Related Video and Audio

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. እስራኤል መሃል ጋዛ ከተማ ገባሁ አለች
  2. ኔታንያሁ ከጦርነቱ በኋላ የጋዛ ሰርጥ ‘የጸጥታ ኃላፊነት’ የእስራኤል ይሆናል አሉ
  3. ሐማስ በእስራኤሉ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎችን አልገደልኩም አለ
  4. ጋዛ ወደ ህጻናት የመቃብር ስፍራነት እየተቀየረች ነው- ተመድ
  5. ከ4 ሳምንታት የእስራኤል-ጋዛ ጦርነት በኋላ በግልጽ የሚታዩ 5 እውነታዎች
  6. ብሊንከን እና የፍልስጤሙ ፕሬዚዳንት በዌስት ባንክ ተገናኙ
  7. በተለያዩ አገራት ለፍልስጤም የሚደረገው የአጋርነት ሰልፍ እንደቀጠለ ነው
  8. አሜሪካ በጋዛ ሰማይ ድሮን ለቅኝት መላኳን አመነች
  9. ዶክተር፣ ልብስ ሰፊ፣ ጨቅላ ሕጻን…- በእስራኤል የአየር ጥቃት ከተገደሉት መካከል የጥቂቶቹ አሳዛኝ ታሪክ
  10. ብሊንከን የጋዛ የተኩስ አቁም ጥሪን ውድቅ አደረጉ
  11. እስራኤል በአል- ማጋዚ የስደተኞች መጠለያ በፈጸመችው የአየር ጥቃት በርካቶች ተገድለዋል ተባለ

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 4:114:11እስራኤል ከ10 ሰዓታት ውጊያ በኋላ የሐማስን ‘ጠንካራ ይዞታ’ ተቆጣጠርኩ አለችየጋዛ ጥቃትReutersCopyright: Reutersየእስራኤል መከላከያ ኃይል በሰሜናዊ ጋዛ ጃባሊያ የሚገኘውን የሐማስን ጠንካራ ይዞታ መቆጣጠሩን አስታወቀ።ጦሩ በኤክስ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው “10 ሰዓታት ከፈጀ ውጊያ በኋላ አሸባሪዎችን ደምስሰናል፤ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ማርከናል። የአሸባሪዎች መመላለሻ ዋሻዎችን አግኝተናል።አንደኛው ዋሻ በመዋዕለ ህጻናት አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን በመሬት ውስጥ ሰፊ ስፍራን የሚሸፍን ነው ነው” ብሏል።የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች በጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ የሚገኝ መኖሪያ ቤትን እንደበደቡ የፍልስጤም የዜና ወኪል ዋፋ ዘግቧል።ነዋሪዎች በፍርስራሾች ውስጥ ተቀብረው ይገኛሉ ብሏል። እስራኤል በጋዛ ከተማ በፈጸመችው ጥቃትም በርካቶች መቁሰላቸውን አክሎ ዘግቧል። ቢቢሲ ሪፖርቶቹን ማረጋገጥ አልቻለም።Article share tools
  2. የታተመዉ 3:543:54በጋዛ የቀጠለው ጥቃትየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበጋዛ ሰርጥ የአየር እና የመሬት ጥቃት እንዲሁም ከባህር በሚወነጨፉ ሚሳኤሎች የተቀናጁ ጥቃቶች መቀጠላቸውን የእስራኤል ጦር አስታውቋል።በጋዛ የማያባራው የአየር ጥቃት በትናትናው ምሽትም ቀጥሏል። የእስራኤል ጦር የሐማስ ወታደራዊ እዝን መትቻለሁ ብሏል።እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ ኻን ዩኒስ በአንድ መኖሪያ ቤት ሌሊቱን በፈጸመችው ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።ከዚህም በተጨማሪ በሰሜናዊ ጋዛ በሚገኘው የጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ እንዲሁም በጋዛ ከተማ በፈጸመችው ጥቃት ጉዳት መድረሱንም በሐማስ ከሚመራው የጋዛ የጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያስረዳል።በርካቶችም ቤተሰቦቻቸውን ከፍርስራሾች ለማውጣት ሲታገሉ የሚያሳዩ ምስሎችን ቢቢሲ አግኝቷል።የጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty ImagesArticle share tools
  3. የታተመዉ 3:063:06ቀይ መስቀል የእርዳታ መኪናው በጋዛ እንደተመታ አስታወቀየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesአለም አቀፉ ቀይ መስቀል በደቡባዊ ጋዛ ወደሚገኘው አልቁድስ ሆስፒታል ህይወት አድን መድኃኒቶች ጭነው ሲጓዙ ከነበሩት ውስጥ አንዱ መኪናው እንደተመታ እና አሸከርካሪውም እንደተጎዳ አስታወቀ።አሽከርካሪው ከሞት “በሳንቲሜትሮች” ርቀት ውስጥ ነበር ብሏል። “እውነት ለመናገር ለሰብዓዊ ረድዔት ተቋማት እርዳታ ለማድረስ ምቹ አይደለም መኖር ይቅርና” ሲሉም ከእርዳታ ጭነቱ ጋር አብረው ሲጓዙ የነበሩት የተቋሙ የጋዛ ቢሮ ኃላፊ ዊልያም ሾምቡርግ ለቢቢሲ ተናግረዋል።”መሰረታዊ የደህንነት ከለላ እና አቅርቦቶች እንፈልጋለን። ሰራተኞቻችን የምናፈራርቅበት ሁኔታም መረጋገጥ አለበት” በማለት የተናገሩት ኃላፊ ሆስፒታሎች ያላቸው ነዳጅ እንደተመናመነ እንዲሁም የሚጠጣ ውሃ ማግኘትም የእለት ተዕለት መሆኑንም ገልጸዋል።”በጋዛ ውስጥ የትኛውም ቦታ ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም” ብለዋል። ኃላፊው በደቡባዊ ጋዛ ያለውን ሁኔታ “ሰብዓዊ ጥፋት” ሲሉ ገልጸውታል።በፍርሓት የተዋጡ ነፍሰ ጡር እናቶች፣ ህጻናት እና አዛውንቶች ህይወታቸውን ለማትረፍ በባዶ እግራቸው አይተናል። በርካቶችም ምግብ እና የሚጠጣ ውሃ ፍለጋ እየተንከራተቱ ነው ብለዋል።Article share tools
  4. የታተመዉ 2:102:10በጋዛ የቦምብ ጥቃት ከቀጠለ ቀጠናዊ ጦርነት እንደሚቀሰቀስ ሄዝቦላህ አስጠነቀቀእስራኤል በጋዛ ሰርጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ እየፈፀመችው ያለችው ግድያ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሊዛመት ይችላል ሲሉ በኢራን የሚደገፈው የጠንካራው የሄዝቦላህ ምክትል አዛዥ አስጠነቀቁ። ሼክ ናይም ቃሴም ለቢቢሲ እንደተናገሩት “በአካባቢው በጣም አሳሳቢ እና በጣም አደገኛ ክስተቶች ሊፈጠሩ ከመቻላቸውም በላይ ማንም መዘዙን ሊያስቆም አይቻለውም” ብለዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  5. የታተመዉ 1:501:50የእስራኤል ጦር በጋዛ 130 የሐማስ ዋሻዎችን ማውደሙን አስታወቀየእስራኤል መከላከያ ኃይልIDFCopyright: IDFየእስራኤል መከላከያ ኃይል በጋዛ ሰርጥ ጦሩን ካስገባ በኋላ 130 የሐማስ ዋሻዎችን ማውደሙን አስታወቀ።”የእስራኤል መከላከያ ተዋጊ መሐንዲሶች በአሁኑ ወቅት በጋዛ ውስጥ የሚገኙ ዋሻዎችን ጨምሮ የሐማስ የሽብር መሰረተ ልማቶችን ለማጋለጥ እና ለማውደም እየሰሩ ነው። በዋሻዎቹ ውስጥ የተገኙት የውሃ እና የኦክስጂን ክምችት ሐማስ ከመሬት በታች ለረጅም ጊዜ ለመቆየት ያለውንም ዝግጅት የሚያሳይ ነው” ሲል የመከላከያው መግለጫ አትቷል።ረቡዕ ዕለት በሰሜን ጋዛ ቤይት ሐኖን አካባቢ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ ድጋፍ በሚያደርግበት ትምህርት ቤት አቅራቢያ የሚገኘውን የሐማስ ዋሻ ማውደሙን አስታውቋል።መከላከያ በትምህርት ቤቱ አቅራቢያ የሚገኘውን እና የሐማስ ዋሻ ነው በሚል አውድሜያለሁ ያለውንም በድሮን የተቀረጸ ቪዲዮ አጋርቷል።እስራኤል ሐማስ መስከረም 26 ላደረሰው ጥቃት ምላሽ ነው በሚል የጋዛ ሰርጥን በማያባራ የአየር ጥቃት እየመታች ትገኛለች።በሙሉ ከበባ ውስጥ በማስገባት መብራት፣ ውሃ እና ነዳጅ የቆረጠች ሲሆን እግረኛ ጦሯም ገብቶ የተቀናጀ ጥቃት እየፈጸመ እንደሚገኝ አስታውቋል።ሐማስ በፈጸመው ጥቃት 1 ሺህ 400 ሰዎች ሲገደሉ ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች ታግተዋል። እስራኤል እየፈጸመች ባለችው የተቀናጀ ጥቃት ከ10 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ሲገደሉ በርካቶቹም ህጻናት መሆናቸውን በሐማስ የሚመራው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።የተባበሩት መንግሥታት ጋዛ ወደ ህጻናት ስፍራ መቀበሪያነት እየተቀየረች ነው ሲል አስከፊነቱን ጠቅሶ የተኩስ አቁም በአፋጣኝ መደረግ አለበት ብሏል።Article share tools
  6. የታተመዉ 0:540:54ተመድ እስራኤል እና ሐማስን የጦር ወንጀሎች በመፈጸም ከሰሰየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኃላፊ እስራኤል እና ሐማስ የጦር ወንጀሎች ፈጽመዋል ሲሉ ከሰሱ።ቮልከር ተርክ ሐማስ ታጋቾቹን አለመልቀቁ እንዲሁም እስራኤል በፍልስጤም ሰላማዊ ዜጎች ላይ እየፈጸመች ያለውን ህዝብን በጋራ የመቅጣት እና ነዋሪዎች በህገወጥ መንገድ በአስገዳጅ ሁኔታ ማፈናቀሏን ጠቅሰዋል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በበኩላቸው በጋዛ የተገደሉ ሰላማዊ ሰዎች አኃዝ የእስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ “በግልጽ ስህተት እየተፈጸመ እንደሆነ ማሳያ ነው” ብለዋል። ሐማስንም ሰላማዊ ሰዎችን እንደ ሽፋን በመጠቀሙ ወቅሰውታል።
    • የእስራኤል ጦር 50 ሺህ የሚሆኑ ፍልስጤማውያን ከሰሜን ጋዛ ወደ ደቡብ መሸሻቸውን አስታውቋል። እስራኤል በሰሜን ጋዛ ነዋሪ የሆኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲሸሹ ማስጠንቀቋ ይታወሳል።
    • የዓለም አቀፉ ቀይ ጨረቃ የጋዛ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በደቡባዊ ጋዛ ያለውን ሁኔታ “ሰብዓዊ ጥፋት” ሲሉ ገልጸውታል። በፍርሓት የተዋጡ ነፍሰ ጡር እናቶች፣ ህጻናት እና አዛውንቶች ህይወታቸውን ለማትረፍ በባዶ እግራቸው አይተናል። በርካቶችም ምግብ እና የሚጠጣ ውሃ ፍለጋ እየተንከራቱ ነው ብለዋል። የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እየፈጸመችው ባለው የማያባራ የአየር ጥቃት ንጹህ ውሃ ማግኘት ተስተጓጉሏል ብሏል። እንዲሁም መጠለያዎች በተፈናቃዮች ስለተጨናነቁ በጋዛ ሰርጥ በሽታዎች ሊዛመቱ እንደሚችሉም አስጠንቅቋል።
    • የህክምና ቁሳቁሶችን የጫነ እርዳታ በጋዛ ከተማ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ደርሷል። እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት ጋዛ በአንድ ወር ውስጥ መድኃኒት ሲደርስ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
    • የአሜሪካ ሪፐብሊካን እጩዎች እስራኤል ከሐማስ ጋር እያደረገችው ላለው ጦርነት ድጋፋቸውን ገልጸው የተኩስ አቁም ጥሪን ውድቅ አድርገዋል።
    • አስራ ሁለት የሚሆኑ ታጋቾችን ለማስለቀቅ እና በምላሹም ለሶስት ቀናት የተኩስ አቁም እንዲደረግም ውይይቶች መጀመራቸውን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጭ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከነዚህም መካከል ግማሾቹ አሜሪካውያን መሆናቸውን ቢቢሲ ሰምቷል።
    • የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እየተደረጉ ነው የተባሉ ውይይቶችን “ሐሰተኛ ወሬዎች” ናቸው ሲሉ አጣጥለዋል። “ታጋቾች እስካልተለቀቁ ድረስ” የተኩስ አቁም አይኖርም ብለዋል።
    • የቢቢሲ አለም አቀፍ ጉዳዮች አዘጋጅ ጄረሚ ባውን ከእስራኤል ጦር ጋር ወደ ጋዛ ተጉዟል። በጋዛ ቆይታውም ጉዳት ያልደረሰበት ህንጻ እንደሌለ ተመልክቷል። የእስራኤል ጦር አንድ የቤተሰብ መኖሪያ ያለበትን እና የጦር መሳሪያዎች ይመረቱበታል የተባለውን ህንጻም ለጋዜጠኛው አሳይቶታል።
    Article share tools
  7. የታተመዉ 23:54 8 ህዳር 202323:54 8 ህዳር 2023ከጦርነቱ በኋላ እስራኤል ጋዛን ይዛ መቆየት እንደሌለባት አሜሪካ አስጠነቀቀችየጋዛ ጥቃትISRAEL DEFENSE FORCESCopyright: ISRAEL DEFENSE FORCESጦርነቱ ከተጠናቀቀ በኋላ እስራኤል ጋዛን ተቆጣጥራ መቆየት እንደሌለባት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን አስጠነቀቁ።ሐማስ ከወር በፊት ያደረሰውን ጥቃት ሊደግም እንደሚችል ስጋት በመደቀኑ ጋዛን በመምራት መቀጠል እንደሌለበትም አጽንኦት ኃላፊው ሰጥተዋል።ነገር ግን እስራኤል ሳትሆን በዌስት ባንክ ተቀማጭነቱን ያደረገው የፍልስጤም አስተዳደር ጋዛን ሊመራ ይገባል ብለዋል።እስራኤል በጋዛ ነዋሪዎች ላይ አስገዳጅ ማፈናቀል፣ ከበባም ሆነ ክልከላ እንዲሁም የጋዛ ግዛትንም መቁረስ የለባትም ሲሉ ተናግረዋል።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እስራኤል ላልተወሰነ ጊዜ በጋዛ ላይ አጠቃላይ የጸጥታ ኃላፊነት እንደሚኖራት ተናግረዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጠቃላይ የጸጥታ ኃላፊነት የእስራኤል ነው ለሚለው ንግግራቸው ማብራሪያ ባይሰጡም አንድ ከፍተኛ የእስራኤል ባለስልጣን እስራኤል ጋዛን እንደገና ይዛ የመቆየት ወይም “ለረዥም ጊዜ ተቆጣጥራ የመቆየት ፍላጎት የላትም” ብለዋል።እስራኤል ሐማስን አጠፋለሁ በሚል በጋዛ ላይ የማያባራ የአየር ጥቃቶችን ከጀመረች አንድ ወር አልፎታል።በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት ጋዛ ኤሌክትሪክ፣ ውሃና ነዳጅ ቆርጣለች እንዲሁም እግረኛ ጦሯን አስገብታ የተቀናጀ ጥቃት መክፈቷን አስታውቃለች።በነዚህ ጥቃቶች ከ10 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ሲገደሉ በርካቶቹም ህጻናት መሆናቸውን በሐማስ የሚመራው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።የተባበሩት መንግሥታት ጋዛ ወደ ህጻናት ስፍራ መቀበሪያነት እየተቀየረች ነው ሲል አስከፊነቱን ጠቅሶ የተኩስ አቁም በአፋጣኝ መደረግ አለበት ብሏል። ሐማስ ባደረሰው ጥቃት ከ1400 በላይ ሰዎች ሲገደሉ፣ 240 ሰዎችም በታጋችነት ተወስደዋል።Article share tools
  8. የታተመዉ 23:40 8 ህዳር 202323:40 8 ህዳር 2023በኢራን የሚደገፈው አማፂ ቡድን የአሜሪካን ወታደራዊ ድሮን መትቶ ጣለየየመን ሁቲ አማፂያን የዩኤስ ወታደራዊ ድሮን መትቶ መጣሉን የአሜሪካ ባለሥልጣናት እና በኢራን የሚደገፈው የሁቲ ንቅናቄ ገልጧል። የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት እንዳሉት ኤምኪው9 የተባለው ድሮን ተመትቶ የወደቀው በየመን ጠረፍ አቅራቢያ ነው። የሁቲ ወታደራዊ ንቅናቄ ድሮኑ ተመትቶ መውደቁን አረጋግጠዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  9. የታተመዉ 23:36 8 ህዳር 202323:36 8 ህዳር 2023“ሐሎ! ከእስራኤል ደኅንነት ቢሮ ነበር የምደውለው። ቤትህን ልናጋየው ትዕዛዝ ተሰጥቶናል”ዶ/ር ማሕሙድ ሻሒን የጥርስ ሐኪም ነው። ሐሙስ ጥቅምት 8/2016 ዓ.ም. ድንገት ስልኩ ጠራ። የሞት ጥሪ ይሆናል ብሎ አልጠበቀም። በዚያ ላይ ገና ከጠዋቱ 12፡30 ነው። ሲፈራ ሲቸር፤ ስልኩን አነሳው። “ሐሎ፣ ከእስራኤል ደኅንነት ቢሮ ነበር የምደውለው። ያለህበትን ሕንጻ ልናጋየው ትዕዛዝ ተሰጥቶናል።”ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  10. የታተመዉ 8:51 8 ህዳር 20238:51 8 ህዳር 2023እርዳታ እንዲቀርብ በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ እስራኤል ጥቃቷን ጋብ ማድረጓ ተነገረእርዳታ እንዲቀርብ በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ እስራኤል ጥቃቷን ጋብ ማድረጓ ተነገረAPCopyright: APእስራኤል በጋዛ ላይ ጥቃት መፈጸም ከጀመረችበት ከአንድ ወር በኋላ ሠራዊቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአራት ሰዓታት የሚቆይ ለሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ጥቃቱን ጋብ ማድረጉን አስታውቋል።በዚህ ለጥቂት ሰዓታት በሚቆየው ከጥቃት ፋታ የሚገኝበት ጊዜ በጋዛ ከተማ ማዕከላዊ ክፍል ውስጥ በሚገኙ ትላልቅ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ውሃ እና ምግብ እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል።ጦርነቱ ከጀመረ አንስቶ ከነበረው የአየር ጥቃት አንጻር ዛሬ ረቡዕ በጋዛ ሰርጥ እና በደቡባዊው ክፍል ውስጥ የተፈጸመው የአየር ጥቃት መጠን ዝቅ ያለ መሆኑ ተዘግቧል።ነገር ግን ረቡዕ ማለዳ ላይ በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ ዴር አል-ባላህ እና በሌሎች ከተሞች ላይ ያነጣጠሩ የአየር ጥቃቶች ተፈጽመው 40 ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸው ተነግሯል።በሰሜን ጋዛ ውስጥ ውጊያ እየተካሄደ በመሆኑ የተነሳ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው በእግራቸው እየወጡ ናቸው።በስምንት ግንባሮች እየተካሄደ ያለው ውጊያ አዝጋሚ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፣ የእስራኤል እግረኛ ወታደሮች በጋዛ ከተማ ላይ ከበባቸውን ለማጥበቅ ከከተማዋ በስተምዕራብ ወደሚገኘው ቁልፍ የባሕር ዳርቻ መንገድ እየገፉ ናቸው።Article share tools
  11. የታተመዉ 5:54 8 ህዳር 20235:54 8 ህዳር 2023የቡድን 7 አገራት ለጋዛ እርዳታ እንዲቀርብ ግጭት እንዲቆም ጥሪ አቀረቡየጂ7 የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮችReutersCopyright: Reutersጃፓን ላይ የተሰባሰቡት የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባወጡት መግለጫ በጋዛ ሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ ከጦርነቱ ፋታ እንዲገኝ እና መተላለፊያ እንዲዘጋጅ ጠየቁ።ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ የሚገኙበት ቡድን ሰባት አባላት “ጋዛ ውስጥ እየተባባሰ ያለው ሰብአዊ ቀውስን ለማስቆም አስቸኳይ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት” በመግለጫቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።“በጋዛ ጦርነቱ ጋብ ብሎ ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ የሚያስችል መተላለፊያ እንዲመቻች በማድረግ ሲቪሎች እንዲንቀሳቀሱ እና ታጋቾች እንዲለቀቁ” ጠይቋል።ቢሆንም ግን መግለጫው በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተኩስ አቁም እንዲደረግ አልጠየቀም። ለሰብአዊ እርዳታ ሲባል የሚደረግ ግጭት የማቆም ፋታ ለአጭር ጊዜ ብቻ የሚቆይ ነው። ተኩስ አቁም የረጅም ጊዜ እና የፖለቲካዊ ሂደት አካል ነው።ጃፓን ቶኪዮ ውስጥ የተሰበሰቡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ መግለጫ፣ “በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት” እስራኤል እራሷን የመከላከል መብት አላት ብሏል።Article share tools
  12. የታተመዉ 3:47 8 ህዳር 20233:47 8 ህዳር 2023ማኅበራዊ ሚድያ እና የጋዛ ግጭት፡ ሞሐመድ ሳላህ ለስፖርቱ ዓለም “አርአያ” ነውሞሐመድ ሳላህ በእስራኤል-ጋዛ ግጭት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሰጠው ምላሽ ለሌሎች አርአያ ሊሆን ይገባል ሲሉ የቀድሞ የስፖርት ምሑራን ገለጡ። ግብፃዊው የሊቨርፑል አጥቂ “ተጨማሪ የንፁሐን ነፍስ ከመጥፋቱ በፊት የዓለም መሪዎች አንድ ነገር እንዲሉ” ሲል ባለፈው ወር ጥሪ አቅርቧል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  13. የታተመዉ 3:37 8 ህዳር 20233:37 8 ህዳር 2023የአሜሪካ ፖለቲከኞች እስራኤላውያንን ሻማ በማብራት አሰቡየአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እስራኤላውያንን ሻማ በማብራት አሰቡEPA-EFE/REX/ShutterstockCopyright: EPA-EFE/REX/Shutterstockየአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እስራኤላውያንን ሻማ በማብራት አሰቡImage caption: የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እስራኤላውያንን ሻማ በማብራት አሰቡአሜሪካውያን ፖለቲከኞች ሐማስ የፈጸመበትን ድንገተኛ ጥቃት አንድ ወር በማስመልከት ሻማ በማብራት እስራኤላውያንን አስበው ዋሉ።የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በዋሽንግተን ዲሲ ባደረጉት የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት በሐማስ ጥቃት የተገደሉትን እና ታግተው የተወሰዱትን ሰዎች አስበዋል።ሐማስ ከአንድ ወር በፊት በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽሞ ከ1ሺህ 400 ያላሱ ሰዎችን ገድሎ 240 ሰዎች ማገቱ ይታወሳል።በተቃራኒው የእስራኤል ጦር በወሰደው የአጸፋ እርምጃ በሐማስ የሚተዳደረው ጤና ሚንስቴር ከ10ሺህ 300 በላይ ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል።Article share tools
  14. የታተመዉ 3:36 8 ህዳር 20233:36 8 ህዳር 2023ጋዛ ሰርጥ ውስጥ ያሉ ዳቦ ቤቶች ተዘጉበጋዛ ያሉ ሁሉም ሊባሉ የሚችሉ ዳቦ ቤቶች በግብዓት እጥረት ምክንያት ተዘጉ።ዳቦ ቤቶቹ በነዳጅ፣ በውሃ እና በስንዴ ዱቄት እጥረት እንዲሁም በአየር ድብደባ ምክንያት ሥራቸውን ማከናወን ባለመቻላቸው ስለመዘጋታቸው ተዘግቧል።በጋዛ በተፈጠረው የምግብ እጥረት ምክንያት አንድ ሰው በአማካይ እየኖረ ያለው በቀን በሚያገኘው ሁለት ዳቦ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከጥቂት ቀናት በፊት አስታውቆ ነበር።Article share tools
  15. የታተመዉ 3:12 8 ህዳር 20233:12 8 ህዳር 2023ካናዳዊው “እየተሰቃዩ ያሉትን 2.3 ሚሊዮን ሰዎች ታሪክ መናገር ግዴታዬ ነው” ብሎ ከጋዛ አልወጣም አለፍልስጥኤማዊ ካናዳዊው ማንሱር ሾማን ከጋዛ ቤተሰቦቹን ይዞ እንዲወጣ ቢፈቀድለትም ጋዛ እንደሚቆይ ይናገራል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  16. የታተመዉ 3:05 8 ህዳር 20233:05 8 ህዳር 2023እስራኤል የሐማስ የጦር መሳሪያ ግምጃ ቤት ኃላፊን ገደልኩ አለችሞሃሰን አቡ ዚናIDFCopyright: IDFሞሃሰን አቡ ዚናImage caption: ሞሃሰን አቡ ዚናየእስራኤል መከላከያ ኃይል የሐማስ ከፍተኛ አመራር የነበረውን ሞሃሰን አቡ ዚናን ገደልኩ አለ።እንደ የእስራኤል ጦር ከሆነ ሞሃሰን አቡ ዚና የሐማስ የደኅንነት እና የጦር መሳሪያ ግምጃ ቤት ኃላፊ ነበር።ጦሩ እንዳለው ግለሰቡ የተተኳሽ እና የሮኬቶች ምርት ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው መሪ ነበር።የእስራኤል መከላከያ ኃይል ረፋድ ላይ ባወጣው መግለጫ ሠራዊቱ በጋዛ ሰርጥ ገብቶ “አሸባሪዎችን እየገደለ እና ለጦር አውሮፕላኖች አቅጣጫ እየሰጠ” ዘመቻዎችን እያካሄደ እንደሆነ ጨምሮ አስታውቋል።በዛሬው የእስራኤል የአየር ጥቃት በጋዛ ያሉ መኖሪያ ቤቶችን አውድሞ ሰላማዊ ሰዎች ስለመገደላቸው ሪፖርቶች እየወጡ ነው።Article share tools
  17. የታተመዉ 2:15 8 ህዳር 20232:15 8 ህዳር 2023የጋዛው ነዋሪ ከእስራኤል ደኅንነት የደረሰው የሕይወትህን አድን የስልክ ጥሪማህሙድ ሻሂንBBCCopyright: BBCማህሙድ ሻሂንImage caption: ማህሙድ ሻሂንእስራኤል ለ12 ቀናት ያህል ጋዛን በቦምብ ስትደበድብ ነበር ማህሙድ ሻሂን የስልክ ጥሪ የደርሰው።በጋዛ ሰርጥ በስተሰሜን ባለ ሦስት መኝታ አፓርታማው ሦስተኛ ወለል ላይ ይገኛል። አካባቢው እስካሁን ድረስ በአየር ድብደባ ብዙም ያልተነካ ነበር።ማህሙድ ከውጪ ከፍተኛ ጩኸት መስማት ጀመረ። “አሁኑኑ ማምለጥ አለብህ። ህንጻዎቹን ሊመቱ ነው” ብሎ መንገድ ላይ ያለ አንድ ሰው ጮክ ብሎ ተናገረ።ከህንጻው ወጥቶ መንገዱን በማቋረጥ መሸሸጊያ ሲፈልግ ስልኩ ጠራ።ማህሙድ እንዳለው አንድ ሰው “የምደውልልህ ከእስራኤል የስለላ ድርጅት ነው” አለው። ማህሙድን በሙሉ ስሙ ከመጥራት ባለፈ ጥረት ያለ አረብኛ ይናገራል።”ሦስት ህንጻዎችን ማጥቃት እንደሚፈልግ ነገረኝ… እናም አካባቢውን እንድለቅ አዘዘኝ።”በዚህ ግጭት ወቅት ጋዛውያንን ከአየር ድብደባ በፊት ለማስጠንቀቅ የእስራኤል ጦር አንዳንድ ጊዜ ስልክ ይደውላል። ይህ የማህሙድ ታሪክም ስለሚደረገው የስልክ ጥሪ ግንዛቤ ይሰጣል።Article share tools
  18. የታተመዉ 0:38 8 ህዳር 20230:38 8 ህዳር 2023ሳዑዲ አረቢያ በጋዛ ግጭት ዙሪያ ጉባኤዎችን እንደምታዘጋጅ አስታወቀችሳዑዲ አረቢያ በእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት ላይ ለመወያየት በሚቀጥሉት ቀናት የአረብ እና የሙስሊም አገራት መሪዎችን እንደሚሰባሰቡ ተገለጸ።የሳዑዲ የኢንቨስትመንት ሚኒስትር “በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ሳዑዲ አረቢያ አስቸኳይ የአረብ ስብሰባ በሪያድ ታዘጋጃለች” ማለታቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።”ከቀናት በኋላ ሳዑዲ አረቢያ እስላማዊ ጉባኤ ታዘጋጃለች” ብለዋል።”በአጭር ጊዜ ውስጥ ሦስት ስብሰባዎችን በሳዑዲ አረቢያ መሪነት የማዘጋቱ ዓላማ ግጭቱን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት ይሆናል” ሲሉ ተናግረዋል።የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ለእስላማዊ ትብብር ድርጅት ጉባኤ ወደ ሳዑዲ አረቢያ እንደሚጓዙ ተዘግቧል።በቻይና አደራዳሪነት ቴህራን እና ሪያድ ለዓመታት የዘለቀ ቁርሿቸውን ካስወገዱ በኋላ ይህ የኢራን መሪ የሚያደረጉት የመጀመሪያ ጉብኝት ይሆናል።ፋሊህ ቀን ሳይጠቅሱ ሳዑዲ አረቢያ የአፍሪካ አገራት መሪዎችን ጉባኤ ትጠራለች ብለዋል። ማክሰኞ አመሻሽ የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በሳምንቱ መጨረሻ የተቀጠረው ስብሰባ በሁለቱ የመሪዎች ጉባኤዎች ላይ ለማተኮር ሲባል ዘግይቷል ብሏል።Article share tools
  19. የታተመዉ 0:36 8 ህዳር 20230:36 8 ህዳር 2023ግብፅ ከጋዛ ወደ ግዛቷ በሚያሻግረው የራፋህ በር ላይ ቁጥጥሯን ያጠነከረችባቸው ምክንያቶችጋዛ እና ግብፅን የሚያገናኘው የራፋህ የድንበር መተላለፊያ በር ከሳምንት በፊት ተከፍቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ጋዛን ለቀው ወደ ግብፅ ተሻግረዋል። ይህ የድንበሩ መተላለፊያ ለዓመታት ሲከፈት እና ሲዘጋ ነው የኖረው። ለመሆኑ የድንበር በሩ ጉዳይ ለግብፅ አሳሳቢ ጉዳይ የሆነው ለምንድን ነው? በእስራኤል- ጋዛ ግጭትስ የግብፅ አቋም ምንድን ነው?ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  20. የታተመዉ 0:35 8 ህዳር 20230:35 8 ህዳር 2023ሂዩማን ራይትስ ዎች በአምቡላንስ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ እንደ ጦር ወንጀል ሊመረመር ይገባል አለአምቡላንስReutersCopyright: Reutersዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዎች እስራኤል በጋዛ በአምቡላንስ ላይ ጥቃት መሰንዘሯ እንደ ጦር ወንጀል መመርመር አለበት አለ።ከጥቂት ቀናት በፊት የእስራኤል ጦር በጋዛ አል-ሺፋ ሆስፒታል አቅራቢያ አምቡላንስ መምታቱ ይታወሳል።እስራኤል በአምቡላንሱ ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ያመነች ሲሆን ተሸከርካሪውን ዒላማ ያደረገችው የሐማስ አባላት እየተጠቀሙበት እንደነበረ መረጃው ስለነበረኝ ነው ብላለች።ሂዩማን ራይትስ ዎች ግን ከጥቃቱ በኋላ የተነሱ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን መመልከቱን እንዲሁም የዓይን እማኞችን ማነጋገሩን ጠቅሶ በጥቃቱ 5 ሕጻናትን ጨምሮ 21 ሰዎች ተገድለዋል ብሏል።ሂዩማን ራይትስ ዎች ጨምሮም አምቡላንሱ ወታደራዊ ዓላማን ለማስፈጸም ጥቅም ላይ ስለመዋሉ ምንም አይነት ማስረጃ አላገኘሁም ብሏል።