November 8, 2023 – Konjit Sitotaw

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ተጫማሪ አራት ከፍተኛ አመራሮችን ከስልጣን አነሱ።
ከስልጣን ያነሷቸው ፦
– አቶ አለም ገ/ዋህድ የህወሓት የፓለቲካዊ ጉዳዮች ሃላፊና ዋና ፓሊት ቢሮ አባል ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት አማካሪ
– የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ሊያ ካሳ ከደቡባዊ ምስራቅ ዋና አስተዳዳሪ
– የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል አቶ ተኽላይ ገ/መድህን ከሰሜናዊ ምእራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
– የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል አቶ አማኒኤል አሰፋ ከጊዚያዊ አስተዳደር ቺፍ ካቢኔ ሰክሬታሪያት ነው።

በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ ተፅፎ ቁጥር ፣ ማህተምና ቲተር ያረፈበት ደብዳቤ እንደሚያመለክተው አራቱ ከፍተኛ አመራሮች ለሰጡት መንግስታዊ አገልግሎት በማመስገን ጥቅምት 17/2016 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ከጥቅምት 15/2016 ዓ.ም ጀምሮ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ከነበራቸው ሃላፊነት መነሳታቸው ይገልፃል።
ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ የምስራቅ ፣ የደቡብ ፣ የማእከላይ ፣ የደቡብ ምስራቅ ፣ የሰሜናዊ ምእራብ ና የምእራብ ዞን የህዝብ ግንኙነት ፅህፈት ቤት ሃላፊ 6 ከፍተኛ አመራሮች ከስልጣን ማሰናበታቸው መዘገባችን ይታወሳል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከስልጣን ያነሱዋቸው ከፍተኛ አመራሮች ቁጥር የአሁኑን ጨምሮ 10 ደርሷል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።