ ታላላቅ ዲፕሎማቶችን በማስደብደብ እና በመዝረፍ ስራ ላይ ተሰማርተዋል። ይህ መንግስታዊ ሽብር ነው። ካሁን ቀደም የነበሩ መንግስታት የገነቡትን የሃገር መልካም ገፅታ እነ አብይ አበላሽተውታል። የውሸታሞች፣ የግፈኞችና የሌቦች ስብስብ የሆነው ብልፅግና በሃገሪቱ ለውጥ ከማምጣት ይልቅ ስርዐት አልበኝነትን አስፍኗል።
ቪዲዮ https://www.facebook.com/RealMinilikSalsawi/videos/179922058517011

በኢትዮጵያ ሰላም መጥፋት እና የሕግ የባላይነት እንዳይኖር ከፍተኛው እንቅፋት እየሆኑ ያሉት የብልጽግና ባለስልጣናት መሆናቸው በተደጋጋሚ እያየን ነው። በሃገር ውስጥ በዜጎች ላይ ከሚፈፅሙት ወንጀል አልበቃ ያላቸው አለም አቀፍ ማጅራት መችነታቸውን በተግባር አሳይተዋል።
የአለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር የሆኑትን ዲፕሎማት የአሕመድ ሸዴ ጠባቂዎች እንደደበደባቸውና ይህን ተከትሎ የአፍሪካ ልማት ባንክ ሰራተኞቼ የደሕንነት ስጋት አለባቸው ብሎ ድርጅቱን እንደዘጋ ባለፉት ሁለት ቀናት ከሰማናቸው መረጃዎች እና ከባንኩ ቢረጋገጥም አሁንም የአብይ አሕመድ መንግስት በይፋ ጥፋቱን አምኖ ይቅርታ መጠየቅ ሲገባው ለማድበስበስ የሚሄድበት መንገድ አሳፋሪ መሆኑን የባንኩ ሰዎች ይናገራሉ።
ኢትዮጵያ በአለም መድረክ እያዋረዱ የሚገኙት የአብይ ባለስልጣናት ሃገሪቷን እና ዜጎቿን በጦርነት መግደላቸው ሳያንሳቸው አለም አቀፍ ወንጀል መፈፀማቸው ለአፍሪካ የነፃነት ቀንዲል የሆነችዋን አገራችንን በአለም አደብባባይ አዋርደዋታል። የሕግ የበላይነት አለመኖሩ ሕዝቡ ሰላሙን እንዲያጣ አብይና ባለስልጣናቱ በሕዝብ ላይ እንዲቀልዱ ሆኗል ፋኖ አዲስ አበባ ደርሶ እስኪገላግለን። #Minilik
