
የዋልያዎቹ አሰልጣኝ በአሜሪካ መቅረታቸው ተሰማ ! በምትካቸው ገብረመድህን ቡድኑን ተረክቧል።
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ቴክኒካል ዳይሬክተር እና የብሔራዊ ቡድኑ ጊዜያዊ አሰልጣኝ የነበሩት ኢንስትራክተር ዳንኤል ገ/ማርያም ወደ አሜሪካ ሄደዋል እንደማይመለሱም ተናግረዋል ። የቴክኒክ ዳይሬክተሩ ስራ እና ሀላፊነታቸውን አቀላጥፎ ለመስራት ምቹ ሁኔታ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ስር ባለመኖሩ ምክንያት ላይመለሱ አሜሪካ መኮብለላቸው ተሰምቷል ።
ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ቴክኒካል ሀላፊነት ስር የሚገኙ ሀላፊዎች አቶ ቴዎድሮስ ፍራንኮ አሜሪካ ላይ መቅረታቸው ይታወቃል ወ/ሮ አልማዝ ፍስሀ ደግሞ በአውስትራሊያ ለስብሰባ ብለው እዛው እንደቀሩ ይታወቃል አሁን ደግሞ ተረኛው ቴክኒካል ዳይሬክተር ኢንስትራክተር ዳንኤል ገ/ማርያም ሆነዋል ። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን በድጋሚ ቴክኒካል ዳይሬክተር አልባ ሆኗል ፤ በዚህ ቦታ ላይ ስራቸውን ለመስራት የሚቀጠሩ ባለሞያዎች ለምን ከሀገር ይወጣሉ ለምንስ ይሰደዳሉ ?
መረጃው @ ስፖርት ዞን-