Skip to content
- የእስራኤል ጦር በጋዛ ትልቁ የሆነውን የአል ሺፋ ሆስፒታሉ ከበባ ውስጥ አስገብቶታል መባሉን ያስተባበለ ሲሆን በአቅራቢያው ግን የተፋፋመ ውጊያ መኖሩን አምኗል። ጦሩ በአል ሺፋ ላይ ጥቃት ፈጽሟል ቢባልም ይህንንም አልተቀበለውም።12 ህዳር 2023
ጭምቅ ሃሳብ
- እስራኤል በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ላይ ጥቃት ፈጽማለች መባሏን አስተባበለች
- በጋዛ ያሉ ሆስፒታሎች ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተመድ አስታወቀ
- ተመድ በጋዛ የሚገኘው ቢሮው ጥቃት እንደደረሰበት አስታወቀ
- በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ሥራ ለማቆም ተቃርቧል
- የእስራኤል መከላከያ ቤይሩት የጋዛ እጣ ፈንታ ሊገጥማት ይችላል ሲል ሄዝቦላህን አስጠነቀቀ
- በአልሺፋ ሆስፒታል ጨቅላ ማሞቂያ ውስጥ ያሉ ሕጻናት በሞት አፋፍ ላይ ናቸው ተባለ
- የታተመዉ 4:594:59በእስራኤል ጋዛ የተከሰቱ የቅርብ ጉዳዮች
ReutersCopyright: Reuters- የእስራኤል ጦር በጋዛ ትልቁ የሆነውን የአል ሺፋ ሆስፒታሉ ከበባ ውስጥ አስገብቶታል መባሉን ያስተባበለ ሲሆን በአቅራቢያው ግን የተፋፋመ ውጊያ መኖሩን አምኗል። በሆስፒታሉ ምስራቃዊ ክፍል በኩልም ታማሚዎችና የተጠለሉ ፍልስጤማውያን መውጣት ይችላሉ ብሏል። ጦሩ በአል ሺፋ ላይ ጥቃት ፈጽሟል ቢባልም ይህንንም አልተቀበለውም። አል ሺፋ ሆስፒታል ውሃ እና መብራት በመቋረጡ እንዲሁም የህክምና ግብዓት እጦት ምክንያት ሆስፒታሉ ተዘግቷል።
- እስራኤል ሐማስ በሆስፒታሉ ስር ያሉ ዋሻዎችን እንደ ማዘዣ ማዕከል ይጠቀማል ስትል የምትከስ ሲሆን ሐማስ ይህንን አይቀበለውም።
- ዓለም አቀፍ የድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) በጋዛ ውስጥ የሚገኙ ሆስፒታሎች የማያባራ የቦምብ ጥቃት እየተፈጸመባቸው ነው ሲል አስጠንቅቋል።
- በአል ሺፋ ሆስፒታል በጨቅላ ማሞቂያ ውስጥ የነበሩ ሁለት ህጻናት መሞታቸውን ተከትሎ ለሆስፒታሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በፍጥነት ካልተለቀቀ ሁሉም ሊሞቱ እንደሚችሉ በዚያ የሚገኙ ሐኪሞች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
- ቢቢሲ 20 የሚሆኑ ጨቅላ ሕጻናት ምስሎች ደርሰውታል። በማሞቂያ ውስጥ መሆን የሚገባቸው ህጻናት በአዋቂዎች አልጋዎች ላይ ይታያሉ።
- እስራኤል ጨቅላዎቹን እንዲወጡ ለማድረግ አግዛለሁ ብትልም ለአልሺፋ ሆስፒታል ሰራተኞች የሰጠችው ዝርዝር መረጃ የለም።
- በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን በሰሜናዊ ጋዛ ከቀጠለው የእስራኤል የተቀናጀ ጥቃት ለማምለጥ ከሰሜን ጋዛ ወደ ደቡብ ጋዛ መሸሻቸውን ቀጥለዋል።
- የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የተኩስ አቁም ጥሪን ውድቅ በማድረግ ሐማስ እስኪጠፋ እና ታጋቾቹ እስኪለቀቁ ድረስ ጦርነቱ ይቀጥላል ብለዋል።
Article share tools
- የታተመዉ 4:054:05በአልሺፋ ሆስፒታል ጨቅላ ማሞቂያ ውስጥ ያሉ ሕጻናት በሞት አፋፍ ላይ ናቸው ተባለ
BBCCopyright: BBCበጋዛ የሚገኘው ትልቁ ሆስፒታል አል ሺፋ ሆስፒታል መብራት በመቋረጡ ጨቅላ ማሞቂያ ውስጥ ያሉ ህጻናት በሞት አፋፍ ላይ ናቸው ተብሏል።እስራኤል በአየር እና በመሬት አቀናጅታ በቀጠለችበት ጋዛ የሚገኘው አል ሺፋ ሆስፒታል ውሃ እና መብራት በመቋረጡ እንዲሁም የህክምና ግብዓት እጦት ምክንያት ሆስፒታሉ ተዘግቷል። መብራት በሆስፒታሉ በመቋረጡ በማሞቂያ ውስጥ ያሉ ሁለት ህጻናት ሞተዋል።37 ሌሎች ጨቅላዎችም በሞት አፋፍ ላይ እንደሆኑም ተነግሯል። እስራኤል በበኩሏ በአል ሺፋ ሆስፒታል የሚገኙ ሕጻናት ወደ ሌላ ሆስፒታል ቢወሰዱ መልካም ነው ስትል መክራለች።እስራኤል ጨቅላዎቹን እንዲወጡ ለማድረግ አግዛለሁ ብትልም ለአልሺፋ ሆስፒታል ሰራተኞች የሰጠችው ዝርዝር መረጃ የለም።የሆስፒታሉ ቀዶ ጥገና ኃላፊ በበኩላቸው መብራት ከመቋረጡ በፊት በጋዛ ያሉ ሌሎች ሆስፒታሎች ጨቅላዎችን ለመንከባብ የሚያስችል መሳሪያም ሆነ ሙያተኞች የሉም ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ቢቢሲ 20 የሚሆኑ ጨቅላ ሕጻናት ምስሎች ደርሰውታል።ጨቅላዎቹ የሚገኙት በአል ሺፋ የቀዶ ጥገና ክፍል ውስጥ እንደሆነና ለሆስፒታሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በፍጥነት ካልተለቀቀ ሁሉም ሊሞቱ እንደሚችሉ በዚያ የሚገኙ ሐኪሞች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከሆስፒታሉ የሚወጡ መረጃዎች አስጨናቂና የሚያውኩ ሆነዋል።በተለይ በቅርብ ጊዜ ቀዶ ጥገና አድርገው ያልዳኑ ታማሚዎችና ሕጻናት አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል።በሆስፒታሉ ታማሚዎች ብቻ ሳይሆኑ ጦርነትን ሸሽተው የተጠለሉ በርካታ ፍልስጤማዊያን ይገኙበታል።Article share tools
- የታተመዉ 3:113:11ተመድ በጋዛ የሚገኘው ቢሮው ጥቃት እንደደረሰበት አስታወቀ
ReutersCopyright: Reutersየተባበሩት መንግሥታት በጋዛ ከተማ ከሚገኙት ቢሮዎች አንዱ ትናንት ምሽት በነበረው ውጊያ ጥቃት እንደደረሰበት አስታወቀ።በስፍራው ተጠልለው የነበሩ ፍልስጤማውያን እንደተገደሉ እና የተጎዱም እንዳለ አስታውቋል።“ይህ በየትኛውም መንገድ ፍጹም ስህተት ነው” ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) አስተዳዳሪ አቺም ስቴይነር በትዊተር ገጻቸው አስታውቋል።“ሰላማዊ ዜጎች፣ የነዋሪዎች መሰረተ ልማቶች እና እና የተባባሩት ተቋማት የማይጣሱ መሆን አለባቸው። ሁልጊዜም ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል” ብለዋል።እስራኤል በአየር እና በመሬት አቀናጅታ በቀጠለችው የጋዛ ጥቃት በርካታ ሆስፒታሎች እንደተጠቁ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። በጋዛ ከተማ ከሚገኘው ሺፋ ሆስፒታል ለመሸሽ የሞከሩ ነዋሪዎች፣ ህመምተኞች እና ሰራተኞችም እንደተተኮሰባቸውም ሪፖርት መድረሱንም ተመድ ገልጿል።Article share tools
- የታተመዉ 3:073:07የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር በለንደን ሰልፍ ላይ የተከሰተውን ነውጥ አወገዙየዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ በሰላማዊ ሰልፈኞች መካከል የተነሳውን ነውጥ አወገዙ። ሱናክ “ነውጡ ተቀባይነት የሌለው ነው ካሉ በኋላ ”ቀኝ አክራሪዎችን” እና “የሐማስ ተቆርቋሪዎች” ያሏቸውን ተጠያቂ አድርገዋል። ከ300ሺህ በላይ እንደሆኑ የሚገመቱ የፍልስጥኤም ደጋፊዎች “የተኩስ አቁም ይደረግ” በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉት ትናንት ቅዳሜ ነበር። ይህ የተቃውሞ ሰልፍ የእስራኤልና ጋዛ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ትልቁ እንደሆነ ተነግሯል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- የታተመዉ 1:361:36የእስራኤል መከላከያ ቤይሩት የጋዛ እጣ ፈንታ ሊገጥማት ይችላል ሲል ሄዝቦላህን አስጠነቀቀ
BBCCopyright: BBCየእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት የሊባኖሷ መዲና ቤይሩት የጋዛ እጣ ፈንታ ሊገጥማት ይችላል ሲሉ ሄዝቦላህን አስጠነቀቁ።የእስራኤል አየር ኃይል በእስራኤል ሊባኖስ ድንበር ላይ እያንዣበበ መሆኑን ገልጸው ጦርነቱን ለሚያባብስ ማንኛውም ተግባር ጦሩም ተዘጋጅቷል ብለዋል።”የሊባኖስ ዜጎች የሄዝቦላህ መሪ ሐሰን ናስራላህ ስህተት ከፈጸመ የቤይሩት እጣ ፈንታ እንደ ጋዛ ሊሆን እንደሚችል ማወቅ አለባቸው” ሲሉም ተናግረዋል።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁም ሄዝቦላህን ያስጠነቀቁ ሲሆን “ጦርነት በመጀመር ስህተት አትፈጽሙ” ብለዋል።ሄዝቦላህ ጦርነት ከከፈተ “የሊባኖስን እጣ ፈንታ የሚወስን ነው” ሲሉም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።Article share tools
- የታተመዉ 1:131:13በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ሥራ ለማቆም ተቃርቧልበጋዛ የሚገኘው አል ሺፋ ሆስፒታል ከፍተኛ ችግር ውስጥ ውድቋል። ሆስፒታሉ ሥራ ለማቆም የተቃረበው በአካባቢው በሐማስና እሰራኤል መካከል ከባድ ጦርነት እየተደረገ መሆኑን ተከትሎ ነው። በሆስፒታሉ ታማሚዎች ብቻ ሳይሆኑ ጦርነትን ሸሽተው የተጠለሉ በርካታ ፍልስጤማዊያን ይገኙበታል። ከሆስፒታሉ አቅራቢያ በሚገኙ ጎዳናዎች ጦርነቱ የተፋፋመ ሲሆን እስራኤል እስከ አሁን በዚህ ሆስፒታል ላይ ጥቃት አላደረስኩም ብላለች።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- የታተመዉ 1:061:06በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ከሰሜን ጋዛ መሸሻቸውን ቀጥለዋል
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል ከማያባራ የአየር ጥቃት በተጨማሪ የእግረኛ ጦሯን በጋዛ ሰርጥ ውስጥ አስገብታለች።ጦሩ ከመግባቱም በፊት ቢሆን በሰሜን ጋዛ የሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ሸሽተው እንዲወጡ ማስጠንቀቋን ተከትሎም በርካቶች ተፈናቅለዋል።አሁንም በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ጥቃቱን በመፍራት ወደ ደቡባዊ ጋዛ እየሸሹ ይገኛሉ።
EPA-EFE/REX/ShutterstockCopyright: EPA-EFE/REX/Shutterstock
ReutersCopyright: Reuters
ReutersCopyright: ReutersArticle share tools
- የታተመዉ 0:550:55እስራኤል በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ላይ ጥቃት ፈጽማለች መባሏን አስተባበለች
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል መከላከያ ኃይል በጋዛ ሰርጥ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ላይ ጥቃት ፈጽሟል መባሉን አስተባበለ። ነገር ግን በአካባቢው ከሐማስ ተዋጊዎች ጋር “ውጊያ” እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።የሆስፒታሉ የቀዶ ጥገና ሐኪም ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጽኑ ህክምና ክፍሉ በጥቃቱ እንደተመታ እንዲሁም ኤሌክትሪክ መቋረጡንና እና ውሃ እና ምግብ አልቋል ብለዋል።የህክምና ባለሙያዎች ሁለት ህጻናት መሞታቸውን እንዲሁም 37 ለጉዳት መጋለጣቸውን መናገራቸውን ተከትሎ እስራኤል ህጻናቱን “ደህንነቱ ወደተጠበቀ ሆስፒታል” ለማስወጣት እንደምታግዝ ገልጻለች።እስራኤል በኃይል በያዘችው ዌስት ባንክ በሚገኘው ጄኒን የስደተኞች መጠለያ ላይ በፈጸመችው ወረራ የተገደሉ 11 ፍልስጤማውያን የቀብር ስነ ስርዓት ተካሂዷል።የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ያለውን በቤይሩት ልትደግመው እንደምትችል ለሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ አስጠንቅቋል።በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ ሊባኖስን ወደ ጦርነት ሊጎትታት ይችላል ሲሉ ዮአቭ ጋላንት ተናግረዋል።ከ36 ቀናት በፊት ሐማስ በእስራኤል ላይ በፈጸመው ጥቃት 1 ሺህ 400 ሰዎች ተገድለዋል። እስራኤል ከአየር ጥቃት በተጨማሪ የእግረኛ ጦሯን በጋዛ ሰርጥ ውስጥ አስገብታለች።በአየር እና በመሬት ጥቃቶች እንዲሁም ከባሕር የሚወነጨፉ ሚሳኤሎችን በማቀናጀት ጋዛን እያጠቃች እንደሆነ ጦሯ አስታውቋል። በእነዚህም ጥቃቶች ከ11 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን የተገደሉ ሲሆን ከነዚህም 4 ሺህ 500 በላይ ህጻናት መሆናቸውን ከጋዛ ጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።