November 10, 2023 

ከወልድያ ከተማ በቅርብ ርቀት ባሉ ገጠራማ መንደሮች ላይ ውጊያ ሲካሄድ አርፍዷል!

በጉባላፍቶ ወረዳ ሰዋ ሜዳ፣ ዋንዛየ፣ አማየ ሚጫ እና ጋላ ጊዮርጊስ ዙሪያ የከባድ መሣሪያ ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል።

በተጨማሪም ከቃሊም ትይዩ ባሉ ጃርሳ መዳህኒአለም እና ቀይ አምባ በተባሉ ቀበሌዎችም የመድፍ ድብደባ ሲፈፀም ማርፈዱን ነው የአማራ ድምፅ የቀይ አምባ ቀበሌ ነዋሪዎችን በማነጋገር ለማረጋገጥ የቻለው።

ጦጣ ማደሪያ ዙሪያ ጥቁር ውሃ እና መቻሬ ሜዳ ላይ የተጠመደ መድፍ ነው እነዚህ አከባቢዎችን ሲደበድብ የዋለው ተብሏል።
👉

በራያ ቆቦ ወረዳ የተኩለሽ ጤና ጣቢያ ሰራተኞች ህክምና እንዳይሰጡ በአገዛዙ ወታደር የታገዱ ሲሆን በዚህም ለ42 ሺ በላይ የአከባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ጤና ጣቢያው መዘጋቱን የአማራ ድምፅ ለማረጋገጥ ችሏል።

የብልፅግና ፓርቲ ወታደር የጤና ተቋማትን በመዝጋት ህዝቡን ህክምና መከልከልን እና አስገድዶ መድፈርን እንደ አንድ የጦር መሣሪያ እየተጠቀመበት መሆኑ ተገልጿል።
👉

ከፊል የሃይቅ ከተማን ጨምሮ የማርየ እና የደላንታ አከባቢዎች በፋኖ ቁጥጥር ገብተዋል።

ምንጭ አሻራ ሚዲያ