Related Video and Audio

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59
Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ
- BBC
Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች
- BBC
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች
- BBC
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC
ጭምቅ ሃሳብ
- ማክሮን እስራኤል ሕጻናት እና ሴቶችን በቦምብ ከመደብደብ ትቆጠብ አሉ
- የእስራኤል ታንኮች ከጋዛ ሆስፒታሎች አቅራቢያ ታዩ
- የሔዝቦላ መሪ ነስራላህ ዛሬ ንግግር ያደርጋሉ ተባለ
- አረብ እና ሙስሊም አገራት ዛሬ በሳዑዲ ሊመክሩ ነው
- በእስራኤል ጦር የተከበበው ሆስፒታል ነዳጅ ጨርሶ ሥራ አቆመ
- እስራኤል በየቀኑ ለአራት ሰዓታት የተኩስ አቁም ፋታ ልትሰጥ ነው
- ኔታኒያሁ ጋዛን የመውረር፣ መያዝ ወይም የማስተዳደር ፍላጎት የለንም አሉ
- እስራኤል 10 ሰዓታት ከፈጀ ወጊያ በኋላ የሐማስ ጠንካራ ይዞታን ያዝኩ አለች
- ቀይ መስቀል የእርዳታ መኪናው በጋዛ እንደተመታ አስታወቀ
- የእስራኤል ጦር በጋዛ 130 የሐማስ ዋሻዎችን ማውደሙን አስታወቀ
- ተመድ እስራኤል እና ሐማስን የጦር ወንጀሎች በመፈጸም ከሰሰ
- ከጦርነቱ በኋላ እስራኤል ጋዛን ይዛ መቆየት እንደሌለባት አሜሪካ አስጠነቀቀች
- እስራኤል መሃል ጋዛ ከተማ ገባሁ አለች
- ኔታንያሁ ከጦርነቱ በኋላ የጋዛ ሰርጥ ‘የጸጥታ ኃላፊነት’ የእስራኤል ይሆናል አሉ
- ሐማስ በእስራኤሉ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎችን አልገደልኩም አለ
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 4:204:20በእስራኤል ጦር የተከበበው ሆስፒታል ነዳጅ ጨርሶ ሥራ አቆመ
ReutersCopyright: Reutersአል-ሺፋ ሆስፒታል ከሦስት ቀናት በፊትImage caption: አል-ሺፋ ሆስፒታል ከሦስት ቀናት በፊትበእስራኤል ጦር ከበባ ስር የገባው አል-ሺፋ ሆስፒታል ነዳጅ በመጨረሱ ስራ ማቆሙን በሐማስ የሚተዳደረው ጤና ሚንስቴር አስታወቀ።ከትናንት አርብ ምሽት ጀምሮ የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ከተማ የሚገኘውን ሆስፒታል ከበው መያዛቸው ተዘግቧል።የጤና ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆስፒታሉ ነዳጅ በመጨረሱ ስራ አቁሟል ብለዋል። “በማሞቂያ ክፍል ውስጥ የነበረ ጨቅላ ሕይወቱ አልፏል። ሌሎች 45 ጨቅላዎች በሆስፒታሉ አሉ” ሲሌ አሽራፍ አል-ቂድራ ተናግረዋል።የድምበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አባል የሆኑት ሐኪም የተኩስ አቁም ካልተደረገ ወይም የሕክምና እርዳታ እንዲገባ ካልተደረገ “በሆስፒታሉ ያሉ ታካሚዎች በሙሉ አልቀው ሆስፒታሉ ወደ መቃብር ስፍራነት ይቀየራል” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።ዶ/ር መሐመድ አቡ የተባሉት ሐኪም ለቢቢሲ ሲናገሩ በሆስፒታሉ የሕጻናት ክፍል ውስጥ ይሰሩ የነበሩ የድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ባለሙያዎች በሽተኞችን ጥለው ለመሸሽ ተገደዋል።ሐኪሙ ጨምረው እንደተናገሩት የሕክምና ግብዓቶች ከፍተኛ እጥረት ስላለ ቀዶ ሕክምናዎች ያለ ማደንዘዣ እየተከናወኑ ነው ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:253:25በለንደን ለፍልስጤም ድጋፍ ለሚሰጥ ትልቅ ሰልፍ ሊደረግ ነው
ReutersCopyright: Reutersከአንድ ሳምንት በፊትም በለንደን ከተማ ለፍልስጤማውያን ድገፍ የሚሰጥ ሰልፍ ተካሂዶ ነበር።Image caption: ከአንድ ሳምንት በፊትም በለንደን ከተማ ለፍልስጤማውያን ድገፍ የሚሰጥ ሰልፍ ተካሂዶ ነበር።የለንደን ፖሊስ በከተማዋ ትልቅ ለፍልስጤም ድጋፍ የሚሰጥ ስልፍ ሊደረግ መሆኑን ገለጸ።ሰልፉ በከተማዋ ከሚገኘው ግዙፉ ሃይድ ፓርክ እስከ የአሜሪካ ኤምባሲ የሚደረግ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ ለፍልስጤማውያን ድጋፍ ለመስጠት የሚወጡ ሰዎች በአይሁድ እና በሙስሊሙ ማኅብረሰብ ውስጥ ያለው ስጋት እና ጭንቀት እንዳይዘነጉ ጠይቀዋል።ከአንድ ሳምንት በፊትም በለንደን ከተማ ለፍልስጤማውያን ድገፍ የሚሰጥ ሰልፍ ተካሂዶ ነበር።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:052:05በአውስትራሊያ በፍልስጤም እና እስራሌል ደጋፊዎች መካከል ግጭት ተከሰተበአውስትራሊያዋ ሁለተኛዋ ትልቋ ከተማ ሜልበርን በፍልስጤም እና በእስራኤል ደጋፊዎች መካከል ግጭት መፈጠሩ ተዘገበ።የአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ኤቢሲ በግጭቱ ወቅት ሰዎች በውሃ የተሞሉ ፕላስቲክ ጠርሙሶችን መወራወራቸውን እና ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ስድቦች መሰንዘራቸውን ዘግቧል።በሁሉቱም ወገን ከ400 ያላነሱ ሰዎች አደባባይ መውጣታቸው ፖሊስ ያስታወቀ ሲሆን ግጭቱን ተከትሎ አንድ ሰው በቁጥጥር ስር መዋሉን ጨምሮ አስታውቋል።በግጭቱ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የተባለ ነገር የለም።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:491:49በምስል፡ ለፍልስጤማውያን ድጋፍ በኒው ዮርክበአሜሪካዋ ኒው ዮርክ ለፍልስጤማውያን ድጋፍ ለመግለጽ ሰልፍ ተካሄደ።ሰልፈኞቹ በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ መጠየቃቸውን አሶሽዬትድ ፕሬስ ዘግቧል።ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዘገባዎቹ ለእስራኤል ያደሉ ናቸው ሲሉ ሰልፈኞቹ ድምጻቸውን ከመስራ ቤቱ ፊት ለፊት አሰምተዋል።
APCopyright: AP
APCopyright: AP
APCopyright: APArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:401:40አረብ እና ሙስሊም አገራት ዛሬ በሳዑዲ ሊመክሩ ነው
BBCCopyright: BBCሳዑዲ አረቢያ የአረብ ሊግ አባል አገራትን እና የእስላማዊ ትብብር ድርጅት አባላትን ለአስቸኳይ ስብበሳ ዛሬ ሪያድ ላይ ጠርታለች።የአረብ እና ሙስሊም አገራቱ የስብሰባ አጀንዳ በጋዛ ያለው ጦርነት እና እርሱን ተከትሎ የመጣው የሰብዓዊ ቀውስ ይሆናል ሲል ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።የስብሰባው ዓላማ ለፍልስጤማውያን ድጋፍ መስጠት እና እስራኤል በጋዛ እያደረገች ያለችው ወረራ እና ድብደባ እንድታቆም ዓለም አቀፍ ጫናን ማሳደር ነው ተብሏል።የስብሰባው ተሳታፊዎችም ሪያድ እየገቡ ነው።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:331:33የሔዝቦላ መሪ ነስራላህ ዛሬ ንግግር ያደርጋሉ ተባለ
JAMARANCopyright: JAMARANየሔዝቦላ መሪ ሐሰን ነስራላህImage caption: የሔዝቦላ መሪ ሐሰን ነስራላህየሔዝቦላ መሪ ሐሰን ነስራላህ ዛሬ ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ያደርጋሉ ተባለ።መቀመጫውን ሌባኖስ ያደረገው የጠንካራው ሔዝቦላ መሪ ዛሬ ከሰዓት የሚያደርጉት ንግግር የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ሁለተኛው ይሆናል።በእስራኤል-ጋዛ ጦርነት ሔዝቦላህ በቀጣይ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ሐሰን ናስራላህ ዛሬ በሚያደርጉት ንግግራቸው ሊጠቁሙ ይችላሉ ተብሏል።ከአንድ ሳምንት በፊት በነበረው ንግግራቸው ጦርነቱን በመለከተ “ሁሉም አማራጭ በጠረቤዛ ላይ ነው” ብለው ነበር።ስለ ሔዝቦላው መሪ የተመለከተውን ዘገባ እነዚህ ያንብቡ፡የእስራኤል ስጋት የሆነው የሔዝቦላህ መሪው ሐሰን ናስራላህ ማን ናቸው?Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:380:38የእስራኤል ታንኮች ከጋዛ ሆስፒታሎች አቅራቢያ ታዩ
BBC VerifyCopyright: BBC Verifyትናንት አርብ የእስራኤል ታንኮች ከጋዛ ሆስፒታሎች አቅራቢያ መገኘታቸውን ተከትሎ በጤና ተቋሟቱ ውስጥ እና አቅራቢያ ፍንዳታዎች እንደነበሩ የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል።ታንኮቹ አል-ሺፋ፣ አል-ቁዱስ፣ አል-ራንቲሲ እና ከኢንዶኔዢያ ሆስፒታል አቅራቢያ ታይተዋል።እስራኤል ቀደም ሲል ሐማስ በሰላማዊ ሰዎች መሠረተ ልማቶች ስር ዋሻዎችን ቆፍሯል ብላለች።ቢቢሲ አል-ናስር ከሚባል ሆስፒታል የሚሸሹ ሰዎች በእስራኤል ጦር እንዳይመቱ ነጭ ጨርቅ ሲያውለበልቡ የሚያሳየውን ምስል ትክክለኛነት አረጋገጧል።በሐማስ የሚመራው የጋዛ የጤና ሚኒስቴር በጦርነቱ እስካሁን የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 11,078 ከፍ ማለቱን ይፋ አድርጓል።እንደ ጤና ሚኒስቴሩ ከሆነ በእስራኤል ጥቃት ከተገደሉት ፍልስጤማውያን መካከል አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ሕጻናት እና ሴቶች ናቸው።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:280:28ማክሮን እስራኤል ሕጻናት እና ሴቶችን በቦምብ ከመደብደብ ትቆጠብ አሉ
BBCCopyright: BBCፕሬዝዳንት ማክሮንImage caption: ፕሬዝዳንት ማክሮንየፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እስራኤል በጋዛ ያሉ ሕጻናት እና ሴቶችን በቦምብ ከመደብደብ መቆጠብ አለባት አሉ።ፕሬዝዳንቱ ከቤተ-መንግሥታቸው ሆነው ለቢቢሲ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ለድብደባዎቹ “ምንም አይነት ማሳመኛ” የለም ያሉ ሲሆን የተኩስ አቁም ቢደረግ ተጠቃሚዋ እስራኤል ነች ብለዋል።የእስራኤልን እራስን የመከላከል መብት ብናምንም፤ በጋዛ “እያደረጉት ያሉትን ድብደባ እንዲያቆሙ እንጠይቃለን” ብለዋል።ፕሬዝዳንት ማክሮን አገራቸው የሐማስን “የሽብር” ተግባራት “በግልጽ ትቃወማለች” ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ አሜሪካ እና ዩኬን ጨምሮ ሌሎች አገራትም የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ ያቀርባሉ ብዬ እጠብቃለሁ ብለዋል።ይህ የፕሬዝዳንቱ ንግግር እስራኤልን አላስደሰተም። ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ መንግሥታት ማውገዝ ያለባቸው ሐማስን እንጂ እስራኤልን መሆን የለበትም ብለዋል።ጠቅላይ ሚንስትሩ ጦራቸው ሰላማዊ ሰዎች ለመለየት ቢጥርም ሐማስ ግን እነርሱን መሸሸጊያ አድርጓል ብለዋል።“ዛሬ በሐማስ-አይሲሲ የተፈጸመው ወንጀል ነገ በፓሪስ፣ ኒው ዮርክ እና በመላው ዓለም ይፈጸማል” ሲሉ ኔታኒያሁ ባወጡት መግለጫ አስጠንቅቀዋል።ፈረንሳይ ልክ እንደ እስራኤል፣ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ሌሎች ምዕራባውያን አገራት ሐማስን አሸባሪ ድርጅት ስትል ፈርጃለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 9:55 10 ህዳር 20239:55 10 ህዳር 2023ጋዛ ውስጥ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ11 ሺህ በላይ መሆኑ ተነገረ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበሐማስ የሚመራው የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ዛሬ አርብ ከሰዓት በኋላ ባወጣው መግለጫ በጦርነቱ አስካሁን የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 11,078 ከፍ ማለቱን አመለከተ።ሰላሳ አምስት ቀናት ባስቆጠረው እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እያካሄደችው ባለው ወታደራዊ ዘመቻ ከተገደሉት ፍልስጤማውያን መካከል አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ሕጻናት እና ሴቶች ናቸው።የጤና ባለሥልጣናቱ ካወጡት 11,078 የሟቾች አሃዝ ውስጥ 4,506ቱ ሕጻናት እና ከ3,000 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ተጠቅሷል።በሐማስ የበላይነት የሚመራው የጤና ሚኒስቴር በቴሌግራም ገጹ ላይ ባሰራጨው መረጃ ላይ ከተገደሉት ከ11 ሺህ በላይ ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች ከ27,000 የሚልቁት ጉዳት ደርሶባቸዋል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጦርነቱን ሰለባዎች ከዚህ በፊት ከተደረጉት ግጭቶች ጋር በማነጻጸር እንዳለው የአሁኑ የሟቾች ቁጥር ከፍተኛ ነው።ሐማስ ጋዛን ከተቆጣጠረበት ከ2007 (እአአ) በኋላ በተለያዩ ጊዜያት በተካሄዱ ግጭቶች በጋዛ ሰርጥ ውስጥ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 5,400 ያህል ነበር። የአሁኑ ግን ከዚህ በእጥፍ ከፍ ማለቱን ድርጅቱ አመልክቷል።አሜሪካ እና አስራኤል የሟቾችን አሃዝ በተመለከተ በሐማስ ከሚመራው የጤና ሚኒስቴር የሚወጣው መረጃ በጥንቃቄ ሊታይ ይገባል ሲሉ፣ የዓለም የጤና ድርጅት ግን ቁጥሩ የሚታመን ነው ብሏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 9:38 10 ህዳር 20239:38 10 ህዳር 2023በጦርነቱ 35ኛ ቀን ዛሬ አርብ በጋዛ ዋና ዋና ክስተቶችከተጀመረ 35 ቀናትን ያስቆጠረው የጋዛ-እስራኤል ጦርነት ተባብሶ ቀጥሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት በመቅጠፍ፣ ጋዛ ውስጥ ከባድ ሰብዓዊ ቀውስን አስከትሏል። የዛሬ አርብ ዋና ዋና ክስተቶች. . .በሐማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር አስካሁን ድረስ 11,078 ሰዎች ጋዛ ውስጥ መገደላቸውን እና ከ27,000 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን አሳውቋል።የዐይን እማኞች ለቢቢሲ እንደተናገሩት የእስራኤል ኃይሎች ጋዛ ውስጥ ወደሚገኙ ወደ ዋና ዋናዎቹ የአል-ሺፋ፣ የአል-ቁዱስ እና የኢንዶኔዢያ ሆስፒታሎች እየተቃረቡ ነው። በተጨማሪም ከሆስፒታሎቹ ውስጥ ወይም አቅራቢያ ፍንዳታዎች እንደተከሰቱ ዘገባዎች እየወጡ ነው።እስራኤል በበኩሏ ጦር ሠራዊቷ በአል-ሺፋ አቅራቢያ ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን አረጋግጣ፣ ነገር ግን በሆስፒታሉ አቅራቢያ እየተካሄደ ስላለው ነገር መረጃ ከመስጠት ተቆጥባለች።ከጋዛ ከተማ የወጣ አንድ የቪዲዮ ምስል እንዳሳየው የእስራኤል ታንኮች ከአል-ራንቲሲ የሕጻናት ሆስፒታል ውጪ ቦታ ይዞ አሳይቷል። ወታደሮች በድምጽ ማጉያ ከሆስፒታሉ ውስጥ ሠራተኞች ወይም ታካሚዎች ያልሆኑ ሰዎች ለቀው እንዲወጡ ሲጠይቁ እንደነበር የዐይን እማኞች ተናግረዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:16 10 ህዳር 20238:16 10 ህዳር 2023“ሐሎ! ከእስራኤል ደኅንነት ቢሮ ነው የምደውለው። ቤትህን ልናጋየው ትዕዛዝ ተሰጥቶናል”
BBC/GETTYCopyright: BBC/GETTYዶ/ር ማሕሙድ ሻሒንImage caption: ዶ/ር ማሕሙድ ሻሒንዶ/ር ማሕሙድ ሻሒን የጥርስ ሐኪም ነው።ሐሙስ ጥቅምት 8/2016 ዓ.ም. ድንገት ስልኩ ጠራ። የሞት ጥሪ ይሆናል ብሎ አልጠበቀም።በዚያ ላይ ገና ከጠዋቱ 12፡30 ነው።ሲፈራ ሲቸር፤ ስልኩን አነሳው።“ሐሎ፣ ከእስራኤል ደኅንነት ቢሮ ነበር የምደውለው። ያለህበትን ሕንጻ ልናጋየው ትዕዛዝ ተሰጥቶናል።”ዶ/ር ማሕሙድ ይህን ጥሪ ቀልድ ነው ማለትን መረጠ። ነገር ግን ከዚያች ዕለት በፊት ለተከታታይ 12 ቀናት እስራኤል በጋዛ ያሉ ሕንጻዎችን ወደ ትቢያነት ስትቀይር ነበር።ስለዚህ የስልክ ጥሪው ቀልድ ተብሎ ሊታለፍ አይችልም።የዶ/ር ማሕሙድ ሰፈራቸው አል ዛሕራ ይባላል። በጣም ሰላማዊ ሰፈር ነው። መካከለኛ ገቢ ያላቸው ጋዛውያን የሚኖሩበት ሰፈር ነው።እሱ የሚኖረው በሦስተኛው ወለል፣ ሦስት መኝታ ቤት ባለው አንድ አፓርትመንት ነው።እስከዚያች የስልክ ጥሪ ዕለት ድረስ በጋዛ ያሉ ሁሉ ውድመት ሲደርስ በሰፈራቸው አንዲት ሕንጻ አልተነካችም ነበር።“ከእስራኤል ደኅንነት ነው የምንደውልልህ፣ ዶክተር። መፍጠን ይኖርብሃል።”ይህ ጥሪ ዶ/ር ማሕሙድ በሕይወቱ ከተቀበላቸው የስልክ ጥሪዎች አስፈሪው ነበር። ሙሉውን እዚህ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:32 10 ህዳር 20233:32 10 ህዳር 2023እስራኤል ሥጋ በል አእዋፋትን በመከተል የሞቱ ዜጎቿን አስክሬን እያነሳች ነው
RSPBCopyright: RSPBየእስራኤል ጦር የሥጋ በል አእዋፋት እንቅስቃሴን በመከተል የሟች ዜጎችን አስክሬን ፈልጎ እያገኘ መሆኑ ተሰማ።ሐማስ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. በእስራኤል ላይ የተፈጸመውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ ከ1400 በላይ እስራኤውያን ተገድለዋል መባሉ ይታወሳል።ታዲያ የአገሪቱ ጦር እስካሁን በተለያዩ ቦታዎች ወድቀው የሚገኙ አስክሬኖችን እያነሳ ስለመሆኑ ተመልክቷል።የአስክሬኖች መገኛን ለመጠቆም የእስራኤል የተፈጥሮ እና ፓርክ ባለሥልጣን ባልደረባ የሆኑት ኦሃድ ሃትዞፍ እንደ ንስር ያሉ ሥጋ በል አእዋፋትን የበረራ አቅጣጫ በመከተል እንዲሁም የሚቆሙባቸውን ቦታ በመለየት መረጃውን በማጋራት ጦሩ አስክሬኖችን እንዲያነሳ እየረዱ ነው።አእዋፋቱ ላይ የአቅጣጫ ጠቋሚ (ጂፒኤስ) የተገጠመ ሲሆን፣ የበረራ አቅጣጫቸውን በመከተል ባለፉት ሁለት ሳምንታት የአራት ሰዎች አስክሬን መነሳቱን ባለሙያው ገልጸዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:13 10 ህዳር 20231:13 10 ህዳር 2023የዩናይትድ ስቴትስ እና አጋሮቿ ባለፉት ሦስት ሳምንታት 46 ጥቃቶች ተፈጽሞባቸዋል- ፔንታጎንፔንታጎን በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች ላይ የደረሱ ጥቃቶችን በተመለከተ መረጃ አጋርቷል።ከጥቅምት 6 ጀምሮ በአሜሪካ እና በጥምር ኃይሎች ላይ “አንድ ጊዜ የተደረጉ የሰው አልባ አውሮፕላን እና የሮኬት ጥቃቶችን ጨምሮ ቢያንስ 46 ጊዜ” ጥቃት እንደደረሰባቸው አስታውቀወል።ጠቃቶቹ በኢራቅ 24 ጊዜ እና በሶሪያ 22 ጊዜ መድረሳቸው ተገልጿል።በእነዚህ ጥቃቶች 56 ሰዎች መጎዳታቸውን ፔንታጎን አክሎ ገልጿል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:56 10 ህዳር 20230:56 10 ህዳር 2023በጋዛ የሚገኙ የውጭ ሚዲያ ጋዜጠኞች ስለሐማስ ጥቃት ቀድመው ያውቁ ነበር ስትል እስራኤል ከሰሰችየእስራኤል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትር ሐማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ሊሰነዝር መሆኑን ቀድመው የሚያውቁ መቀመጫቸውን በጋዛ ያደረጉና ለምዕራባዊያን መገናኛ ብዙሃን የሚሠሩ አራት ጋዜጠኞች እንደነበሩ አስታወቀ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:56 10 ህዳር 20230:56 10 ህዳር 2023ትምህርት ቤት ላይ በድሮን ጥቃት ያደረሰውን ቡድን መምታቷን እስራኤል ገለጸችሐሙስ ዕለት በደቡባዊ እስራኤል በሚገኝ ትምህርት ቤት ላይ ከደረሰው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ጀርባ ይገኛል ያለውንና መቀመጫውን በሶሪያ ያደረገውን ድርጅት መምታቱን የእስራኤል ጦር አስታወቀ።ሰው አልባ አውሮፕላኑ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ቢመታም ምንም ጉዳት አላደረሰም።”ከሶሪያ የመጣው ድሮን በኤላት ትምህርት ቤት ላይ ላደረሰው ጥቃት ምላሽ ለመስጠት የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ጥቃቱን ያደረሰውን ድርጅት መትቷል” ሲል ኤክስ ላይ አስፍሯል።ጦሩ የቡድኑን ማንነት ባይገልጽም፤ “ከግዛቱ ለሚነሱት የሽብር እንቅስቃሴዎች የሶሪያን አስተዳደር ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳል” ብሏል።ሶሪያ ለእስራኤል መግለጫ እስካሁን ምላሽ አልሰጠችም።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:20 10 ህዳር 20230:20 10 ህዳር 2023ኳታር ምዕራባውያን አሸባሪ ያሉትን ሐማስ ለምን አስጠለለች? ማደራደሩስ ይሳካላታል?መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ሐማስ በፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት ከ1400 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ከ200 ሰዎች በላይ አግቶ ወስዷል። ታጋቾቹን የማስለቀቁ ተግባር ለትንሿ በነዳጅ የበለጸገች አገር ኳታር ተሰጥቷል። የሐማስ አንዱ ቢሮ የሚገኘው በኳታር ነው። ከአረብ አገራት ለምዕራባውያን ቅርብ አጋር እንደ ኳታር ያለ ብዙም የለም። አሁን የታጋቾቹ ሕልውና በኳታር እጅ ላይ የወደቀ ይመስላል? ለምን?ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 23:51 9 ህዳር 202323:51 9 ህዳር 2023ተመድ 99 ሠራተኞቹ በጋዛ መገደላቸውን ገለጸ
BBCCopyright: BBCየእስራኤል ሐማስ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በጋዛ ሰርጥ 99 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞች መገደላቸው ተገለጸ።የተመድ የፍልስጤማውያን ስደተኞች ኤጀንሲ ተቋም ቃል አቀባይ 99 ባለደረቦች መገደላቸውን ተናግረዋል።ጁሊዬት ቱማ ለቢቢሲ ሲናገሩ የተመድ ተቋም በ150 መጠለያ ጣቢያዎች ከ700 ሺህ ያላነሱ ፍልስጤማውያንን እየረዳ ቢሆንም ባልደረቦቻችን ግን አሁንም መገደላቸው ቀጥሏል ብለዋል።ቃል አቀባይዋ ተቋማቸው የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ የግብዓት ችግር በከፍተኛ መጠን እያጠረው መሆኑንንም ጨምረው ተናግረዋል።እርዳታ ለማድረስ ሁለት ነገር ያስፈልገናል ብለዋል ጁሊዬት፤ ነዳጅ እና ለሰብዓዊነት ሲባል የሚደረግ የተኩስ አቁም።ሐማስ እስራኤል ላይ መስከረም 26 ጥቃት ካደረሰ ወዲህ ወደ ጋዛ ነዳጅ እንዲገባ አልተፈቀደም። እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ሐማስ ደብቆ ይዞ እንጂ በቂ ነዳጅ አለ ትላለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 23:43 9 ህዳር 202323:43 9 ህዳር 2023ኔታኒያሁ ጋዛን የመውረር፣ መያዝ ወይም የማስተዳደር ፍላጎት የለንም አሉ
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁImage caption: የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁየእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ አገራቸው ከሐማስ ጋር የምታደርገው ጦርነት ካበቃ በኋላ የጋዛ ሰርጥን ወርራ የመያዝ፣ ተቆጣጥሮ የመቆየት ወይም የማስተዳደር ፍላጎት የላትም አሉ።ጠቅላይ ሚንስትሩ ለፎክስ ኒውስ ሲናገሩ “ጋዛን የመውረር ፍላጎት የለንም፣ ጋዛን የመቆጣጠር ፍላጎት የለንም፣ ጋዛን የማስተዳደር ፍላጎት የለንም” ካሉ በኋላ ጋዛን የሚያስተዳደር የሲቪል መንግሥት ግን መቋቋም አለበት ብለዋል።ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደፊት የመስከረም 26 አይነት ጥቃት ተመልሶ እንደማይከሰት እስራኤል ማረጋገጥ ትፈልጋለች ብለዋል።“አሳማኝ ኃይል ሊኖረን ይገባል፤ አስፈላጊ ከሆነ ጋዛ ገብተን ገዳዩን መግደል መቻል አለብን። ምክንያቱም ይህ አይነቱ እርምጃ እንደ ሐማስ ያሉ ቡድኖች መልሰው እንዳይመጡ ያደርጋል” ብለዋል።ኔታኒያሁ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ የሰጡት አስተያየት አገራቸው የጋዛ የደኅንነት ሁኔታ ትቆጣጠራለች የሚል ነበር።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 11:46 9 ህዳር 202311:46 9 ህዳር 2023እስራኤል በየቀኑ ለአራት ሰዓታት የተኩስ አቁም ፋታ ልትሰጥ ነው
EPACopyright: EPAእስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ ጥቃት ከመፈጸም ለአራት ሰዓታት ተቆጥባ ፋታ ልስትሰጥ መሆኑን አሜሪካ አስታወቀች።የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ በሰሜናዊ የጋዛ አካባቢዎች እስራኤል በየቀኑ ለአራት ሰዓታት ተኩስ ታቆማለች ሲሉ ለሪፖርተሮች ተናግረዋል።እስራኤል ፋታ በምትሰጥባቸው አራት ሰዓታት ምንም አይነት ወታደራዊ ዘመቻዎችን እንደማትፈጽም አሳውቃናለች ብለዋል ቃል አቀባዩ።የእስራኤል ጦር ቀደም ሲል በጋዛ ለሚኖሩ ፍልስጤማውያን የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ ፋታ እንደሚሰጥ ገልጾ ነበር።የጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ መንግሥት በምንም መልኩ የተኩስ አቁም እንደማያደርግ ግን አስታውቋል።የተኩስ አቁም ስምምነት በሁለቱም ተዋጊ ወገን መካከል ተፈጻሚ የሚሆን፤ ለረዥም ጊዜ የሚከበር እና የፖለቲካዊ ሂደት አካል ነው።ለሰብአዊ እርዳታ ሲባል የሚደረግ ግጭት የማቆም ፋታ ግን ለአጭር ጊዜ ብቻ የሚቆይ ነው።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 10:13 9 ህዳር 202310:13 9 ህዳር 2023ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች ከሰሜን ወደ ደቡብ ጋዛ ተፈናቀሉ
ReutersCopyright: Reutersበሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ቀያቸውን ጥለው ከሰሜን የጋዛ ክፍል ወደ ደቡባዊው መፈናቀላቸው ተዘገበ።እስራኤል በምድር፣ በአየር እና በባሕር ኃይል የታገዘ ጥቃት በሰሜን ጋዛ ላይ አጠናክራ ስታካሂድ ቆይታለች።የእስራኤል ጦር ሰላማዊ ሰዎች ለደኅንነታቸው ሲባል ከሰሜናዊ ጋዛ ወደ ደቡብ ጋዛ እንዲያመሩ በተደጋጋሚ ሲያሳስብ ቆይቷል።ሰዎች ወደ ደቡባዊ የጋዛ ሰርጥ እንዲሸጋገሩ የእስራኤል ጦር መንገዶችን ለስድስት ሰዓታት ክፍት ማድረጉን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ወደ ደቡብ ፈልሰዋል።
ReutersCopyright: Reuters
ReutersCopyright: ReutersArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ