
Ethiopian American Civic Council – EACC

ዳንኤል ክብረት ጭርሷል ጥይት! ከንቱ ፕሮፓጋንዳው ዘቅጧል!በብልፅግናው ካምፕ ዋይታ በርክቷል!!!
አንዳንዱ ካድሬ እፍረት የለውም! ልክ እንደ አለቃው አቢይ አህመድ እራሱን የአዋቂም አዋቂ አድርጎ
ይመድባል:: ይሳደባይ! ይዘልፋል! ስም ያወጣል! ዳንኤል ክብረት እንዲህ ነው:: በተለይ የፕሮፓጋንዳው መኪና ሹፌር ነው::
ዳንኤል ክብረት በጌታው ላይ የመጣበትን ሁሉ ይናከሳል:: ትጉ ነው! የአገራችን ኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ ዋና ምንጫቸው አሜሪካ ይመስለዋል:: ሆዱን የሚጎዳ የአቢይ ስልጣን ማጣት መሆኑን ጠንቅቆ ተረድቷል! ብልጥ ነው:: ስለዚህ በየጊዜው አዲስ ስም ! አዲስ ስድብ ያፈልቃል::ስድብን የገቢ ምንጭ አድርጎታል::ለአዲሱ የኦሮሙማ የገዢ መደብ ያገለግላል::
ዳንኤል ክብረት ጌታውን ለስልጣን እሱን ለሳሎን አጫዋችነት ያበቃው የዳያስፖራው ትግል መሆኑን ይክዳል! ከተማሪዎች ማኅበር አንስቶ ስንት መስዋእት የተከፈለበትን ትግል ዳንኤል ክብረት ዛሬ ሊሸናበት ሞክሯል! በጣም በጣም ባለጌ ነው::
ዳንኤል ክብረት ዘንግቶ ሳይሆን እሳደብ ብሎ ነው:: ህወሓት ዳያስፖራውን ሊከፋፍል! ሊያማልል! ሞክሮ ሞካክሮ አቅቶት እንደ ወደቀ ይደብቃል! ከሞቀ ቤታቸው አሁን በቅርብ አመታት ” ጥራኝ ደኑ” እያሉ ትግል ሜዳ ወርደው የተሰው መኖራቸው ለዳንኤል ክብረት የተሰወረ ነው:: ድሮም ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ትግል የሄዱት ዳያስፖራዎች ነበሩ:: ይህንን አገር ወዳድነት ያመነጨው ምስዋእትነት ይህ ትንሽ ሰው ይንቀዋል:: እርግጥነው “በአሜሪካ የኢትዮጵያ ስደተኞች ታሪክ ወደ 70 ዓመት እየተጠጋው ነው።” እነዚህ ዓመታት ዳያስፖራ የህወሓት ከፋፋይ እና አፍራሽ ተንኮልን ተቋቁሞ እራሱን ከሌሎች ተለይቶ የሚታይ(ዓይን የሚጣልበት) መሆን ችሏል:: በያለበት ቤተ እምነቶቹን መስርቷል:: ንግዱን አስፋፍቷል! ትውልድ አፍርቶ! አስተምሯል:: ተከብሯል:: እዚህ ባለው የፖለቲካ ስርአትም ተሳትፏል:: ተሳትፎውም ታውቆለታል:: ይህንን አናንቃለሁ ብሎ ዳንኤል ክብረት ልክ እንደ ውሻዋ ሲጮህ ይሰማል:: ሰው ሰርቶ ለመብላት መጣሩ ለዚህ ትንሽ ሆዳም እንግዳ ነገር ሆኖ ተገኝቷል::
“የስቴት ዲፓርትመንት እና የዋይት ሐውስ አጥሮች ፊት ለፊት” የተደረጉት እየተደረጉ ያሉት ሰልፎች ፍትህ ተጉዋደለ! ሰብአዊ መብት ተጣሰ የሚሉ እንጂ ኮንዶሚኒየም ስጡን የሚሉ አይደሉም:: መሬት እንመራ የሚሉ አይደሉም:: ለተበደለው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥብቅና የመቆም አገራዊ! ወገናዊ! ተግባሮች/ግዴታዎች ናቸው! ሰው በበረዶ በፀሀይ እየወጣ ባይጮህ አቢይ እና ዳንኤል ክብረትን አራት ኪሎ ማን ያደርሳቸው ነበር? ዳያስፖራው የወገኑን ትግል ደግፏል:: አሁንም ይደፋል! ወደ ፊትም አገሩንእንደተቆራኘ ይኖራል:: ዳያስፖራው የአሜሪካን ፖለቲካ ያሾርዋል::ጀመረው እንጂ መች ነካው?
ዳያስፖራው “የአሜሪካው ፖለቲካ ” አቅቶት ከሆነ ለምን ዳንኤል ክብረት እና መንጋ የካድሬው ስብስብ ሶሻል ሚዲያ ላይ ተሰጥቶ ይውላል?! ያድራል?! ቢቆጠቁጠው ቢለበልበው አደለምን?!
“አዲሱ የአሜሪካ የዳያስፖራ ትውልድም አሜሪካን በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ መስኮች ከሚመሯት ወገን እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ” ይህ እውነት ነው! የጊዮርጊስን መገበሪያ የበላ ሳትጠይቁት ይለፈልፋል ተብሏ:: አዲሱን ትውልድ ያፈራው ማን ነው? ይህ ለተራው ደብተራ ዳንኤል ክብረት ግልፅ አልሆነለትም:: አባቱን ሰድቦ ልጁ ያሞግሳል:: ህወሓትን ተሳድቦ እግሯ ስር የወደቀው ቀላሉ ዳንኤል!
የዳያስፖራው ትግል በአሜሪካ “ሀገሬን ቅጡልኝ፣ ሀገሬን አስፈራሩልኝ” ሳይሆን አቢይ እና ብልፅግና የሚያደርሱትን ግድያ! እስራት ዝርፊያ ማፈናቀል እንዲቆም የመጠየቅ ነው:: ለግትህ ጩኸት ነው:: ወንጀለኞች ይጠየቁ! ይቀጡ! የዘረፉትን ይዘው አሜሪካ ሆነ የትም መሸሽ እንዳይችሉ ይደረጉ ነው:: ለእመስገን ባዩ የአቢይ ዝንጀሮ ሁሉ ግን አገር ጠልነት ጉዳይ ነው::
ባጭሩ ዛሬ ዳንኤል ክብረትን ሆነ ሌላውን ካድሬ የሚያስጮኸው ዛር ፋኖ ነው:: ፍርሀት ለቆባቸዋል! ደንግጠዋል:: የዳያስፖራው የተባበረ ትግል ወያኔን አስወግዶ ብሶ ለተገኘው ብልፅግና ለምን ርህራሄ ይኖረዋል?! ትግሉ እያሸነፈ ይቀጥላል!!!