ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባል

“የመከላከያ ሠራዊቱን ምስጢር አውጥተሃል”፣ “ሠራዊቱ እንዲከፋፈል አድርገሃል” እና “የተቋሙን ስም አጥፍተሃል” የሚሉ ሦስት የውሸት ክሶች ተመስረተውበ ከግንቦት 18/2013 እስከ ህዳር 7/2014 ዓ.ም ድረስ እስር ቤት የቆየው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ክሱን ሲመለከት በነበረው የከፍተኛው ፍርድ ቤት የካቲት 29/2015 ዓ.ም በሙሉ ድምጽ በነጻ መሰናበቱ ይታወሳል፡፡
ይህም ሆኖ፣ ዐቃቢ ሕግ ገና ክሱ ሳይቋጭ ጥቅምት 21/2015 ዓ.ም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በብይኑ ላይ ያቀረበው ይግባኝ፣ ፍርድ ቤቱ ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ተቀብሎ “ያስቀርባል” ሲል ወስኗል፡፡ በዚህም መሰረት ይግባኙ በቀረበ በዓመቱ ጥቅምት 5/2016 ዓ.ም ጉዳዩን ያየው ይኸው ፍርድ ቤት ለነገ ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም ለውሳኔ ቀጥሯል፡፡
እዚህ ጋ ሳይገለጽ የማይታለፈው፣ ከዚህ ቀደም በጠቅላይ ፍርድ ቤት የነበሩት የይግባኝ ሰሚ ችሎቶች ሁለት የነበሩ ሲሆን፤ ከዚህ ዓመት ጀምሮ አንድ ብቻ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ይህን ችሎትም ለረዥም ጊዜ ሰበር ላይ የነበረውና ብዙ ቅሬታ ሲነሳበት የነበረው ሸምሱ ሲርጋጋ በሰብሳቢነተ እንዲመራው ሲመደብ፤ ግራና ቀኝ ደግሞ ኦሮሞኝ ተናጋሪ የሆኑት ሃቪዝ አባጀማል እና መሀመድ የተባሉ ዳኞች ተመድበዋል፡፡ ይህን ተከትሎም በችሎቱ ነፃነት ላይ ከባድ ጥርጣሬ መፈጠሩ እየተነገረ ነው፡፡
(ፍትሕ)
