
ከ 5 ሰአት በፊት
የተዋናዩ ሮበርት ዲ ኒሮ ድርጅት የቀድሞ ሠራተኛ ግራሀም ቼስ ሮቢንሰን ላይ ባደረሰው የጾታ መድልዎና በቀል ምክንያት 1.2 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ታዘዘ።
የቀድሞዋ ሠራተኛ ግራሀም የሮበርት ዲ ኒሮን ‘ካናል ፕሮዳክሽን’ ፍርድ ቤት አቁማ ለዓመታት ተሟግተዋል።
የከሰሰችው 12 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፈላት ነበር።
ብዝበዛና ንቀት እንደደረሰባት፣ አነስተኛ ክፍያ እንደተሰጣትና የዲ ኒሮ ‘የቢሮ ሚስት’ እንደሆነች እንዲሰማት መደረጉን በፍርድ ቤት ገልጻለች።
ለ11 ዓመታት ነው ለዲ ኖሮ የሠራችው።
የግል ረዳቱ ሆና ስትሠራ ቆይታ የድርጅቱ ፕሮዳክሽንና ፋይናንስ ምክንትል ፕሬዝዳንት ሆናለች።
- የመንግሥት ኃይሎች ላሊበላ ከተማን መልሰው መቆጣጠራቸው ተነገረ9 ህዳር 2023
- በምሥራቅ ሐረርጌ በውርስ ምክንያት አባቱን በመግደል የተጠረጠረው በቁጥጥር ሥር ዋለ9 ህዳር 2023
- በምዕራብ ሐረርጌ የባለቤቱን መራቢያ አካል በእሳት ያቃጠለው በጽኑ እስራት ተቀጣከ 6 ሰአት በፊት
በ2019 ከመሥሪያ ቤቱ ወጥታ “የስሜት ጫና ደርሶብኛል። በጎ ስሜም ጠፍቷል” ስትል ከሳለች።
ዲ ኒሮ “ልቅና ያልተገባ ጾታዊ አስተያየት እንደሚሰጥ” እንዲሁም “በዘልማድ የሴት ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ኃላፊነቶችን እንደሚሰጥ” ተናግራለች።
ዲ ኒሮ ብዝበዛ እንዳልፈጸመ ተናግሯል። አንዳንዴ ቁጡ ቢሆንም ክሱ እውነት እንዳልሆነ ተከራክሯል።
ድርጅቱ የቀድሞዋን ሠራተኛ መልሶ በ6 ሚሊዮን ዶላር ከሷል። ይህም የድርጅቱን ገንዘብ ያላግባብ በመጠቀም፣ ከድርጅቱ በመስረቅና ከ450 ሺህ ዶላር በላይ የድርጅቱን የአየር መንገድ ማይል ወደ ግሏ በማዞር ነው።
ሆኖም ግን ይህ ክስ በፍርድ ቤት ተቀባይነት አላገኘም።

በፍርድ ቤት ውሳኔ ደስተኛ እንደሆኑ የከሳሿ ጠበቃ ተናግረዋል።
“እኛ ያየነውን ፍርድ ቤቱም በማየቱ ደስ ብሎናል” ብለዋል።
ዲ ኒሮ ለምስክርነት ሲጠራ ምንም ብዝበዛ አልፈጸምኩም ብሎ ተከታክሮ ከሳሹን “አሳፋሪ ነገር ነው ያደረግሽው” ብሏል።
ሆኖም ግን ቢያንስ ሁለት ጊዜ ጀርባውን እንድታክለት እንደጠየቀ አምኗል።
ወደ ሌላ ኃላፊነት ለመሻገርና ደመወዟ እንዲጨምር ብትጠይቅም ሥራዋ ግን የተለየ እንዳልነበር ተናግሯል።
ከሳሿ ግን በማንኛውም ሰዓት ስልክ እንድታነሳ እንደሚጠበቅባት፣ ዓመት በዓል እንኳን እንደማታርፍና ይጮህባት እንደነበር ተናግራለች።
“የስሜትና አእምሮ መሰበር” ከገጠማት በኋላ ሥራውን ጥላ እንደወጣች ተናግራለች።
ጭንቀትና ድባቴ እንደገጠማት፣ ከማኅበራዊ ትስስር እንደወጣችም ገልጻለች።
“ሕይወቴን አጣሁ። ሥራዬን አጣሁ። ገንዘቤን አጣሁ። ሁሉንም ነገር አጣሁ” ብላለች።