November 13, 2023 – Konjit Sitotaw 

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ በትጥቅ ትግል ላይ የነበሩ የጉሙዝ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) አባላት ትናንት ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለሳቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።ሕዝቡ ያለፈው እንዳይደገም ሰግቷል።

አማጺዎቹ “የመንግሥትን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሰላማዊ ሕይወት የተመለሱት፣ በአካባቢው ሽማግሌዎች አማካኝነት ከኅብረተሰብ ጋር በተደረገ የእርቅ ስነ ሥርዓት እንደኾነ የዞኑ ኮምንኬሽን ቢሮ ገልጧል።

በባሕላዊ የእርቅ ስነ ሥርዓት ከኅብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለዋል የተባሉትን የቀድሞ አማጺዎች ብዛት ግን ቢሮው አልጠቀሰም። በቤንሻንጉል ወደ ሰላማዊ ሕይወት ገቡ የተባሉ አማፅያን አሁንም ተመልሰው ጫካ በመግባት ግድያ እንዳይጀምሩ ተሰግቷል።

ካሁን ቀደም ወደ ሰላማዊ ኑሮ ገቡ የተባሉ ትጥቅና ገንዘብ ከተሰታቸው በሗላ ወደ ጫካ ተመልሰው መግባታቸው ይታወሳል። እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች አማራ የሆኑትን በመግደልና ቤታቸውን በማቃተል ከባድ ውጥረት በመፍጠር ከፍተኛ ወንጀል መፈፀማቸው ይታወሳል።