- ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጦርነቱ ካበቃ በኋላ በጋዛ ሰርጥ ላይ አጠቃላይ የፀጥታ ኃላፊነቱ ላልተወሰነ ጊዜ የእስራኤል እንደሚሆን ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ከአሜሪካው ኤቢሲ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው።5 ህዳር 2023
ቀጥታ
ኔታንያሁ ከጦርነቱ በኋላ የጋዛ ሰርጥ ‘የፀጥታ ኃላፊነት’ የእስራኤል ይሆናል አሉ
Related Video and Audio

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59
Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ
- BBC
Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች
- BBC
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች
- BBC
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC
ጭምቅ ሃሳብ
- ኔታንያሁ ከጦርነቱ በኋላ የጋዛ ሰርጥ ‘የጸጥታ ኃላፊነት’ የእስራኤል ይሆናል አሉ
- ሐማስ በእስራኤሉ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎችን አልገደልኩም አለ
- ጋዛ ወደ ህጻናት የመቃብር ስፍራነት እየተቀየረች ነው- ተመድ
- ከ4 ሳምንታት የእስራኤል-ጋዛ ጦርነት በኋላ በግልጽ የሚታዩ 5 እውነታዎች
- ብሊንከን እና የፍልስጤሙ ፕሬዚዳንት በዌስት ባንክ ተገናኙ
- በተለያዩ አገራት ለፍልስጤም የሚደረገው የአጋርነት ሰልፍ እንደቀጠለ ነው
- አሜሪካ በጋዛ ሰማይ ድሮን ለቅኝት መላኳን አመነች
- ዶክተር፣ ልብስ ሰፊ፣ ጨቅላ ሕጻን…- በእስራኤል የአየር ጥቃት ከተገደሉት መካከል የጥቂቶቹ አሳዛኝ ታሪክ
- ብሊንከን የጋዛ የተኩስ አቁም ጥሪን ውድቅ አደረጉ
- እስራኤል በአል- ማጋዚ የስደተኞች መጠለያ በፈጸመችው የአየር ጥቃት በርካቶች ተገድለዋል ተባለ
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 10:0310:03አል-ሲሲ ከሲአይኤ ኃላፊ ጋር በካይሮ ተወያዩየግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል-ሲሲ ከአሜሪካው የስለላ ተቋም ሲአይኤ ኃላፊ ዊሊያም በርንስ ጋር ተገናኝተው በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ።ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ ከሲአይኤው ኃላፊ ጋር በተገናኙ ወቅት በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።ሁለቱ ባለሥልጣናት ትኩረታቸውን እስራኤል በጋዛ ሰርጥ አጠናክራ ስለቀጠለችው ወደታደራዊ ዘመቻ ላይ ያድርጉ እንጂ ዓለም አቀፍ እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ወይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።የፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ አል-ሲሲ ሰላማዊ ሰዎች ለመጠበቅ እና የሰብዓዊ እርዳታ ሥርጭትን ለማስተባበር የተኩስ አቁም ማድረግ እጅግ ቁልፍ መሆኑን አጽንኦት መስጠታቸውን ገልጸዋል።የሲአይኤው ኃላፊ በርንስ በመካከለኛው ምሥራቅ ጉብኝት እያደጉ ሲሆን፣ በጉዟቸው ከደኅንነት ተቋማት ኃላፊዎች እና መሪዎች ጋር ይገናኛሉ ተብሏል።በርንስ ሰኞ ዕለት እስራኤል እንደነበሩ ተዘግቧል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 7:367:36ፍልስጤማዊው ጋዜጠኛ ከ42 የቤተሰቡ አባላት ጋር ተገደለ
WafaCopyright: Wafaሞሐመድ አቡ ሐሲርImage caption: ሞሐመድ አቡ ሐሲርፍልስጤማዊው ጋዜጠኛ ሞሐመድ አቡ ሐሲር ከ42 የቤተሰቡ አባላት ጋር መገደሉን የሚሠራበት ተቋም አስታወቀ።የፍልስጤም ዜና ወኪል የሆነው ዋፋ ጋዜጠኛው ከቤሰብ አባላቱ ጋር የተገደለው የእስራኤል የአየር ኃይል መኖሪያ ቤቱን በመምታቱ ነው።ከሟች የቤተሰብ አባላት መካከል የጋዜጠኛው ልጆች እና ወንድሞች እንደሚገኙበት የዜና ወኪሉ ጨምሮ አስታውቋል።ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒጄ እንደሚለው ከሆነ ሐማስ በእስራኤል ላይ መስከረም 26̀/2016 ዓ.ም. ድንገተኛ ጥቃት ከፈጸመ በኋላ በጋዛ እና እስራኤል 36 ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች ተገድለዋል ብሏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 7:357:35የእስራኤል ጦር የሐማስን ጠንካራ ይዞታ ተቆጣጠርኩ አለ
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤል ጦር ዛሬ ማክሰኞ ረፋድ ላይ ባወጣው መግለጫ በጋዛ ሰርጥ የሐማስ ጠንካራ ይዞታን መቆጣጠሩን አስታወቀ።በመግለጫው ጦሩ በሰሜናዊ ጋዛ የሐማስን ጠንካራ ይዞታ ከተቆጣጠረ በኋላ ፀረ ታንክ ሚሳኤሎችን፣ ላውንቸሮችን፣ መሳሪያዎችን እና መረጃ ለመሰብሰብ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን መያዙን ይፋ አድርጓል።የእስራኤል ባሕር ኃይልም የቴክኖሎጂ ውጤት የሚገኙባቸው የሐማስ ወታደራዊ የመመልከቻ ቦታዎችን ስለመምታቱም ተገልጿል።ጦሩ ሐማስ ያከማቻቸው ተቀጣጣይ ነገሮች ፍንዳታ ፈጥረዋል ያለ ሲሆን፣ ይህም ቡድኑ በሰላማዊ ሰዎች መኖሪያ አካባቢ መሳሪያ እንደሚያከማች ማሳያ ነው ብሏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:344:34እስራኤል ከወር በፊት በሐማስ ጥቃት የተገደሉትን ሻማ በማብራት አሰበች
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል ከአንድ ወር በፊት በሐማስ ጥቃት የተገደሉትን 1 ሺህ 400 በተለያዩ ዝግጅቶች አሰበች። በጥንታዊቷ ኢየሩሳሌም ከተማም በርካቶች ሻማ በማብራት አስበዋቸዋል።በርካቶች አንድ ሺህ 400 ሻማዎችን በማብራት እና 240 የሚሆኑትን ታጋቾች ፎቶ በግንቡ ላይ በፕሮጀክተር እንዲታይ ተደርጓል።በሌላ ስፍራም በጥቃቱ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ሰዎች ባዘጋጁት ዝግጅትም ጥቁር ሸሚዝ ለብሰው ብሔራዊ መዝሙር ዘምረዋል።በትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሰቲዎች የመታሰቢያ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው። በጋዛ ታግተው የሚገኙ 240 የሚጠጉ ቤተሰቦቻቸውም እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።
Getty ImagesCopyright: Getty ImagesArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:114:11በጋዛ የሚገኙ የተመድ መጠለያዎች በመጨናነቃቸው ተፈናቃዮችን መቀበል ተስኗቸዋል ተባለ
EPA-EFE/REX/ShutterstockCopyright: EPA-EFE/REX/Shutterstockበጋዛ የሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መጠለያዎች በከፋ ሁኔታዎች በመጨናነቃቸው ተፈናቃዮችን መቀበል እንደተሳናቸው ተገለጸ። በርካታ ተፈናቃዮችም በተቋሙ አቅራቢያ በሚገኙ ጎዳናዎች ለመተኛት መገደዳቸውንም አስታውቋል።እስራኤል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰሜን ጋዛውያን አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ መስጠቷን ተከትሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ወደ ደቡብ ጋዛ ሸሽተዋል።”የኛ መጠለያዎች በሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተጨናንቀዋል” የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ለቢቢሲ ተናግረዋል።የተባበሩት መንግሥታት ትምህርት ቤቶች ወደ መጠለያዎች የተቀየሩ ሲሆን መያዝ ከሚችሉት በላይ በአራት እጥፍ እንደያዙም ጁሊየት ቱማ ተናግረዋል።ከሰሜን ጋዛ ከተፈናቀሉት 1.5 ሚሊዮን መካከል 717 ፍልስጤማውያን በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ ብሏል።የተባበሩት መንግሥታት መጠለያዎች ክፉኛ ተጨናንቀዋል። በደቡብ ጋዛ የሚገኙትም ጣቢያዎች አዳዲስ ተፈናቃዮች መቀበል አቁመዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:363:36እስራኤል በጋዛዎቹ ኻን ዩኒስ እና ራፋህ ባደረሰቻቸው ጥቃቶች በርካቶች ተገደሉእስራኤል በደቡብ ጋዛዎቹ ኻን ዩኒስ እና ራፋህ ባደረሰቻቸው የአየር ጥቃቶች በርካቶች መገደላቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።በሁለቱ የተለያዩ ጥቃቶች 23 ሰዎች መገደላቸውን በሐማስ አስተዳደር ስር ያለውን የጋዛ ጤና ሚኒስትርን ዋቢ አድርጓል ኤኤፍፒ የእስራኤል መከላከያ ጥቃቶቹን በተመለከተ ያለው ነገር የለም።ከጥቃቶቹ ያገኘናቸው ምስሎች፦
ReutersCopyright: Reuters
ReutersCopyright: Reuters
ReutersCopyright: ReutersArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:442:44በኢራቅ እና በሶሪያ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች 38 ጊዜ ተመትተዋል- ፔንታገን
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበኢራቅ እና በሶሪያ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ከጥቅምት 6/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ 38 ጊዜ መመታታቸውን ፔንታገን አስታወቀ።አብዛኛዎቹ ጥቃቶች በሮኬቶች እና በድሮኖች እንደተፈጸሙ እና አድራሾቹም ከኢራን ጋር ግንኙነት ባላቸው ቡድኖች ነው ተብሎ እንደሚታመን የፔንታገን ቃለ አቀባይ ብሪክ ጄነራል ፓት ራይደር ተናግረዋል።ኢራን የጋዛን አስተዳዳሪ ሐማስ እና የሊባኖሱን ታጣቂ ቡድን ሔዝቦላህን ትደግፋለች። በነዚህ ጥቃቶች 24 አሰቃቂ የአዕምሮ ጉዳቶችን ጨምሮ ቢያንስ 45 የአሜሪካ ሰራተኞች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።ቃለ አቀባዩ አሜሪካ በአሁኑ ወቅት በመካከለኛው ምስራቅ አራት ዋና አላማዎች አሏት ሲሉም ተናግረዋል።እነዚህም “በቀጣናው ውስጥ ያሉ የአሜሪካ ኃይል አባላትን መጠበቅ፣ እስራኤል ከሐማስ ጋር ለምታደርገው ውጊያ ወሳኝ የደህንንት እርዳታ መስጠት፣ ታጋቾች እንዲለቀቁ ለእስራኤል አርዳታ መለገስ እንዲሁም ቀውሱ ከጋዛ አልፎ እንዳይዘመት ለመከላከል በአካባቢው ያለውን የኃይል ዝግጁነት ማጠናከር ነው” ብለዋልArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:541:54በጋዛ- እስራኤል የተከሰቱ የቅርብ ጉዳዮች
AFPCopyright: AFPየእስራኤል የማያባራ ጥቃቶች የቀጠሉባት ጋዛ ወደ ህጻናት የመቃብር ስፍራነት እየተቀየረች ነው ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አሳስበዋል።ወር ባስቆጠረው የጋዛ- እስራኤል ቀውስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ተፈናቅለዋል የከተማ ህንጻዎች ወደ አመድነት ተቀይረዋል።በቅርብ የተከሰቱ ጉዳዮችን እንዳስ፦
- ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጦርነቱ ካበቃ በኋላ በጋዛ ሰርጥ ላይ አጠቃላይ የጸጥታ ኃላፊነቱ ላልተወሰነ ጊዜ የእስራኤል እንደሚሆን ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ከአሜሪካው ኤቢሲ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው።
- በተጨማሪም መስከረም 26 ከ1 ሺህ 400 በላይ ሰዎች በተገደሉበት የሐማስ ጥቃት የተወሰዱ ከ200 በላይ ታጋቾች ሳይፈቱ የተኩስ አቁም ጥሪ መደረጉንም ውድቅ አድርገዋል። ሆኖም ለሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ ወይም ታቀቾች እንዲለቀቁ ለማድረግ “በጊዜያዊነት ሊገታ” እንደሚችልም ፍንጭ ሰጥተዋል።
- የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጋዛ ያለውን ሁኔታ “የሰብዓዊነት ቀውስ” ሲሉ የጠሩት ሲሆን በማያባራ የእስራኤል ጥቃት ውስጥ ያለችውንም ጋዛ ወደ “ህጻናት የመቃብር ስፍራነት” እየተቀየረች ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
- እስራኤል እየፈጸመቻቸው ባለቻቸው ጥቃቶች ከ4 ሺህ 100 በላይ ህጻናትን ጨምሮ ከ10 ሺህ በላይ ህጻናት መገደላቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ባለፉት ቀናት ጥቃቶቹ ክፉኛ ተጠናክረው ቀጥለዋል ተብሏል።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 1:231:23ሐማስ በእስራኤሉ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎችን አልገደልኩም አለአንድ ከፍተኛ የሃማስ መሪ ቡድናቸው በእስራኤል ሰላማዊ ሰዎች አልገደሉም አሉ። ዒላማ የተደረጉት ወታደሮች ብቻ ናቸው ብለዋል። ሙሳ አቡ ማርዙክ ለቢቢሲ እንደተናገሩት “የሐማስ ጥቃት ሴቶች፣ ህጻናት እና ሲቪሎች ላይ አላነጣጠረም” ብለዋል። አስተያየታቸው የሐማስ ታጣቂዎች ሲቪል ወጣቶች እና ህጻናት ላይ ሲተኩሱ ከሚያሳየው የቪዲዮ ማስረጃ ጋር በእጅጉ የሚቃረን ነው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 23:51 6 ህዳር 202323:51 6 ህዳር 2023ጋዛ ወደ ህጻናት የመቃብር ስፍራነት እየተቀየረች ነው- ተመድ
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤል የማያባራ ጥቃቶች የቀጠሉባት ጋዛ ወደ ህጻናት የመቃብር ስፍራነት እየተቀየረች ነው ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አሳሰቡ።ዋና ጸሐፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጋዛ ሰርጥ ያለው ሁኔታ “ከሰብዓዊ ቀውስነት” አልፏል ሲሉም አስጠንቅቀዋል።”በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታዳጊ ሴቶች እና ወንዶች እየተገደሉ ነው እንዲሁም እየቆሰሉ መሆናቸው ሪፖርት እየተደረገ ነው” ሲሉም ነው ዋና ጸሐፊው የተናገሩት።የጋዛው ጦርነት “ዓለምን እያናወጠ” እና “የብዙኃን ንጹሓንን ህይወት እየቀጠፈ ነው” ሲሉም አክለዋል።እስራኤል እየፈጸመችው ባለው ጥቃት እስካሁን ከ10 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን የተገደሉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ከ4 ሺህ በላይ ህጻናት መሆናቸውን ከጋዛ ጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያስረዳል።አንድ ወር ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እንዲያከትምም የተኩስ አቁም ይደረግ ሲሉም በድጋሜ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።የተመዱ ዋና ጸሐፊ በዚሁ ንግግራቸው ሐማስ መስከረም 26 “በእስራኤል ሰላማዊ ዜጎች” ላይ ያደረሰውን “የሽብር ጥቃት” ኮንነዋል። “ሰላማዊ ሰዎችን ለመግደልም ሆነ ለማሰቃየት ምንም ምክንያት ሊቀርብበት አይገባም” ሲሉም ነው የተናገሩትArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 23:46 6 ህዳር 202323:46 6 ህዳር 2023ደቡብ አፍሪካ ሁሉንም ዲፕሎማቶቿን ከእስራኤል ጠራችደቡብ አፍሪካ ሁሉም ዲፕሎማቶቿ ከቴል አቪቭ እንዲወጡ አዘዘች። ደቡብ አፍሪካ ይህን እርምጃ የወሰደችው እስራኤል በጋዛ ላይ መጠነ ሰፊ የአየር ድብደባ ማድረሷን ተከትሎ ነው። በተለይ እስራኤል ከትናንት በስቲያ እሑድ በጋዛ ላይ ያዘነበችው ቦምብ ጦርነቱ ከተጀመረ ከአንድ ወር ወዲህ ከፍተኛው ነው ተብሏል። የጋዛ አልሺፋ ሆስፒታል እንዳስታወቀው ወደ 200 ሰዎች በዚህ ጥቃት ተገድለዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:32 6 ህዳር 20238:32 6 ህዳር 2023በጋዛ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ10ሺህ አለፈ
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል ጋዛ ላይ እየፈጸመችው ያለው ጥቃት በቀጠለበት ሁኔታ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ10 ሺህ ማለፉን በጋዛ ያለው የሐማስ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።የሐማስን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ላይ ቀን ከሌት ጥቃት ማካሄድ ከጀመረች ዛሬ አንድ ወር የደፈነ ሲሆን እስካሁን 10,022 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል::ትላንት እሁድ ምሽት እስራኤል ከፍተኛ ጥቃት በጋዛ ከፈጸመች በኋላ ነው የተገደሉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ ይፋ የተደረገው።እስራኤል የሐማስ ወታደራዊ ቅጥር ጊቢን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዒላማዎች መምታቷን ገልጻለች።በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ዳይሬክተር ለቢቢሲ እንደገለጹት በቅርቡ ወደ 200 ሰዎች ናቸው የተገደሉት።የተባበሩት መንግሥታት ሰብአዊ ተቋማትና እርዳታ ሰጭዎች በጋዛ በንጹኃን ዜጎች የደረሰውን “አሰቃቂ ግድያ” ሲሉ ገልጸዋል።ከሞቱት መካከል በሺዎች የሚቆጠሩት ሕጻናት ናቸው።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ውስን ፖለቲከኞች የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ያወጣው የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ላይ ጥያቄ አንስተዋል።የዓለም ጤና ድርጅት ስለቁጥሩ ተጠይቆ እንደገለጸው ከሆነ ግን የተጠቀሰው የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ተአማኒነት ያለው ነው።እስራኤል በጋዛ ላይ ጥቃት የሰነዘረችው በሐማስ ጥቃት 1,400 ሰዎች በእስራኤል ከተገደሉና ከ240 በላይ ሰዎች ከታገቱ በኋላ ነው።
Getty ImagesCopyright: Getty ImagesArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:11 6 ህዳር 20238:11 6 ህዳር 2023ብሊንከን ከመካከለኛው ምሥራቅ ጉብኝት በኋላ ምን አሉ?
ReutersCopyright: Reutersየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን የመካከለኛው ምሥራቅ ጎብኝታቸውን አጠናቀው ከቱርክ ወጥተዋል።በቀጠናው ስላለው ሁኔታ ያደረጉት ውይይት በሦስት ነጥቦች ላይ ያጠነጠነ እንደሆነ ተናገረዋል።እነዚህም እንዴት ሰብአዊ እርዳታ ማስፋፋት ይቻላል፣ እንዴት ግጭቱ እንዳይሰፋ ማድረግ ይቻላል እና ለእስራኤላውያን እና ፍልስጥኤማውያን ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም እንዲመጣ ምን ማድረግ ይቻላል የሚሉት ናቸው ተብሏል።ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሐካን ፊደን ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ቀጣዮቹን ነጥቦች ብሊንከን አንስተዋል።• እርዳታ- አሜሪካ ተጨማሪ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ “በከፍተኛ ሁኔታ” እና “በተጨባጭ መንገድ” እየሠራች ነው ብለዋል።እርዳታ ለመጨመር ተስፋ ሰጭ ሥራዎች እንደተሠሩና “በቀጣይ ቀናት” ለውጥ እንደሚኖር ተናግረዋል። በጋዛ ፍልስጥኤማውያን የደረሰባቸውን “አስከፊ ጫና” አሜሪካ እንደምትረዳ ገልጸዋል።• ታጋቾች- በሐማስ የታገቱ ሰዎችን “በሰላም ወደ ቤታቸው ለመመለስ” እየሠሩ እንደሆነና “ትኩረት የሚሰጡት” ጉዳይ መሆኑንም ተናግረዋል።• በጋዛ ያለው ሞት- እስራኤል “ሰብአዊ ቀውስን መቀነስ በምትችልበት መንገድ ላይ” እንደተነጋገሩ ገልጸዋል።ብሊንከን ግባቸውን አሳክተው ከሆነ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ “ሁሉም ሂደት ላይ ያለ ነው” ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 7:57 6 ህዳር 20237:57 6 ህዳር 2023የአውሮፓ ኅብረት ለጋዛ የሚያደርውን ድጋፍ በድጋሚ ጨመረ
EPACopyright: EPAየአውሮፓ ኅብረት ለጋዛ የሚላከውን ሰብአዊ እርዳታ በ25 ሚሊዮን ዩሮ ለመጨመር ቃል ገባ።ዘንድሮ የሚደረገው ድጋፍ በድጋሚ እንዲጨምር ነው የተወሰነው።የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኧርሴላ ቮን ደር ሌይን፣ ከሦስት ሳምንታ በፊት እርዳታ በሦስት እጥፍ ለመጨመር መወሰናቸውን ተናግረዋል።አሁን ድጋፍ እንዲጨመር ከተወሰነ በኋላ ለጋዛ የሚሰጠው አጠቃላይ እርዳታ 100 ሚሊዮን ዮሮ ይሆናል።ድጋፉ ለሰብአዊ ተቋማት የሚሰጥ ሲሆን፣ በዋናነት ምግብ፣ የመጠጥ ውሃ፣ የጤና እና ሌሎችም መሠረታዊ አገልግሎቶች ላይ በማተኮር ነፍስ አድን እርዳታ እንደሚደረግበት ተገልጿል።የአውሮፓ ኅብረት የፍልስጥኤም ትልቁ የውጭ እርዳታ ሰጭ ሲሆን፣ ተጨማሪ የሚሰጠው እርዳታ የጋዛ ነዋሪዎችን ስለመድረሱ ግን ግልጽ አይደለም።በጋዛ እና ግብፅ መካከል ያለው ራፋ ድንበር የእርዳታ መተላለፊያ ቢሆንም እየገባ ያለው እርዳታ በቂ እንዳልሆነ ሰብአዊ ተቋማት ገልጸዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:49 6 ህዳር 20234:49 6 ህዳር 2023የአንቶኒ ብሊንከን ጉብኝት የፈጠራቸው ጭላንጭል ተስፋዎችየአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ለሦስት ቀናት የተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ አገራትን ረግጠዋል። ዓላማቸው ደግሞ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ያለው ግጭት ወደ ሌሎች አገራት እንዳይዛመት ለማድረግ ነው። አርብ እስራኤል። ቅዳሜ ዮርዳኖስ። እሑድ ዌስት ባንክ፣ ኢራቅ እና ቱርክ። በየደረሱበት ሁሉ ተግዳሮት ነበር።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:58 6 ህዳር 20233:58 6 ህዳር 2023ከፍተኛ የእስራኤል ጥቃትን ያስተናገደችው ጋዛ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesሰሜናዊቷ ጋዛ በትናንትናው ዕለት ከፍተኛ የአየር ጥቃቶች እና ፍንዳታዎችን አስተናግዳለች።በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ያለው የመገናኛ ዘዴ ተቋርጧል።ነገር ግን ትናንት ምሽት በጋዛ የሚገኘው የቢቢሲ ጋዜጠኛ ራሽዲ አቡአሎፍ ጋዛ ከጦርነቱ መጀመሪያ ጀምሮ የከፋ የተባለውን የአየር ጥቃት እንደደረሰባት ተናግሯል።የእስራኤል የአየር ጥቃት ያተኮረው በሰሜን ምዕራብ ጋዛ ላይ ሲሆን የባህር ዳርቻው ወይም ሻቲ ተብሎ የሚጠራው የተፈናቃዮች መጠለያ ከፍተኛ ጥቃቶችን አስተናግዷል።በርካቶችም ቤተሰቦቻቸውን ከፍርስራሾች ለማውጣት ሲሞክሩም ታይተዋል።እስራኤል ተዋጊ ጄቶቿ 450 ኢላማዎችን ማጥቃት እንደመታች አስታውቃለች።እስራኤል በተቀናጀ ሁኔታ እየፈጸመችው ባለው ጥቃት ከ9 ሺህ 700 በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ከነዚህም አብዛኞቹ ህጻናት መሆናቸውን በሐማስ የሚመራው ሚኒስቴር ገልጿል።
Getty ImagesCopyright: Getty Images
EPACopyright: EPA
EPACopyright: EPA
ReutersCopyright: Reuters
ReutersCopyright: ReutersArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:36 6 ህዳር 20232:36 6 ህዳር 2023ቻድ በጋዛ ጦርነት ምክንያት በእስራኤል ያሉ ልዑኳን ጠራች
ReutersCopyright: Reutersየማዕከላዊ አፍሪካዊቷ አገር ቻድ “በጋዛ ሰርጥ እየደረሰ ባለው አሰቃቂ ጥቃት ምክንያት” በእስራኤል ተቀማጭ የሆኑ ልዑኳን ጠራች።ልዑኳንም የጠራችው ምክክር ለማድረግ ነው ብላለች።የአገሪቱ መንግሥት “የበርካታ ንጹሓን ህይወት መቀጠፍን” አውግዞ “ለፍልስጤም ጥያቄ ዘላቂ መፍትሔ የሚያመጣውን የተኩስ አቁም” እንዲደረግ መጠየቁንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አትቷል።በርካታ የሙስሊም ህዝብ ያለች ቻድ በአውሮፓውያኑ 1972 ከእስራኤል ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያቋረጠች ሲሆን ከአራት ዓመታትም በፊት ግንኙነታቸው ተሻሽሎ ነበር። ጦርነቱ ከተነሳም በኋላ በእስራኤል ያለውን ልዑኳን የጠራች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት አገር ሆናለች።እስካሁን ድረስ ቱርክ፣ ቺሊ፣ ባህሬን፣ ሆንዱራስ፣ ኮሎምቢያ እና ዮርዳኖስ አምባሳደሮቻቸውን ከእስራኤል ጠርተዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:02 6 ህዳር 20232:02 6 ህዳር 2023በጋዛ ማንኛውም የመገናኛ ዘዴዎች መቋረጣቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ዶ/ር ቴድሮስ ተናገሩ
ReutersCopyright: Reutersበከበባ ውስጥ በምትገኘው የጋዛ ሰርጥ የኢንተርኔት እንዲሁም የስልክ አገልግሎቶች መቋረጣቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናገሩ።ከመገናኛ ዘዴዎች መቋረጥ በተጨማሪ በጋዛ እየደረሰ ያለው የማያባራ የአየር ጥቃትም ስጋት እንዳሳሰባቸው በኤክስ ገጻቸው አስፍረዋል።”የመገናኛ ዘዴዎች ከተቋረጡ አፋጣኝ የህክምና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ወደ ሆስፒታሎች መሄድም ሆነ አምቡላንሶችን ማግኘት አይችሉም” ብለዋል።አክለውም “ሁሉም የመገናኛ ዘዴዎች እንዲቀጠሉም” አሳስበዋል። የፍልስጤም የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያ ፓልቴል በጋዛ ውስጥ የመገናኛ እና ኢንተርኔት አገልግሎቶች ሙሉ ለሙሉ እንደተቋረጠ ገልጿል።ኩባንያው እንዳስታወቀው “የመገናኛ ዘዴዎቹ ዋና ዋና መስመሮች ለእስራኤል ጥቃት በመጋለጣቸው” ተቋርጧል ብሏል።በአንድ ወር ውስጥ የመገናኛ ዘዴዎች ሙሉ በሙሉ ሲቋረጡ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑንም ኢንተርኔት ተቆጣጣሪው ቡድን ኔትብሎክስ አስታውቋል።የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ ድርጅት በጋዛ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ በተፈጠረው የመገናኛ ዘዴዎች መቋረጥ ሰራተኞቻቸው ጋር መገናኘት እንዳልቻሉ አስታውቋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:36 6 ህዳር 20231:36 6 ህዳር 2023የተመድ ኤጀንሲዎች በጋዛ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ
EPACopyright: EPAየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲዎች በጋዛ አስቸኳይ ሰብዓዊ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ።ሁሉም ኃላፊዎች “ሲበቃ ይበቃል” ብለዋል በጋራ ባወጡት መግለጫ “ለአንድ ወር ያህል ዓለም በእስራኤል እና እስራኤል በወረራ በያዘቻቸው የፍልስጥኤም ግዛት እየተከሰተ ያለውን ሁኔታ በድንጋጤ እና በፍርሃት እየተመለከተ ነው። እየጠፋ ያለውን ህይወት እና ቀውሱንም ታዝቧል” ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኃላፊዎች ተናግረዋል።ዩኒሴፍ፣ የዓለም ጤና ድርጅት፣ የዓለም የምግብ ፕሮግራም እንዲሁም እንደ ሴቭ ዘ ችልድረን ያሉ የረድዔት ድርጅቶችን ጨምሮ የኤጀንሲዎቹ ኃላፊዎች በሁለቱም ወገኖች ላይ የደረሰውን የህይወት መቀጠፍ ” አሰቃቂ” ሲሉ ገልጸውታል።ሐማስ ከአራት በፊት የወሰዳቸውን ታጋቾች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታም ጠይቀዋል። አክለውም “ነገር ግን በጋዛ ሰርጥ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ እየተገደሉ ያሉ በርካታ ሰላማዊ ዜጎች ቁጣን የሚፈጥር ነው። እንዲሁም 2.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ፍልስጤማውያንን ምግብ፣ ውሃ፣ መድኃኒት፣ ኤሌክትሪክ እና ነዳጅ መከልከልም እንዲሁ የሚያስቆጣ ነው” ብለዋል በመግለጫቸው።መግለጫው አክሎም የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጤም የስደተኞች ኤጀንሲ 88 ሰራተኞቹ መገደላቸውን ገልጾ በአንድ ግጭት ውስጥ ከፍተኛ ግድያም እንደሆነም ነው ያስታወቀው።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:32 6 ህዳር 20230:32 6 ህዳር 2023የዮርዳኖስ አየር ኃይል ለጋዛ የህክምና ግብዓቶችን ከአየር ላይ ጣለ
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል በከበባ ውስጥ ባስገባቻት የጋዛ ሰርጥ መሰረታዊ የህክምና ግብዓቶችን እና መድኃኒቶችን ከአየር ላይ መጣሉን የዮርዳኖስ የአየር ኃይል አስታወቀ።እነዚህ የህክምና ግብዓቶች በጋዛ ለሚገኘው የዮርዳኖስ ሆስፒታል እንደሚደርስም የዮርዳኖሱ ንጉስ አብዱላህ ገልጸዋል።በጋዛ ቆስለው እየተሰቃዩ ያሉትን መርዳት ወታደራዊ ግዴታቸው እንደሆነም ንጉስ አብዱላህ በማህበራዊ የሚዲያ ገጻቸው አስፍረዋል።ፍልስጤማውያን ወንድሞቻችን ናቸው ያሉት ንጉሱ አገራቸው በጠንካራ አጋርነቷ ትቀጥላለች ብለዋል።እስራኤል በበኩሏ የዮርዳኖስ አየር ኃይል በፓራሹት ያደረገው እርዳታ ከመከላከያዋ ጋር በትብብር እንደሆነ አስታውቃለች።በአሁኑ ግጭት በፓራሹት እርዳታ ሲደረግ የመጀመሪያው ነው።