
ከ 9 ሰአት በፊት
የሮማው ሊቃነ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ ያቀረቡትን ማሻሻያዎች በሰላ ሁኔታ የተቹትን የቴክሳሱን ጳጳስ ጆሴፍ ስትሪክላንድን ከኃላፊነታቸው አነሱ።
ቫቲካን ባወጣው መግለጫ በጳጳሱ ሐገረ ስብከት ምርመራ መደረጉን ተከትሎም ከኃላፊነታቸው መነሳታቸቸውን አስታውቋል።
ፖፕ ፍራንሲስ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ልታደርጋቸው የሚገቡ ማሻሻያዎችን በተመለከተ በግንባር ቀደምትነት ከሚቃወሙት መካከል ጳጳሱ አንዱ ናቸው።
ፖፕ ፍራንሲስ አንዳንድ የአሜሪካ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪዎችንም በ “ኋላ ቀርነት” ተችተዋል።
ፖፕ ፍራንሲስ ጽንስ ማቋረጥንን እና የተመሳሳይ ጾታን ጋብቻን ጨምሮ በማህበራዊ ጉዳዮች ቤተክርስቲያኗ ያላትን አቋም መፈተሽ እንዲሁም ለማሻሻል ያደረጉትንም ጥረት በመቃወምም ጳጳሱ ተከታታይ ትችቶችን እና ወቀሳዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ።
ከጥቂት ወራት በፊት የካቶሊክ አስተምህሮት ማዕከል የሆኑትን መሰረታዊ እውነቶች እየተገዳደሩ መሆናቸውንም አስጠንቅቀዋል። ጳጳሱ ከጠቀሷቸውም መካከል በአምላክ ጋብቻ ተበሎ የተደነገገውን በወንድ እና በሴት መካከል ብቻ መደረግ የሚገባውን መጣመር “ለማፍረስ” የሚደረጉ ሙከራዎችን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችንም ዋቢ አድርገዋል።
“አምላክ የሰጣቸውን የማይካድ የጾታ ማንነታቸውን የማይቀበሉ” ሰዎች የሚያደርጉትንም ሙከራ የተዛባ ሲሉም ተችተዋል።
- የጦርነት ዳፋ የመጨረሻው ውጤት የሚታየው ጦር ሜዳ ላይ ሳይሆን ቤተሰብ ውስጥ ነው – ይፍቱሥራ ምትኩ12 ህዳር 2023
- በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ሥራ ለማቆም ተቃርቧል12 ህዳር 2023
- የፎቶግራፍ ጥበብን በማኅበረሰብ ውስጥ ያሉ ልዩነቶችን ለማጥበብ የሚያውለው ወጣት11 ህዳር 2023
ጳጳሱ በደብዳቤያቸውም ላይ መለወጥ የማይቻልን ነገር ለመለወጥ መመሞከር ቤተ ክርስቲያኒቷን ወደማይቀለበስ መከፋፋል እንደሚመራትም ነው ያስጠነቀቁት።
ለውጥን እየሻቱ ያሉትም “መከፋፈልን የሚፈልጉ ናቸው” ሲሉም አስጠንቅቀዋል።
ጳጳሱ በቫቲካን ምርመራ የተከፈተባቸው ሲሆን ቀደም ሲልም ስልጣናቸውን ለመልቀቅ የተሰጣቸውን ዕድል ውድቅ በማድረግም በቅርቡም በጻፉት ደብዳቤ ፖፕ ፍራንሲስ እንዲያባርሯቸውም ተገዳድረዋል።
“ከታይለር ጳጳስነቴ ልለቅ አልችልም ምክንያቱም ምዕመኑን እርግፍ አድርጎ አልተውም” ሲሉም ተናግረዋል።
የቀኝ ክንፍ አክራሪ የሆኑ “የተወገዙ የካህናት ጥምረት” ቡድን በምርመራው ወቅት እሳቸውን ለመደገፍ ጉባኤ አካሂዷል።
እንደ ካቶሊክ መገናኛ ብዙኃን ከሆነ ምርመራው በሐገረ ስብከቱ ከገንዘብ የተያያዙ ጉዳዮችን እንደተመለከተ አስነብበዋል።
የ65 ዓመቱ ጳጳስ የጵጵስና ማዕረጋቸውን ያገኙት በአውሮፓውያኑ 2012 በፖፕ ቤኔዲክት የቤተ ክርስቲያኗ መሪ በነበሩበት ነው።
