ዛፍ

ከ 6 ሰአት በፊት

የ300 ዓመት ዕድሜ ያለው ዝነኛ የኮላ ዛፍ በደቡብ ጋና ከተቆረጠ በኋላ አንድ ግለሰብ ፍርድ ቤት ቀረበ።

ፌይሴ በተባለው ግዛት የነበረው ዛፍ ተቆርጦ ምሥሉ ከታየ በኋላ ጋናውያን ቁጣቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ገልጸዋል።

ዛፉ በኣሻንቲ ዘመነ መንግሥት የነበረና የዘመናዊ ጋና ታሪከe አካል ተደርጎ የሚወሰድም ነበር።

የማዳን አቅም አለው ተብሎ ከመታመኑም ባሻገር የጋናውያን እንዲሁም የቱሪስቶች መዳረሻ ነበር።

ስሙ ያልተጠቀሰው ግለሰብ ዛፉን አልቆረጥኩም ብሎ ተከራክሮ በዋስ ተለቋል።

በ1970ዎቹ ታዋቂው ቄስ ሞምፎ አንኮዬ የኮላ ፍሬ ተፍተው ዛፉ እንደበቀለ ይታመናል።

ጥቁርና ነጩ የኮላ ፍሬ ሕመም እንዲሁም እርግማን እንደሚያድን በርካቶች ያምናሉ።

የጋና የንግድ ቀጠና ኩማሲ ከቦሶምታዌ ወንዝ ጋር በሚገናኝበት መንገድ ላይ ነበር ዛፉ።

ዝነኛ ዛፍ ስለሆነ አውራ ጎዳና ሲሠራ አልተቆረጠም።

አሁን ለምን እንደተቆረጠ ግልጽ አይደለም።

የአሻንቲ ንጉሣዊ ቤተሰብ መቀመጫ በሆነው ማንሀያ ቤተ መንግሥት የጥናት ዳይሬክተር ቦንሱ ሳፎ ካታንካ ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ ዛፉ ያለበት ቦታ በአሻንቲ ሥርወ መንግሥት ታሪክ ከፍተኛ ቦታ አለው።

የፈይሲ ውጊያ የአሻንቲ ሕዝብ ከዴንኬርያ አገዛዝ ራሱን ነጻ ለማውጣት የታገለበት ነው።

አጥኚው እንዳሉትም ዛፉ ያለበት ቦታ “የአሻንቲ ሕዝብ የዴንኬርያ ሕዝብ ያሸነፈበት” ነው።

ኮምፎ አንኮዬ የተባለው ከዛፉ ጀርባ እንዳለ የሚታመነው ቄስ በሕይወት ባሉና በመናፍስት መካከል የሚደራደር ሰው እንደሆነ ይታመናል።

በሥነ ቃል እንደሚነገረው ከሆነ ይህ ሰው መሬት ውስጥ ጎራዴ ቀብሯል።

የቀበረው ጎራዴ አሁንም መሬት ውስጥ ያለ ሲሆን ማንም ነቅሎ ሊያወጣው አይችልም።

ይህ ጎራዴ ይገኛል የተባለው በሰውየው በተሰየመና ኩማሱ በተባለ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው።

ሲያደርጋቸው የቆውን ለማስታወስ ዛፉ ተምሳሌታዊ ነበር።